Telegram Web Link
ጋርዲዮላ በኮምፓኒ የሙኒክ ዜና መደሰታቸውን ገለፁ !

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ እውነት ሆኖ የሚሳካ ከሆነ ቪንሴንት ኮምፓኒ ባየር ሙኒክን በሀላፊነት ለመረከብ መቃረቡ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።

" እውነት ሆኖ ከተረከበ ዜናውን ስሰማ በጣም ተደስቻለሁ " ያሉት ፔፕ ጋርዲዮላ " ስለ ስራው ፣ ባህሪው እና የጨዋታ እውቀቱ ጥሩ አስተያየት አለኝ ትልቅ ነገር እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ዩናይትድ በትልቅ ደረጃ ለመወዳደር ዝግጁ አይደለም " - ቴንሀግ

የቀያይ ሴጣኖቹ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ማንችስተር ዩናይትድ በአሁን ሰዓት ሁሉንም ጨዋታዎች እያሸነፈ በትልቅ ደረጃ ለመፎካከር ዝግጁ አለመሆኑን ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በንግግራቸውም " ክለቡ ሊጉን ያሸነፈው ከአስራ አንድ አመታት በፊት ነው ነገርግን ሁሉንም ጨዋታዎች እያሸነፍን በትልቅ ደረጃ ላይ እንድንፎካከር ይፈልጋሉ ይህ ክለብ ለዚህ ዝግጁ አይደለም።"ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#FACupFinal

የእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ በዛሬው ዕለት በማንችስተር ዩናይትድ እና ማንችስተር ሲቲ መካከል በዌምብሌይ ስታዲየም ይደረጋል።

ማንችስተር ሲቲ የኤፌ ካፕ ዋንጫውን ለሁለተኛ ተከታታይ አመታት ተቀናቃኙ ማንችስተር ዩናይትድን በማሸነፍ ለማሳካት ይፋለማሉ።

ደካማ የውድድር አመት ያሳለፈው ማንችስተር ዩናይትድ በበኩሉ ዋንጫውን ከማሳካትም በዘለለ የዩሮፓ ሊግ ተሳትፎ ቦታን ለማግኘት ይጫወታሉ።

ማንችስተር ዩናይትድ በታሪኩ ሀያ አንድ ጊዜ ለኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ ሲደርስ አስራ ሁለቱን ማሸነፍ ችሏል።

ማንችስተር ሲቲ በበኩላቸው አስራ ሁለት ጊዜ ለኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ መድረስ ሲችሉ በሰባቱ ሻምፒዮን ሆነዋል።

ጨዋታው ዛሬ አመሻሽ 11:00 በግዙፉ ዌምብሌይ ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል።

ጨዋታውን ማን ያሸንፋል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ቡድኑን ከእኔ ጋር መገንባት እንደሚፈልጉ ነግረውኛል " ቴንሀግ

የቀያይ ሴጣኖቹ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ አዲሱ የማንችስተር ዩናይትድ ባለቤት ሰር ጂም ራትክሊፍ በወደፊቱ የክለቡ ሁኔታ ላይ እንዳነጋገሯቸው ገልጸዋል።

ባለቤቶቹ በቀጣይ በክለቡ ውስጥ ያለውን ሁሉንም ነገር ለመቀየር እንዳሰቡ እንደነገሯቸው አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ቡድኑን በድጋሜ ከእኔ ጋር በመሆን ለመገንባት እንደሚፈልጉ ቃል በቃል ነግረውኛል ሲሉ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ አሳውቀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🎁 በፍፃሜው #ይገምቱ#ይሸለሙ! 🎁

🏆 በዛሬው የእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ማን አሸንፎ ዋንጫውን ያነሳ ይሆን?

🇬🇧 ማንቺስተር ዩናይትድ ወይስ ማንቺስተር ሲቲ 🇬🇧

💬 ግምትዎን በቴሌግራም ገፃችን (https://www.tg-me.com/wanawsportwear) ኮሜንት ላይ ብቻ ያስቀምጡልን!

⚠️ የውድድሩ ህጎች፦
👉🏾 የዋንጫውን አሸናፊ ክለብ እና ውጤት እስከ ግብ መጠኑ #በትክክል ቀድመው የሚገምቱ #3 ተከታታዮቻችን የዋናውን የጂም ማልያዎች ይሸለማሉ።
👉🏾 የዋናውን ማህበራዊ ገፆች መከተል፣ መወዳጀትና ማጋራት አይዘንጉ።
👉🏾 የተስተካከሉ መልሶች በፍፁም ተቀባይነት የላቸውም።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የላሊጋ ክለቦች በአመቱ መጨረሻ ስንት ያገኛሉ ?

በሪያል ማድሪድ አሸናፊነት በተጠናቀቀው የስፔን ላሊጋ የ2023/24 የውድድር አመት ክለቦች በአመቱ መጨረሻ የሚያገኙት ገቢ ታውቋል።

የውድድሩ አሸናፊ ሪያል ማድሪድ 58.4 ሚልዮን ዩሮ እንደሚያገኝ ሲገለፅ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው ባርሴሎና 51.5 ሚልዮን ዩሮ እንደሚያገኝ ተነግሯል።

ክለቦች ስንት ያገኛሉ ?

1️⃣ ሪያል ማድሪድ :- 58.4 ሚልዮን ዩሮ

2️⃣ ባርሴሎና :- 51.5 ሚልዮን ዩሮ

3️⃣ ጂሮና :- 44.6 ሚልዮን ዩሮ

4️⃣ አትሌቲኮ ማድሪድ :- 37.8 ሚልዮን ዩሮ እንደሚያገኙ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጁቬንቱስ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተስማማ !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ጁቬንቱስ ጥሩ የሚባል የውድድር አመት ያሳለፈውን የሞንዛ ግብ ጠባቂ ሚሼል ዲ ግሪጎርዮ ለማስፈረም መስማማታቸው ተገልጿል።

በቀጣይ አሰልጣኝ ቲያጎ ሞታን በሀላፊነት ይሾማል ተብሎ የሚጠበቀው ጁቬንቱስ ለግብ ጠባቂው ዝውውር 20 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ ክፍያ ለመፈፀም መስማማቱ ተነግሯል።

ጣልያናዊው ግብ ጠባቂ ሚሼል ዲ ግሪጎርዮ የጣልያን ሴርያ የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ ተብሎ መመረጡ የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ምሽት ከሞንዛ ጋር ጁቬንቱስን የሚገጥም ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ባርሴሎና አሰልጣኝ ዣቪን አሰናበተ ! የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ስፔናዊውን አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ በዛሬው ዕለት ከሀላፊነታቸው ማሰናበቱን ይፋ አድርጓል። የባርሴሎናው ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ በዛሬው እለት ከአሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ ጋር እንደተነጋገሩ እና ውሳኔውን እንዳሳወቁ ተዘግቧል። አሰልጣኝ ዣቪ ከወራት በፊት በአመቱ መጨረሻ ባርሴሎናን እንደሚለቁ አሳውቀው የነበረ ቢሆንም በቅርቡ ክለቡ…
" አንድ ቀን ወደ ባርሴሎና መመለስ እፈልጋለሁ " ዣቪ

የባርሴሎና የመጨረሻ ጨዋታቸውን በነገው ዕለት የሚመሩት ስፔናዊው አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ ከጨዋታው በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ ምን አሉ ?

- " አንድ ቀን ወደ ባርሴሎና መመለስ እፈልጋለሁ ፣ ባርሴሎና የህይወቴ አካል ነው ወደ ባርሴሎና የመመለሻ በሩ ሁልጊዜም ክፍት ሆኖ ይቆያል።

- በቀጣይ እረፍት ማድረግ እፈልጋለሁ በቀጥታ ስለሌላ ስራ ማሰብ የምጀምር አይመስለኝም አሁን ላይ የማስበው ይህንን ነው።

- ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ አንድ ተጨማሪ የባርሴሎና ደጋፊ እሆናለሁ ባርሴሎና ከደጋፊዎች ጋር መደገፌን እቀጥላለሁ።

- ትላንት ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታን አግኝቻቸው ውሳኔያቸውን እና ምክንያታቸውን ነግረውኛል እኔም ተቀብያለሁ ውሳኔውን ማክበር አለብኝ እኔ የክለቡ ሰው ነኝ።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኮምፓኒ ባየር ሙኒክን ለመረከብ ተቃረበ ! የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ ቤልጂየማዊውን የበርንሌይ ዋና አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ በአሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ምትክ በሀላፊነት ለመሾም መቃረባቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ በሚቀጥሉት ቀናት ባየር ሙኒክን በሀላፊነት ለመረከብ ሙሉ ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ባየር ሙኒክ አሁን ላይ በአሰልጣኙ የውል ካሳ ክፍያ ዙሪያ ከበርንሌይ ጋር…
ባየር ሙኒክ አሰልጣኝ ለመሾም ተስማማ !

የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ ቤልጂየማዊውን የበርንሌይ ዋና አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ በአሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ምትክ በሀላፊነት ለመሾም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ በባየር ሙኒክ ቤት እስከ 2027 የሚያቆየውን ውል ለመፈረም ከስምምነት መደረሱ ተዘግቧል።

ባየር ሙኒክ ለበርንሌይ ለአሰልጣኙ የካሳ ክፍያ የሚሆን 12 ሚልዮን ዩሮ የሚጠጋ ገንዘብ ለመክፈል መስማማታቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዋይን ሩኒ ወደ አሰልጣኝነት ሊመለስ ነው ! የእንግሊዝ ሻምፒየን ሺፑ ክለብ ፕለይ ማውዝ እንግሊዛዊውን የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች ዋይን ሩኒ በአሰልጣኝነት ለመሾም በማሰብ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል። ዋይን ሩኒ ከወራት በፊት በርሚንግሃም ሲቲን ከተረከበ ሰማንያ ሶስት ቀናት በኋላ ከክለቡ ከተሰናበተ በኋላ ያለ ሀላፊነት ይገኛል ። የሻምፒየን ሺፑ ክለብ ፕለይ ማውዝ በዚህ አመት ወደ ታችኛው…
ዋይን ሩኒ በአሰልጣኝነት ተሾመ !

የእንግሊዝ ሻምፒዮን ሺፑ ክለብ ፕለይ ማውዝ እንግሊዛዊውን የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች ዋይን ሩኒ በአሰልጣኝነት መሾሙን ይፋ አድርጓል።

አሰልጣኝ ዋይን ሩኒ የሻምፒየን ሺፑን ክለብ ፕለይ ማውዝ ለሚቀጥሉት ሶስት አመታት ለማሰልጠን ፊርማውን ማኖሩ ተገልጿል።

ዋይን ሩኒ ከፊርማው በኋላ ክለቡ ለሰጠው እድል አመስግኖ በቀጣይ ቡድኑን ለመገንባት እና በሻምፒዮን ሺፑ ለመወዳደር መጓጓቱን ገልጿል።

የሻምፒየን ሺፑ ክለብ ፕለይ ማውዝ በዚህ አመት ወደ ታችኛው ሊግ ለመውረድ ተቃርቦ በመጨረሻ ሰዓት በሻምፒዮን ሺፑ መቆየቱን አረጋግጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Tecno #Camon30Pro5G

Tecno Camon 30 pro 5G እያንዳንዱ ፎቶ እና ቪድዮ ከፍተኛ ጥራት እንዲላበሱ የSony IMX890 ካሜራ ሴንሰር ገጥሞ ቀርቧል!

#Camon30Et #Camon30Pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
"ባሸነፉት ውርርድ ላይ እስከ 300% ACCA ጉርሻ ያግኙ! ቤቲካ ላይ ይወራረዱ! ያሸንፉ!
የዛሬውን ዕለታዊ ጃክፖት ላይ ለመወራረድ - (betika.et/dailyjackpot)
የዛሬው የተመረጡ ዕለታዊ ጨዋታዎች ላይ ለመወራረድ - (betika.et)
የሳምንታዊ ጃክፖት ላይ ለመወራረድ - (betika.et/weeklyjackpot)"
የጨዋታ አሰላለፍ !

11:00 ማንችስተር ሲቲ ከ ማንችስተር ዩናይትድ ( ኤፌ ካፕ ፍፃሜ ) 

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ለማሸነፍ ሁሉንም እንሰጣለን " ፈርናንዴዝ

የማንችስተር ዩናይትድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ብሩኖ ፈርናንዴዝ ቡድናቸው በዛሬው የፍፃሜ ጨዋታ ውጤቱን ከአምናው በተቃራኒ ለማድረግ ሁሉንም እንደሚሰጥ ተናግሯል።

መልበሻ ቤቱ በጥሩ ስሜት ላይ መሆኑን የገለፀው ብሩኖ ፈርናንዴዝ " ጨዋታውን ለማሸነፍ ሁሉንም ነገር እንሰጣለን ውጤቱ ከባለፈው አመት ተቃራኒ እንደሚሆን ተስፋ አለኝ።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ጨዋታውን ማሸነፍ እንፈልጋለን " ኤሪክ ቴንሀግ

ከደቂቃዎች በኋላ በማንችስተር ሲቲ እና ማንችስተር ዩናይትድ መካከል ከሚደረገው የእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ በፊት አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

" ጨዋታውን ማሸነፍ እንፈልጋለን ለማሸነፍ ሁሉንም ነገር እንሰጣለን የአስተሳሰብ ጉዳይ ነው ዋጋ ከፍለን ተጭነን መጫወት አለብን።"ሲሉ የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ተናግረዋል።

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በበኩላቸው " በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ ፍፃሜውን ስለማሸነፍ ካሰብን ትኩረታችን ይከፈላል ሙሉ ሀሳባችን ጨዋታው ላይ መሆን አለበት።"ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሪነቱን አጠናከረ !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፋሲል ከነማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የማሸነፊያ ግብ አዲስ ግደይ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማሸነፉን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግን በአምስት ነጥቦች ልዩነት መምራት ጀምሯል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

1️⃣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ :- 56 ነጥብ

7️⃣ ፋሲል ከነማ :- 40 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ሐሙስ - ባሕር ዳር ከተማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

አርብ - ፋሲል ከነማ ከ መቻል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጀመረ

ማንችስተር ሲቲ 0-0 ማንችስተር ዩናይትድ ( ኤፌ ካፕ ፍፃሜ ) 

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
10 ' ማንችስተር ሲቲ 0-0 ማንችስተር ዩናይትድ ( ኤፌ ካፕ ፍፃሜ ) 

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
15 ' ማንችስተር ሲቲ 0-0 ማንችስተር ዩናይትድ ( ኤፌ ካፕ ፍፃሜ ) 

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/27 19:22:43
Back to Top
HTML Embed Code: