Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
ፋቢዮ ካናቫሮ ወደ ሀላፊነት ተመለሰ ! የቀድሞ ጣልያናዊ ተከላካይ ፋብዮ ካናቫሮ እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ የጣልያን ሴርያው ክለብ ዩዲኒዜ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ መሾሙ ይፋ ሆኗል። የባሎን ዶር እና የዓለም ዋንጫ አሸናፊው የቀድሞ ተጨዋች ፋብዮ ካናቫሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የጣልያን ሴርያ ክለብ የሚያሰለጥን ይሆናል። አሰልጣኝ ፋብዮ ካናቫሮ በከፍተኛ የመውረድ ስጋት ውስጥ የሚገኘውን ዩዲኒዜ በሊጉ ለማቆየት…
ፋቢዮ ካናቫሮ ከሀላፊነት ሊነሳ መሆኑን ገለጸ !

የቀድሞ ጣልያናዊ ተከላካይ ፋብዮ ካናቫሮ በቅርቡ በተረከበው በጣልያን ሴርያው ክለብ ዩዲኒዜ ዋና አሰልጣኝነት እንደማይቀጥል የክለቡ ፕሬዝዳንት እንደነገሩት አስታውቋል።

የባሎን ዶር እና የዓለም ዋንጫ አሸናፊው የቀድሞ ተጨዋች ፋብዮ ካናቫሮ የመውረድ ስጋት ውስጥ የነበረውን ዩዲኒዜ በሊጉ የማቆየት ሀላፊነት ወስዶ በመረከብ ክለቡን ከመውረድ አትርፎ ነበር።

ዩዲኒዜን እየመራ የሊጉ የመጨረሻ አምስት ጨዋታዎችን ያልተሸነፈው ፋብዮ ካናቫሮ በመጨረሻ ሰዓት የሰበሰባቸው ዘጠኝ ነጥቦች ክለቡን ከመውረድ መታደጋቸው ይታወሳል።

ዩዲኒዜ በውድድር አመቱ ስድስት ጨዋታዎች ብቻ ማሸነፍ ሲችል ሁለቱ ድሎች የተገኙት ፋብዮ ካናቫሮ በሀላፊነት በመራቸው የመጨረሻ አምስት ጨዋታዎች ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ፈረንሳይ በሁሉም ቦታዎች ምርጥ ተጨዋቾች አሏት "

የካናዳ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጄሴ ማርሽ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በሁሉም የሜዳ ክፍሎች የአለም ምርጥ ተጨዋቾችን መያዙን በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

ለኮፓ አሜሪካ ዝግጅት ላይ የሚገኘው የካናዳ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ምሽት ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ጋር ፈረንሳይ ላይ የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋሉ።

ከጨዋታው አስቀድሞ አስተያየታቸውን የሰጡት አሰልጣኝ ጄሴ ማርሽ " ፈረንሳይ ትልቅ ተሰጥኦ ያላቸው ጠንካራ ተጨዋቾች ይዛለች ፣ በሁሉም የሜዳ ክፍል የአለም ምርጥ ተጨዋቾችን ይዘዋል።"ብለዋል።

አሰልጣኙ ቀጥለውም በምሽቱ ጨዋታ ቡድናቸው ኪሊያን ምባፔን እና ሌሎች የፈረንሳይ ተጨዋቾችን የማስቆም ተግባር እንደሚሰጠው እና ለዚህም ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

የካናዳ ብሔራዊ ቡድን ከአስር ቀናት በኋላ የኮፓ አሜሪካ የመክፈቻ ጨዋታውን ከአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#MatchDay 🇪🇹

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አራተኛ ጨዋታውን ከጅቡቲ ብሔራዊ ቡድን ጋር ዛሬ ምሽት ሞሮኮ ላይ የሚያደርግ ይሆናል።

የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት 1:00 ሰዓት ሞሮኮ ኤል አብዲ ስታዲየም ላይ የሚደረግ ይሆናል።

በምድቡ ኢትዮጵያ በሁለት ነጥቦች አምስተኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ጅቡቲ ምንም ነጥብ ማስመዝገብ ሳትችል ቀርታ የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች።

ጨዋታውን ማን ይመራዋል ?

ጨዋታውን ዩጋንዳዊያን ዳኞች አሊ ሳሊባ በመሐል ዳኝነት ሮናልድ ካቴንያ እና ሀኪም ሙሊንድዋ በረዳት ዳኝነት እንዲሁም ዊልያም ኦሎያ በአራተኛ ዳኝነት ይመሩታል።

ጨዋታውን በምን መመልከት ይቻላል ?

ጨዋታውን ከአንድ ሰዓት ጀምሮ በተከታዩ ሊንክ መከታተል ይቻላል።

https://www.plus.fifa.com/en/content/433b88f1-a77d-4d70-8550-1541f6eee493?gl=ma

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የኮንጎ ተጨዋቾች ሞሮኮ አንሄድም ማለታቸው ተገለጸ !

የሪፐብሊክ ኮንጎ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ከሞሮኮ ጋር ላለባቸው የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታ ወደ ስፍራው ለማቅናት ፍቃደኛ አለመሆናቸው ተገልጿል።

ተጨዋቾቹ ወደ ሞሮኮ ለማምራት ፍቃደኛ ያልሆኑት በጉዞው ወቅት የተለያዩ ወጪዎችን በራሳቸው እንዲሸፍኑ ስለተነገራቸው መሆኑ ተዘግቧል።

ተጨዋቾቹን ቅሬታ ውስጥ ካስገባቸው ምክንያቶች መካከልም :-

- ለተጨዋቾች ልምምድ ቁሳቁስ የቡድኑ ሰራተኞች በራሳቸው እንዲገዙ ስለተነገራቸው

- ተጨዋቾቹ ወደ ሞሮኮ የመሄጃ ጉዞ ትኬት ብቻ እንደሚሸፈንላቸው እና የመመለሻ በራሳቸው እንዲሸፍኑ ስለተጠየቁ

- በቡድኑ ውስጥ የነበሩ ነባር ሰራተኞች ከልዑካን ቡድኑ ተቀንሰው በማይታወቁ ሰዎች በመተካታቸው መሆኑ ተነግሯል።

በተጨማሪም የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት በቅሬታዎቹ ዙሪያ ለማነጋገር ቀጠሮ ቢይዙም ያለምክንያት እንደተሰረዘባቸው ተገልጿል።

ምንም ጨዋታ ማሸነፍ ሳይችል የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ የያዘው የኮንጎ ብሔራዊ ቡድን የሜዳ ጨዋታውን ለማድረግ ባስመዘገበው የሞሮኮ ስታዲየም ለማድረግ ዛሬ ጠዋት ወደ ስፍራው ለማቅናት ቀጠሮ ይዞ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📢 ለድርጅትዎ ልዩ የሆነ የምስራች ከ #ዋናው!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 0995114226፣ 09119552210910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ዘላቂ የብረት ህትመቶች!
የምትፈልጉትን ምስል ላኩልን እኛ በጥራት አናትማለን።

ህትመቶቻችንን በተለያዩ ሳይዞች ማግኘት ይችላሉ። A4 | A3 | A2

አሁኑኑ በ 0912689730 ወይም 0913336591 በመደወል ይዘዙ።

ለበለጠ መረጃ:
Telegram: @silverpoint_printss
Instagram: https://www.instagram.com/silverpoint_prints/
TikTok: https://www.tiktok.com/@silverpoint.prints
ቼክ ተጨዋቿ ከአውሮፓ ዋንጫ ውጪ ሆነ !

የቼክ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ቡድን በኔዘርላንድ ሊግ ጥሩ ጊዜን ማሳለፍ የቻለው የመሐል ሜዳ ተጨዋቻቸው ሚሼል ሳዲሌክ ከቀጣዩ አውሮፓ ዋንጫ ውጪ መሆኑን ይፋ አድርገዋል።

ተጨዋቹ ከአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ውጪ የሆነው ብስክሌት በሚያሽከረክርበት ወቅት ወድቆ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት መሆኑን የሀገሪቱ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

ቼክ ሪፐብሊክ በአውሮፓ ዋንጫው ከጆርጅያ ፣ ፖርቹጋል እና ቱርክ ጋር በምድብ ስድስት ተደልድላለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጂዮቫኒ ሎ ሴልሶ የቶተንሀም ቆይታ ?

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም በዚህ ክረምት ከአርጀንቲናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጂዮቫኒ ሎ ሴልሶ ጋር ለመለያየት ማሰባቸው ተገልጿል።

የ 28ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጂዮቫኒ ሎ ሴልሶ በቶተንሀም ቤት ቀሪ የአንድ አመት ኮንትራት አለው።

የስፔን ላሊጋው ክለብ ሪያል ቤቲስ የተጨዋቹ ፈላጊ ክለብ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን የተጫዋቹን ወኪል ማነጋገር መጀመራቸውም ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባየር ሙኒክ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ !

የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ የፉልሀሙን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጇ ፓልሂንሀ ለማስፈረም ከተጨዋቹ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

ባየር ሙኒክ ፖርቹጋላዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጇ ፓልሂንሀን ለማስፈረም እስከ 45 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ሊያወጡ እንደሚችሉ ተነግሯል።

የ 28ዓመቱ ተጨዋች በዚህ አመት በሊጉ ለፉልሀም ባደረጋቸው ሰላሳ ሶስት ጨዋታዎች አራት ግቦች አስቆጥሮ አንድ አመቻችቶ አቀብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ፈረንሳይ ልታሸንፍ ትችላለች " ጉንዶጋን

ጀርመናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኢልካይ ጉንዶጋን በቀጣዩ የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ፈረንሳይ ግምት የሚሰጣት ሀገር መሆኗን ተናግሯል።

የአውሮፓ ዋንጫውን ሊያሸነፉ የሚችሉ ሀገራትን ሲጠቅስ ፈረንሳይን በቀዳሚነት ያስቀመጠው ኢልካይ ጉንዶጋን " ነገርግን ፖርቹጋል ፣ ስፔን እና እንግሊዝም ይኖራሉ "ብሏል።

የጀርመን ብሔራዊ ቡድንን ከእጩነት ስላወጣበት ምክንያት የተጠየቀው የቡድኑ አምበል ኢልካይ ጉንዶጋን " በቅርቡ ካሳየነው እንቅስቃሴ አንፃር ስለ አሸናፊነት ማውራት ማጋነን ይሆናል።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:00 ጅቡቲ ከ ኢትዮጵያ ( የአለም ዋንጫ ማጣሪያ )

ጨዋታውን ሰዓቱ ሲደርስ በተከታዩ ሊንክ መከታተል ይቻላል።

https://www.plus.fifa.com/en/content/433b88f1-a77d-4d70-8550-1541f6eee493?gl=ma

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥🔥 ለባልትና ቤቶች 🔥🔥
🫓🫓 ለወፍጮ ቤቶች 🫓🫓

አዲስ እና ዘመናዊ በኖርማል ቆጣሪ የሚሰራ ድንጋይ አልባ ዘመናዊ ማሽን ይዘንልዎ መጣን
ሩዝ፣ሽምብራ፣ገብስ አሳምሮ ይከካል ይፈትጋል ያበጥርራል
በሰአት  4 ኩንታል ይሰራል

ማንኛውም እህል፣ እንዲሁም ዛላ በርበሬን ጨምሮ በተለያየ ደረጃ ይፈጫል

የስፔር ፓርት ችግር እንዳያስቦ
ለበለጠ መረጃ መልእክት ይላኩልን
0951906772
@balagertech
https://www.tg-me.com/balager_technologies
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
TIKVAH-SPORT
ዩናይትድ ቴንሀግን ካሰናበተ ማንን ሊሾም ይችላል ? ማንችስተር ዩናይትድ የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን የክለቡ የወደፊት ቆይታ ከሚያደርገው የድህረ የውድድር አመት ግምገማ በኋላ ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል። ክለቡ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን የሚያሰናብት ከሆነ አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄልን ለመሾም ይመለከታል ሲባል የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ቶማስ ቱሄል ከመጀመሪያ ተመራጭነት መውጣታቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ ኤሪክ…
ቱሄል ዩናይትድን የመረከብ እቅድ እንደሌላቸው ተገለጸ !

ጀርመናዊው አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል አሁን ላይ ስማቸው በስፋት ሲያያዝ የነበረውን ማንችስተር ዩናይትድ በሀላፊነት ተረክበው የመምራት እቅድ እንደሌላቸው ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ ኤሪክ ቴንሀግን የሚያሰናብት ከሆነ ለመሾም ይመለከታቸዋል የተባሉትን አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ከመጀመሪያ ተመራጭነት እንዳወጣቸው መዘገቡ አይዘነጋም።

አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል በቅርቡ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር መነጋገራቸው የተገለፀ ሲሆን አሰልጣኙ በዚህ ክረምት እረፍት ለማድረግ መወሰናቸው ተነግሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን የወደፊት ቆይታ በዚህ ሳምንት ያሳውቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የኮንጎ ተጨዋቾች ሞሮኮ አንሄድም ማለታቸው ተገለጸ ! የሪፐብሊክ ኮንጎ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ከሞሮኮ ጋር ላለባቸው የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታ ወደ ስፍራው ለማቅናት ፍቃደኛ አለመሆናቸው ተገልጿል። ተጨዋቾቹ ወደ ሞሮኮ ለማምራት ፍቃደኛ ያልሆኑት በጉዞው ወቅት የተለያዩ ወጪዎችን በራሳቸው እንዲሸፍኑ ስለተነገራቸው መሆኑ ተዘግቧል። ተጨዋቾቹን ቅሬታ ውስጥ ካስገባቸው ምክንያቶች መካከልም…
የኮንጎ ተጨዋቾች ወደ ሞሮኮ አቅንተዋል !

የሪፐብሊክ ኮንጎ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች በሀገሪቱ ስፖርት ሚንስቴር ላይ በነበረባቸው ቅሬታ ምክንያት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ለማድረግ ወደ ሞሮኮ እንደማያመሩ መግለፃቸው ይታወሳል።

አሁን ላይ የተጨዋቾቹ ቅሬታዎች መፈታታቸው እና ጨዋታውን ለማድረግ ወደ ሞሮኮ ለማምራት መዘጋጀታቸው ተነግሯል።

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጣልቃ በመግባት ተጨዋቾቹን ያላስማሙ ክፍያዎች እንዲስተካከሉ እንዲሁም በተቀነሱ ሰራተኞች ተካተው የነበሩ ግለሰቦች እንዲቀሩ መደረጉ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
5 ' ጅቡቲ 0 - 0 ኢትዮጵያ ( የአለም ዋንጫ ማጣሪያ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
14 ' ጅቡቲ 0 - 0 ኢትዮጵያ ( የአለም ዋንጫ ማጣሪያ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
23 ' ጅቡቲ 0 - 0 ኢትዮጵያ ( የአለም ዋንጫ ማጣሪያ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
29 ' ጅቡቲ 1 - 0 ኢትዮጵያ ( የአለም ዋንጫ ማጣሪያ )

ዳድዜ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
30 ' ጅቡቲ 1 - 1 ኢትዮጵያ ( የአለም ዋንጫ ማጣሪያ )

ዳድዜ ምንይሉ ወንድሙ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/01 09:30:58
Back to Top
HTML Embed Code: