Telegram Web Link
" ጨዋታውን ተሸንፈናል " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከምሽቱ የፍፃሜ ጨዋታ በኋላ በሰጡት አስተያየት ለማንችስተር ዩናይትድ " እንኳን ደስ አላችሁ " ብለዋል።

በጨዋታው ምን እንደተፈጠረ የተጠየቁት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ " ፍፃሜ ጨዋታውን ተሸንፈናል ለእነሱ እንኳን ደስ አላችሁ " በማለት ተናግረዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ ጨዋታውን ያሸነፈው ከማንችስተር ሲቲ የተሻለ ተጫውቶ እንደሆነ አስተያየት የተጠየቁት አሰልጣኙ " የተሻለ አልነበረም " ሲል መልሰዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፈረሰኞቹ ድል አድርገዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሲዳማ ቡና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የፈረሰኞቹን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አማኑኤል ኤርቦ ከመረብ አሳርፏል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሰባት ጨዋታዎች በኋላ የመጀመሪያ ድሉን ማስመዝገብ ችሏል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

4️⃣ ቅዱስ ጊዮርጊስ :- 43 ነጥብ

1️⃣2️⃣ ሲዳማ ቡና :- 31 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በቆይታዬ ምንም ጥርጣሬ የለኝም " ቴንሀግ

የኤፌ ካፕ ዋንጫን ያሳካው የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በሚቀጥለው አመት የክለቡ አሰልጣኝ ስለመሆኔ " ጥርጣሬ የለኝም " በማለት ተናግረዋል።

እኔ የማደርገው ብቸኛው ነገር ቡድኔን ማዘጋጀት እና ማሻሻል ነው ያሉት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ " በሚቀጥለው የውድድር አመት የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ስለመሆኔ ጥርጣሬ የለኝም " ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" በቆይታዬ ምንም ጥርጣሬ የለኝም " ቴንሀግ የኤፌ ካፕ ዋንጫን ያሳካው የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በሚቀጥለው አመት የክለቡ አሰልጣኝ ስለመሆኔ " ጥርጣሬ የለኝም " በማለት ተናግረዋል። እኔ የማደርገው ብቸኛው ነገር ቡድኔን ማዘጋጀት እና ማሻሻል ነው ያሉት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ " በሚቀጥለው የውድድር አመት የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ስለመሆኔ ጥርጣሬ የለኝም " ብለዋል።…
" ዩናይትድ ካልፈለገኝ ዋንጫ ለማሸነፍ ሌላ ቦታ እሄዳለሁ " ኤሪክ ቴንሀግ

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በቀጣይ ክለቡ እንደማይፈልጋቸው ከነገራቸው ዋንጫ ለማሸነፍ ሌላ ቦታ እንደሚሄዱ ተናግረዋል።

" በሁለት አመት ውስጥ ሶስት ፍፃሜ መድረስ እና ሁለት ዋንጫ ማሸነፍ መጥፎ አይደለም " ያሉት ኤሪክ ቴንሀግ በቀጣይ እንደማይፈልጉኝ ከነገሩኝ ዋንጫ ለማሸነፍ ሌላ ቦታ እሄዳለሁ ይህንን ነው የማደርገው ብለዋል።

" እዚህ ያለሁት ዋንጫ ለማሸነፍ ነው ቡድኑን መገንባት እፈልጋለሁ በአሰልጣኝነት ህይወቴ ሁሉ ዋንጫዎች እና ጨዋታዎችን አሸንፌያለሁ ፣ ባለፉት አስር አመታት ክለቡ ብዙ ፍፃሜ እና ዋንጫ የለውም።" ቴንሀግ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የባርሴሎና ሴቶች ቡድን ሻምፒዮን ሆነ !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ሴቶች ቡድን ከልዮን ጋር ያደረገውን የሴቶች የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫ አሸናፊ ሆኗል።

የባርሴሎናን የማሸነፊያ ግቦች ያለፈው አመት የባሎን ዶር አሸናፊ ስፔናዊት የመሐል ሜዳ ተጫዋች አይታና ቦንማቲ እና አሌክስያ ፑቴላስ አስቆጥረዋል።

የባርሴሎና ሴቶች ቡድን #ሶስተኛ የሴቶች የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫቸውን ማሳካት ችለዋል።

የስፔን ሱፐር ካፕ ዋንጫን ጨምሮ የሀገር ውስጥ የሶስትዮሽ ዋንጫ ስኬትን ያስመዘገበው የባርሴሎና ሴቶች ቡድን በአመቱ ውስጥ አራተኛ ዋንጫውን አሳክቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አል አህሊ ሻምፒዮን ሆኗል !

የግብፁ ክለብ አል አህሊ ከቱኒዚያው ክለብ ኤስፔራንስ ጋር ያደረገውን የአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ የደርሶ መልስ ጨዋታ በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆኗል።

ከሳምንት በፊት ቱኒዚያ ላይ አቻ የተለያየው አል አህሊ ግብፅ ካይሮ የተደረገውን የፍፃሜ የመልስ ጨዋታ 1ለ0 በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነዋል።

አል አህሊ በታሪኩ ለአስራ ሁለተኛ ጊዜ የአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ማሸነፍ ችለዋል።

ካለፉት አምስት የአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎች አራቱን አል አህሊ በማሸነፍ በአህጉሪቱ የበላይነቱን ማሳየት ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባየር ሌቨርኩሰን ሻምፒዮን ሆኗል !

ባየር ሌቨርኩሰን ከካይሰርስላውተርን ጋር ያደረጉትን የጀርመን " DFB " ፖካል ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን መሆን ችለዋል።

የባየር ሌቨርኩሰንን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ግራኒት ዣኪ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

በአሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ የሚመራው ባየር ሌቨርኩሰን በአመቱ ውስጥ ሁለተኛ ዋንጫቸውን ማሳካት ችለዋል።

ባየር ሌቨርኩሰን ከሰላሳ አንድ አመታት በኋላ የመጀመሪያውን የጀርመን " DFB " ፖካል ዋንጫ አሸንፏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማድሪድ የሊጉ የመጨረሻ ጨዋታውን አድርጓል !

የስፔን ላሊጋ አሸናፊው ሪያል ማድሪድ ከሪያል ቤቲስ ጋር ያደረገውን የስፔን ላሊጋ የመጨረሻ ሳምንት መርሐግብር 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

ሪያል ማድሪድ የውድድር አመቱን ዘጠና አምስት ነጥቦችን በመሰብሰብ ማጠናቀቅ ችለዋል።

ሪያል ቤቲስ በበኩሉ በሀምሳ ሰባት ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን በመያዝ ሲያጠናቅቁ በቀጣይ በአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ይሳተፋሉ።

ጁድ ቤሊንግሀም በአስራ ዘጠኝ ግቦች የሪያል ማድሪድ የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን ማጠናቀቅ ችሏል።

በጨዋታው ጀርመናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶኒ ክሩስ የመጨረሻ ጨዋታውን ሲያደርግ ከክለቡ ደማቅ ሽኝት ተደርጎለታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፒኤስጂ ሻምፒዮን ሆነዋል !

የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ከልዮን ጋር ያደረገውን የኮፕ ዴ ፍራንስ ፍፃሜ ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የውድድሩ አሸናፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

የፒኤስጂን የማሸነፊያ ግቦች ኦስማን ዴምቤሌ እና ፋብያን ሩይስ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ፒኤስጂ በታሪኩ ለአስራ አምስተኛ ጊዜ የኮፕ ዴ ፍራንስ ዋንጫን ማሸነፍ ችሏል።

የፈረንሳይ ሊግ ሻምፒዮኑ ፒኤስጂ በውድድር አመቱ ሁለተኛ ዋንጫቸውን ማሳካት ችለዋል።

በጨዋታው ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ የፒኤስጂ የመጨረሻ ጨዋታውን አድርጓል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ በሚቀጥለው ሳምንት ግምገማ ያደርጋል !

የኤፌ ካፕ ዋንጫን ያሳካው ማንችስተር ዩናይትድ በሚቀጥለው ሳምንት የድህረ የውድድር ዘመን ግምገማ ለማድረግ እቅድ መያዛቸው ተገልጿል።

ክለቡ በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የወደፊት ቆይታ ዙሪያ የመጨረሻ ውሳኔ ከማሳለፉ በፊት አሰልጣኙ የሰሩትን ስራ ለመገምገም ማሰቡ ተነግሯል።

አሰልጣኙ ከኤፌ ካፕ ዋንጫ ድላቸው በኋላ በሰጡት አስተያየት ጨዋታው የመጨረሻቸው ስለመሆኑ እንደማያውቁ ለጋዜጠኞች ገልፀው ነበር።

ማንችስተር ዩናይትድ ምንም እንኳን አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን እንደሚያሰናብት እስካሁን ፍንጭ ባይሰጥም ባለፉት ቀናቶች የሌሎች አሰልጣኞችን ተወካዮች ሲያነጋግሩ እንደነበር ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5
•Playstaion 5 Slim

•PlayStation 4 Slim
•PlayStation 4 Pro

•Playstaion portal
•PlayStation VR

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !

9:00 ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀምበሪቾ

12:00 ሀድያ ሆሳዕና ከ ሀዋሳ ከተማ

1:00 ናፖሊ ከ ሊቼ

3:45 ኢምፖሊ ከ ሮማ

3:45 ሄላስ ቬሮና ከ ኢንተር ሚላን

4:00 ሲቪያ ከ ባርሴሎና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሲቲ የጎዳና ላይ ክብረበዓል ያዘጋጃሉ !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫን አሸናፊው ማንችስተር ሲቲ የዋንጫ ድሉን ከደጋፊዎቻቸው ጋር በጎዳና ላይ እንደሚያከብሩ ተገልጿል።

ማንችስተር ሲቲዎቹ የጎዳና ላይ ክብረበዓሉን በዛሬው ዕለት በማንችስተር ከተማ የተለያዩ ቦታዎች በክፍት ባስ እየተዟዟሩ እንደሚያከብሩ አሳውቀዋል።

በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመራው ማንችስተር ሲቲ ለአራት ተከታታይ አመታት ፕርሚየር ሊጉን በማሳካት ደማቅ ታሪክ መፃፋቸው ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ማርቲኔዝ የጨዋታው ልዩነት ፈጣሪ ነበር " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የማንችስተር ዩናይትድ ተከላካይ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በትላንትናው ጨዋታ ልዩነት ፈጣሪ እንደነበር ገልጸዋል።

" ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ከአለም ምርጥ አምስት የመሐል ተከላካዮች አንዱ ነው " በማለት የገለፁት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በትላንቱ ጨዋታ ልዩነት ፈጣሪው ተጨዋች እሱ ነበር።"ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ምባፔ ከቀናት በኋላ ማረፊያውን ያሳውቃል !

ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ቀጣይ ማረፊያው የሚሆነው ክለብ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ በይፋ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

በቅርቡ ከፒኤስጂ ጋር እንደሚለያይ ያስታወቀው ኪሊያን ምባፔ ሪያል ማድሪድን እንደሚቀላቀል የሚጠበቅ ቢሆንም እስካሁን በይፋ አላረጋገጠም።

ተጨዋቹ ትላንት ምሽት የፒኤስጂ የመጨረሻ ጨዋታውን አድርጎ ክለቡን በተሰናበተበት ጨዋታ በሰጠው አስተያየት " ቀጣይ ክለቤን በትክክለኛው ሰዓት አሳውቃለሁ ጥቂት ቀናቶች ይቀራሉ " በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📢 #የዋናውን አዲስ ብስራት እናስታውስዎ!

👉🏾 በፕሪሚየር ሊግ የጥራት ደረጃ የተዘጋጁ፣ በፈለጉት ዲዛይንና ቀለም የሚሰሩ ውብና ልዩ ማሊያዎች ለእናንተ።

👉🏾 ከ20 ብዛት ጀምሮ በ1400 ብር ብቻ እንደምርጫዎ ማዘዝ ይችላሉ።

🔥 ይፍጠኑ፣ ይዘዙን፣ በፍጥነት ሰርተን ባሉበት በነፃ እናደርሳለን!

📍አድራሻችን:- ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት፣ አለም ገብሬ ህንፃ፣ 2ተኛ ፎቅ።

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WANAWSbot በኩል ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
2024/09/27 23:26:38
Back to Top
HTML Embed Code: