Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
ቶኒ ክሩስ በሪያል ማድሪድ አካዳሚ ይሰራል ! ጀርመናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶኒ ክሩስ በቀጣይ በሪያል ማድሪድ የታዳጊዎች ማሰልጠኛ አካዳሚ መስራት እንደሚጀመር አስታውቋል። ቶኒ ክሩስ በዚህ ክረምት ኮንትራቱ ሲጠናቀቅ ደማቅ የእግርኳስ ህይወት ካሳለፈበትከሪያል ማድሪድ ጋር እንደሚለያይ ይታወቃል። ቶኒ ክሩስ በተጨማሪም ከቀጣዩ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር በኋላ በይፋ ራሱን ከእግርኳስ እንደሚያገል ማስታወቁ…
ቶኒ ክሩስ የራሱን አካዳሚ ይከፍታል !

ጀርመናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶኒ ክሩስ  በቀጣይ ስፔን ማድሪድ ውስጥ የራሱን አካዳሚ ለመክፈት እየሰራ እንደሚገኝ ይፋ አድርጓል።

ቶኒ ክሩስ በቀጣይ ጫማውን ከሰቀለ በኋላ በሚከፍተው የራሱ አካዳሚ መስራት እንደሚጀምር ገልጿል።

ቶኒ ክሩስ በሪያል ማድሪድ አካዳሚ ስራ እንደሚጀመር ተገልፆ የነበረ ቢሆንም ዜናው " የትርጉም ስህተት " እንደነበረው እና የራሱን አካዳሚ እንደሚከፍት ታማኝ የመረጃ ምንጮች ገልፀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
✈️ አውሮፓ እንሂድ

🏆የምትወዱዋቸውን የአውሮፓ ታላላቆችን ዋንጫ ፍልሚያ በወር 350 ብር!

⚽️በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአውሮፓ ዋንጫ ሊጀመር ነው! በጀርመን የሚደረጉትን ደማቅ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,999 ብር ከ1 ወር ነፃ ሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#Euro2024 #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
🔥🔥 ለባልትና ቤቶች 🔥🔥
🫓🫓 ለወፍጮ ቤቶች 🫓🫓

አዲስ እና ዘመናዊ በኖርማል ቆጣሪ የሚሰራ ዘመናዊ ማሽ ይዘንልዎ መጣን
ሩዝ፣ሽምብራ፣ገብስ አሳምሮ ይከካል ይፈትጋል ያበጥርራል
በሰአት  4 ኩንታል ይሰራል

ማንኛውም እህል፣ እንዲሁም ዛላ በርበሬን ጨምሮ በተለያየ ደረጃ ይፈጫል

የስፔር ፓርት ችግር እንዳያስቦ
ለበለጠ መረጃ መልእክት ይላኩልን
0951906772
@balagertech
https://www.tg-me.com/balager_technologies
" ኤል ክላሲኮ አሜሪካ ውስጥ አይደረግም " ዣቪየር ቴባስ

የስፔን ላሊጋ ጨዋታዎችን በቀጣይ ከስፔን ውጪ በሌሎች ሀገሮች እንደመጀመሪያም በአሜሪካ ለማድረግ እቅድ መያዙ ይታወቃል።

የስፔን ላሊጋው ፕሬዝዳንት ዣቪየር ቴባስ በሰጡት አስተያየትም አሜሪካ ከሚደረጉ የላሊጋ ጨዋታዎች መሐል የኤል ክላሲኮ እንደማይካተት ገልጸዋል።

" የኤል ክላሲኮ ከስፔን ውጪ ሊደረግ የማይችል ጨዋታ ነው ሌሎች ጨዋታዎች ግን በቀጣይ አሜሪካ መደረግ ይችላሉ።" ሲሉ ፕሬዝዳንት ዣቪየር ቴባስ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጄሚ ቫርዲ ውሉን አራዝሟል !

እንግሊዛዊው የሌስተር ሲቲ የፊት መስመር ተጨዋች ጄሚ ቫርዲ በክለቡ ለተጨማሪ አመት ለመቆየት ውሉን ማራዘሙ ይፋ ተደርጓል።

የ 37ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ጄሚ ቫርዲ በሌስተር ሲቲ ቤት ለአንድ የውድድር አመት ለመቆየት መስማማቱ ተገልጿል።

ሌስተር ሲቲ ከአንድ የውድድር አመት የሻምፒዮን ሺፕ ቆይታ በኋላ በዚህ አመት ወደ ፕርሚየር ሊግ ሲያድግ ጄሚ ቫርዲ ሀያ ግቦችን በማስቆጠር የአንበሳውን ድርሻ መወጣት ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ካርሎ አንቾሎቲ የራሳቸውን መንገድ ይፈልጋሉ " ሮድሪጎ

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሮድሪጎ አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በቀጣይ የሎስ ብላንኮዎቹን ከዋክብት በአንድ ላይ ለማጫወት መንገድ ይፈልጋሉ ብሎ እንደሚጠብቅ ተናግሯል።

" ቡድናችንን ከተቀላቀሉት ኪሊያን ምባፔ እና ኢንድሪክ ጋር አንድ ላይ መጫወት እንችላለን " ያለው ሮድሪጎ " ካርሎ አንቾሎቲ የራሳቸውን መንገድ ይፈልጋሉ ብዬ እጠብቃለሁ ፣ ጥሩ ተጨዋቾች አንድ ላይ መጫወት አለባቸው።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዴክላን ራይስ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል ! እንግሊዛዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዴክላን ራይስ የተጠናቀቀው የውድድር አመት የአርሰናል የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን በሁለተኝነት ማጠናቀቅ ችሏል። ዴክላን ራይስ ከተሰጠው አጠቃላይ ድምፅ ሀያ አራት በመቶውን ( 24% ) በማግኘት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ተገልጿል። ፈረንሳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ዊሊያም ሳሊባ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ…
የአርሰናል የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

ኖርዌያዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማርቲን ኦዴጋርድ የተጠናቀቀው የውድድር አመት የአርሰናል የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን በአብላጫ ድምፅ መመረጥ ችሏል።

ማርቲን ኦዴጋርድ ከተሰጠው አጠቃላይ ድምፅ ሰላሳ ሶስት በመቶ ( 33% ) በማግኘት ማሸነፉ ተገልጿል።

እንግሊዛዊው ተጨዋች ዴክላን ራይስ ሁለተኛ እንዲሁም ፈረንሳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ዊሊያም ሳሊባ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ሲቲ ተጫዋቹን ሊሸጥ ነው !

የስፔን ላሊጋው ክለብ ሪያል ሶሴዳድ የማንችስተር ሲቲውን የግራ መስመር ተጫዋች ሰርጂዮ ጎሜዝ ለማስፈረም ንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ስፔናዊው የመስመር ተጨዋች ሰርጂዮ ጎሜዝ በዚህ ክረምት ማንችስተር ሲቲን እንደሚለቅ የሚጠበቅ ሲሆን ሪያል ሶሴዳድ በበኩሉ ተጫዋቹን ለማስፈረም በመስራት ላይ መሆናቸው ተነግሯል።

የ 23 ዓመቱ ተጫዋች ሰርጂዮ ጎሜዝ ከሁለት አመታት በፊት ከአንደርሌክት ማንችስተር ሲቲን በአራት ዓመት ኮንትራት መቀላቀሉ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የፈረንሳዩ ክለብ ኒስ ለሽያጭ ሊቀርብ ነው !

በእንግሊዛዊው ቢሊየነር ሰር ጂም ራትክሊፍ በሚመራው " INEOS " ባለቤትነት የተያዘው የፈረንሳዩ ክለብ ኒስ ለሽያጭ ሊቀርብ መሆኑ ተገልጿል።

ሰር ጂም ራትክሊፍ በኒስ ያላቸውን ከፍተኛ ድርሻ ለሽያጭ ለማቅረብ የፈለጉት በቅርቡ የአነስተኛ ድርሻ ባለቤት በሆኑበት ማንችስተር ዩናይትድ ለማተኮር እንደሆነ ተነግሯል።

በተጨማሪም በፈረንሳይ ሊግ እየተቀዛቀዘ የመጣው የፋይናንስ ሁኔታ እንግሊዛዊው ቢሊየነር ሰር ጂም ራትክሊፍ ኒሴን ለመሸጥ ካሳሰባቸው ምክንያቶች አንዱ መሆኑ ተገልጿል።

ዩኤፋ ባለቤቶቹ ማንችስተር ዩናይትድ እና ኒስን በዩሮፓ ሊግ ማሳተፍ እንዲችሉ የአንድ አመት ጊዜ የሰጠ መሆኑን ተከትሎ ሽያጩ ከዚህ ጋር እንደማይገናኝ ተጠቁሟል።

የፈረንሳይ ሊግ በሚቀጥለው የውድድር አመት ለማስተላለፍ ፍላጎት ያለው ተቋም እስካሁን አለማግኘቱ እና የስርጭት ገቢውም በግማሽ ሊቀንስ እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Stock Clearance Discount

📞 0925927457 @eBRO4
📞 0953964175 @heymobile

• iPhone 13, Black, 128 GB/ 80%
   54,000 ETB
• iPhone 13, Pink, 128 GB/ 85%
   56,000 ETB
• iPhone 13, White, 128 GB/ 86%
   56,000 ETB
• iPhone 13,  Black, 128 GB/ 90%
   57,000 ETB
• iPhone 13, Pink, 256 GB/ 84%
   58,000 ETB
• iPhone 13, Black, 256 GB 91%.  
   59,000 ETB
• iPhone 13 Pro, Blue, 128 GB/ 90%
   61,000 ETB
• iPhone 13 Pro, Black, 256 GB/ 83%
  65,000 ETB
• iPhone 13 Pro, Gold, 256 GB/ 87%. 
   67,000 ETB
• iPhone 13 Pro, Blue, 512 GB/ 88%
   65,000 ETB ⚠️
• 13 Pro Max, Black, 128 GB/ 87%
   74,000 ETB
• 13 Pro Max, white, 128 GB/ 87%. 
   72,000 ETB
• 13 Pro Max, Blue, 128 GB/ 98%.
   77,000 ETB
• 13 Pro Max, Blue, 256 GB/ 83%
   79,000 ETB 
• 13 Pro Max, Blue, 256 GB/ 85%
   77,000 ETB ⚠️
• 13 Pro Max, Blue, 256 GB/ 85%
   81,000 ETB 
• 14 Pro, Purple, 512 GB/ 90%,  
   75,000 ETB (E-SIM)
• 14 Pro Max, Purple 256 GB/ 89% 
   97,000

Exchange Available!
Free Delivery 🚚

@heyonlinemarket
❇️SMART ያልሆኑ TV SMART ለማድረግ ምን መግዛት እንዳለብዎ ካላወቁ  ይሄን እቃ ምርጫው ያድርጉ።

❇️የራሱ የሆነ BLUETOOTH ሪሞት ያለው ትክክለኛ 4K ምስል ጥራት ያለው

❇️የተለያዩ የፊልም እና የኳስ ቻናሎች የተጫኑበት በአጭር ጊዜ በሚቆ ይ ቅናሽ 3200 ብር ብቻ

Inbox Us 📩Admin @Sadikethio
Call 📱 +251 91 178 5693

የተለያዩ ነፃ የኳስ ቻናሎች የሚያገኙበት የዲሽ ቻናል 👇👇 https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAEnaa5LpZrcwQ-E0Tw
TIKVAH-SPORT
ለቲያጎ ሲልቫ አቀባበል በርካታ ትኬቶች ተሸጡ ! ብራዚላዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቲያጎ ሲልቫ ከቼልሲ ጋር በመለያየት ወደ ልጅነት ክለቡ ፍሉሚኔንሴ ለመመለስ ፊርማውን ማኖሩ ይታወሳል። ከአስራ አራት አመታት በኋላ ወደ ልጅነት ክለቡ ፍሉሚኔንሴ የሚመለሰው ቲያጎ ሲልቫ በሚቀጥለው ሳምንት አርብ በክለቡ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግለት ተገልጿል። በማራካኛ ስታዲየም ለቲያጎ ሲልቫ በሚደረገው አቀባባል…
ቲያጎ ሲልቫ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት !

በቅርቡ ከቼልሲ ጋር የተለያየው ብራዚላዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቲያጎ ሲልቫ በልጅነት ክለቡ ፍሉሚኔንሴ ደመቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

ቲያጎ ሲልቫ ከአስራ አራት አመታት በኋላ ወደ ልጅነት ክለቡ ፍሉሚኔንሴ በመመለስ ፊርማውን ማኖሩ የሚታወስ ነው።

በማራካኛ ስታዲየም ለቲያጎ ሲልቫ በተደረገው ደማቅ አቀባበል 55,000 የክለቡ ደጋፊዎች መገኘታቸው ተገልጿል።

በብራዚል እግርኳስ ታሪክ በርካታ ተመልካች የተገኘበት ይፋዊ የተጨዋች ትውውቅ በመሆንም አዲስ ሪከርድ መመዝገብ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊዮኔል ሜሲ በሌላ አለም ዋንጫ ይሳተፍ ይሆን ?

አርጀንቲናዊው የኢንተር ሚያሚ የፊት መስመር ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ በቀጣዩ የ2026 አለም ዋንጫ ውድድር ሊሳተፍ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል።

ሊዮኔል ሜሲ ሲናገርም በውድድሩ መሳተፌ " በአካል ብቃት ሁኔታዬ ፣ በሚሰማኝ ስሜት እንዲሁም መወዳደር በምችልበት ደረጃ እና ቡድኑን መርዳት በመቻሌ " ላይ የተመሰረተ ነው ብሏል።

የ2026 አለም ዋንጫ ውድድር ከሁለት አመት በኋላ በአሜሪካ ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ አዘጋጅነት የሚካሄድ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ቪንሰስ ባሎን ዶር ይገባዋል " ማርቲኔሊ

ብራዚላዊው የአርሰናል ፊት መስመር ተጨዋች ጋብሬል ማርቲኔሊ ቪንሰስ ጁኒየር የዘንድሮውን የባሎን ዶር ሽልማት ማሸነፍ እንደሚገባው በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

" ከቪንሰስ ጋር አብሮ መጫወት እና አብሮ መዋል ትልቅ ክብር ነው " ያለው ማርቲኔሊ ብራዚላውያን ደምቀው ስናይ በጣም እንደሰታለን በእኔ አስተያየት ቪንሰስ የባሎን ዶር ሽልማትን ማሸነፍ አለበት ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አሜሪካ ኮፓ አሜሪካን የማሸነፍ አቅም አላት "

የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን እና ኤሲ ሚላን የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቲያን ፑልሲች ቡድናቸው ቀጣዩን የኮፓ አሜሪካ ውድድር ማሸነፍ እንደሚፈልግ ተናግሯል።

ክርስቲያን ፑልሲች በንግግሩም " ዋንጫውን ማሸነፍ እንፈልጋለን " ያለ ሲሆን በውድድሩ ከመጀመሪያው የቻልነውን ሁሉ እናደርጋለን ለአላማችን ዋንጫ ማሸነፍ ነው ሲል ተደምጧል።

ለጁቬንቱስ የሚጫወተው ማኬኒ በበኩሉ " እኛ በትልቅ ክለብ የሚጫወቱ ጥሩ ተጨዋቾች አሉን ፣ ዋንጫውን ማሸነፍ እንፈልጋለን ፣ አሜሪካ የዋንጫ ተፎካካሪ የመሆን አቅም አላት ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ስቴፋን ኦርቴጋ ውሉን ያራዝማል !

ጀርመናዊው የማንችስተር ሲቲ ግብ ጠባቂ ስቴፋን ኦርቴጋ በክለቡ ለተጨማሪ ሁለት የውድድር አመታት ለመቆየት ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።

ግብ ጠባቂው ከማንችስተር ሲቲ ጋር ሙሉ የቃል ስምምነት መፈፀሙ ሲገለፅ በቀጣይ በይፋ ውሉን ያራዝማል ተብሎ ይጠበቃል።

ስቴፋን ኦርቴጋ በእንግሊዝ እና አውሮፓ ክለቦች ቢፈለግም በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን ውስጥ ለመቆየት መወሰኑ ተነግሯል።

ማንችስተር ሲቲዎች በቅርቡ የ 38ዓመቱን እንግሊዛዊ ግብ ጠባቂ ስኮት ካርሰን ኮንትራት ለአንድ የውድድር አመት ማራዘማቸው አይዘነጋም።

ብራዚላዊው የማንችስተር ሲቲ ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ ኤደርሰን በበኩሉ እስካሁን በክለቡ ያለው የወደፊት ቆይታ የተረጋገጠ አይደለም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በቤቲካ ፋስታ ወዲያው ያሸንፉ!  አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
2024/10/04 21:18:12
Back to Top
HTML Embed Code: