Telegram Web Link
#እረፍት

ስኮትላንድ 1 - 1 ስዊዘርላንድ

ማክ ቶሚናይ     ሻኪሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
60 '

ስኮትላንድ 1 - 1 ስዊዘርላንድ

ማክ ቶሚናይ      ሻኪሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
78 '

ስኮትላንድ 1 - 1 ስዊዘርላንድ

ማክ ቶሚናይ        ሻኪሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የስኮትላንድ ብሔራዊ ቡድን ከስዊዘርላንድ አቻቸው ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የስኮትላንድ ብሔራዊ ቡድን ግብ ስኮት ማክ ቶሚናይ ከመረብ ሲያሳርፍ ጆርዳን ሻኪሪ ስዊዘርላንድን አቻ ማድረግ ችሏል።

የስዊዘርላንዱ ተጨዋች ጆርዳን ሻኪሪ በሶስት የአውሮፓ ዋንጫ ውድድሮች ላይ ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

ስዊዘርላንድ ጥሎ ማለፉን ለመቀላቀል ስትቃረብ ስኮትላንድ በበኩሏ የመጨረሻ ጨዋታዋን ማሸነፍ ቀጣዩን ዙር የመቀላቀል እድልን እንድታገኝ ያደርጋታል።

የምድብ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ ጀርመን :- 6 ነጥብ

2️⃣ ስዊዘርላንድ :- 4 ነጥብ

3️⃣ ስኮትላንድ :- 1 ነጥብ

4️⃣ ሀንጋሪ :- ምንም ነጥብ

በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ እሁድ ስዊዘርላንድ ከጀርመን እንዲሁም ስኮትላንድ ከሀንጋሪ ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Denmark - England
Spain - Italyለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from HEY Online Market
Play More and Spend less!

•PS4 Slim, 34,999 Birr
•PS4 PRO, 41,999 Birr
•Original Controller 6,499 Birr

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
" በአቻ ውጤቱ ደስተኞች ነን " ሮበርትሰን

የስኮትላንድ ብሔራዊ ቡድን አምበል አንዲ ሮበርትሰን ቡድናቸው ትላንት ምሽት አቻ በተለያዩበት ጨዋታ ያሳየው አቋም ጥሩ መሆኑን በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ባሳየነው እንቅስቃሴ ደስተኞች ነን " ያለው አንዲ ሮበርትሰን " አንድ ነጥብ አሳክተን ጥሎ ማለፉን የመቀላቀል እድላችንን አቆይተናል ነገርግን እሁድ ትልቅ ጨዋታ ይጠብቀናል።" ሲሉ አሳስቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እንግሊዝ የሉክ ሾውን ግልጋሎት አታገኝም !

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ምሽት ከዴንማርክ ጋር በሚያደርገው የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የሉክ ሾውን ግልጋሎት እንደማያገኝ አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት አረጋግጠዋል።

" ሉካ ሾው ከጉዳቱ ለማገገም በመስራት ላይ ነው ነገርግን በዛሬው ጨዋታ እንዲሁም በምድብ የመጨረሻ ጨዋታ አይሳተፍም ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገዋል።" ሲሉ አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ገልጸዋል።

አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ቀጥለውም በዛሬው ጨዋታ ከመጀመሪያ ጨዋታቸው የአሰላለፍ ለውጥ እንደማያደርጉ የገለፁ ሲሆን አርኖልድ በአማካይ ስፍራ እንዲሁም ፎደን በግራ መስመር ይጫወታሉ ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ራሳችንን ከአውሮፓ ምርጥ ቡድኖች በአንዱ መፈተሽ እንፈልጋለን " - ሉቺያኖ ስፓሌቲ

የጣልያን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ የዛሬ ምሽት ተጋጣሚያቸው ስፔን ብሔራዊ ቡድን ኳስ ከኋላ መስርቶ የሚጫወትበትን መንገድ እንደሚወዱት ገልጸዋል።

" ኳስን ከኋላ መስርቶ ወደ ተጋጣሚ ግብ ክልል የማጥቃት ሂደትን የሚከተለውን የስፔንን አጨዋወት እወደዋለሁ " ያሉት አሰልጣኙ እኛም የባለፈውን አጨዋወት እንከተላለን ራሳችንን ከአውሮፓ ምርጥ ቡድኖች በአንዱ መፈተሽ እንፈልጋለን።"ብለዋል።

" ለስፔን ታሪክ ትልቅ አክብሮት አለን ነገርግን እነሱ ከእኛ የተሻሉ ናቸዉ ብለን ማሰብ የለብንም ይህ ትልቅ ስህተት ነው ፣ እነሱ ላይ ጫና መፍጠር እና ኳስ በነፃነት እንዳይዙ ማድረግ አለብን።" ስፓሌቲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" ራሳችንን ከአውሮፓ ምርጥ ቡድኖች በአንዱ መፈተሽ እንፈልጋለን " - ሉቺያኖ ስፓሌቲ የጣልያን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ የዛሬ ምሽት ተጋጣሚያቸው ስፔን ብሔራዊ ቡድን ኳስ ከኋላ መስርቶ የሚጫወትበትን መንገድ እንደሚወዱት ገልጸዋል። " ኳስን ከኋላ መስርቶ ወደ ተጋጣሚ ግብ ክልል የማጥቃት ሂደትን የሚከተለውን የስፔንን አጨዋወት እወደዋለሁ " ያሉት አሰልጣኙ እኛም የባለፈውን አጨዋወት…
" ስፓሌቲ እኛን ማወደሱ አያዘናጋንም " ሉዊስ ዴ ላፉንቴ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላፉንቴ ቡድናቸው ዛሬ ምሽት ከጣልያን ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ ለማሸነፍ ብቻ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ከጨዋታው በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ ያደረጉት አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላፉንቴ ካነሷቸው ሀሳቦች መካከልም :-

- " አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ ጥሩ አሰልጣኝ ነው የእኛን ተጨዋቾችም ያደንቃል ፣ ነገርግን የሚቀርብልን ውዳሴ ጨዋታውን ከማሸነፍ አያዘናጋንም።

- ጨዋታው በጣም አስፈላጊ ጨዋታ ነው ማሸነፍ አለብን ፣ ለአቻ ውጤት እንዴት ማቀድ እንዳለብኝ አላውቅም ይህ እኛ አናውቅበትም የምንጫወተው ለማሸነፍ ብቻ ነው።

- ጣልያን በጣም ተፎካካሪ ቡድን ነው እርስበርስ በደንብ እንተዋወቃለን ትልቅ የቴክኒክ ደረጃ ያለው ውስብስብ ጨዋታ እጠብቃለሁ።"ሲሉ ተደምጠዋል።

የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋች ፋቢያን ሩይዝ በበኩሉ በሰጠው አስተያየት " የአውሮፓ ዋንጫውን ለማሸነፍ ሁሉንም እንሰጣለን " ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ማድሪድ ያለበት ቦታ ላይ መድረስ እንፈልጋለን " ራትክሊፍ

የማንችስተር ዩናይትዱ አነስተኛ ድርሻ ባለቤት እንግሊዛዊው ቢሊየነር ሰር ጂም ራትክሊፍ በቀጣይ ክለቡን ሪያል ማድሪድ ያለበት ደረጃ ለማድረስ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

" ሁሉንም ነገሮች ማሻሻል እንፈልጋለን " ያሉት ቢሊየነሩ በቀጣይ ሪያል ማድሪድ ያለበት ደረጃ ላይ መድረስ እንፈልጋለን ነገርግን የተሻለ ደረጃ ላይ ለመሆን ሁለት ወይም ሶስት የዝውውር መስኮቶች ያስፈልጋሉ ብለዋል።

" አለም ማንችስተር ከተማን የሚያውቃት በማንችስተር ዩናይትድ ነው " የሚሉት ሰር ጂም ራትክሊፍ ዩናይትድ ልክ እንደ ኮካ ኮላ ነው የማያውቀው ሰው የለም ሲሉ ገልጸዋል።

"ፈርጉሰን ከለቀቁ በኋላ ዩናይትድ 1.1 ቢልዮን ፓውንድ ሲያወጣ ሪያል ማድሪድ ከዚህ በብዙ ያነሰ ገንዘብ ነው ያወጣው ነገርግን ማድሪድ አሁን ከ100 ሚልዮን በላይ የሚያወጡ ስድስት ሰባት ተጨዋቾች አሉት ዩናይትድ ምንም የለውም።" ራትክሊፍ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሰርቢያ ውድድሩን ልታቋርጥ እንደምትችል ገለጸች !

የሰርብያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ከሚደረግ የ2024 የጀርመን አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ራሳቸውን ሊያገሉ እንደሚችሉ ገልፀዋል።

ሰርቢያ ይህንን ውሳኔ ልትወስን እንደምትችል የገለጸችው ትላንት ምሽት ክሮሽያ እና አልባንያ ባደረጉት ጨዋታ የሁለቱ ሀገራት ደጋፊዎች " ሰርብያውያን ይገደሉ " የሚል ዝማሬ ካሰሙ በኋላ ነው።

የሰርቢያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ክሮሽያ እና አልባንያ ላይ ትልቅ ቅጣት የማይጥል ከሆነ ከውድድሩ ልንወጣ እንችላለን በማለት አሳውቋል።

ክሮሽያዊያን እና አልባናውያን በሰርቢያውያን ላይ ያላቸው ጥላቻ እ.ኤ.አ 1995 ከዩጎዝላቪያ መገንጠል ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይነገራል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሌስተር ሲቲን በአሰልጣኝነት በመረከቤ ኮርቻለሁ " ስቲቭ ኩፐር

አዲስ አዳጊውን ክለብ ሌስተር ሲቲ በሀላፊነት የተረከቡት አሰልጣኝ ስቲቭ ኩፐር ሌስተርን እንዲመሩ በመሾማቸው ኩራት እንደተሰማቸው ከፊርማው በኋላ ተናግረዋል።

የቀድሞ የኖቲንግሀም እና ስዋንሲ ሲቲ አሰልጣኝ ስቲቭ ኩፐር ሌስተር ሲቲን ለሚቀጥሉት ሶስት የውድድር አመታት በሀላፊነት እንዲመሩ በይፋ ተሾመዋል።

አሰልጣኙ ከፊርማው በኋላ በሰጡት አስተያየትም " የሌስተር አሰልጣኝ ሆኜ በመሾሜ ኮራት እና ደስታ ተሰምቶኛል ከወጣት ቡድን ስብስብ ጋር ለመስራት ጓጉቻለሁ።"ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

10:00 ስሎቬኒያ ከ ሰርቢያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
ተጀመረ | ስሎቬኒያ 0 - 0 ሰርቢያ

- የስሎቬኒያ እና ሰርቢያ ብሔራዊ ቡድኖች ከዚህ በፊት ስምንት ጊዜ እርስበርስ የተገናኙ ሲሆን ስድስቱ በአቻ ውጤት ነው የተጠናቀቀው።

- ስሎቬኒያ በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር በታሪኳ አስካሁን ካደረገቻቸው አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለችም።

- ጨዋታውን የማሸነፍ ግምት ያገኘችው ሰርቢያ በእንግሊዝ ከተሸነፈችበት የመጀመሪያ ጨዋታ የሶስት ተጨዋቾች ለውጥ አድርጋለች።

- በጨዋታው ሰርቢያ አምበሏ ዱሳን ታዲችን ወደ ቋሚ አሰላለፍ መልሳለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት |  ስሎቬኒያ 0 - 0 ሰርቢያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥 የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎች በድምቀት ቀጥለዋል!

የዛሬ ጨዋታዎች መርሃ ግብር፡

⚽️ Denmark vs England ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት | 7፡00 PM በSS Football 225 ጎጆ ፓኬጅ በSS Euro2024 222 በሜዳ  ፓኬጅ

🤔ዋንጫው የማን ነው? የእርሶን አስተያየት ያጋሩን                        

በጀርመን የሚደረጉትን ደማቅ ጨዋታዎች በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ቻናሎች በወር ከ350 ብር ከጎጆ ፓኬጅ ጀምሮ ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#Euro2024onDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
ፋሲል ከነማ ድል አድርጓል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ከሻሸመኔ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የፋሲል ከነማን የማሸነፊያ ግቦች ፍቃዱ አለሙ 2x ከመረብ ሲያሳርፍ ለሻሸመኔ ከተማ ሁዛፍ ዓሊ አስቆጥሯል።።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

7️⃣ ፋሲል ከነማ :- 43 ነጥብ

1️⃣5️⃣ ሻሸመኔ ከተማ :- 14 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

- ሻሸመኔ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

- ወላይታ ድቻ ከ ፋሲል ከነማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/29 22:28:20
Back to Top
HTML Embed Code: