Telegram Web Link
#PremiereLeague

ስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ማንችስተር ሲቲን በሀላፊነት እየመሩ ስድስተኛ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫቸውን ማሳካት ችለዋል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከማንችስተር ሲቲ ጋር በተከታታይ አራተኛ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫቸውን በማሳካትም አዲስ ታሪክ ፅፈዋል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በሰባት የውድድር አመት ውስጥ ስድስት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫዎችን አሳክተዋል።

ፔፕ ጋርዲዮላ በሲቲ ቤት ምን አሳኩ ?

6️⃣ ፕርሚየር ሊግ

4️⃣ ካራባኦ ካፕ

2️⃣ ኤፌ ካፕ እና ኮሚኒቲ ሺልድ

1️⃣ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ

1️⃣ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ፣ የፊፋ ክለቦች ዋንጫ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ የሰራነውን ታሪክ ለመናገር ከባድ ነው “ ፊል ፎደን

የ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የዘንድሮው ውድድር የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ፊል ፎደን “ ማንም ቡድን ያለደረገውን አድርግናል “ ሲል ከዋንጫ ድሉ በኋላ ተናግሯል።

ለአራተኛ ተከታታይ አመት ሊጉን ማሸነፋቸውን “ የሰራነውን ታሪክ ለመናገር ከባድ ነው ፣ ታሪክ ሰርተናል “ ብሏል።

“ ይህን ለማድረግ አመቱን ሙሉ ለፍተናል ፣ ለክለቡ እና ለደጋፊው ምን ማለት እንደሆነ ተመልክታችኋል “ ፊል ፎደን

የ 23ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ፊል ፎደን ስድሰተኛ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫውን ማሸነፍ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ አንዳንዴ እግር ኳስ ፍትሀዊ አይደለችም “ ሀቨርትዝ

የመድፈኞቹ የፊት መስመር ተጫዋች ካይ ሀቨርትዝ የሊጉን ዋንጫ ማጣታቸው እንዳስከፋው በመግለፅ በቀጣይ ዓመት ጠንክረው እንደሚመጡ አሳስቧል።

“ አንዳንዴ እግር ኳስ ፍትሀዊ አይደለችም ነገር ግን ሁኔታውን በፀጋ መቀበል አለብን “ ያለው ሀቨርትዝ አሁን ካለን ነገር የተሻለ ነገር እንደሚገባን ይሰማኛል “ ብሏል።

ለመላው የክለቡ ደጋፉዎች ባስተላለፈው መልዕክት “ በቀጣይ ዓመት የተሻለ ጠንካራ ቡድን እና ያለውን የሚሰጥ ክለብ እንደምንሆን ልነግራችሁ እወዳለሁ “ ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ በውጤቱ ሁላችንም አዝነናል “

የመድፈኞቹ አምበል ማርቲን ኦዴጋርድ የሊጉን ዋንጫ ባለማሸነፋቸው ማዘኑን ገልጿል።

“ እውነት ለመናገር በውጤቱ ሁላችንም አዝነናል “ ያለው ኦዴጋርድ “ የቡድን አጋሮቼ ባሳዩት ነገር ኩራት ይሰማኛል “ በማለት ተናግሯል።

ክለቡ መቀየሩን የገለፀው ኦዴጋርድ “ ሁሉም ደጋፊ በእኛ እምነት አላችሁ ፣ በቀጣይ ሁሉንም ለማሸነፍ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን “ ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ባደረግነው ነገር አትደሰቱ የተሻለ እናደርጋለን "

የአርሰናሉ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የክለቡ ደጋፊዎች በቀጣይ የተሻለ ስኬት እንዲጠብቁ እና የተመዘገበው ውጤት በቂ ነው ብለው እንዳያስቡ ተናግረዋል።

ባስመዘገብነው ውጤት ደስተኛ መሆን የለባችሁም ሲሉ ለደጋፊው መልዕክት ያስተላለፉት ሚኬል አርቴታ " ምክንያቱም እኛ ትልቅ ነገር ነው ማሳካት የምንፈልገው ድጋፋችሁን ቀጥሉ በቀጣይ እናደርገዋለን " በማለት ተናግረዋል።

ሚኬል አርቴታ ለደጋፊው ያስተላለፉትን መልዕክት በጎል ቻናላችን ማግኘት ይችላሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TikvahGoal

የ 2023/24 የውድድር ዘመን የፕርሚየር ሊግ ሻምፒዮኖቹ ማንችስተር ሲቲ የሊጉን ዋንጫ በይፋ ተረክበዋል።

በጎል ቻናላችን በቪዲዮ መመልከት ይችላሉ።

የጎል ቻናላችን 👉
https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቲያጎ ሲልቫ የቼልሲ ደጋፊዎችን ተሰናብቷል !

ከቼልሲ ጋር እንደሚለያይ ያሳወቀው ብራዚላዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቲያጎ ሲልቫ በዛሬው ዕለት በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም ደጋፊውን በእምባ ታጅቦ ተሰናብቷል።

ቲያጎ ሲልቫ ለደጋፊው ባደረገው ንግግርም " ህልሜ ልጆቼ ለቼልሲ ሲጫወቱ መመልከት ነው ፣ ቼልሲን እና እናንተ ደጋፊዎችን አመሰግናለሁ እወዳችኋለሁ " ሲል ተናግሯል።

የ 39ዓመቱ ተጨዋች ቲያጎ ሲልቫ በቼልሲ ቤት ባሳለፋቸው አራት አመታት ውስጥ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፣ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ እና የአለም ክለቦች ዋንጫ ድሎችን አሳክቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ I WILL NEVER WALK ALONE “ የርገን ክሎፕ

በሊቨርፑል ቤት የመጨረሻ ጨዋታቸውን የመሩት አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ የመጨረሻ መልዕክታቸውን ለደጋፊዎች አስተላልፈዋል።

“ እኔ የእናንተ ነኝ “ በማለት ለክለቡ ያላቸውን ፍቅር የገለፁት ክሎፕ ደጋፊዎቹን “ የአለም ሁሉ ምርጦች ናችሁ “ ሲሉ አሞካሽተዋል።

“ ከክለቡ ጋር የመጨረሻዬ እንደሆነ አይሰማኝም “ ሲሉ “ I WILL NEVER WALK ALONE “ በማለት ለደጋፉዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ በእንግሊዝ እግርኳስ ታሪክ ፅፈናል “

የማንችስተር ሲቲ የመሐል ሜዳ ተጫዋች ሮድሪ ስኬታቸውን “ ታሪክ ሰርተናል “ ሲል ገልፆታል።

“ ታሪክ ከመስራት ባለፈ አዲስ ምዕራፍ ፅፈናል “ ያለው ሮድሪ “ ለተከታታይ አራት ዓመታት የሊጉን ዋንጫ ማሸነፍ ቀላል አይደለም “ ብሏል።

ሮድሪ በመጨረሻም “ ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መጥቼ ብዙ ነገሮችን አሳክቻለው “ ሲል ከታሪካዊው ድል በኋላ ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አሁን ቀጣዩን ዋንጫ ማሸነፍ እንፈልጋለን " ሀላንድ

የፕርሚየር ሊጉን የወርቅ ጫማ ለሁለተኛ ተከታታይ አመት ማሸነፍ የቻለው ኤርሊንግ ሀላንድ በቡድኑ መኩራቱን ገልጿል።

" በክለቡ ኮርቻለሁ አስደሳች ድል ነበር ሁሉም ተጨዋቾች ክብር ይገባቸዋል የዘንድሮው ዋንጫ ለአራተኛ ተከታታይ አመት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል " ሲል ኤርሊንግ ሀላንድ ተናግሯል።

ኤርሊንግ ሀላንድ ቀጥሎም አሁን ቡድናቸው ቀጣዩን የውድድር አመት ዋንጫ ማሸነፍ እንደሚፈልግ ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#laliga 🇪🇸

በስፔን ላሊጋ የሰላሳ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባርሴሎና ራዮ ቫዬካኖን 3ለ0 ሲያሸንፍ ሪያል ማድሪድ ከቪያሪያል 4ለ4 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።

የባርሴሎናን የማሸነፊያ ግቦች ፔድሪ 2x እና ሮበርት ሊዋንዶውስኪ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ለሪያል ማድሪድ ግቦችን አርዳ ጉለር 2x ፣ ሆሴሉ እና ሉካስ ቫስኩዌስ አስቆጥረዋል።

የቪያሪያልን አራት የአቻነት ግቦች አሌክሳንደር ሶርሎት 4x ከመረብ ማሳረፍ ችሏሰ።

በሌላ ጨዋታ አትሌቲኮ ማድሪድ በኦሳሱና 4ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

ባርሴሎና ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁን አረጋግጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ፔፕ ጋርዲዮላ በሲቲ እንደሚቀጥሉ ገለጹ ! ስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በማንችስተር ሲቲ አሰልጣኝነታቸው እንደሚቀጥሉ በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል። በማንችስተር ሲቲ ቤት እስከ 2025 የሚያቆይ ኮንትራት ያላቸው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ " ውሌ እስከሚጠናቀቅ እዚህ አለሁ " ብለዋል። እኔ እዚህ እስካለሁ ሌሎች ክለቦች ሊጉን ለማሸነፍ ይቸገራሉ የሚል እምነት የለኝም ያሉት…
ፔፕ ጋርዲዮላ ሲቲን ሊለቁ እንደሚችሉ ገለጹ !

ስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በሚቀጥለው የውድድር አመት መጨረሻ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ሊለያዩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

" ማንችስተር ሲቲን ለመልቀቅ ተቃርቢያለሁ " ያሉት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በሚቀጥለው አመት እዚሁ ለመቆየት አስቢያለሁ ከዛ በኋላ ለመልቀቅ የምቃረብ ይሆናል በማለት ተናግረዋል።

በሚቀጥለው የውድድር አመት መጨረሻ ውላቸው የሚጠናቀቀው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከክለቡ ጋር በቀጣይ ለመነጋገር ማሰባቸውንም ጠቁመዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
•MacBook Air, M1
•MacBook Pro, M1

•MacBook Air, M2
•MacBook Pro, M2

•MacBook, M1 Pro
•MacBook, M2 Pro

•MacBook, M1 Max
•MacBook, M2 Max

Contact Us
0953964175 @heymobile
@heyonlinemarket
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
የርገን ክሎፕ ይናፍቀኛል “ ፔፕ ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የመጨረሻ ጨዋታቸውን በሊጉ ለመሩት የርገን ክሎፕ ልዩ ቦታ እንዳላቸው ተናግረዋል።

“ የርገን ክሎፕ በጣም ይናፍቀኛል “ ያሉት ፔፕ ጋርዲዮላ “ በህይወቴ ውስጥ አስፈላጊው ሰው ነበር የመጨረሻ ጨዋታው ልዩ እንደነበረ ተስፋ አደርጋለሁ “ ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
2024/09/27 07:19:35
Back to Top
HTML Embed Code: