Telegram Web Link
#EthiopiaPL

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ ከፋሲል ከነማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ወላይታ ድቻ ካለፉት አስራ ስድስት የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በሁለቱ ነው።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

6️⃣ ፋሲል ከነማ :- 44 ነጥብ

1️⃣3️⃣ ወላይታ ድቻ :- 34 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ምን ይመስላል ?

እሮብ - ወላይታ ድቻ ከ ሀዋሳ ከተማ

ሐሙስ - ፋሲል ከነማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:00 ጣልያን ከ ስዊዘርላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
38 '

ስዊዘርላንድ 1 - 0  ጣልያን

ፍሩለር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#እረፍት

ስዊዘርላንድ 1 - 0  ጣልያን

ፍሩለር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሸገር ደርቢ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያደረጉትን የሸገር ደርቢ ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የቡናማዎቹን ግብ መሐመድ ኑር ናስር ከመረብ ማሳረፍ ሲችል ፍሪምፖንግ ክዋሜ ፈረሰኞቹን አቻ ማድረግ ችሏል።

ኢትዮጵያ ቡና ከአምስት ተከታታይ ድል በኋላ ነጥብ ጥለዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ካለፉት አስራ አንድ የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት አንዱን ሲሆን በአምስቱ አቻ ተለያይተዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

3️⃣ ኢትዮጵያ ቡና :- 51 ነጥብ

5️⃣ ቅዱስ ጊዮርጊስ :- 45 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ምን ይመስላል ?

እሮብ - ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀድያ ሆሳዕና

ሐሙስ - ፋሲል ከነማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
45 '

ስዊዘርላንድ 2 - 0  ጣልያን

ፍሩለር
ቫርጋስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ጀርመን ከ ዴንማርክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጣልያን ከአውሮፓ ዋንጫ ውጪ ሆነች !

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጥሎ ማለፍ የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ከጣልያን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

የስዊዘርላንድን የማሸነፊያ ግቦች ራሞ ፍሩለር እና ሩበን ቫርጋስ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ውጤቱን ተከትሎ የወቅቱ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ሻምፒዮን ጣልያን ብሔራዊ ቡድን ከውድድሩ ውጪ ሆነዋል።

ስዊዘርላንድ በሩብ ፍፃሜው የእንግሊዝ እና ስሎቫኪያን አሸናፊ ቀጣይ ሳምንት ቅዳሜ የሚገጥሙ ይሆናል።

ያለፉት ሶስት የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር አሸናፊ ሀገራት ስፔን ፣ ፖርቹጋል እና ጣልያን በቀጣዩ ውድድር በጥሎ ማለፉ ተሸንፈው ተሰናብተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ደጋፊዎችን ይቅርታ እንጠይቃለን " ዶናሩማ

ከአውሮፓ ዋንጫ የተሰናበተው ጣልያን ብሔራዊ ቡድን አምበል ጂያንሉጂ ዶናሩማ ከጨዋታው በኋላ በሰጠው አስተያየት ደጋፊዎችን ይቅርታ ጠይቋል።

" በጨዋታው ጥሩ አልነበርንም የሆነው ነገር ተቀባይነት የሌለው ነው ፣ እውነታውን መቀበል ያስፈልጋል ደጋፊዎቻችንን ይቅርታ መጠየቅ እንፈልጋለን።" ሲል ዶናሩማ ከጨዋታው በኋላ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ተጨዋቾቹን ለማወቅ በቂ ጊዜ አልነበረኝም " ስፓሌቲ

የጣልያን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ ተጨዋቾቻቸውን ለማወቅ በቂ ጊዜ አለማግኘታቸውን ከአውሮፓ ዋንጫው ከተሰናበቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

" ተጨዋቾቹን ለማወቅ በቂ ጊዜ አልነበረኝም " ያሉት አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ የበፊት አሰልጣኞችን ብንመለከት ከሀያ በላይ ጨዋታዎች ሞክረው ነበር ተጨማሪ ጨዋታዎች ያግዙኝ ነበር።"ብለዋል።

ጥሩ ቡድን ለመገንባት የተወሰነ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው የጠቆሙት አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ የቡድኑን መሰናበት ሀላፊነቱን እኔ እወስዳለሁ በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ብራይተን ተጨዋች ሊያስፈርሙ ነው !

ብራይተን ጋምቢያዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ያንኩባ ሚንቴህ በ33 ሚልዮን ፓውንድ ከኒውካስል ዩናይትድ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

የ 19ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ያንኩባ ሚንቴህ በግል ጥቅማጥቅም ዙሪያ ከብራይተን ጋር እንዲነጋገር ፍቃድ እንደተሰጠው ተገልጿል።

ኒውካስል ዩናይትድ የነጥብ ቅነሳ ቅጣት ሊያጋልጣቸው የሚችለውን የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግ ለማስተካከል በቀጣይ ሰዓታት ተጨዋቾችን ለመሸጥ እንደሚገደዱ ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ ኒውካስል ቀነ ገደቡ ሳይጠናቀቅ ለማስተካከል ከተለያዩ ክለቦች ጋር በርካታ የዝውውር ግብይቶችን ለመፈፀም እና ለማስተካከል በንግግር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጀርመን እና ዴንማርክ ጨዋታ ተቋርጧል !

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ከዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን ጋር እያደረጉ የነበረው የአውሮፓ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ተቋርጧል።

ጨዋታው የተቋረጠበት ምክንያት በጀርመን ዶርትመንድ ባለው አስቸጋሪ የአየር ንብረት ለውጥ መሆኑ ይፋ ተደርጓል።

የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ተጨዋቾች ወደ መልበሻ ቤት ያመሩ ሲሆን እሰካሁን ጨዋታው ስለመቀጠሉ የተገለፀ ነገር የለም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#እረፍት

ጀርመን  0 - 0 ዴንማርክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
50 '

ጀርመን  0 - 0 ዴንማርክ

- የዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን አስቆጥሮ የነበረው ግብ ከጨዋታ ውጪ በሚል በቫር ተሽሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
53 '

ጀርመን  1 - 0 ዴንማርክ

ሀቨርትዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
70 '

ጀርመን  2 - 0 ዴንማርክ

ሀቨርትዝ
ሙሲያላ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጀርመን ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል !

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ከዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን የአውሮፓ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀል ችለዋል።

ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቦች ካይ ሀቨርትዝ እና ጀማል ሙሲያላ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ጀማል ሙሲያል በአውሮፓ ዋንጫው ያስቆጠራቸውን ግቦች ሶስት ማድረስ ችሏል።

ጀርመን በሩብ ፍፃሜው የስፔን እና ጆርጂያን አሸናፊ አርብ ምሽት 1:00 ስዓት የምትገጥም ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/29 14:30:59
Back to Top
HTML Embed Code: