Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
የዌምበልደን ፍፃሜ ተፋላሚዎች ታወቁ ! ለአንድ መቶ ሰላሳ ሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደው የዘንድሮው የ 2024 የታላቁ የዌምበልን የሜዳ ቴነስ ውድድር ፍፃሜ ተፋላሚዎች በሁለቱም ፆታዎች ተለይተው ታውቀዋል። በወንዶች የዌምበልደን ፍፃሜ የባለፈው አመት የፍፃሜ ተፋላሚዎች ስፔናዊው ካርሎስ አልካራዝ እና ሰርቢያዊው ኖቫክ ጆኮቪች በድጋሜ ተገናኝተዋል። ባለፈው አመት ስፔናዊው ካርሎስ አልካራዝ የሰባት ጊዜ…
ዌምበልደን በካርሎስ አልካራዝ አሸናፊነት ተጠናቀቀ !

ወጣቱ ስፔናዊ ካርሎስ አልካራዝ ለአንድ መቶ ሰላሳ ሰባተኛ ጊዜ የተካሄደውን የ 2024 ዌምበልደን የሜዳ ቴኒስ ውድድር ፍፃሜ ኖቫክ ጆኮቪችን በመርታት አሸናፊ ሆኗል።

የ 21ዓመቱ ካርሎስ አልካራዝ ሁለተኛ የዌምበልን የሜዳ ቴኒስ ውድድር ድሉን በተከታታይ አመታት ኖቫክ ጆኮቪችን በመርታት ማሳካት ችሏል።

በተጨማሪም ወጣቱ ካርሎስ አልካራዝ አራተኛ የግራንድ ስላም ዋንጫውን በማሳካት አስደናቂ ጊዜን በማሳለፍ ላይ ይገኛል።

ካርሎስ አልካራዝ በተመሳሳይ አመት የዌምበልደን እና ሮላንድ ጋሮስ ውድድርን ያሸነፈው በእድሜ ትንሹ ተጨዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ፅፏል።

በተጨማሪም በተከታታይ አመት የዌምበልደን ውድድርን ያሸነፈ የመጀመሪያው ስፔናዊ እንዲሁም ሶስተኛው በእድሜ ትንሹ ተጨዋች መሆን ችሏል።

ስፔናዊው ካርሎስ አልካራዝ ከውድድሩ ፍፃሜ በፊት በሰጠው አስተያየት " እሁድ ለስፔናዊያን አስደሳች ቀን ይሆናል " ሲል አስተያየቱን ሰጥቶ ነበር።

ከድሉ በኋላ ስለ አውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ አስተያየቱን የሰጠው ካርሎስ አልካራዝ " የራሴን ስራ አጠናቅቄያለሁ በእግርኳስ ደግሞ የሚፈጠረውን እናያለን " ሲል ሀገሩ ስፔንን ለመደገፍ ጨዋታውን እንደሚመለከት ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ስፔን ከ እንግሊዝ ( አውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ዊሊያምስን ለማስቆም የቻልኩትን አደርጋለሁ " ዎልከር

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የመስመር ተጨዋች ካይል ዎከር በምሽቱ ጨዋታ ኒኮ ዊሊያምስን ለማስቆም የቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ከጨዋታው በፊት ተናግሯል።

የኒኮ ዊሊያምስን በርካታ ቪድዮች መመልከቱን የገለፀው ካይል ዎከር " እሱ ፈጣን እና የተዋጣለት ባለተሰጥኦ ተጨዋች ነው ፣ ለማስቆም የቻልኩት ሁሉ አደርጋለሁ " ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ታሪክ የምንፅፍበት እድል አለን " ሳውዝጌት

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ቡድናቸው ዛሬ ምሽት ትልቅ ታሪክ የሚፅፍበት እድል እንዳለው በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

" ለታሪክ የሚቀመጥ ምሽት ማድረግ እንፈልጋለን " የሚሉት አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ቡድናችን ጥሩ መንፈስ ላይ ነው ዛሬ ታሪክ የምንፅፍበት ትልቅ እድል አለን ብለዋል።

አሰልጣኙ አያይዘውም በጨዋታው በቋሚ አሰላለፍ የገባው ሉክ ሾው ለጨዋታው ዝግጁ መሆኑን ሲገልፁ ልምድ ያለው እና ቡድኑ ሚዛኑን እንዲጠብቅ እንደሚያግዝ ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
#CopaAmerica2024 በአሜሪካ አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የዘንድሮው የ2024 የኮፓ አሜሪካ ውድድር ፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ሌሊት 9:00 በአርጀንቲና እና ኮሎምቢያ መካከል ይደረጋል። ትላንት በተደረገ የደረጃ ጨዋታ ዩራጓይ ካናዳን በመለያ ምት በማሸነፍ የውድድሩን ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቅ ችለዋል። የኮፓ አሜሪካ ፍፃሜ ጨዋታን ብራዚላዊው የ 44ዓመት ዳኛ ራፋኤል ክላውስ በመሐል ዳኝነት…
" ሜሲን ለማስቆም የሚያስችል መፍትሔ አላየሁም " ሀሜስ ሮድሪጌዝ

በኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ጥሩ ግዜን በማሳለፍ ላይ የሚገኘው ኮሎምቢያዊው ተጨዋች ሀሜስ ሮድሪጌዝ ቡድናቸው በዛሬው ፍፃሜ አርጀንቲናን ለማሸነፍ መጓጓቱን ገልጿል።

አርጀንቲና ልምድ ያለው ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን ነው የሚለው ሀሜስ ሩድሪጌዝ " ነገርግን እኛ ዋንጫውን ለማሸነፍ ጓጉተናል ዋናው ነገር ይህ ነው ፣ ከሜሲ ጋር ስፔን ውስጥ ተጫውቻለሁ ነገርግን እሱን ማስቆም የሚችል መፍትሔ ያገኘ አሰልጣኝ አላየሁም " ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የእረፍት ሰዓት !

በአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ እንግሊዝ ከ ስፔን ጋር እያደረጉ የሚገኙትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል።

🟨 የቢጫ ካርድ የተመለከቱ ተጫዋቾች እነማን ናቸው ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ በእንግሊዝ በኩል ሀሪ ኬን እንዲሁም በስፔን በኩል ዳኒ ኦልሞ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክተዋል።

የጨዋታው የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ ስፔን 69% - 31% የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ነበራቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
46 ’

ስፔን 1 - 0 እንግሊዝ ( አውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ )

ኒኮ ዊሊያምስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
54 ’

ስፔን 1 - 0 እንግሊዝ ( አውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ )

ኒኮ ዊሊያምስ

- ላሚን ያማል በአውሮፓ ዋንጫው አራት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል ቀዳሚው ተጨዋች መሆን ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
72 ’

ስፔን 1 - 1 እንግሊዝ ( አውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ )

ኒኮ ዊሊያምስ ፓልመር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
82 ’

ስፔን 1 - 1 እንግሊዝ ( አውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ )

ኒኮ ዊሊያምስ           ፓልመር

- ኮል ፓልመር በአውሮፓ ዋንጫው ምንም ጨዋታ በቋሚነት ሳይጀምር ለእንግሊዝ አንድ ግብ አስቆጥሮ አንድ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
87 ’

ስፔን 2 - 1 እንግሊዝ ( አውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ )

ኒኮ ዊሊያምስ           ፓልመር
ኦያርዛባል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🏆🏆 CHAMPION 🏆🏆

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን መሆን ችለዋል።

ለስፔን ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቦችን ኒኮ ዊሊያምስ እና ሚኬል ኦያርዛባል ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ ኮል ፓልመር ማስቆጠር ችሏል።

የስፔን ብሔራዊ ቡድን የአውሮፓ ዋንጫ ውድድርን አራት ጊዜ በማሸነፍ የመጀመሪያው ብሔራዊ ቡድን መሆን ችሏል።

አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት በውድድሩ ታሪክ ሁለት የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ የተሸነፉ የመጀመሪያው አሰልጣኝ ሆነዋል።

ሀሪ ኬን ፣ ዳኒ ኦልሞ ፣ ሙሲያላ ፣ ኮዲ ጋክፖ ፣ ሽራንዝ እና ሚካውታድዝ በሶስት ግቦች የውድድሩን የወርቅ ጫማ ተጋርተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የውድድሩ ምርጥ ተጨዋቾች ይፋ ሆኑ !

የስፔን ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮድሪ የዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ምርጥ ተጨዋች በመሆን መመረጡ ይፋ ሆኗል።

ወጣቱ የስፔን ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ምርጥ ወጣት ተጨዋች በመሆን መመረጡ ይፋ ተደርጓል።

የ 17ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል በውድድሩ አራት ለግብ የሆኑ ኳሶች ማቀበል ሲችል አንድ ግብ በማስቆጠር ጥሩ ጊዜን ማሳለፍ ችሏል።

ሮድሪ እና ላሚን ያማል የውድድሩ ምርጥ ተጨዋች ሽልማቱን ከዩኤፋ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሴፈሪን መቀበል ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ በፍፃሜ መሸነፍ በጣም ከባድ ነው “ ሀሪ ኬን

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አምበል ሀሪ ኬን በፍፃሜው የገጠማቸው ሽንፈት ሀዘኑ ከባድ መሆኑን ከጨዋታው በኋላ በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

“ በፍፃሜ መሸነፍ በጣም ከባድ ነው “ ሲል የገለፀው ሀሪ ኬን ጥሩ ተጫውተናል የአቻነት ግብ አስቆጥረን ወደ ጨዋታው ተመልሰንም ነበር ነገርግን ልንጠቀምበት አልቻልንም " ሲል ተናግሯል።

ቡድናቸው ኳስ ተቆጣጥሮ መቆየት ሳይችል ቀርቶ ግብ ማስተናገዱን ያስረዳው ሀሪ ኬን " ምንም እንኳን እግርኳስ ቢሆንም ህመሙ ጥልቅ ነው " ሲል በውጤቱ ማዘኑን ገልጿል።

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሀሪ ኬን እስካሁን ስድስት የፍፃሜ ጨዋታዎች ማድረግ ቢችልም ምንም ዋንጫ ማሳካት አልቻለም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአውሮፓ ሻምፒዮኖቹ ምን አሉ ?

የ 2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር አሸናፊው የስፔን ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ከድሉ በኋላ ተከታዩን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

- ኒኮ ዊሊያምስ :- " እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል አሁን የአውሮፓ ሻምፒዮን ሆነናል በቀጣይ የአለም ሻምፒዮን መሆን እንፈልጋለን።"

- ሮድሪ :- " ምናልባት ዛሬ የእግርኳስ ህይወቴ ምርጡን ቀን ነው ያሳለፍኩት ትልቅ ታሪክ ፅፈናል በዚህ ብቻም አናቆምም "

- ላሚን ያማል :- " ህልሜ እውን ሆኖልኛል እስካሁን ከተቀበልኳቸው የልደት ስጦታዎች ሁሉ ይሄኛው የተለየ እና ትልቁ ነው።

- ኡናይ ሲሞን :- " የሽልማት ሜዳልያዬን ለወላጅ እናቴ ሰጥቻታለሁ ምክንያቱም እሷ ከዚህ በፊት ልትመለከተኝ መጥታ አታውቅም ነበር። "

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/01 19:17:44
Back to Top
HTML Embed Code: