Telegram Web Link
ሪያል ማድሪድ ተጫዋቹ ሊለቅ ይችላል !

ሪያል ማድሪድ ከስፔናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዳኒ ሴባዮስ ጋር በዚህ ክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ሊለያይ እንደሚችል ተገልጿል።

በሎስ ብላንኮዎቹ ቤት በቂ የጨዋታ ጊዜ እያገኘ የማይገኘው ዳኒ ሴባዮስ አሁን ላይ በበርካታ ክለቦች እየተፈለገ እንደሚገኝ ተነግሯል።

ተጨዋቹ ሪያል ማድሪድን የሚለቅ ከሆነ ክለቡ አዲስ ተጨዋች እንደማያስፈርም እና ከአካዳሚው ማርዮ ማርቲን እና ኒኮ ፓዝን እንደሚያሳድግ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዩናይትድ ማትያስ ዴሊትን ማስፈረም ይፈልጋል ! ማንችስተር ዩናይትድ ኔዘርላንዳዊውን የባየር ሙኒክ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ማትያስ ዴሊት በዚህ ክረምት ለማስፈረም በማሰብ ላይ መሆናቸው ተገልጿል። ቀያዮቹ ሴጣኖች ተጨዋቹን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ቢጀምሩም እስካሁን ይፋዊ ጥያቄ እንዳላቀረቡ እና ከባየር ሙኒክ ጋርም ንግግር እንዳልጀመሩ ተዘግቧል። በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመራው ማንችስተር ዩናይትድ…
ዩናይትድ ዴሊትን ለማስፈረም ንግግር ጀመረ !

ማንችስተር ዩናይትድ ኔዘርላንዳዊውን የባየር ሙኒክ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ማትያስ ዴሊት ለማስፈረም ከክለቡ ጋር ይፋዊ ንግግር መጀመራቸው ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ የ 24ዓመቱን ተጨዋች ማትያስ ዴሊት ለማስፈረም በአያክስ ቤት እያለ ጀምሮ ሲከታተሉ እንደነበር ይታወቃል።

ማትያስ ዴሊት አሁን ላይ በባየር ሙኒክ ቤት እስከ 2027 የሚደርስ ኮንትራት እንዳለው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" በዚህ እድሜዬ ስለ ገንዘብ ማሰብ አለብኝ " ዴብሮይን የማንችስተር ሲቲው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬቨን ዴብሮይን ከሳውዲ አረቢያ የሚቀርቡለትን ከፍተኛ ገንዘብ የሚያስገኙ ጥያቄዎች ለመመልከት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል። በማንችስተር ሲቲ ቤት የአንድ አመት ውል የቀረው ኬቨን ዴብሮይን " በዚህ እድሜዬ ለሁሉም ጥያቄዎች ክፍት መሆን አለብኝ በዚህ የእግርኳስ የመጨረሻ ጊዜ ላይ ስለ ትልቅ ገንዘብ ማሰብ አለብኝ።"በማለት…
" በማንችስተር ሲቲ እቆያለሁ " ዴብሮይን

ቤልጂየማዊው የማንችስተር ሲቲ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬቨን ዴብሮይን በሚቀጥለው የውድድር አመት በክለቡ እንደሚቀጥል በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

" ማንችስተር ሲቲ ውስጥ እቆያለሁ የእኔን የሌላ ክለብ ዝውውር የተመለከቱ ዜናዎች አይቻለሁ ነገርግን እኔ በጭራሽ ሲቲን መልቀቅ እንደምፈልግ አልተናገርኩም ያለኝን ውል አከብራለሁ።"ሲል ዴብሮይን ተናግሯል።

ስለ ዛሬ ምሽቱ የፈረንሳይ ጨዋታ የተናገረው ኬቨን ዴብሮይን " ፈረንሳይ በርካታ ጥራት ያላቸው ተጨዋቾች አሏቸው ከሁለት በላይ ምርጥ አስራ አንድ መሆን ይችላሉ።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
France - Belgium
Portugal - Slovenia
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from HEY Online Market
Stock Clearance Discount 2

📞 0925927457 @eBRO4
📞 0953964175 @heymobile

•iP 7+, Black, 128GB, 99% 12K
•iP X, Black, 256 GB, 100%,12K ⚠️
•iP XS, White, 64 GB, 100% 19K
•iP XS Max, Gold, 64GB, 83%, 25K
•iP XS Max, Gold, 256GB, 88% 29K
•iP 11, Red, 64GB, 100% 28K ⚠️
•iP 11, Black, 128GB, 85%, 33K
•iP 11, Purple, 128GB, 88% 33K
•11 Pro, Black, 64GB, 100% 39K ⚠️
•11 Pro, White, 64GB, 87% 36K
•11 Pro Max, Black, 64GB, 86%, 46K

•11 Pro Max, Black, 256GB, -% 40⚠️
•iP 12, Red, 128GB, 88%, 42K
•iP 12, White, 128GB, 88% 42K
•iP 12, Green, 128GB, 86% 42K
•12 Pro, Blue, 128GB, 89% 49K
•12 Pro Max, Blue, 512GB, 84% 64K
•iP 13 Min, Pink, 256GB, 92% 34K
•iP 13, Blueback, 128GB, 90% 56K
•iP 13, Black, 128GB, 92% 49K ⚠️

•iP 13, Red, 128GB, 86%, 56K
•iP 13, Black, 128GB, 89%, 58K
•13 Pro, Golden, 256GB, 87% 69K
•13 Pro, Blue, 512GB/88% 69K ⚠️
•13 ProMax, Black, 128 GB, 87% 74K
•13 ProMax, 256GB, 86%, 64K⚠️
•13 ProMax, 256GB, 85%, 74K⚠️
•13 ProMax, Gold, 256GB, 86%, 79K
•13 Pro Max, Gold, 256 GB,88% 79K
•13 Pro Max, Blue, 256GB, 94% 79K
•13 Pro Max, 1TB, 88%, 69K ⚠️
•13 Pro Max, Blu, 256GB/ -% 70K ⚠️

Exchange Available!
Free Delivery 🚚

@heyonlinemarket
https://heymobile.store/catalogue
ዩናይትድ አዲሱን ማልያቸውን አስተዋውቀዋል !

በሚቀጥለው የውድድር አመት የማልያ ላይ ስፖንሰራቸውን በአሜሪካው የቴክኖሎጂ ተቋም " Qualcomm " የቀየሩት ማንችስተር ዩናይትዶች አዲሱን ማልያቸውን አስተዋውቀዋል።

ዩናይትድ በሚቀጥለው የውድድር አመት ታዋቂውን የ " Qualcomm " ምርት " Snapdragon " የንግድ ምልክት በማልያቸው ላይ የሚያስቀምጡ ይሆናል።

በተጨማሪም ማንችስተር ዩናይትድ በየውድድር አመቱ ለአንድ ጨዋታ የበጎ አድራጎት ማስታወቂያ ስም በማልያቸው ላይ እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ ከማልያ ላይ ስፖንሰሩ በአመት የሚያገኘው 75 ሚልዮን ዶላር ክለቡ ለሻምፒየንስ ሊግ ባያልፍም እንደማይቀንስ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:00 ፈረንሳይ ከ ቤልጅየም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አስቶን ቪላ ባርክሌይን ለማስፈረም ተስማማ ! አስቶን ቪላ እንግሊዛዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮስ ባርክሌይ ወደ ሻምፒዮን ሽፑ ከወረደው ክለብ ሉተን ታውን ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። አስቶን ቪላ ከሉተን ታውን ጋር በግሉ ጥሩ የሚባል የውድድር አመት ማሳለፍ ለቻለው ሮስ ባርክሌይ አምስት ሚልዮን ፓውንድ ወጪ እንደሚያደርጉ ተነግሯል። ተጨዋቹ በቀጣይ በአስቶን ቪላ የህክምና ምርመራውን…
አስቶን ቪላ ተጨዋች አስፈርመዋል !

በአሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ የሚመራው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ተሳታፊው አስቶን ቪላ ተጨዋች ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

አስቶን ቪላ እንግሊዛዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮስ ባርክሌይ ወደ ሻምፒዮን ሽፑ ከወረደው ክለብ ሉተን ታውን ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

አስቶን ቪላ ከሉተን ታውን ጋር በግሉ ጥሩ የሚባል የውድድር አመት ማሳለፍ ለቻለው ሮስ ባርክሌይ አምስት ሚልዮን ፓውንድ ወጪ ማድረጋቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ስፔናዊውን ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ማርክ ጉዩ ከካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ለማስፈረም ሙሉ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል። ለስፔን ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን የሚጫወተው ማርክ ጉዩ በሰማያዊዎቹ ቤት እስከ 2030 የሚያቆየውን የስድስት አመት ኮንትራት ለመፈረም ከስምምነት መድረሱ ተነግሯል። ተጨዋቹ በባርሴሎና ኮንትራቱ ውስጥ ያለው…
ቼልሲ በይፋ ተጨዋች አስፈርሟል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ስፔናዊውን ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ማርክ ጉዩ ከካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ለስፔን ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን የሚጫወተው ማርክ ጉዩ በሰማያዊዎቹ ቤት እስከ 2030 የሚያቆየውን የስድስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተነግሯል።

የ 18ዓመቱን ተጨዋች ማርክ ጉዩ ከፊርማው በኋላ " ፕርሚየር ሊግ ውስጥ መጫወት ህልሜ ነበር " ያለ ሲሆን ወደዚህ ከመምጣቴ በፊት በደስታ እንቅልፍ አልተኛሁም ፣ ለቼልሲ በመፈረሜ ተደስቻለሁ " ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
34 ' ፈረንሳይ 0 - 0 ቤልጅየም

- አድሬን ራብዮ ቢጫ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ ፈረንሳይ ሩብ ፍፃሜ የምትደርስ ከሆነ በቅጣት ጨዋታው የሚያልፈው ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | ፈረንሳይ 0 - 0 ቤልጅየም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዳን አሽዎርዝ ዩናይትድን መቀላቀል ይፈልጋሉ ! በማንችስተር ዩናይትድ እየተፈለጉ የሚገኙት የ 52ዓመቱ የኒውካስል ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ዳን አሽዎርዝ የዩናይትድን ጥያቄ እንደሚቀበሉ ማረጋገጣቸው ተገልጿል። ማንችስተር ዩናይትድ ያቀረበውን ጥያቄ እንደ ትልቅ እድል እንደተመለከቱት የተገለፀው ዳን አሽዎርዝ ስራውን በይፋ ለመቀበል መዘጋጀታቸውም ተነግሯል። ማንችስተር ዩናይትድ በበኩሉ ከኒውካስል ዩናይትድ…
ማንችስተር ዩናይትድ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሾመ !

ማንችስተር ዩናይትድ የኒውካስል ዩናይትዱን ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ዳን አሽዎርዝ በሀላፊነት ለመሾም ከኒውካስል ጋር ከስምምነት መድረሳቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 52ዓመቱ ሀላፊ ዳን አሽዎርዝ በቀጣይ የማንችስተር ዩናይትድን የስፖርቲንግ ዳይሬክተርነት ሚና በሀላፊነት እንደሚረከቡ ይፋ ሆኗል።

ኒውካስል ዩናይትድ ማንችስተር ዩናይትድ ለሀላፊው ውል ማፍረሻ አቅርበውት የነበረውን 10 ሚልዮን የሚደርስ ክፍያ መቀበሉ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
84 ' ፈረንሳይ 1 - 0 ቤልጅየም

ቨርቶንገን ( በራስ ላይ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፈረንሳይ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቀሉ !

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጥሎ ማለፍ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ከቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

የፈረንሳይን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ቨርቶንገን በራሱ መረብ ላይ ማስቆጠር ችሏል።

አድሬን ራብዮ የማስጠንቀቂያ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ በሩብ ፍፃሜው በቅጣት ለፈረንሳይ ግልጋሎት የማይሰጥ ይሆናል።

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በሩብ ፍፃሜው ከፖርቹጋል እና ስሎቬኒያ ብሔራዊ ቡድኖች አሸናፊ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ፖርቹጋል ከ ስሎቬኒያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" መጥፎ እድል አብሮን ነበር " ዴብሮይን

የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ኬቨን ዴብሮይን በምሽቱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ቡድናቸው እድለኛ እንዳልነበረ ከጨዋታው በኋላ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ጥሩ መጫወት ብንችልም ያገኘነውን አጋጣሚ መጠቀም አልቻልንም " ያለው ዴብሮይን ያልሆነ ኳስ ተቆጥሮብናል በዛሬው ጨዋታ መጥፎ እድል ነበረን እጅግ ያበሳጫል ሲል ተደምጧል።

" በግል በውድድሩ ጥሩ ጊዜ ነበረኝ ቡድኑን ለማገዝ ሁሉንም ነገር ሰጥታቻለሁ ፣ ያገኘኋቸውን የግብ እድሎች አልተጠቀምኩም ይህ አለመታደል ነው ነገርግን ሁሉንም ሰጥቻለሁ።" ዴብሮይን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በራስ ላይ የሚቆጠር ግብ የፈረንሳይ ምርጥ አጥቂ ሆኗል " ቼሊኒ

የቀድሞ ጣልያናዊ ተከላካይ ጆርጂዮ ቼሊኒ በአውሮፓ ዋንጫው በራስ ላይ የሚቆጠር ግብ " የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ምርጥ አጥቂ ሆኗል " በማለት ከምሽቱ ጨዋታ በኋላ ተናግሯል።

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በአውሮፓ ዋንጫው ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች በጨዋታ ምንም ግብ ሳያስቆጥር ሩብ ፍፃሜ መድረስ የቻለ በውድድሩ ታሪክ የመጀመሪያው ብሔራዊ ቡድን ሆኗል።

ፈረንሳይ ባደረገቻቸው ጨዋታዎች ካስቆጠረቻቸው ሶስት ጎሎች ሁለት ግቦቿ በተቃራኒ ተጨዋቾች በራስ ላይ ሲቆጠሩ አንድ ግብ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ዴቪድ ራያን በቋሚነት አስፈርሟል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በውሰት ከብሬንትፎርድ ያስፈረሙትን ስፔናዊ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራያ ኮንትራት የመግዛት አማራጫቸውን ተጠቅመው ቋሚ ማድረጋቸው ተገልጿል።

መድፈኞቹ ለግብ ጠባቂው የዝውውር ሒሳብ በውሉ ውስጥ ተካቶ የነበረውን የመግዛት አማራጭ ሒሳብ 27 ሚልዮን ፓውንድ መክፈላቸው ተነግሯል።

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የወርቅ ጓንት አሸናፊው ዴቪድ ራያ አሁን ላይ በይፋ የአርሰናል ተጨዋች መሆኑ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/01 18:46:15
Back to Top
HTML Embed Code: