Telegram Web Link
69 '  ስሎቬኒያ 1 - 0 ሰርቢያ

ካርኒችኒክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:00 እንግሊዝ ከ ዴንማርክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጠናቀቀ |  ስሎቬኒያ 1 - 1 ሰርቢያ

ካርኒችኒክ ጆቪች

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🎁 እንደገና #ይገምቱ#ይሸለሙ!

🏆  በዛሬዎቹ የ2024 አውሮፓ ዋንጫ 7ኛ ቀን ጨዋታዎች ማን ድል ያደርጋል?

🇩🇰 ዴንማርክ ወይስ እንግሊዝ 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿
🇪🇸 ስፔን ወይስ ጣልያን 🇮🇹

💬 ግምትዎን #በገፃችን ኮሜንት ላይ ብቻ ያስቀምጡልን!

⚠️ የውድድሩ ህጎች፦
👉🏾 የሁለቱንም ጨዋታዎች አሸናፊ ሀገሮች እስከ የግብ መጠኑ #በትክክል ቀድመው የሚገምቱ #2 ተከታታዮቻችን የዋናውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማልያዎች ይሸለማሉ።
👉🏾 የዋናውን ማህበራዊ ገፆች መከተል፣ መወዳጀትና ማጋራት አይዘንጉ።
👉🏾 የተስተካከሉና ተደጋጋሚ መልሶች በፍፁም ተቀባይነት የላቸውም።

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
#EURO2024

በአሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት የሚመራው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በምሽቱ የዴንማርክ ጨዋታ በመጀመሪያ ጨዋታው የተጠቀመውን አሰላለፍ ይዞ ወደ ሜዳ ይገባል።

በጨዋታው አሌክሳንደር አርኖልድ በተለመደው መልኩ የመሐል ሜዳውን የዴላን ራይስ ጋር ተጣምሮ የሚመራው ይሆናል።

የማንችስተር ሲቲው ተጨዋች ፊል ፎደን በበኩሉ በጨዋታው በግራ መስመር ተጨዋችነት ብሔራዊ ቡድኑን ያገለግላል።

ኬራን ትሪፔር ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ሀምሳኛ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።

የዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ በመጀመሪያው አሰላለፍ ከተጠቀመበት ስብስብ የአንድ ተጨዋች ለውጥ አድርጎ ወደ ሜዳ ይገባል።

ክርስቲያን ኤሪክሰን በተመሳሳይ ከሁለቱ የፊት መስመር አጥቂዎች ጀርባ የአስር ቁጥር ሚናን በመያዝ ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
18 ' እንግሊዝ 1 - 0 ዴንማርክ

ኬን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
34 ' እንግሊዝ 1 - 1 ዴንማርክ

ኬን ሁልማንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | እንግሊዝ 1 - 1 ዴንማርክ

ኬን      ሁልማንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እንግሊዝ ከዴንማርክ ነጥብ ተጋርተዋል !

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ከዴንማርክ አቻቸው ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ግቧን ሀሪ ኬን ከመረብ ሲያሳርፍ ሞርተን ሁልማንድ ዴንማርክን አቻ ማድረግ ችሏል።

ሀሪ ኬን ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ስልሳ አራተኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የምድብ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣  እንግሊዝ :- 4 ነጥብ

2️⃣ ስሎቬኒያ :- 2 ነጥብ

3️⃣ ዴንማርክ :- 2 ነጥብ

4️⃣ ሰርቢያ :- 1 ነጥብ

በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ እንግሊዝ ከስሎቬኒያ እንዲሁም ዴንማርክ ከሰርቢያ ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ስፔን ከ ጣልያን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

በአሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ የሚመራው የጣልያን ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ምሽት ከስፔን ጋር በሚያደርገው ጨዋታ በመጀመሪያው የአልባኒያ ጨዋታ የተጠቀመውን አሰላለፍ ይዞ ይገባል።

የስፔን ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ ክሮሽያን ከረታበት የመጀመሪያ ጨዋታው የአንድ ተጨዋች ለውጥ አድርጎ ጣልያንን የሚገጥም ይሆናል።

የስፔን ብሔራዊ ቡድን በሳውዲ አረቢያ ሊግ ለአል ናስር የሚጫወተውን ተከላካዩ አይመሪክ ላፖርቴ በቋሚ አሰላለፍ አካቷል።

የመጀመሪያ ጨዋታውን በቋሚነት የጀመረው ናቾ ፈርናንዴዝ መጠነኛ ጉዳት እንዳጋጠመው ሲገለፅ ጨዋታውን በተጠባባቂነት ይጀመራል።

ከሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የሚያሸንፈው ቡድን ከወዲሁ ምድቡን በበላይነት በማጠናቀቅ ጥሎ ማለፉን መቀላቀሉን ያረጋግጣል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#እረፍት

ስፔን 0 - 0 ጣልያን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
55 '

ስፔን 1 - 0 ጣልያን

ካላፊዮሪ ( በራስ ላይ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ስፔን ጥሎ ማለፉን ተቀላቀለች !

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከጣልያን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

ለስፔን ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቧን ሪካርዶ ካላፊዮሪ በራሱ ግብ ላይ ከመረብ አሳርፏል።

በዘንድሮው የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር እስካሁን በተደረጉ ጨዋታዎች ብቻ አምስት ግቦች በራስ መረብ ላይ ተቆጥረዋል።

ሪካርዶ ካላፊዮሪ በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ታሪክ በራሱ ላይ ግብ ያስቆጠረ የመጀመሪያው የጣልያን ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ሆኗል።

የምድብ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ ስፔን :- 6 ነጥብ

2️⃣ ጣልያን :- 3 ነጥብ

3️⃣ አልባንያ :- 1 ነጥብ

4️⃣ ክሮሽያ :- 1 ነጥብ

በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ የፊታችን እሁድ ስፔን ከአልባንያ እንዲሁም ጣልያን ከክሮሽያ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Poland - Austria
Netherlands - France
Spain - Italyለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
" ሁሉም ተጋጣሚዎች ከእኛ ጋር በተለየ መንገድ ይጫወታሉ " ሊዮኔል ሜሲ

ተጠባቂው የ2024 የአሜሪካ የኮፓ አሜሪካ ውድድር ትላንት ምሽት አርጀንቲና ከካናዳ ጋር ባደረጉት የመክፈቻ ጨዋታ ጀምሯል።

የመክፈቻ ጨዋታውን አርጀንቲና በጁሊያን አልቫሬዝ እና ላውታሮ ማርቲኔዝ ግቦች ካናዳን 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች።

አርጀንቲናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ በጨዋታው በኮፓ አሜሪካ ውድድር ሰላሳ አምስት ጨዋታዎች በማድረግ በሌላ ተጨዋች ተይዞ የነበረውን ብዙ ጨዋታ የማድረግ ሪከርድ ሰብሯል።

ሊዮኔል ሜሲ በኮፓ አሜሪካ ውድድር አስራ ሰባት ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል እሱ በውድድሩ መካፈል ከጀመረ ወዲህ ከአምስት በላይ ኳስ አመቻችቶ ማቀበል የቻለ ተጨዋች የለም።

ከጨዋታው በኋላ አስተያየቱን የሰጠው ሊዮኔል ሜሲ " ጨዋታው ከባድ እንደሚሆን እናውቅ ነበር ፣ አስቸጋሪ ጨዋታ ነበር የጠበቅነው ሁሉም ቡድኖች እኛን ሲገጥሙ ከሚጠቀሙት በተለየ መንገድ ነው የሚጫወቱት።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ስፔን ማሸነፍ ይገባታል " ስፓሌቲ

የጣሊያን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ በምሽቱ የምድብ ጨዋታ ስፔን ማሸነፍ እንደሚገባት በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

" በጨዋታው ውጤት አልተበሳጨሁም " ያሉት አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ እነሱ በጨዋታው ከእኛ የበለጠ ብልህ ነበሩ ስፔን ጨዋታውን ማሸነፍ ይገባታል በማለት ተናግረዋል።

" ኳስ በአጋጣሚ ስናገኝ እንኳን ማቆየት አልቻልንም በፍጥነት እንቀማለን ፣ ራሳችን ላይ አስቆጥረናል ሌላም ሊቆጠርብን ይችል ነበር ለመጨረሻው ጨዋታ በደንብ መዘጋጀት አለብን።" ስፓሌቲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/29 20:22:02
Back to Top
HTML Embed Code: