Telegram Web Link
" ዩናይትድን ወደነበረበት መመለስ እንፈልጋለን " ቴንሀግ

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ቡድኑን ከአስር አመታት በፊት ወደነበረበት ደረጃ መመለስ እንደሚፈልጉ በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

" ይህንን ክለብ ከአስር አመታት በፊት የነበረበት ደረጃ መመለስ እንፈልጋለን " ያሉት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ክለቡን ፕርሚየር ሊጉን የሚያሸንፍ እና ሻምፒየንስ ሊግ ማሸነፍ የሚችል ማድረግ እንፈልጋለን ብለዋል።

በዚህ ደረጃ ለመድረስ ብዙ ርቀት መጓዝ እንዳለብን እናውቃለን ነገርግን ቡድኑን ማሻሻል አለብን በማለት አሰልጣኙ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አል ናስር ለኤደርሰን የዝውውር ጥያቄ አቀረበ ! የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ናስር ብራዚላዊውን ግብ ጠባቂ ኤደርሰን ለማስፈረም ለማንችስተር ሲቲ ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል። አል ናስር ለዝውውሩ 30 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ሲያቀርቡ ማንችስተር ሲቲ በበኩሉ ውድቅ ማድረጉ ተነግሯል። ማንችስተር ሲቲ ኤደርሰንን ከለቀቀው ከ 50 ሚልዮን ዩሮ በላይ እንደሚፈልግ የተገለፀ…
የኤደርሰን የማንችስተር ሲቲ ቆይታ ?

የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ኢትሀድ የማንችስተር ሲቲውን ግብ ጠባቂ ኤደርሰን ለማስፈረም እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተገልጿል።

ሌላኛው የሳውዲ ክለብ አል ናስር በቅርቡ ለማንችስተር ሲቲ ያቀረበው 30 ሚልዮን ዩሮ ውድቅ ሲደረግበት ሀሳባቸውን በመቀየር የአትሌቲኮ ፓራኔንሱን ግብ ጠባቂ ቤንቶ በ18 ሚልዮን ዩሮ አስፈርመዋል።

ማንችስተር ሲቲ አሁንም ግብ ጠባቂውን ለመልቀቅ እስከ 60 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ ክፍያ እንደሚፈልጉ ማሳወቃቸው ተገልጿል።

ኤደርሰን ወደ ሳውዲ አረቢያ ለማምራት ዝግጁ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን አል ኢትሀድ ዝውውሩ ከባድ ቢሆንም ለመሞከር መወሰናቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተስማማ ! ግብ ጠባቂ ለማስፈረም በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው አርሰናል እንግሊዛዊውን ወጣት ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ ለማስፈረም ከአያክስ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል። ባለ ጥሩ ተሰጥኦ ባለቤት መሆኑ የተነገረው የ 18ዓመቱ ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ በአርሰናል ቤት የአራት አመት ኮንትራት ለመፈረም ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል። መድፈኞቹ እንግሊዛዊውን ግብ ጠባቂ…
አርሰናል ግብ ጠባቂ አስፈረመ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል እንግሊዛዊውን ወጣት ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ ከአያክስ ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

መድፈኞቹ የ 18ዓመቱን ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ የቡድኑ ሶስተኛ ግብ ጠባቂ በማድረግ በአራት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

አርሰናል ለግብ ጠባቂው ቶሚ ሴትፎርድ ዝውውር አንድ ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ማውጣታቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማድሪድ ልዩ መቀመጫዎችን ማዘጋጀቱ ተገለጸ !

የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ በአዲሱ ስታዲየሙ ሳንቲያጎ በርናቦ " Super VIP " ሲል የገለፃቸውን እጅግ ቅንጡ 300 መቀመጫዎችን ማዘጋጀቱ ተገልጿል።

1.5 ቢሊየን ፓውንድ ወጥቶበት በተገነባው ዘመናዊው ሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም ውስጥ የተዘጋጀው ቅንጡ መቀመጫ ጨዋታ ለመመልከት ጥሩ እይታ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ሪያል ማድሪድ የልዩ መቀመጫ ቦታውን ትኬት የሚፈልጉ 300 ሰዎች አስቀድመው የአባልነት 250 ሺህ ዩሮ መክፈልና የአመት ትኬት መግዛት እንዳለባቸው ማሳወቁ ተነግሯል።

በተጨማሪም የልዩ መቀመጫ ትኬት የሚገዙ ሰዎች ከእግርኳስ በተጨማሪ ሳንቲያጎ በርናቦ በሚዘጋጁ የሙዚቃ ኮንሰርቶች እና የ " NFL" ጨዋታዎችን ያለ ተጨማሪ ክፍያ መመልከት እንደሚችሉ ተዘግቧል።

ሪያል ማድሪድ የ" Super VIP " መቀመጫዎችን ከሚቀጥለው አዲስ አመት በኋላ ክፍት ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል ግብ ጠባቂ አስፈረመ ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል እንግሊዛዊውን ወጣት ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ ከአያክስ ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል። መድፈኞቹ የ 18ዓመቱን ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ የቡድኑ ሶስተኛ ግብ ጠባቂ በማድረግ በአራት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል። አርሰናል ለግብ ጠባቂው ቶሚ ሴትፎርድ ዝውውር አንድ ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ማውጣታቸው ተገልጿል።…
" አርሰናል ለሰጠኝ እድል አመሰግናለሁ " ሴትፎርድ

አርሰናልን በይፋ የተቀላቀለው እንግሊዛዊው ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ ክለቡ ለሰጠው እድል ማመስገን እንደሚፈልግ ከፊርማው በኃላ ተናግሯል።

" በክለቡ እስክጀምር ጓጉቻለሁ " የሚለው ግብ ጠባቂው አርሰናል ለሰጠኝ እድል አመሰግናለሁ በሚቀጥለው የውድድር አመት አዲስ ነገር ለመማር እና ደረጃዬን ከፍተኛ ለማድረግ ተዘጋጅቻለሁ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ከተመረጡ ባንኮች ወደ M-PESA ገንዘብ በማስተላልፍ በቀላሉ ክፍያዎችን እንፈፅም ፤ እስከ 50 ብር ተመላሽ ስጦታ እናግኝ።

M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom  #FurtherAheadTogether
Forwarded from WANAW SPORT
🇪🇹 WANAW IN THE UK 🇬🇧

ዋናው ስፖርት በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ከሐምሌ 12-14፣ 2024 የተካሄደው 12ኛው ዓመታዊ የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ይፋዊ ስፖንሰር እና ትጥቅ አቅራቢ ስለነበር የተሰማውን ኩራት ለመግለፅ ይወዳል።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
" ክሎፕ እንግሊዝን ከተረከበ ካቆምንበት እንቀጥላለን " አርኖልድ

የሊቨርፑሉ የመስመር ተጨዋች አሌክሳንደር አርኖልድ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ስማቸው እየተያያዘ የሚገኘውን የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ከተረከቡ እንደሚደሰት ተናግሯል።

" ከክሎፕ ጋር በሰራሁበት ጊዜ በጣም ደስተኛ ነበርኩ ፣ ከእሱ ጋር ጥሩ ትዝታዎችን አሳልፈናል ሁልጊዜ ጥሩ ግንኙነት ነበረን እንግሊዝን ከተረከበ ካቆምንበት እንቀጥላለን።" ሲል አርኖልድ ተናግሯል።

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ከአሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ጋር ከተለያየ በኋላ አዲስ አሰልጣኝ በሀላፊነት ለመሾም እያፈላለገ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" አምራባት በዩናይትድ መቆየት ይፈልጋል " ሞሮኳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሶፍያን አምራባት በቀጣይ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት መቆየት እንደሚፈልግ የፊዮሬንቲና ዳይሬክተር ፕሬድ ገልጸዋል። ዳይሬክተሩ በንግግራቸውም " ሶፍያን አምራባት ፕርሚየር ሊግ ውስጥ መቆየት ይፈልጋል ማንችስተር ዩናይትድ ምንም ነገር አልነገሩንም ከፊዮሬንቲና ጋር እንዲቆይ እንፈልጋለን ነገርግን እሱ ሌላ አቅም ያለው ይመስለኛል።"ብለዋል።…
የሶፍያን አምራባት የማንችስተር ዩናይትድ ቆይታ ?

ማንችስተር ዩናይትድ ሞሮኳዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሶፍያን አምራባት ለማስፈረም በውሰት ውሉ የተቀመጠውን የመግዛት አማራጭ እንደማይጠቀሙ ተገልጿል።

በተጨዋቹ የውስት ውል ውስጥ በ20 ሚልዮን ዩሮ የመግዛት አማራጭ የተካተተ ሲሆን ቀያዮቹ ሴጣኖች መክፈል እንደማይፈልጉ ለፊዮረንቲና ማሳወቃቸው ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን ማቆየት እንደሚፈልግ ሲገለፅ በቀጣይ በሌላ የዝውውር ሂደት የማቆየት ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ወደ አሜሪካ የሚጓዘውን ስብስብ አሳውቋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ለቅድመ ውድድር ዝግጅት ወደ አሜሪካ የሚያመራውን የተጨዋቾች ስብስብ ይፋ አድርገዋል።

በስብስቡ ውስጥ ታኬሂሮ ቶሚያሱ እና ኬራን ቴርኒ በጉዳት ምክንያት አለመካተታቸውን ክለቡ አሳውቋል።

መድፈኞቹ በአሜሪካ ቆይታቸው ከበርንማውዝ ፣ማንችስተር ዩናይትድ እና ሊቨርፑል ጋር በተከታታይ የወዳጅነት ጨዋታዎች ያደርጋል።

*የተጨዋቾች ዝርዝር ከላይ በምስሉ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ማሬስካ በጣም ጥሩ ሀሳብ ይዞ መጥቷል " ንኩንኩ

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቶፈር ንኩንኩ አዲሱ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ወደ ቡድኑ አዲስ ሀሳብ ይዘው መምጣታቸውን ገልፀዋል።

" አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ወደ ቡድኑ በጣም ጥሩ የሆነ የጨዋታ ሀሳብ ይዘው መጥተዋል " የሚለው ክርስቶፈር ንኩንኩ በአሁን ሰዓት ሁላችንም በመማር ላይ ነን ብሏል።

ክርስቶፈር ንኩንኩ ቀጥሎም ሁሉም ተጨዋቾች የአዲሱን አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ሀሳብ የሚከተሉ ከሆነ በቀጣዩ አመት የሚያምር እግርኳስ እንደምንጫወት እርግጠኛ ነኝ በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቢኒያም ግርማይ ለሶስተኛ ጊዜ አሸናፊ ሆነ ! ኤርትራዊው ብስክሌተኛ ቢኒያም ግርማይ በታላቁ የቱር ደ ፍራንስ ውድድር በአስራ ሁለተኛው ቀን ውድድር ቀድሞ በመግባት ለሶስተኛ ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ መሆን ችሏል። በመጨረሻዎቹ መቶ ሜትሮች የነበረውን ከባድ ፉክክር መርታት የቻለው ቢኒያም ግርማይ በቱር ደ ፍራንስ በርካታ ነጥብ በመሰብሰብ አረንጓዴ ማሊያውን ( Green Jersey ) አስጠብቋል። ቢኒያም…
ቢኒያም ግርማይ ወርቃማ ታሪክ ፃፈ !

ኤርትራዊው ብስክሌተኛ ቢኒያም ግርማይ የታላቁን የቱር ደ ፍራንስ ውድድር " Points Classification " አሸናፊ ሆኖ በማጠናቀቅ ወርቃማ ታሪክ መፃፍ ችሏል።

ቢኒያም ግርማይ የቱር ደ ፍራንስ ውድድር አረንጓዴ ማሊያ ( Green Jersey ) ያሸነፈ የመጀመሪያው አፍሪካዊ በመሆን አዲስ ታሪክ ፅፏል።

ቢኒያም ግርማይ በ2024 ቱር ደ ፍራንስ ውድድር የ3ኛ ፣ 8ኛ እና 12ተኛ ደረጃ ውድድሮችን በማሸነፍ የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ መሆን ችሏል።

ቢኒያም ግርማይ አረንጓዴ ማልያውን ካረጋገጠበት ከዛሬው የመጨረሻ ውድድር በኋላ በሰጠው አስተያየት “ ምን ልል እችላለሁ ? በቃ የህይወቴ ምርጡ ቀን ነው “ ሲል ተደምጧል።

“ ወደዚህ የመጣሁት መጥፎ ብስክሌተኛ እንዳልሆንኩ ብቻ ለማሳየት እንጂ ይህንን ድል አልሜ አልነበረም የሚደነቅ ነው “።ሲል ቢኒያም ግርማይ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማድሪድ ለዴቪስ ስንት መክፈል ይፈልጋል ?

ሪያል ማድሪድ ካናዳዊውን የባየር ሙኒክ የመስመር ተጨዋች አልፎንሶ ዴቪስ ለማስፈረም ከተጨዋቹ ጋር በግል ስምምነት እንዳላቸው ሲገለፅ ነበር።

ሎስ ብላንኮዎቹ አልፎንሶ ዴቪስን በዚህ ክረምት የሚያስፈርሙ ከሆነ ከ25 ሚልዮን ዩሮ በላይ መክፈል እንደማይፈልጉ ተገልጿል።

ሪያል ማድሪድ ባየር ሙኒክ 25 ሚልዮን ዩሮ የማይቀበል ከሆነ በሚቀጥለው አመት ውሉ ሲጠናቀቅ በነፃ ማስፈረም እንደሚመርጡ ተነግሯል።

ባየር ሙኒክ በበኩሉ የተጫዋቹን ውል ማራዘም እንደሚፈልጉ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/04 17:22:29
Back to Top
HTML Embed Code: