Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ አሰልጣኙን መቼ ያስተዋውቃል ? የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ጣልያናዊውን የሌስተር ሲቲ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካን በሀላፊነት መሾማቸውን በዛሬው ዕለት በይፋ ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በሰማያዊዎቹ ቤት ለአንድ ተጨማሪ አመት የማራዘም አማራጭ ያካተተ የአምስት አመት ኮንትራት መፈረማቸው ተገልጿል። የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ተሳታፊው ሌስተር ሲቲ ከቼልሲ የአስር ሚልዮን…
ቼልሲ በይፋ አሰልጣኝ መሾሙን አሳወቀ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ጣልያናዊውን የቀድም የሌስተር ሲቲ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በዋና አሰልጣኝነት መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በሰማያዊዎቹ ቤት ለአንድ ተጨማሪ አመት የማራዘም አማራጭ ያካተተ የአምስት አመት ኮንትራት መፈረማቸው ተገልጿል።

በዚህ አመት ከአንድ የውድድር ዘመን የሻምፒዮን ሺፕ ቆይታ በኋላ ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ያደገው ሌስተር ሲቲ ከቼልሲ የአስር ሚልዮን ፓውንድ የካሳ ክፍያ ማግኘታቸው ተነግሯል።

አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ወደ ቼልሲ ቤት የሚመጡት #ስድስት የራሳቸውን የአሰልጣኞች ቡድን በመያዝ መሆኑ ታውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ በይፋ አሰልጣኝ መሾሙን አሳወቀ ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ጣልያናዊውን የቀድም የሌስተር ሲቲ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በዋና አሰልጣኝነት መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል። አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በሰማያዊዎቹ ቤት ለአንድ ተጨማሪ አመት የማራዘም አማራጭ ያካተተ የአምስት አመት ኮንትራት መፈረማቸው ተገልጿል። በዚህ አመት ከአንድ የውድድር ዘመን የሻምፒዮን ሺፕ ቆይታ በኋላ ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር…
" ቼልሲን ማሰልጠን የሁሉም አሰልጣኝ ህልም ነው " ኢንዞ ማሬስካ

ሰማያዊዎቹን በሀላፊነት የተረከቡት ጣልያናዊው አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ከፊርማው በኋላ ቼልሲን የሚያክል ትልቅ ክለብ ማሰልጠን ህልማቸው መሆኑን ገልፀዋል።

" ቼልሲ በአለም ላይ ካሉ ትልቅ ክለቦች አንዱ ነው " ያሉት አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ " በዚህም ምክንያት ቼልሲን ማሰልጠን የሁሉም አሰልጣኝ ህልም ነው እድሉን በማግኘቴ ተደስቻለሁ " ሲሉ ተደምጠዋል።

ከባለተሰጥኦ የቼልሲ ተጨዋቾች ስብስብ ጋር ለመስራት " ጓጉቻለሁ " ያሉት አሰልጣኙ በቀጣይ የቼልሲ ባህል የሆነውን #ስኬት ለማስቀጠል እና ደጋፊውን ለማስደሰት እንሰራለን ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📢 እስከ ግንቦት 30 ብቻ የሚቆይ የሽያጭ ብስራት!

🔥 #እንዳያመልጥዎ፣ አሁኑኑ ይዘዙን!

📍አድራሻችን:- ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት፣ አለም ገብሬ ህንፃ፣ 2ተኛ ፎቅ።

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WANAWSbot በኩል ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
TIKVAH-SPORT
" ቼልሲን ማሰልጠን የሁሉም አሰልጣኝ ህልም ነው " ኢንዞ ማሬስካ ሰማያዊዎቹን በሀላፊነት የተረከቡት ጣልያናዊው አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ከፊርማው በኋላ ቼልሲን የሚያክል ትልቅ ክለብ ማሰልጠን ህልማቸው መሆኑን ገልፀዋል። " ቼልሲ በአለም ላይ ካሉ ትልቅ ክለቦች አንዱ ነው " ያሉት አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ " በዚህም ምክንያት ቼልሲን ማሰልጠን የሁሉም አሰልጣኝ ህልም ነው እድሉን በማግኘቴ ተደስቻለሁ…
ቼልሲ ቀጣይ አመት ከአሰልጣኙ ምን ይጠብቃል ?

አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካን በሀላፊነት የሾሙት ቼልሲዎች በሚቀጥለው የውድድር ዘመን አሰልጣኙ ሊያሳኳቸው የሚገቧቸውን የመጀመሪያ ግቦች ማስቀመጣቸው ተገልጿል።

ጣልያናዊው አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን ቼልሲን በሀላፊነት እየመሩ

- የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ቦታን ማግኘት

- ለኤፌ ካፕ እና ካራባኦ ካፕ ዋንጫዎች መፎካከር

- በኮንፈረንስ ሊግ ለዋንጫ መፎካከር

- ለአዲሱ የክለቦች አለም ዋንጫ መፎካከር የመጀመሪያ ግባቸው እንደሚሆን ተገልጿል።

አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በበኩላቸው አሁን ያለው የቼልሲ የቡድን ስብስብ የአውሮፓ የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ቦታን ለማግኘት ከበቂ በላይ መሆኑን መግለፃቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
Photo
ፖርቹጋል ተጨዋቿ ከአውሮፓ ዋንጫ ውጪ ሆነ !

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ጥሪ አቅርቦለት የነበረው የአል ናስር የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኦታቪዮ በጉዳት ምክንያት ከአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ውጪ መሆኑ ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ በኦታቪዮ ምትክ የማንችስተር ሲቲው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማቲውስ ኑኔስ ከፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ለአውሮፓ ዋንጫው ጥሪ እንደቀረበለት ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፋብዮ ግሮሶ በሀላፊነት ተሾመ !

የቀድሞው ጣልያናዊ ተጨዋች ፋብዮ ግሮሶ ወደ ጣልያን ሁለተኛ ሊግ የወረደው ሳሱሎ ዋና አሰልጣኝ በመሆን መሾሙ ይፋ ተደርጓል።

ጣልያን እ.ኤ.አ 2006 ፈረንሳይን በመለያ ምት አሸንፋ የዓለም ዋንጫን ስታሳካ የመጨረሻዋን መለያ ምት ማስቆጠር የቻለው ፋብዮ ግሮሶ በቅርቡ ሊዮንን በሀላፊነት ተረክቦ በሁለት ወራት መሰናበቱ አይዘነጋም።

ፋብዮ ግሮሶ በዚህ አመት አስራ ዘጠነኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ወደ ሲሪ ቢ የወረደውን ሳሱሎ ለሁለት አመት ለማሰልጠን መስማማቱ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማድሪድ የምባፔን ዝውውር ይፋ ሊያደርጉ ነው ! ሪያል ማድሪድ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔን ከፒኤስጂ በነፃ ዝውውር ማስፈረማቸውን ዛሬ ወይም በሚቀጥሉት ቀናት በይፋ  እንደሚያሳውቁ ተገልጿል። በቅርቡ ፒኤስጂን ከሰባት አመት በኋላ እንደሚለቅ ይፋ ያደረገው ኪሊያን ምባፔ ለሪያል ማድሪድ የአምስት አመት ኮንትራት መፈረሙን ለክለቡ ቅርበት ያላቸው ምንጮች አረጋግጠዋል። ኪሊያን ምባፔ…
ሪያል ማድሪድ ኪሊያን ምባፔን በይፋ አስፈረመ !

የስፔኑ ሀያል ክለብ ሪያል ማድሪድ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ከፒኤስጂ በነፃ ዝውውር ማስፈረማቸውን ከደቂቃዎች በፊት ይፋ አድርገዋል።

የ 25ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ለሪያል ማድሪድ እስከ 2029 የውድድር ዘመን የሚያቆየውን የ#አምስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ይፋ ሆኗል።

ኪሊያን ምባፔ ለሪያል ማድሪድ በመፈረሙ ምክንያት የፊርማ ጉርሻ በአምስት አመታት ተከፋፍሎ የሚከፈል 100 ሚልዮን ዩሮ እንደሚያገኝ ተገልጿል።

ኪሊያን ምባፔ በሪያል ማድሪድ ቤት የዘጠኝ ቁጥር ማልያ እንደሚለብስ ሲገለፅ በቀጣይ የሉካ ሞድሪችን አስር ቁጥር እንደሚረከብ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሪያል ማድሪድ ኪሊያን ምባፔን በይፋ አስፈረመ ! የስፔኑ ሀያል ክለብ ሪያል ማድሪድ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ከፒኤስጂ በነፃ ዝውውር ማስፈረማቸውን ከደቂቃዎች በፊት ይፋ አድርገዋል። የ 25ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ለሪያል ማድሪድ እስከ 2029 የውድድር ዘመን የሚያቆየውን የ#አምስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ይፋ ሆኗል። ኪሊያን ምባፔ ለሪያል ማድሪድ በመፈረሙ…
" የአመታት ህልሜ እውን ሆኖልኛል " ምባፔ

ሪያል ማድሪድን በይፋ የተቀላቀለው ፈረንሳዊው ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ የአመታት ህልሙ እውን እንደሆነለት በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው መልዕክት ገልጿል።

" ህልሜ እውን ሆኗል ለአመታት ሳልመው ለነበረው ሪያል ማድሪድ በመፈረሜ ከፍተኛ ደስታ እና ኩራት ተሰምቶኛል " ያለው ምባፔ በአሁን ሰዓት የሚሰማኝን ስሜት ለመግለጽ እቸገራለሁ ሜዳ ላይ እስክጀምር ጓጉቻለሁ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሳድዮ ማኔ ከሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ውጪ ሆነ !

ሴኔጋላዊው የአል ናስር የፊት መስመር ተጨዋች ሳዲዮ ማኔ በጉዳት ምክንያት ከሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውጪ መሆኑ ተገልጿል።

ሳድዮ ማኔ ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ከጉዳት ጋር መምጣቱን እና በተደረገለት ምርመራ ለጨዋታ ብቁ አለመሆኑ እንደተረጋገጠ የሴኔጋል እግርኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል።

ሴኔጋል በቀጣይ ከኮንጎ እና ሞሪታንያ ብሔራዊ ቡድኖች ጋር የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታዋን የምታደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኦማሪ ፎርሰን ዩናይትድን ሊለቅ ነው !

የማንችስተር ዩናይትዱ ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ኦማሪ ፎርሰን በዚህ ክረምት ኮንትራቱ ሲጠናቀቅ ክለቡን ሊለቅ መሆኑ ተገልጿል።

በቅርቡ ለዋናው ቡድን ተሰልፎ በመጫወት ጥሩ እንቅስቃሴ ማሳየት የቻለው ኦማሪ ፎርሰን በነፃ ዝውውር ማንችስተር ዩናይትድን እንደሚለቅ ተነግሯል።

የ 19ዓመቱን የፊት መስመር አጥቂ ኦማሪ ፎርሰንን በነፃ ዝውውር ለማስፈረም በርካታ ክለቦች ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Austria - Serbia
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 15 Promax
•256GB = 139,000 Birr
•512GB = 159,000 Birr

Samsung 24 Ultra
•256GB = 111,000 Birr
•512GB = 128,000 Birr

Contact us :
0953964175 @heymobile
0925927457

@Heyonlinemarket
" ከእነሱ የተሻለ ለመሆን እንጥራለን " አርቴታ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው በሚቀጥለው የውድድር አመት ማንችስተር ሲቲን መፎካከሩን እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

" በመጨረሻው ሰዓት ዋንጫ ማጣታችን ያበሳጫል " ያሉት ሚኬል አርቴታ ለፔፕ ጋርዲዮላ እና ሰራተኞቻቸው እንኳን ደስ አላችሁ ብያቸዋለሁ በመጨረሻ ይገባቸዋል አሸናፊ ናቸው።"ብለዋል።

" ነገርግን እኛ አሁንም እነሱን ለማቆም መሞከራችንን አናቋርጥም " ያሉት አሰልጣኙ  ከእነሱ የተሻልን የመሆን ጥረት ማድረጋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጎንሳሎ ኢናስዮ ወዴት ያመራ ይሆን ?

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊስበኑ የመሐል ተከላካይ ጎንሳሎ ኢናስዮ በእንግሊዝ ታላላቅ ክለቦች እየተፈለገ እንደሚገኝ ተዘግቧል።

ካለፈው አመት ጀምሮ ፖርቹጋላዊውን ጎንሳሎ ኢናስዮ ሲከታተሉ የቆዩት ሊቨርፑሎች አሁን ላይ በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ሊንቀሳቀሱ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህ ክረምት ሁለት የመሐል ተከላካይ ለማስፈረም ያቀደው ማንችስተር ዩናይትድ በበኩሉ ተጫዋቹን አንዱ ፈራሚ ለማድረግ እየተከታተሉ እንደሚገኙ እና ማስፈረም እንደሚፈልጉ ተነግሯል።

የ 22ዓመቱ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጎንሳሎ ኢናስዮ በፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊስበን ቤት ያለው ውል ማፍረሻ 60 ሚልዮን ዩሮ እንደሚደርስ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኔይማር በአል ሂላል እንደሚቀጥል ገለጸ !

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኔይማር በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ሂላል ቤት እንደሚቀጥል ተናግሯል።

ከአል ሂላል ጋር ሶስት ዋንጫዎች በማሳካቱ መደሰቱን የገለፀው ኔይማር " ቀጣይ አመት በአል ሂላል እቆያለሁ እዚህ አንድ አመት ውል አለኝ ቀጣይ አመት ከአል ሂላል ጋር ጥሩ አመት ማሳለፍ እፈልጋለሁ።"ብሏል።

ኔይማር አያይዞም አል ሂላል አል ናስርን አሸንፎ የሳውዲ አረቢያ ኪንግስ ካፕ ዋንጫን ካሸነፈ በኋላ ሊዮኔል ሜሲ የእንኳን ደስ አለህ መልዕክት እንደላከለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል በቀጣይ ምን ማስፈረም ይፈልጋል ?

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት የፊት መስመራቸውን ለማጠናከር አጥቂ ለማስፈረም በዝግጅት ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም መድፈኞቹ የግራ መስመር ተጨዋች ለማስፈረም እየተመለከቱ መሆኑ ሲዘገብ ሶስተኛ ግብ ጠባቂም ለማስፈረም ከሚመለከቱት የሜዳ ክፍል አንዱ መሆኑ ተነግሯል።

አርሰናል በቀጣይ ለማስፈረም የሚመለከተው የፊት መስመር ተጨዋች የሌፕዚጉ ቤንጃሚን ሴስኮ መሆኑ ሲገለፅ ተጨዋቹ በውሉ ውስጥ ውል ማፍረሻ 65 ሚልዮን ዩሮ መኖሩ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም የኒውካስል ዩናይትዱ አሌክሳንደር አይሳክ ፣ የዎልቭሱ ፔድሮ ኔቶ እና የአትሌቲክ ቢልባኦው ኒኮ ዊልያምስ በዝርዝራቸው ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ አዲስ አጥቂ ማስፈረም ይፈልጋል !

አዲስ አሰልጣኝ የሾመው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በቀጣይ አዲስ የፊት መስመር አጥቂ ለማስፈረም ወደ ዝውውር ገበያው እንደሚገቡ ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ ስማቸው በስፋት ሲያያዝ ከቆዩት ቪክቶር ኦሲሜን እና ኢቫን ቶኒ ዝውውር በተለያዩ ምክንያቶች ራሳቸውን ማስወጣታቸው ተነግሯል።

ቼልሲ በቀጣይ ክረምት የክሪስታል ፓላሶቹን ተጨዋቾች ሚሼል ኦሊሴ እና ኢበሪች ኢዜ ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል።

በአሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የሚመራው ቼልሲ በተጨማሪም ወደ ሻምፒዮን ሺፑ የወረደው በርንሌይ ግብ ጄምስ ትራፎርድን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ጎንሳሎ ኢናስዮ ወዴት ያመራ ይሆን ? የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊስበኑ የመሐል ተከላካይ ጎንሳሎ ኢናስዮ በእንግሊዝ ታላላቅ ክለቦች እየተፈለገ እንደሚገኝ ተዘግቧል። ካለፈው አመት ጀምሮ ፖርቹጋላዊውን ጎንሳሎ ኢናስዮ ሲከታተሉ የቆዩት ሊቨርፑሎች አሁን ላይ በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ሊንቀሳቀሱ መሆኑ ተገልጿል። በዚህ ክረምት ሁለት የመሐል ተከላካይ ለማስፈረም ያቀደው ማንችስተር…
ዩናይትድ በቀጣይ ምን ሊያስፈርም ይችላል ?

ማንችስተር ዩናይትድ በሚቀጥለው ክረምት የመሐል ተከላካዮች ፣ አማካይ እና የፊት መስመር አጥቂ ለማስፈረም ወደ ዝውውር ገበያው እንደሚገቡ ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች በቀጣይ ክረምት ለማስፈረም ከተመለከቷቸው ተከላካዮች የኤቨርተኑ እንግሊዛዊ ተጨዋች ጃሬድ ብራንዝዌት ቀዳሚው መሆኑ ተነግሯል።

ኤቨርተን ለ 21ዓመቱ ተከላካይ ጃሬድ ብራንዝዌት ጥሩ ዋጋ እንደሚፈልጉ ሲገለፅ ሀሪ ማጓየር ፣ ዊስሌይ ፎፋና እና ጆስኮ ቫርዲዮል ባለፉት ጊዜያት የተሸጡበት ሒሳብ ( ከ £75m በላይ ) ይገባዋል የሚል እምነት እንዳላቸው ተዘግቧል።

በተጨማሪም ማንችስተር ዩናይትድ የኒሱን ተከላካይ ጂያን ቶዲቦ እና ቼልሲን በነፃ ለመቀላቀል የተቃረበውን የፉልሀም ተጨዋች ቶሲን አዳራብዮ የማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል።

በፊት መስመሩ በኩል ማንችስተር ዩናይትድ ለአመታት የተከታተሉትን የሌፕዚግ ተጨዋች ቤንጃሚን ሴስኮ በቅርበት እየተከታተሉ መሆኑ ሲገለፅ ከሌላኛው የሊጉ ክለብ አርሰናል ከፍተኛ ፉክክር ይጠብቃቸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/03 23:29:56
Back to Top
HTML Embed Code: