Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
ቪንሴንት ኮምፓኒ ወዴት ሊያመራ ይችላል ? ቤልጂየማዊው የበርንሌይ ዋና አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ በቀጣይ ታላላቅ ክለቦችን በሀላፊነት ለመረከብ ንግግር መጀመሩ በመዘገብ ላይ ይገኛል። የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ ቪንሴንት ኮምፓኒን በሀላፊነት ለመሾም እንደሚፈልጉ እና የክለቡ ሀላፊዎች ተደጋጋሚ የስልክ ልውውጥ ማድረጋቸው ተነግሯል። በትላንትናው ዕለት ከማውሪስዮ ፖቼቲኖ ጋር የተለያየው…
ኮምፓኒ ባየር ሙኒክን ለመረከብ ተቃረበ !

የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ ቤልጂየማዊውን የበርንሌይ ዋና አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ በአሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ምትክ በሀላፊነት ለመሾም መቃረባቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ በሚቀጥሉት ቀናት ባየር ሙኒክን በሀላፊነት ለመረከብ ሙሉ ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ባየር ሙኒክ አሁን ላይ በአሰልጣኙ የውል ካሳ ክፍያ ዙሪያ ከበርንሌይ ጋር በንግግር ላይ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን በሚቀጥሉት ቀናት ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኬቨን ዴብሮይን ወደ አሜሪካ ያመራ ይሆን ?

የአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከሩ ክለብ ሳን ዲያጎ ቤልጂየማዊውን የማንችስተር ሲቲ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬቨን ዴብሮይን የማስፈረም ሀሳብ እንዳላቸው ተገልጿል።

የኬቨን ዴብሮይን ተወካዮች ከአሜሪካው ክለብ ሳን ዲያጎ ጋር አንድ ጊዜ ተገናኝተው ለውይይት ተቀምጠው እንደነበር ተዘግቧል።

ይሁን እንጂ የማንችስተር ሲቲው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬቨን ዴብሮይን ወደ አሜሪካ ለማምራት ዝግጁ መሆኑን የሚያመላክት ነገር አለመኖሩ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኮምፓኒ ባየር ሙኒክን ለመረከብ ተቃረበ ! የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ ቤልጂየማዊውን የበርንሌይ ዋና አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ በአሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ምትክ በሀላፊነት ለመሾም መቃረባቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ በሚቀጥሉት ቀናት ባየር ሙኒክን በሀላፊነት ለመረከብ ሙሉ ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ባየር ሙኒክ አሁን ላይ በአሰልጣኙ የውል ካሳ ክፍያ ዙሪያ ከበርንሌይ ጋር…
ባየር ሙኒክ ለበርንሌይ ስንት አቀረበ ?

የቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ ቤልጂየማዊውን የበርንሌይ አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ ወደ ክለባቸው ለመውሰድ ለስምምነት እንደተቃረቡ መገለፁ ይታወቃል።

ከበርንሌይ ጋር በአሰልጣኙ ካሳ ክፍያ ዙሪያ ንግግር ላይ የሚገኙት ባየር ሙኒኮች #አስር ሚልዮን ዩሮ ማቅረባቸው ተገልጿል።

በርንሌይ በበኩላቸው የቀረበውን ሒሳብ ለመቀበል አለመፈለጋቸው እና #ሀያ ሚልዮን ዩሮ ክፍያ እንዲፈፀምላቸው እንደሚፈልጉ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Tecno #Camon30Pro5G

ፍጥነት እና ቅልጥፍና መገለጫው የሆነውን MediaTek Dimensity 8200 ፕሮሰሰር አካቶ Tecno Camon 30 pro 5G ቀርቦሎታል

#Camon30Et #Camon30proEt #Camon30 #Camon30Pro #TecnoEt
📢 #ልዩ_የሽያጭ_ብስራቱ_ቀጥሏል!

⚽️#ዋናው ለእግር ኳስ ቡድንዎ  ማሊያ በቁምጣ እስከ #ግንቦት_30 ብቻ በሚቆየው ዋጋ በ #699 ብር ፦

👉🏾 ከ20 ብዛት ጀምሮ ሲገዙ ተጨማሪ 2 ባለኮሌታ ቲ-ሸርቶችን በነፃ ያገኛሉ።
👉🏾 ከ 50 ብዛት ጀምሮ ሲገዙ 5 ባለኮሌታ ቲ-ሸርቶችን እና 1 ባንዲራን በነፃ እንሰጥዎታለን።
👉🏾 ከ100 ብዛት ጀምሮ ሲገዙ ደግሞ 1 Molten 1ኛ ደረጃ ኳስ እና 1 ባንዲራን በነፃ የሚያገኙ ይሆናል።

🔥 #እንዳያመልጥዎ፣ አሁኑኑ ይዘዙን!

📍አድራሻችን:- ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት፣ አለም ገብሬ ህንፃ፣ 2ተኛ ፎቅ።

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 0901138283፣ 0910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WANAWSbot በኩል ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
TIKVAH-SPORT
ዌስትሀም አሰልጣኝ ለመሾም ተስማማ ! በውድድር አመቱ መጨረሻ ከአሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ ጋር የሚለያዩት ዌስትሀም ዩናይትዶች በምትኩ አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። ዌስትሀም ዩናይትድ በሚቀጥለው የውድድር አመት አሰልጣኝ ጁሊያን ሎፕቲጌን በሀላፊነት ለመሾም ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል። የቀድሞ የሪያል ማድሪድ ፣ ሲቪያ ፣ ዎልቭስ እና ስፔን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጁሊያን…
ዌስትሀም ዩናይትድ በይፋ አሰልጣኝ ሾመ !

በውድድር አመቱ መጨረሻ ከአሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ ጋር የተለያየው ዌስትሀም ዩናይትድ አዲስ አሰልጣኝ በሀላፊነት መሾሙን ይፋ አድርጓል።

ዌስትሀም ዩናይትድ የ 57ዓመቱን የቀድሞ የሪያል ማድሪድ ፣ ሲቪያ ፣ ዎልቭስ እና ስፔን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጁሊያን ሎፕቲጌን በሀላፊነት መሾሙን በይፋ አሳውቋል።

አሰልጣኝ ጁሊያን ሎፕቲጌ ከሀላፊነቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት " እንደ አሰልጣኝ ሁልጊዜ ምኞቴ በየጊዜው መሻሻል ፣ ተጨዋቾችን ማሻሻል እና ትልቅ ነገሮችን ማሳካት ነው ለመጀመር ጓጉተናል " በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሰልጣኝ ቲያጎ ሞታ ከቦሎኛ ጋር ተለያዩ !

አሰልጣኝ ቲያጎ ሞታ ከጣልያን ሴርያው ክለብ ቦሎኛ ጋር መለያየታቸውን ክለቡ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ አረጋግጧል።

በሴርያው ስኬታማ የውድድር አመት ያሳለፉት አሰልጣኝ ቲያጎ ሞታ ቦሎኛን ከስልሳ አመታት በኋላ ለአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ በማሳለፍ አዲስ ታሪክ መፃፍም ችለዋል።

አሰልጣኝ ቲያጎ ሞታ በቀጣይ ጁቬንቱስን በሀላፊነት ለመረከብ ከስምምነት የደረሱ ሲሆን በቀጣይ ክለቡ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሪያል ማድሪድ ትልቅ ዋጋ ያለው ክለብ ሆኗል !

የስፔን ላሊጋው ክለብ ሪያል ማድሪድ ለሶስተኛ ተከታታይ አመታት የአለማችን ከፍተኛ ዋጋ ያለው ውድ ክለብ መሆን መቻሉ ተገልጿል።

የስፔን ላሊጋ ሻምፒዮኑ ሪያል ማድሪድ እንደ ፎርብስ መረጃ አሁን ላይ 6.6 ቢልዮን ዶላር የሚደርስ ዋጋ ይኖረዋል ተብሎ እንደሚገመት ተገልጿል።

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊጉ ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ በ6.5 ቢልዮን ዶላር ዋጋ ሁለተኛ ደረጃን መያዙ ተነግሯል።

ትልቅ ዋጋ ያላቸው አስር ክለቦች የትኞቹ ናቸው ?

1️⃣ ሪያል ማድሪድ   :- 6.6 ቢልዮን ዶላር
2️⃣ ማንችስተር ዩናይትድ :- 6.5 ቢልዮን ዶላር
3️⃣ ባርሴሎና :- 5.6 ቢልዮን ዶላር
4️⃣ ሊቨርፑል :- 5.3 ቢልዮን ዶላር
5️⃣ ማንችስተር ሲቲ :- 5.1 ቢልዮን ዶላር

6️⃣ ባየር ሙኒክ :- 5 ቢልዮን ዶላር
7️⃣ ፒኤስጂ :- 4.4 ቢልዮን ዶላር
8️⃣ ቶተንሀም :- 3.2 ቢልዮን ዶላር
9️⃣ ቼልሲ :- 3.1 ቢልዮን ዶላር
1️⃣0️⃣ አርሰናል 2.6 ቢልዮን ዶላር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ተጨዋቹ በቋሚነት ይቀጥላል !

ከማንችስተር ዩናይትድ በውሰት ለፖርቹጋሉ ክለብ ቤኔፊካ የሚጫወተው አልቫሮ ፈርናንዴዝ በክለቡ በቋሚነት ለመቀጠል የረጅም ጊዜ ውል መፈረሙ ተገልጿል።

ቤኔፊካ በተጨዋቹ ውል ውስጥ የተካተተውን የመግዛት አማራጭ መጠቀማቸውን ተከትሎ ማንችስተር ዩናይትድ #ስድስት ሚልዮን ዩሮ ክፍያ እንደሚያገኙ ተነግሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ በተጨማሪም በውሉ ውስጥ የመልሶ የመግዛት አማራጭ እና ከተጨዋቹ ቀጣይ ሽያጭ ተጠቃሚ የሚያደርጋቸው ውል ማካተታቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ በቀጣይ ማንን ሊሾም ይችላል ?

ከአሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ጋር የተለያየው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በቀጣይ አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም በማፈላለግ ላይ ይገኛሉ።

ሰማያዊዎቹ በቀጣይ ለመሾም በዝርዝራቸው ውስጥ ከያዟቸው አሰልጣኞች መካከል

- የሌስተር ሲቲው አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ

- የኢፕስዊች ታውኑ አሰልጣኝ ኬራን ማክኬና

- የብሬንትፎርዱ አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ እንደሚገኙበት ተገልጿል።

ክለቡ ሲመለከታቸው የነበሩትን የጂሮና አሰልጣኝ ሚቼል እና የስቱትጋርቱን አሰልጣኝ ሴባስቲያን ሆኔስ ከዝርዝሩ ውስጥ ማስወጣቱ ተዘግቧል።

ቼልሲዎቹ በቀጣይ ተጨማሪ እጩ አሰልጣኞችን ለመመልከት ዝግጁ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በውስጥ ንግግሮች መቀጠላቸው ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጣልያን ስብስቧን አሳውቃለች !

የጣልያን ብሔራዊ ቡድን ለቀጣዩ የ2024 የጀርመን አውሮፓ ዋንጫ ውድድር የመጀመሪያ ሰላሳ የቡድን ስብስቡን አሳውቋል።

ብሔራዊ ቡድኑ ከስብስቡ ውስጥ አራት ተጨዋቾችን ቀንሶ ወደ አውሮፓ ዋንጫው ያመራል ተብሎ ይጠበቃል።

በአሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ ከአውሮፓ ዋንጫው በፊት ከቱርክ እና ቦስኒያ ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎች ያደርጋል።

ሙሉ የቡድን ስብስቡ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ድሬዳዋ ከተማ ድል አድርጓል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ከወልቂጤ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የድሬዳዋ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ካርሎስ ዳምጠው 2x እና ሱራፌል ጌታቸው ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የድሬዳዋ ከተማው የፊት መስመር ተጨዋች ካርሎስ ዳምጠው ሰባተኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ወልቂጤ ከተማ ያለፉትን ስድስት የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግደዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

8️⃣ ድሬዳዋ ከተማ :- 37 ነጥብ

1️⃣4️⃣ ወልቂጤ ከተማ :- 16 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ሐሙስ - ወልቂጤ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና

አርብ - ድሬዳዋ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዩናይትድ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

ማንችስተር ዩናይትድ የ 2023/24 የውድድር አመት የአመቱን ምርጥ ተጨዋች ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ፖርቹጋላዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ብሩኖ ፈርናንዴዝ የማንችስተር ዩናይትድ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን በአብላጫ ድምፅ መመረጥ ችሏል።

ብሩኖ ፈርናዴዝ አርባ በመቶ የሚሆነውን ድምፅ በማግኘት ማሸነፉ ሲገለፅ ዲያጎ ዳሎት ሁለተኛ ፣ ኮቢ ማይኖ ሶስተኛ እንዲሁም አሌሀንድሮ ጋርናቾ አራተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቃቸው ታውቋል።

ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለሶስተኛ ጊዜ የማንችስተር ዩናይትድ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን ሲያሸንፍ ከእሱ በላይ በዙ ግዜ ያሸነፉት ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ዴቪድ ዴህያ አራት ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ዲያጎ ዳሎት የተጨዋቾች የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን በማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋቾች መመረጡ ይፋ ተደርጓል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
"ስለ ቤቲካ ማን መረጃ ይነግራችኋል?
ልብ በሉ እንግዲህ… የቤቲካን የማኅበራዊ ሚዲያ ገፆች ስትፈልጉ እነዚህን አድራሻዎች ተጠቀሙ FB/Messanger - https://m.me/BetikaET Telegram - https://www.tg-me.com/betikaeth Email - [email protected]
ቤቲካ በሁሉም ዋና ዋና የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ ይገኛል።
ወደ 8692 ነጻ የስልክ መስመር ይደውሉልን!
የአሸናፊዎች ቤት የሆነው ቤቲካ ሁሌም ጥያቄዎችዎን ለማስተናገድ ዝግጁ ነው"
TIKVAH-SPORT
የማድሪድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል በአሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የሚሰለጥነው የላሊጋው መሪ ሪያል ማድሪድ የወርሀ ሚያዚያ የወሩ ምርጥ ተጨዋች #አምስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል። በዚህም መሰረት ሮድሪጎ ፣ ቪንሰስ ጁኒየር ፣ ዳኒ ካርቫል ፣ ሩዲገር ፣ እና ቫልቬርዴ የወርሀ ሚያዝያ የሪያል ማድሪድ ወሩ ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
የማድሪድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

በአሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የሚመራው የስፔን ላሊጋ አሸናፊው ሪያል ማድሪድ የወርሀ ሚያዝያ የወሩ ምርጥ ተጨዋቻቸውን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ጀርመናዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አንቶኒዮ ሩዲገር የወርሀ ሚያዝያ የሪያል ማድሪድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጥ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሉካስ ፓኩዌታ ክስ ተከፈተበት !

የዌስትሀም ዩናይትድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካስ ፓኩዌታ ከህገ-ወጥ የስፖርት ውርርድ ጋር በተያያዘ ከእንግሊዝ እግርኳስ ማህበር ክስ እንደቀረበበት ተገልጿል።

ተጨዋቹ በሚቀጥሉት አስር ቀናት ውስጥ ንፁህ መሆኑን ለእንግሊዝ እግርኳስ ማህበር ማረጋገጥ ካልቻለ ቅጣት እንደሚጣልበት ተነግሯል።

በማንችስተር ሲቲ የሚፈለገው ሉካስ ፓኩዌታ ባለፈው ክረምት ሲቲን ለመቀላቀል ተቃርቦ የእንግሊዝ ኤፍኤ ከዚሁ ጋር የተያያዘ ምርመራ መክፈቱን ተከትሎ ዝውውሩ መቋረጡ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ የተጫዋቹን ግልጋሎት አያገኝም !

ማንችስተር ዩናይትድ በቅዳሜው የእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ፍፃሜ የወሳኝ ተጫዋቹን ግልጋሎት እንደማያገኝ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ አረጋግጠዋል።

በጨዋታው እንግሊዛዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሀሪ ማጓየር በጉዳት ምክንያት እንደማይደርስ አሰልጣኙ ገልጸዋል።

ሜሰን ማውንት ፣ ቪክቶር ሊንድሎፍ እና አንቶኒ ማርሻል በበኩላቸው ለጨዋታው ዝግጁ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ወደዚህ የመጣሁት ዋንጫ ለማሸነፍ ነው " ቴንሀግ

የማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ቡድናቸው ቅዳሜ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ከሚያደርገው የኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ምን አሉ ?

- " ወደዚህ የመጣሁት ዋንጫ ለማሸነፍ ነው ቅዳሜ ደግሞ የምናሸንፍበት እድል አለን እንደ ቡድን ለፍፃሜ መድረስ ይገባናል ዋንጫውን ማሸነፍ እንፈልጋለን።

- ስለወደፊት ቆይታዬ ማውራት አልፈልግም ትኩረት የማደርገው ስራዬ ላይ ነው የቅዳሜውን ፍፃሜ ማሸነፍ እና የጀመርነውን እቅድ መቀጠል።

- ሁሉም ነገር ዋንጫ ስለማሸነፍ ነው ቅዳሜ የማሸነፍ ትልቅ እድል አለን ማንችስተር ዩናይትድ ባለፉት አስር አመታት ብዙ ዋንጫ አላሸነፈም ነገርግን እኛ በሁለት አመት ሁለት ዋንጫ የማሸነፍ እድል አለን።

- ስለቀጣዩ ክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት በማሰብ ላይ ነኝ ነገርግን በዚህ ሰዓት ሙሉ ትኩረታችንን ማድረግ የምንፈልገው ፍፃሜው ላይ ነው።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ መድን በአሸናፊነቱ ቀጥሏል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከአዳማ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 4ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ ደረጃቸውን ማሻሻል ችለዋል።

የኢትዮጵያ መድንንን የማሸነፊያ ግቦች አቡበከር ሳኒ ፣ ሀይደር ሸረፋ ፣ አለን ካይዋ እና አብዲሳ ጀማል ሲያስቆጥሩ ለአዳማ ከተማ ጀሚል ያዕቆብ ከመረብ አሳርፏል።

ያለፉትን ዘጠኝ ጨዋታዎች ያልተሸነፈው ኢትዮጵያ መድን ስድስተኛ ተከታታይ ድሉን ማስመዝገብ ችሏል።

ኢትዮጵያ መድን ባለፉት ስድስት ጨዋታዎች አስራ ሰባት ግቦችን በተጋጣሚ መረብ ላይ ሲያስቆጥር የተቆጠረበት ሁለት ግብ ብቻ ነው

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

5️⃣ አዳማ ከተማ :- 41 ነጥብ

1️⃣0️⃣ ኢትዮጵያ መድን :- 34 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

እሁድ - ሻሸመኔ ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድን

ቅዳሜ - ሀዋሳ ከተማ ከ አዳማ ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማድሪድ በሜዳው የፍፃሜ ጨዋታውን ያስመለክታል !

ሪያል ማድሪድ ከዶርትመንድ ጋር የሚያደርገውን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ወደ ለንደን ተጉዘው መመልከት ላልቻሉ ደጋፊዎች በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም እንዲመለከቱ ማዘጋጀቱ ተገልጿል።

ክለቡ ሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም ሜዳ ላይ ግዙፍ የጨዋታ መመልከቻ ስክሪኖችን በማዘጋጀት ለደጋፊዎቹ ክፍት እንደሚያደርግ አሳውቋል።

ጨዋታውን በስታዲየሙ ተገኝቶ ለመከታተል የቲኬቶች ዋጋ ለህዝብ በ15 ዩሮ ከዛሬ ጀምሮ ለሽያጭ እንደሚቀርቡ ተዘግቧል።

ጨዋታውን ለመመልከት እስከ 80,000 የሚደርሱ የሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች በስታዲየሙ ሊገኙ እንደሚችሉ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/26 22:51:25
Back to Top
HTML Embed Code: