Telegram Web Link
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
አርጀንቲና ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል !

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ትላንት ሌሊት ከቺሊ ብሔራዊ ቡድን ያደረጉትን የኮፓ አሜሪካ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ በላውታሮ ማርቲኔዝ ግብ 1ለ0 ማሸነፍ ችለዋል።

አርጀንቲና የምድብ ሁለት ጨዋታዎችን ማሸነፏን ተከትሎ በስድስት ነጥቦች ወደ ሩብ ፍፃሜ መቀላቀሏን አረጋግጣለች።

አርጀንቲና አሁንም በኮፓ አሜሪካ ውድድር ታሪክ በመደበኛ ጨዋታ በቺሊ ብሔራዊ ቡድን ያላትን ያለመሸነፍ ጉዞ አስቀጥላለች።

ለአስራ ዘጠኝ ወራት ለአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ግብ ሳያስቆጥር የቆየው ላውታሮ ማርቲኔዝ ባለፉት አምስት ጨዋታዎች አምስት ግቦች አስቆጥሯል።

አርጀንቲና የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዋን ከፔሩ ጋር ቅዳሜ ሌሊት የምታደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊዮኔል ሜሲ መጠነኛ ጉዳት አጋጥሞታል !

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አምበል ሊዮኔል ሜሲ በትናንቱ ምሽቱ የቺሊ የኮፓ አሜሪካ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ መጠነኛ ጉዳት እንዳጋጠመው ተገልጿል።

የጨዋታውን ሙሉ ዘጠና ደቂቃ ተጫውቶ ያጠናቀቀው ሊዮኔል ሜሲ ይሁን እንጂ ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ ምቾት እንዳልተሰማው ተናግሯል።

" በቀኝ እግሬ ላይ ከመጀመሪያው ምቾት እየተሰማኝ አልነበረም ነገርግን ጨዋታውን ማጠናቀቅ ችያለሁ በቀጣይ እንዴት እንደሚሆን እናያለን።"ሲል ሊዮኔል ሜሲ ከጨዋታው በኋላ ለጋዜጠኞች ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሮናልዶ በቋሚ አሰላለፍ ይጀምራል " ሮቤርቶ ማርቲኔዝ

አስራ ስድስቱን የተቀላቀለው ፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ በዛሬው የጆርጂያ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቋሚ አሰላለፍ እንደሚጀመር ገልጸዋል።

ቡድኑ ጥሎ ማለፉን መቀላቀሉን ተከትሎ ሮናልዶን ሊያሳርፉ ይችሉ እንደሆነ የተጠየቁት አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ " ክርስቲያኖ ሮናልዶ በጨዋታው በቋሚ አስራ አንድ ውስጥ ይካተታል " ብለዋል።

" የአውሮፓ ዋንጫውን ያሸንፋል ተብሎ የሚገመት ቡድን መኖሩን እጠራጠራለሁ " ያሉት አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ሁሉም ብሔራዊ ቡድኖች በውድድሩ የተለያዩ ናቸው "ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በኮፓ አሜሪካ ረዳት ዳኛው ራሳቸውን ስተዋል !

ትላንት ሌሊት በኮፓ አሜሪካ ውድድር ፔሩ ከካናዳ ጋር ባደረጉት የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የጨዋታው ረዳት ዳኛ ራሳቸውን ስተው ሜዳ ላይ መውደቃቸው ተገልጿል።

ረዳት ዳኛው ራሳቸውን ስተው የወደቁት በነበረው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በህክምና ባለሞያዎች እርዳታ ከተደረገላቸው በኋላ ከሜዳ መውጣታቸው እና በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

ጨዋታውን የካናዳ ብሔራዊ ቡድን በጆናታን ዴቪድ ግብ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#ዳሽን_ከፍታ: በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው "ዳሽን ከፍታ" የሥራ ፈጠራ ውድድር ሶስተኛ ምዕራፍ ሊጀመር ነው፡፡

በዳሸን ከፍታ የመጀመሪያውና ሁለተኛው ዙር የስራ ፈጠራ ውድድሮች ተሳትፈው አሸናፊ የሆኑ ተወዳዳሪዎች ሸልማትና የፋይናስ ድጋፍ አግኝተው በተለያዩ የስራ ዘርፎች ስኬታማ እየሆኑ ነው፡፡ ለሌሎችም የስራ ዕድል መፍጠር ችለዋል፡፡

በዚህ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ ነዎት?

ዳሽን ከፍታ የሥራ ፈጠራ ውድድር በምዕራፍ ሶስት የቅድመ ውድድር ጅማሬ ስልጠና ለመስጠት በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ይንቀሳቀሳል!

የስልጠና ቦታዎች ፡ አዲስ አበባ ፣ ባህርዳር ፣ አዳማ ፣ መቀሌ ፣ ድሬዳዋ ፣ ሀዋሳ ፣ ወላይታ ፣ ጅማ እና ደሴ

ምዝገባ እስከ #ሰኔ_22/2016 ዓ.ም. ድረስ በሁሉም የዳሸን ባንክ ቅርንጫፎች የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ ወደ 6333 ይደውሉ ወይም የባንኩን የማህበራዊ ትስስር ገጾች ይጎብኙ፡፡

ዳሸን ባንክ ሁልጊዜም አንድ እርምጃ ቀዳሚ!
" የቤልጅየም ወርቃማ ትውልድ አያልቅም " ታዴስኮ

የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዶሜኒኮ ታዴስኮ የቤልጅየም ወርቃማ ትውልድ እንደማያልቅ እና አሁንም መኖሩን በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል።

" አንዳንድ ተጨዋቾች ጫማ ቢሰቅሉም የቤልጅየም ወርቃማ ትውልድ መቼም አያልቅም " ያሉት አሰልጣኝ ዶሜኒኮ ታዴስኮ " ከወጣት ተጨዋቾች ጋር አዲስ ነገር እየገነባን ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

ስለ ምሽቱ የዩክሬን ጨዋታ አስተያየት የሰጡት አሰልጣኝ ዶሜኒኮ ታዴስኮ " ሶስት ነጥቡን ማሳካት እንፈልጋለን ዩክሬን ጠንካራ ቡድን ናቸው ነገርግን ፍላጎታችን ማሸነፍ ብቻ ነው።"ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሜክሲኮ አምበሏ በጉዳት ከኮፓ አሜሪካ ውጪ ሆነ !

የሜክሲኮ ብሔራዊ ቡድን አምበል ኤድስን አልቫሬዝ በጉዳት ምክንያት እየተካሄደ ከሚገኘው የኮፓ አሜሪካ ውድድር ውጪ መሆኑ ተገልጿል።

የዌስትሀም ዩናይትዱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኤድስን አልቫሬዝ ከቀናት በፊት ጃማይካን ባሸነፉበት ጨዋታ ጉዳት ማስተናገዱ ይታወሳል።

ኤድስን አልቫሬዝ በጉዳት ምክንያት ተሰልፎ መጫወት ባይችልም በብሔራዊ ቡድኑ በመቆየት ቡድኑን እንደሚያበረታታ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ምድብ ሶስትን ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ማን ነው ?

የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ምድብ ሶስትን በሁለተኝነት ያጠናቀቀው የዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን መሆኑን የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር በይፋ አስታውቋል።

ዴንማርክ እና ስሎቬኒያ የምድብ ውድድሩን በእኩል ነጥብ ፣ የጎል ልዩነት እንዲሁም ተመሳሳይ የተጨዋቾች ቢጫ ካርድ ቁጥር በማስመዝገብ ማጠናቀቃቸው ይታወቃል።

ይሁን እንጂ የስሎቬኒያ ምክትል አሰልጣኝ የማስጠንቀቂያ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ ዴንማርክ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋን ዩኤፋ አስታውቋል።

ይህንንም ተከትሎ በጥሎ ማለፉ የዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን የሚገናኝ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥በቤቲካ እለታዊ ጃክፖት ቀኖን ይጀምሩ!🔥


🤩በየእለቱ የ100 ሺ ብር አሸናፊነት ይጠብቅዎታል!

👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾
የዛሬውን ጃክፖት https://betika.com.et/et/daily-jackpot ላይ ይጫወቱ!

ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
Forwarded from WANAW SPORT
📢 የዋናውን አዲስና የተሻሻለ ቦት እናስተዋውቅዎ!

➡️ @WanawSportBot ⬅️

በእጅግ ቀላል መንገድ የሚፈልጉትን የስፖርት አልባሳት በፍጥነት በ #ቴሌግራም ብቻ ይዘዙን።

👉🏾 ቦቱን በቴሌግራም ያስጀምሩ፣
👉🏾 ቅደም ተከተሉን ጠብቀው የሚፈልጉትን የስፖርት ልብስ ዓይነትና ተያያዥ ጉዳዮችን ይምረጡና ይዘዙን።

ዛሬውኑ ይሞክሩት፣ ትዕዛዝዎን ያድርሱን!

➡️ @WanawSportBot ⬅️

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
የኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ መቼ ይደረጋል ?

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ አሸናፊውን ማንችስተር ሲቲ እና የኤፌ ካፕ አሸናፊውን ማንችስተር ዩናይትድ የሚያገናኘው የእንግሊዝ ኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ የሚደረግበት ቀን ታውቋል።

በዚህም መሰረት የዘንድሮው የእንግሊዝ ኮሚኒቲ ሺልድ ካፕ ጨዋታ በዌምብሌይ ስታዲየም ቅዳሜ ነሀሴ 4/2016 ዓ.ም እንደሚደረግ ተገልጿል።

ከጨዋታው አንድ ሳምንት በኋላ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ2024/25 የውድድር ዘመን የሚጀምር ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ የስታዲየሙን ስም መብት ሊሸጥ ነው !

የፕርሚየር ሊጉ ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ የ ኦልድትራፎርድ ስታዲየምን የስም መብት ለመሸጥ በማሰብ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች የኦልድትራፎርድን የስም መብት ለመሸጥ ያሰቡት በቀጣይ ስታዲየሙን ለማደስ ወይም አዲስ ለመገንባት ላቀዱት እቅድ ገቢያቸውን ለማሳደግ በማለም መሆኑ ተነግሯል።

በተጨማሪም ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ የስታዲየም መግቢያ ትኬቶች ዋጋን ለመጨመር በማሰብ ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሀንጋሪ ተጨዋቿ ከሆስፒታል ወጥቷል !

የሀንጋሪ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች በርናባስ ቫርጋ አሁን ላይ ካጋጠመው ጉዳቱ አገግሞ ከሆስፒታል መውጣቱ ተገልጿል።

ተጨዋቹ ከቀናት በፊት ሀንጋሪ ስኮትላንድን ባሸነፈችበት ጨዋታ ከባድ ጉዳት አጋጥሞት ሜዳ ውስጥ ራሱን ስቶ ወድቆ ነበር።

የ 29ዓመቱ ተጨዋች በርናባስ ቫርጋ ከስኮትላንድ ግብ ጠባቂ ጋር በነበረው ግጭት በፊቱ ላይ የአጥንት ስብራቶች እንዳጋጠሙት ተነግሯል።

ተጨዋቹ አሁን ላይ ከሆስፒታል በመውጣት በሀንጋሪ መኖሪያ ቤቱ ሆኖ ከጉዳቱ እንደሚያገግም የሀንጋሪ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታወቋል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተቃርበዋል ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ስፔናዊውን ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ማርክ ጉዩን ከባርሴሎና ለማስፈረም መቃረባቸው ተገልጿል። ሰማያዊዎቹ ለ 18ዓመቱን የፊት መስመር ተጨዋች ማርክ ጉዩ ዝውውር የውል ማፍረሻ #ስድስት ሚልዮን ዩሮ ወጪ እንደሚያደርጉ ተነግሯል። ባለፈው አመት ለባርሴሎና ዋናው ቡድን በሰባት ጨዋታዎች ተሰልፎ የተጫወተው ማርክ ጉዩ በቼልሲ ቤት…
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ስፔናዊውን ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ማርክ ጉዩ ከካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ለማስፈረም ሙሉ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።

ለስፔን ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን የሚጫወተው ማርክ ጉዩ በሰማያዊዎቹ ቤት እስከ 2030 የሚያቆየውን የስድስት አመት ኮንትራት ለመፈረም ከስምምነት መድረሱ ተነግሯል።

ተጨዋቹ በባርሴሎና ኮንትራቱ ውስጥ ያለው የውል ማፍረሻ #ስድስት ሚልዮን ዩሮ መሆኑ ተዘግቧል።

የ 18ዓመቱን የፊት መስመር ተጨዋች ማርክ ጉዩ በቀጣይ ወደ ቼልሲ የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ለንደን የህክምና ምርመራውን እንደሚያደርግ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፊል ፎደን የብሔራዊ ቡድኑን ስብስብ ለቋል !

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ፊል ፎደን በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር እተሳተፈ ከሚገኘው የሶስቱ አናብስት ስብስብ በመልቀቅ ወደ እንግሊዝ መመለሱ ተገልጿል።

የማንችስተር ሲቲው ተጨዋች ፊል ፎደን የብሔራዊ ቡድኑን ስብስብ የለቀቀው አስቸኳይ የቤተሰብ ችግር ገጥሞት መሆኑን የእንግሊዝ እግርኳስ ማህበር ገልጿል።

የእንግሊዝ እግርኳስ ማህበር ባወጣው መግለጫ ተጨዋቹ ወደ እንግሊዝ የተመለሰው " በጊዜያዊነት " ነው ከማለት በቀር ተጨማሪ ማብራሪያ አልሰጠም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:00 ስሎቫኪያ ከ ሮማንያ

1:00 ዩክሬን ከ ቤልጅየም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/29 12:33:03
Back to Top
HTML Embed Code: