Telegram Web Link
" የቱርክ እግርኳስ እንዲሻሻል መርዳት እፈልጋለሁ " ሞሪንሆ

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ በዛሬው ዕለት የቱርኩ ክለብ ፌነርባቼ ዋና አሰልጣኝ በመሆን በይፋ በሀላፊነት ተሾመዋል።

የክለቡ ደጋፊዎች በተገኙበት በስታዲየሙ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ " እግርኳስ ፍቅር ነው ለእሱ ደግም ከዚህ የተሻለ ቦታ ፈፅሞ አይገኝም " ሲሉ ገልጸዋል።

የቱርክ እግርኳስ እንዲሻሻል ማገዝ እንደሚፈልጉ ለደጋፊው ባደረጉት ንግግር የገለፁት አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ " ነገርግን ቅድሚያ የምሰጠው ለፌነርባቼ ነው አሁን ህልማችሁ ህልሜ ሆኗል " በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 15 Promax
•256GB = 139,000 Birr
•512GB = 159,000 Birr

Samsung 24 Ultra
•256GB = 111,000 Birr
•512GB = 128,000 Birr

Contact us :
0953964175 @heymobile
0925927457

@Heyonlinemarket
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Germany - Ukraine
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
ማድሪድ በርካታ ደጋፊዎቹን ይዞ ድሉን አክብሯል !

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አሸናፊው ሪያል ማድሪድ የዋንጫ ድላቸውን ወደሚያከብሩበት ታሪካዊ ቦታ ሴቤሌስ በማምራት እንዲሁም በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም ከደጋፊዎቻቸው ጋር አክብረዋል።

ሪያል ማድሪድ ባዘጋጀው የጎዳና ላይ ክብረ በዓሉ ላይ ከ550,000 በላይ ደጋፊዎች የዋንጫ ድሉን ለማክበር መገኘታቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም 80,000 ደጋፊዎች ሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም መገኘታቸው ሲገለፅ በድምሩ ከ600,000 በላይ ደጋፊዎች በዓሉን አደባባይ በመውጣት ማክበራቸው ተነግሯል።

በክብረ በዓሉ ላይ ለደጋፊው ንግግር ያደረጉት አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ " ዋንጫ የማሸነፍ ቆንጆው ነገር ደስታውን ከእናንተ ጋር መካፈል ነው ይህ ለእኛ ትልቅ ደስታ ይሰጠናል።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማርኮ ሪዮስ ወደ አሜሪካ ? በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከ ቦርስያ ዶርትመንድ ጋር የሚለያየው ማርኮ ሪዮስ ከአሜሪካ ሊግ ክለቦች ጥያቄ እየቀረበለት መሆኑ ተገልጿል። የሊጉ ክለብ ሴንት ሉዊስ ማርኮ ሪዮስን ለማስፈረም የቅድመ ውይይት ማድረጋቸው ተዘግቧል። ማርኮ ሪዮስ የቅርብ ጓደኛው እና የቀድሞ የቡድን አጋሩ ግብ ጠባቂው ሮማን ቡርኪ በሴንት ሉዊስ መጫወቱ ወደ አሜሪካ የሚያቀናበትን እድል ሰፊ አድርጎታል።…
ማርኮ ሪዮስ ወደ አሜሪካ ሊያቀና ነው !

በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከ ቦርስያ ዶርትመንድ ጋር የተለያየው ማርኮ ሪዮስ በቀጣይ ወደ አሜሪካ ሜጀር ሊግ ለማምራት ንግግር ላይ መሆኑ ተገልጿል።

ማርኮ ሪዮስን ለማስፈረም የአሜሪካው ሎስ አንጀለስ ጋላክሲ ክለብ ንግግር መጀመሩ ሲገለፅ ለስምምነት መቃረባቸው ተዘግቧል።

የ 35ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማርኮ ሪዮስ ከቦርስያ ዶርትመንድ ጋር ከአስራ ሁለት አመታት ቆይታ በኋላ መለያየቱ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ብራይተን ግራም ፖተርን መመለስ ይፈልጋል !

ብራይተን የቀድሞ እንግሊዛዊ አሰልጣኛቸውን ግራም ፖተር በድጋሜ በሀላፊነት ለመሾም በማሰብ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

የ 49ዓመቱ አሰልጣኝ ግራም ፖተር ባለፈው አመት ሚያዝያ ወር ከምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ከተሰናበቱ በኋላ ያለ ሀላፊነት ይገኛሉ።

ብራይተን በበኩሉ በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ከጣልያናዊው አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ ጋር መለያየቱ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ አሰልጣኝ ለመሾም ተስማማ ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የሌስተር ሲቲውን አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካን በሀላፊነት ለመሾም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በሰማያዊዎቹ ቤት ለአንድ ተጨማሪ አመት የማራዘም አማራጭ ያካተተ የአምስት አመት ኮንትራት ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል። በዚህ አመት ከአንድ አመት በኋላ ወደ ፕርሚየር ሊግ የተመለሱት ሌስተር ሲቲዎች ከቼልሲ የካሳ ክፍያ…
ቼልሲ አሰልጣኙን መቼ ያስተዋውቃል ?

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ጣልያናዊውን የሌስተር ሲቲ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካን በሀላፊነት መሾማቸውን በዛሬው ዕለት በይፋ ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በሰማያዊዎቹ ቤት ለአንድ ተጨማሪ አመት የማራዘም አማራጭ ያካተተ የአምስት አመት ኮንትራት መፈረማቸው ተገልጿል።

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ተሳታፊው ሌስተር ሲቲ ከቼልሲ የአስር ሚልዮን ፓውንድ የካሳ ክፍያ መቀበላቸው ተነግሯል።

አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ወደ ቼልሲ ቤት የሚመጡት #ስድስት የራሳቸውን የአሰልጣኞች ቡድን በመያዝ መሆኑ ታውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማድሪድ የምባፔን ዝውውር መቼ ያሳውቃል ? ሪያል ማድሪድ የፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ዝውውር ከ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር መጀመር በፊት ይፋ ለማድረግ ማሰባቸው ተገልጿል። የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ኪሊያን ምባፔ ከ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር በፊት ቀጣይ ክለቡን እንዲያሳውቅ ፍቃድ መስጠታቸው ተነግሯል። ሎስ ብላንኮዎቹ አዲስ ፈራሚያቸው የሚሆነውን ኪሊያን ምባፔ የተለየ…
ማድሪድ የምባፔን ዝውውር ይፋ ሊያደርጉ ነው !

ሪያል ማድሪድ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔን ከፒኤስጂ በነፃ ዝውውር ማስፈረማቸውን ዛሬ ወይም በሚቀጥሉት ቀናት በይፋ  እንደሚያሳውቁ ተገልጿል።

በቅርቡ ፒኤስጂን ከሰባት አመት በኋላ እንደሚለቅ ይፋ ያደረገው ኪሊያን ምባፔ ለሪያል ማድሪድ የአምስት አመት ኮንትራት መፈረሙን ለክለቡ ቅርበት ያላቸው ምንጮች አረጋግጠዋል።

ኪሊያን ምባፔ በሪያል ማድሪድ ቤት ከዚህ በፊት ቀርቦለት ከነበረው ደሞዝ ያነሰ እንደሚያገኝ ሲገለፅ ከክለቡ ከፍተኛ ተከፋይ ተጨዋቾች እኩል ያገኛል ተብሏል።

ተጫዋቹን ያለምንም የዝውውር ሒሳብ በነፃ የሚያስፈርሙት ሎስ ብላንኮዎቹ ለኪሊያን ምባፔ የፊርማ ጉርሻ በአምስት አመታት ውስጥ የሚከፈል ከ100 ሚልዮን ዩሮ በላይ እንደሚያወጡ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኪሊያን ምባፔ ከኦሎምፒክ ውጪ ሆነ !

የፈረንሳይ ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቴሪ ሄንሪ ለቀጣዩ የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ለተጨዋቾች ጥሪ አቅርበዋል።

ፈረንሳይ ኪሊያን ምባፔን በኦሎምፒክ ውድድር ለማሳተፍ ጥረት ብታደርግም ሳይሳካላት ቀርቶ ተጫዋቹን በቡድኑ ስብስብ ማካተት አልቻለችም።

አሌክሳንደር ላካዜት እና የክሪስታል ፓላሱ ጂያን ፊሊፕ ማቴታ በበኩላቸው በአሰልጣኝ ቴሪ ሄንሪ የኦሎምፒክ ቡድን ውስጥ መካተት ችለዋል ።

ሙሉ የቡድን ስብስቡ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ከተጨዋቹ ጋር እንደሚለያይ ይፋ አደረገ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በውድድር አመቱ መጨረሻ ኮንትራታቸው ከሚጠናቀቅ ሶስት ሴት ተጨዋቾችን ጨምሮ ከሀያ ሁለት ተጨዋቾቻቸው ጋር እንደሚለያዩ ይፋ አድርገዋል።

ክለቡን በነፃ ዝውውር ከሚለቁ ተጨዋቾች መካከል ፖርቹጋላዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሴድሪክ ሱዋሬዝ አንዱ መሆኑን መድፈኞቹ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ከግብፃዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች መሐመድ ኤልኔኒ ጋር መለያየታቸው በይፋ ገልፀዋል።

አርሰናልን የሚለቁ ቀሪ ተጨዋቾች ከላይ በምስሉ ተያይዘዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የሆሴሉ የሪያል ማድሪድ ቆይታ ? የሎስ ብላንኮዎቹ ዋና አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ እንዲሁም ክለቡ የፊት መስመር አጥቂው ሆሴሉ ለቡድኑ በሚያደርገው ነገር ደስተኛ መሆናቸው ተገልጿል። ተጨዋቹ በሪያል ማድሪድ ቤት በፍጥነት መላመዱ እና እያሳየ የሚገኘው እንቅስቃሴ ሁሉንም ማሳመኑ ሲነገር በቀጣይ ስለወደፊት ቆይታው ዙሪያ እንደሚነጋገሩ ተዘግቧል። ባለፈው ክረምት በውሰት ሪያል ማድሪድን የተቀላቀለው ሆሴሉ…
ሆሴሉ ለሪያል ማድሪድ በቋሚነት ይፈርማል !

ሪያል ማድሪድ በውሰት እየተጫወተ የሚገኘውን ስፔናዊው የፊት መስመር አጥቂ ሆሴሉ ለሚቀጥለው የውድድር አመት በቋሚነት ለማስፈረም መወሰናቸው ተገልጿል።

ሎስ ብላንኮዎቹ ሆሴሉን ባለፈው ክረምት በውሰት 500,000 ዩሮ በማውጣት ያስፈረሙት ሲሆን ተጫዋቹም በወሳኝ ጨዋታዎች ግብ በማስቆጠር ለክለቡ ጥሩ ግልጋሎት መስጠት ችሏል።

ሪያል ማድሪዶች ተጫዋቹን በውሉ ውስጥ የተካተተውን በቋሚነት የማስፈረም አማራጭ ተጠቅመው 1.5 ሚልዮን ዩሮ ወጪ በማድረግ እንደሚያስፈርሙት ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ካሴሚሮ ወደ አል ናስር ?

የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ናስር ብራዚላዊውን የማንችስተር ዩናይትድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ካሴሚሮ ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል።

አል ናስር በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ካሴሚሮን ለማስፈረም እስከ 80 ሚልዮን ፓውንድ የሚደርስ ሒሳብ ለማቅረብ መዘጋጀታቸው ተነግሯል።

በቀያዮቹ ሴጣኖች ቤት የአንድ አመት ውል ያለው ካሴሚሮ በዚህ ክረምት ጥሩ የዝውውር ጥያቄዎች የሚቀርቡለት ከሆነ ማንችስተር ዩናይትድን እንደሚለቅ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/04 09:32:13
Back to Top
HTML Embed Code: