Telegram Web Link
ምባፔ የራሱን ክለብ ሊገዛ መሆኑ ተገለጸ !

ፈረንሳዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በቀጣይ የራሱን እግርኳስ ክለብ ለመግዛት ማቀዱ ተገልጿል።

ኪሊያን ምባፔ እና ቤተሰቡ በቀጣይ በፈረንሳይ ሁለተኛ ሊግ የሚወዳደረውን ኮን እግርኳስ ክለብ ለመግዛት ማሰባቸው ተነግሯል።

ምባፔ በልጅነቱ ተጫውቶበት እንደነበር የተገለፀው ክለቡ በአሁን ሰዓት በፈረንሳይ ሊግ ሁለት ሲወዳደር ባለፈው አመት ዘጠነኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ሲቲ ከተጫዋቹ ጋር ተለያየ !

ስፔናዊው የግራ መስመር ተጫዋች ሰርጂዮ ጎሜዝ ማንችስተር ሲቲን በመልቀቅ የስፔኑን ክለብ ሪያል ሶሴዳድ መቀላቀሉ ይፋ ተደርጓል።

ከሁለት አመታት በፊት ከአንደርሌክት ማንችስተር ሲቲን የተቀላቀለው ተጨዋቹ በ 10 ሚልዮን ዩሮ ሪያል ሶሴዳድን መቀላቀሉ ተገልጿል።

ተጨዋቹ በሪያል ሶሴዳድ ቤት አስከ 2030 የሚያቆየውን የስድስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ጆኒ ኢቫንስ በዩናይትድ ሊቆይ ነው ! ማንችስተር ዩናይትድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋቹን ጆኒ ኢቫንስ ኮንትራት ለተጨማሪ አመት ለማራዘም ንግግር ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል። እንግሊዛዊው ግብ ጠባቂ ቶም ሂተን በተመሳሳይ ውሉን ለማራዘም ከክለቡ ጋር በንግግር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል። የክለቡ አካዳሚ ውጤት የሆነው ብራንደን ዊሊያምስ በበኩሉ ከክለቡ ጋር ከአመታት በኋላ መለያየቱ ይፋ ተደርጓል። ማንችስተር…
ዩናይትድ የተጫዋቹን ውል አራዘመ !

ማንችስተር ዩናይትድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋቹን ጆኒ ኢቫንስ ኮንትራት ለተጨማሪ አመት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ጆኒ ኢቫንስ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ለተጨማሪ አንድ የውድድር አመት ለመቆየት ፊርማውን ማኖሩ ተገልጿል።

“ ውሌን በማንችስተር ዩናይትድ በማራዘሜ ተደስቻለሁ ፣ ባለፈው በጋራ ያሳካነው ኤፌ ካፕ የማይረሳ ነበር አሁንም በቀጣይ ተጨማሪ ዋንጫዎችን ማሸነፍ እንደምንችል አውቃለሁ።"ሲል ኢቫንስ ከፊርማው በኋላ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኬፓ አሪዛባላጋ ወደ ሳውዲ ሊያመራ ነው !

ስፔናዊው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ በቀጣይ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊግ ለማምራት በንግግር ላይ መሆኑ ተገልጿል።

የ 29ዓመቱ ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ አሁን ላይ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ኢትሀድ ለመቀላቀል በንግግር ላይ እንደሚገኝ ተዘግቧል።

ኬፓ አሪዛባላጋ ያለፈውን የውድድር አመት በሪያል ማድሪድ ቤት በውሰት ማሳለፉ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ደረሰ!

ከከባድ ትንቅንቅ በኋላ ስፔን እና እንግሊዝ ለፍፃሜ ሐምሌ 7 ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት በጀርመን ኦሎምፒያስታዲዮን ይገናኛሉ!

እንግሊዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን ታነሳ ይሆን? ስፔንስ የአሸናፊነት መንገዷን ትቀጥል ይሆን? 

⚽️ Spain vs England ሐምሌ 7 ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት | 10፡00 PM

👉SS Football ቻናል 225 በጎጆ ፓኬጅ
👉SS Euro2024 ቻናል 222 በሜዳ  ፓኬጅ

ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ልዩ በቀጥታ ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#Euro2024onDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
ኢንተር ሚላን የአሰልጣኙን ውል አራዘመ !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ኢንተር ሚላን የአሰልጣኝ ሲሞን ኢንዛጊን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ከኢንተር ሚላን ጋር የመጀመሪያ የስኩዴቶ ዋንጫቸውን ያሳኩት ጣልያናዊው አሰልጣኝ ሲሞን ኢንዛጊ በክለቡ ለተጨማሪ ሁለት አመታት ለመቆየት ፊርማቸውን አኑረዋል።

ሲሞን ኢንዛጊ ከኢንተር ሚላን ጋር ባለፉት አመታት ምን አሳኩ ?

1️⃣ የሴርያ ዋንጫ

2️⃣ ኮፓ ኢጣልያ

3️⃣ ሱፐር ኮፓ እንዲሁም አንድ ጊዜ ለአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ መድረስ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ጆሽዋ ዚርክዜ ዛሬ ምሽት ወደ እንግሊዝ ያመራል ! ኔዘርላንዳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜ ከቦሎኛ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ዛሬ ምሽት ወደ እንግሊዝ እንደሚያመራ ተገልጿል። የ 23ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜ በነገው ዕለት የህክምና ምርመራውን በማድረግ በይፋ ማንችስተር ዩናይትድን ይቀላቀላል። ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን በ 42.5 ሚልዮን…
ጆሽዋ ዚርክዜ ለዩናይትድ ፊርማውን አኖረ !

ኔዘርላንዳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ የሚያደርገውን ዝውውር  ለማጠናቀቅ ያደረገውን የህክምና ምርመራ ማጠናቀቁ ተገልጿል።

ተጨዋቹ አሁን ላይ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ለአንድ ተጨማሪ አመት የማራዘም አማራጭ ያካተተ የአምስት አመት ኮንትራቱን መፈረሙ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ የተጫዋቹን ዝውውር ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ጄደን ሳንቾ ወደ ዩናይትድ ልምምድ ሊመለስ ነው ! የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋቾች በነገው እለት ሰኞ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ለማድረግ ካሪንግተን ልምምድ ማዕከል ሪፖርት እንደሚገኙ ተገልጿል። በውሰት ለዶርትመንድ ሲጫወት የነበረው እና ከአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ጋር ያለውን ችግር ያልፈታው ጄደን ሳንቾ ነገ ወደ ክለቡ መመለስ እንደሚጠበቅበት ተነግሯል። ማንችስተር ዩናይትድን በቋሚ ዝውውር ለመልቀቅ…
ጄደን ሳንቾ ወደ ልምምድ ተመለሰ !

እንግሊዛዊው የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች ጄደን ሳንቾ ከቡድኑ ጋር መደበኛ ልምምድ መጀመሩን ክለቡ ይፋ አድርጓል።

ጄደን ሳንቾ በዚህ ሳምንት ከአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ጋር ለንግግር ተቀምጦ እንደነበር ሲገለፅ አዎንታዊ ውይይት ማድረጋቸው ተነግሯል።

ባለፈው የውድድር አመት ተጨዋቹ ከአሰልጣኝ ኤሪክ ጋር የገባውን አለመግባባት ተከትሎ ከቡድኑ ተገሎ እንደቆየ እና በኋላም በውሰት ወደ ዶርትመንድ እንዳመራ ይታወሳል።

አሁን ላይ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ እና ሳንቾ አለመግባባታቸውን ወደ ጎን በመተው ወደፊት ለመቀጠል መስማማታቸው ሲገለፅ ለቀጣይ የቅድመ ውድድር ጨዋታዎች ዝግጁ እንደሚሆንም ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በክለቡ ውስጥ መጠነ ሰፊ ለውጥ መጥቷል " አርቴታ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ባለፉት ጥቂት አመታት በክለቡ በሁሉም ቦታዎች ከአመት አመት መጠነ ሰፊ ለውጦች እየመጡ መሆኑን ገልጸዋል።

" አርሰናል አሁን የአስተሳሰብ ለውጥ አድርጎ ስለ ማሸነፍ እያሰበ ነው " ያሉት ሚኬል አርቴታ በክለቡ በሁሉም ቦታዎች የሚታዩ መጠነ ሰፊ ለውጦች እየመጡ ነው ብለዋል።

ለውጥ የመጣው በዋናው ቡድን ብቻ አለመሆኑን ያነሱት ሚኬል አርቴታ " የአካዳሚ እና ሴት ቡድናችን አቋምም ተቀይሯል ፣ በዋናው ቡድን የፈጠርነው ከባቢ የተለየ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቀጥለውም ቡድናቸው በቀጣይ ቡድኑን በሚፈልግበት ቦታ ማስቀመጥ እና ለማሸነፍ ከበቂ በላይ መሆኑን ማመን እንዳለበት አሳስበዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኬፓ አሪዛባላጋ ወደ ሳውዲ ሊያመራ ነው ! ስፔናዊው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ በቀጣይ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊግ ለማምራት በንግግር ላይ መሆኑ ተገልጿል። የ 29ዓመቱ ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ አሁን ላይ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ኢትሀድ ለመቀላቀል በንግግር ላይ እንደሚገኝ ተዘግቧል። ኬፓ አሪዛባላጋ ያለፈውን የውድድር አመት በሪያል ማድሪድ ቤት በውሰት ማሳለፉ…
ቼልሲ ለኬፓ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ኢትሀድ ስፔናዊውን ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ ለማስፈረም ያቀረበውን ይፋዊ ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ ግብ ጠባቂውን በቋሚ ዝውውር ለመሸጥ ከአል ኢትሀድ እና ሌሎች ክለቦች ጋር ንግግራቸውን መቀጠላቸው ተነግሯል።

የ 29ዓመቱ ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ ያለፈውን የውድድር አመት በሪያል ማድሪድ ቤት በውሰት ማሳለፉ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 35,000 Birr
•Meta Quest 2, 55,000 Birr
•Meta Quest 3, 83,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Mjallby - Malmo FF
National Bank Egypt - Smouha
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
TIKVAH-SPORT
Video
ፖርቹጋላዊው ሉዊስ ናኒ አዲስ አበባ ደርሷል !

ፖርቹጋላዊው የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች ሉዊስ ናኒ ዛሬ ጠዋት ወደ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ መጥቷል።

ተጨዋቹ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው የመቻል 80ኛ አመት የምስረታ በዓል ላይ ተካፋይ ለመሆን የቀረበለትን ግብዣ ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ናይጄሪያዊው የቀድሞ የአርሰናል ተጨዋች ንዋንኮ ካኑ በምስረታ በዓሉ ለመካፈል ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱ ታውቋል።

ለተጫዋቾቹ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ ፣ የመቻል ስፖርት ክለብ ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ሰይፈ ጌታሁን እና የመከላከያ ሚዲያ ስራዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ኩማ ሚደቅሳ አቀባበል አድርገዋል።

ምንጭ - የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሚዲያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዌምበልደን ፍፃሜ ተፋላሚዎች ታወቁ !

ለአንድ መቶ ሰላሳ ሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደው የዘንድሮው የ 2024 የታላቁ የዌምበልን የሜዳ ቴነስ ውድድር ፍፃሜ ተፋላሚዎች በሁለቱም ፆታዎች ተለይተው ታውቀዋል።

በወንዶች የዌምበልደን ፍፃሜ የባለፈው አመት የፍፃሜ ተፋላሚዎች ስፔናዊው ካርሎስ አልካራዝ እና ሰርቢያዊው ኖቫክ ጆኮቪች በድጋሜ ተገናኝተዋል።

ባለፈው አመት ስፔናዊው ካርሎስ አልካራዝ የሰባት ጊዜ የዌምበልደን አሸናፊውን ኖቫክ ጆኮቪች በመርታት የውድድሩ ወጣት አሸናፊ መሆን ችሎ ነበር።

በፍፃሜው ኖቫክ ጆኮቪች ከአራት ተከታታይ የዌምበልደን ድል በኋላ ባለፈው አመት የተቀማውን ክብር ለመመለስ ሲፋለም ወጣቱ ካርሎስ አልካራዝ በድጋሜ የድል ካባውን ለመድፋት ይፋለማል።

የአለም ቁጥር ሁለቱ የሜዳ ቴኔስ ተጨዋች ኖቫክ ጆኮቪች ከአለም ቁጥር ሶስቱ ካርሎስ አልካራዝ የሚያደርጉት የፍፃሜ ፍልሚያ የፊታችን እሁድ ይደረጋል።

በሴቶች የዌምበልን የሜዳ ቴነስ ውድድር ፍፃሜ ቼክ ሪፐብሊካዊቷ ባርቦራ ክሬቺኮቫ ከጣልያናዊቷ ጃሴሚን ፓኦሊኒ ጋር ተገናኝተዋል።

የአለም ቁጥር ሰባቷ ጃሴሚን ፓኦሊኒ እና የአለም ቁጥር ሰላሳ ሁለቷ ባርቦራ ክሬቺኮቫ የፍፃሜ ጨዋታቸውን በዛሬው ዕለት ያደርጋሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የዩራጓይ ተጨዋቾች ቅጣት ሊጣልባቸው ይችላል ! የደቡብ አሜሪካ እግርኳስ ማህበር ትላንት ሌሊት በዩራጓይ ተጨዋቾች እና ኮሎምቢያ ደጋፊዎች መካከል የተፈጠረውን ክስተት እየመረመረ እንደሚገኝ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ አስታውቋል። በጨዋታው ዳርዊን ኑኔዝን ጨምሮ የዩራጓይ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ወደ ተመልካች መቀመጫ ወንበር በመግባት ከኮሎምቢያ ደጋፊዎች ጋር ተደባድበው ነበር። ተጨዋቾቹ ከደጋፊዎች ጋር…
" እንዴት ለቤተሰብህ ላትከላከል ትችላለህ " ማርሴሎ ቤልሳ

የዩራጓይ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ማርሴሎ ቤልሳ በኮሎምቢያ ጨዋታ በተፈጠረው ክስተት የደቡብ አሜሪካ እግርኳስ ፌዴሬሽን እና አዘጋጇ አሜሪካን ተጠያቂ አድርገዋል።

አሜሪካ ውድድሩን በብቃት ልታስተናግድ አለመቻሏን የገለፁት አሰልጣኝ ማርሴሎ ቤልሳ ቡድናቸው የተጫወተባቸውን ሜዳዎች " ተቀባይነት የሌላቸው " ሲሉ ተችተዋል።

የቀረቡት የልምምድ ስፍራዎች ጥራት የሌላቸው መሆኑንም አያይዘው የገለፁት አሰልጣኙ የነበረው የደህንነት ሁኔታም አስተማማኝ አለመሆኑ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።

በስታዲየሙ የነበረው የፀጥታ አካል የዩራጓይ ተጨዋቾች ቤተሰቦችን ከሰከሩ ደጋፊዎች እንኳን ሊጠብቅ አልቻለም ነበር ሲሉ ማርሴሎ ቤልሳ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

የዩራጓይ ተጨዋቾች ሊጣልባቸው ስለሚችል ቅጣት ሀሳብ የተጠየቁት አሰልጣኝ ማርሴሎ ቤልሳ " ለእናትህ ፣ እህትህ እና ልጅህ እንዴት ላትከላከል ትችላለህ ?" ሲል መልሰዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ጀርመን ውስጥ የኬንን የዋንጫ ጥማት አስቀጥያለሁ “ ዳኒ ኦልሞ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዳኒ ኦልሞ ሀሪ ኬን ዋንጫ እንዳያሸንፍ የማድረግ ስራውን ገና አለማጠናቀቁን በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ጀርመን ውስጥ የዋንጫ እርግማኑን ሊያጠፋ የተቃረበውን ሀሪ ኬን አስቁሜው አስቀጥዬለታሁ " የሚለው ዳኒ ኦሎም " አሁንም ስራዬ ገና አልተጠናቀቀም " ሲል ተናግሯል።

ባለፈው አመት ባየር ሙኒክ ላይ ሀትሪክ በመስራት የጀርመን ሱፐር ካፕ ዋንጫን ሌፕዚግ እንዲያሳካ ያገዘው ዳኒ ኦልሞ " ነገም ሀትሪክ መስራት እና ማሸነፍ ህልሜ ነው " ብሏል።

የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ነገ ምሽት 4:00 በስፔን እና እንግሊዝ መካከል ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ከሜሲ ጋር መጫወት እፈልጋለሁ " ላሚን ያማል

ስፔናዊው የባርሴሎና ተስፈኛ ኮከብ ላሚን ያማል አርኣያው እንደሆነ ከሚናገርልት አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ ጋር መጫወት እንደሚፈልግ ተናግሯል።

" ከሜሲ ጋር መጫወት እፈልጋለሁ " የሚለው ያማል በቀጣይ አርጀንቲና ኮፓ አሜሪካን እንደምታሸንፍ ተስፋ አደርጋለሁ ስፔን የአውሮፓ ዋንጫን ካሸነፈች በ " Finalissima " ከእሱ ጋር መጫወት እችላለሁ " ሲል ተናግሯል ።

በኮፓ አሜሪካ እና አውሮፓ ዋንጫ አሸናፊዎች መካከል የሚደረገው የ " Finalissima " ዋንጫ ጨዋታ በሚቀጥለው ክረምት ሊደረግ እንደሚችል ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የወርቅ ጫማውን ስድስት ተጨዋቾች ሊያሸንፉ ይችላሉ !

ዩኤፋ ያለውን ህግ ማሻሻሉን ተከትሎ የዘንድሮውን የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ስድስት ተጨዋቾች ሊጋሩት እንደሚችሉ ተገልጿል።

በነገው የፍፃሜ ጨዋታ ሀሪ ኬን እና ዳኒ ኦልሞ ወይም ሌላ ተጨዋች ግብ ማስቆጠር የማይችል ከሆነ የወርቅ ጫማው ለስድስት ተጨዋቾች እንደሚሰጥ ተነግሯል።

የወርቅ ጫማውን ለማሸነፍ ሀሪ ኬን ፣ ዳኒ ኦልሞ ፣ ሙሲያላ ፣ ኮዲ ጋክፖ ፣ ሽራንዝ እና ሚካውታድዝ በሶስት ግቦች በመምራት ላይ ይገኛሉ።

ዩኤፋ ከዚህ በፊት ተጨዋቾች በእኩል ግቦች ሲያጠናቅቁ ብዙ ለግብ የሆኑ ኳሶች አመቻችቶ ያቀበለውን ተጨዋች ይመርጥ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አስቶን ቪላ አማዱ ኦናናን ሊያስፈርም ነው !

በአሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ የሚመራው አስቶን ቪላ ቤልጂየማዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች አማዱ እናና ከኤቨርተን ለማስፈረም መቃረባቸው ተነግሯል።

የ 22ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጫዋች አማዱ ኦናና በአስቶን ቪላ ቤት የረጅም ጊዜ ኮንትራት ለመፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊው ክለብ አስቶን ቪላ አማዱ ኦናናን በ50 ሚልዮን ፓውንድ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም መስማማታቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/01 07:37:44
Back to Top
HTML Embed Code: