Telegram Web Link
ማድሪድ የተጨዋቾቹን ውል ሊያራዝም ነው !

የስፔን ላሊጋ አሸናፊው ሪያል ማድሪድ እድሚያቸው የገፋ ታሪካዊ ተጨዋቾቻቸውን ኮንትራት ለተጨማሪ አመት ለማራዘም በማሰብ ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

ሎስ ብላንኮዎቹ ሁለቱን የመሐል ሜዳ ተጨዋቾች ሉካ ሞድሪች እና ቶኒ ክሩስ በሚቀጥለው የውድድር አመት በቡድናቸው ውስጥ ለማቆየት ማሰባቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ካርሎሎ አንቾሎቲ ተጨዋቾቹ በስብሰባቸው ውስጥ እንዲቆይ መጠየቃቸው የተነገረ ሲሆን ተጨዋቾቹም የመቆየት ፍላጎት አላቸው ተብሏል።

በተጨማሪም ሪያል ማድሪድ የሉካስ ቫስኩዌስን ውል ለተጨማሪ አመታት ለማራዘም ከውሳኔ መድረሳቸው ታውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቶማስ ቱሄል በሙኒክ ቤት አይቀጥሉም !

ጀርመናዊው አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ከባየር ሙኒክ ጋር በሚቀጥለው የውድድር አመት የሚቀጥሉበት እድል እንደሌለ በይፋ አሳውቀዋል።

አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ከወራት በፊት ባየር ሙኒክን እንደሚለቁ አሳውቀው የነበረ ሲሆን ከቀናት በፊት በክለቡ ለመቀጠል ለንግግር ተቀምጠው ነበር።

አሰልጣኙ " ከባየር ሙኒክ ጋር ንግግር ነበረን ነገርግን በስምምነት አልተጠናቀቀም " ያሉ ሲሆን ነገ የማደርገው የመጨረሻ ጨዋታዬን ነው ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የህይወቴ ከባድ ሳምንት ነው " ክሎፕ

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በሊቨርፑል ቤት የመጨረሻ ጨዋታቸውን ከማድረጋቸው አስቀድመው ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገዋል።

የርገን ክሎፕ በቆይታቸው ምን ጉዳዮች አነሱ ?

- " ይህ ሳምንት በህይወቴ ውስጥ ከባድ ሳምንት ነው ፣ ትላንት ከተጨዋቾቹ ጋር የጋራ ጊዜ ነበረን ፣ መሰናበት በጣም ከባድ ነው።

- ቫር ላይ የሚሰሩ ሰዎች በትክክል ሊጠቀሙበት አልቻሉም ሰዎችን መቀየርም አልቻልንም ስለዚህ እንዲቀር ድምጽ እሰጣለሁ።

- ምርጡ እግርኳስ የተጫወትነው ከማንችስተር ሲቲ ጋር በዚህ አመት ያደረግነው ጨዋታ ነው ፣ የምወደው ቅፅበት ከባርሴሎና ጋር የነበረንን የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ።

- አንፊልድ ባሉት ደጋፊዎች ምክንያት በጣም የተለየ ቦታ ነው ስታዲየሙ ውብ ነው ነገርግን ደጋፊዎቹ የተለየ እንዲሆን አድርገውታል።" ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሴቶች ሱፐር ሊግ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ታወቀች !

የእንግሊዝ ሴቶች ሱፐር ሊግ የ2023/24 የውድድር አመት የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት ጃማይካዊቷ የማንችስተር ሲቲ ሴቶች ቡድን የፊት መስመር አጥቂ ቡኒ ሾው የእንግሊዝ ሴቶች ሱፐር ሊግ የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋች ተብላ መመረጥ ችላለች።

የ 27ዓመቷ የፊት መስመር አጥቂ ቡኒ ሾው በውድድር አመቱ ባደረገቻቸው አስራ ስምንት ጨዋታዎች ሀያ አንድ የሊግ ግቦችን በማስቆጠር ጥሩ ጊዜን ማሳለፍ ችላለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዴቪድ ራያ የወርቅ ጓንት አሸናፊ ሆኗል ! ስፔናዊው የአርሰናል ግብ ጠባቂ ዲቪድ ራያ የዘንድሮው የ2023/24 የውድድር አመት ምርጥ ግብ ጠባቂ በመሆን የወርቅ ጓንት አሸናፊ መሆኑን ከወዲሁ አረጋግጧል። ዲቪድ ራያ በዘንድሮው የ2023/24 የውድድር አመት ባደረጋቸው ሀያ ዘጠኝ የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች በአስራ አራቱ ላይ ግብ ሳይቆጠርበት መውጣት ችሏል። ዴቪድ ራያ በ2015/16 የውድድር አመት…
ዴቪድ ራያ ሽልማቱን በይፋ ተቀብሏል !

ስፔናዊው የአርሰናል ግብ ጠባቂ ዲቪድ ራያ የዘንድሮው የውድድር አመት የፕርሚየር ሊጉ የወርቅ ጓንት አሸናፊ በመሆኑ ከአወዳዳሪው አካል ሽልማቱ በይፋ ተበርክቶለታል።

ዲቪድ ራያ በዘንድሮው የውድድር አመት ባደረጋቸው ሰላሳ አንድ የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች በአስራ ስድስቱ ምንም ግብ ሳይቆጠርበት መውጣት ችሏል።

ግብ ጠባቂው በዚህ አመት በሊጉ ከተሞከሩበት የግብ ሙከራዎች ውስጥ ስልሳ ስድስት በመቶውን ( 66% ) የማዳን ሪከርድ እንዳለው ተገልጿል።

ዴቪድ ራያ በ2015/16 የውድድር አመት ፒተር ቼክ ካሳካ ወዲህ የወርቅ ጓንቱን ያሸነፈ የመጀመሪያው የአርሰናል ግብ ጠባቂም ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ኤቨርተን አንድ ነገር ያደርጋል ብላችሁ አትጠብቁ " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ተጨዋቾቻቸው በእሁዱ ጨዋታ ኤቨርተን የሆነ ነገር ያደርጋል የሚል ሀሳብ እያሰባችሁ ከሆነ " አሁኑኑ እርሱት " ሲሉ አሳስበዋል።

ፔፕ ጋርዲዮላ ለተጨዋቾቻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ጨዋታቸውን ማሸነፍ እንደሚገባ በመግለፅ " ኤቨርተን ከአርሰናል በሚያደርገው ጨዋታ የሆነ ነገር ያደርጋል ብላችሁ እያሰባችሁ ከሆነ እርሱት " ሲሉ ጠይቀዋል።

ሁሉም የማንችስተር ሲቲ ተጨዋች ማሸነፍ እና ማሸነፍ ብቻ እንዳለበት ማወቅ አለበት ያሉት አሰልጣኙ ካልሆነ ግን አርሰናል የፕርሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ይሆናል ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" ኤቨርተን አንድ ነገር ያደርጋል ብላችሁ አትጠብቁ " ጋርዲዮላ የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ተጨዋቾቻቸው በእሁዱ ጨዋታ ኤቨርተን የሆነ ነገር ያደርጋል የሚል ሀሳብ እያሰባችሁ ከሆነ " አሁኑኑ እርሱት " ሲሉ አሳስበዋል። ፔፕ ጋርዲዮላ ለተጨዋቾቻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ጨዋታቸውን ማሸነፍ እንደሚገባ በመግለፅ " ኤቨርተን ከአርሰናል በሚያደርገው ጨዋታ የሆነ ነገር ያደርጋል ብላችሁ…
" ዌስትሀም ህልማችንን እንድናሳካ እንዲያግዘን እመኛለሁ " አርቴታ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ እሁድ ከሚደረገው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሐግብር በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታን አድርገዋል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ምን አሉ ?

- መጀመሪያ የራሳችንን ስራ መስራት እና ጨዋታውን ማሸነፍ አለብን በመቀጠል ጥሩ ነገር እንመኛለን ዌስትሀም በዚህ አመት ጥሩ ነገር እየሰራ ይገኛል።

- ዌስትሀም ዩናይትድ በማንችስተር ሲቲ ጨዋታ ጥሩ ቀን እንደሚያሳልፍ እና ህልማችንን እንድናሳካ እንደሚያግዘን ተስፋ አደርጋለሁ።

- ከአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ጋር ምንም ግንኙነት አላደረግኩም ፣ በማሰብ ላይ የምገኘው ኤቨርተንን ስለማሸነፍ እና የሆነ ነገር እስከሚፈጠር መጠበቅ ነው።

- ለአብዛኞቻችን በጣም ትልቅ ሳምንት ነው አሁን በጣም ወሳኙ ወቅት ላይ ነን ቀኑ እስኪደርስ ጓጉቻለሁ ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ መዘጋጀት አለብን።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጣና ሞገዶቹ ድል አድርገዋል !

ባሕር ዳር ከተማ ከሀምበሪቾ ዱራሜ ጋር ያደረጉትን የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የባሕር ዳር ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ፍፁም ጥላሁን 2x ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ሀምበሪቾ ዱራሜ በውድድር አመቱ አስራ ዘጠነኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

የሀምበሪቾ ዱራሜ አብዛኞቹ ተጨዋቾች ከጨዋታው በፊት ከደሞዝ ክፍያ ጋር የተያያዘ ቅሬታቸውን ለማቅረብ ሳያሟሙቁ ጨዋታቸውን አድርገዋል።

በሊጉ ደረጃ ስንተኛ ናቸው ?

3️⃣ ባሕር ዳር ከተማ :- 44 ነጥብ

1️⃣6️⃣ ሀምበሪቾ ዱራሜ :- 8 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

አርብ - ባሕር ዳር ከተማ ከ ወላይታ ድቻ

እሁድ - ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀምበሪቾ ዱራሜ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🇪🇹 WANAW 🤝 ESCFUK 🇬🇧

ዋናው ስፖርት በኢትዮጵያ ስፖርት እና ባህል ፌደሬሽን በዩናይትድ ኪንግደም አዘጋጅነት ከጁላይ 12 እስከ 14፣ 2024 የሚካሄደው 12ኛው ዓመታዊ የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ስፖንሰር እና የተወዳዳሪዎች ይፋዊ የስፖርት ትጥቅ አቅራቢ በመሆኑ የተሰማውን ልባዊ ኩራት ይገልፃል።

Wanaw Sport is very proud to announce that it is the Official Kit Supplier and Festival Sponsor of the 12th Annual Ethiopian Sports and Cultural Festival organized by The Ethiopian Sports and Culture Federation in the United Kingdom that will be held on 12-14 July, 2024.

#ውድድር ካለ #ዋናው አለ!

When there's #competition, there's #Wanaw!

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔥 የዘንድሮውን የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን በኤቨርተን እና ዌስትሃም ይወስናሉ

የሊጉ የመጨረሻ ጨዋታዎች እሁድ ከምሽቱ 12፡00 ስዓት

⚽️ Manchester City vs Westham በ SS Premier League
⚽️ Arsenal vs Everton በ SS Liyu

🤔ዋንጫው የማን ነው? የእርሶን አስተያየት ያጋሩን             

👉 ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ለመከታተል ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#PremierLeagueOnDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
" ሲቲን ማሸነፍ ከባድ ነው " - ሞይስ

የዌስትሀም ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ ማንችስተር ሲቲ ለዋንጫ ባይፋለም እንኳን በሌሎች ጨዋታዎችም ለማሸነፍ አስቸጋሪ መሆኑን ገልጸዋል።

አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ ሲናገሩም " እንደ እውነቱ ከሆነ ማንችስተር ሲቲ ለዋንጫ እየተፎካከረ ይቅርና በሌሎች ብዙም አስፈላጊ ባልሆኑ ጨዋታዎችም ለማሸነፍ ከባድ ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

ለቀድሞ ተጨዋቻቸው ዴክላን ራይስ ሲሉ ማንችስተር ሲቲን ለማሸነፍ ይነሳሱ እንደሆነ በጋዜጠኞች የተጠየቁት አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ " አይመስለኝም " በማለት አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሊቨርፑል አሰልጣኝ ለመሾም ተስማማ ! የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ኔዘርላንዳዊውን አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በአሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ምትክ በሀላፊነት ለመሾም ከፊኖርድ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ይፋ ሆኗል። ሊቨርፑል ለአሰልጣኙ ውል ማፍረሻ ካሳ ያቀረበው ዘጠኝ ሚልዮን ዩሮ ዋጋ ውድቅ ሆኖበት እንደነበር የሚታወስ ሲሆን አሁን ላይ ክለቦቹ ሙሉ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል። የ 45ዓመቱ አሰልጣኝ…
አርኔ ስሎት ሊቨርፑልን እንደሚረከቡ ይፋ አደረጉ !

ኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በሚቀጥለው የውድድር አመት የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ በመሆን መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በዛሬው እለት አሰልጣኝ የርገን ክሎፕን በመተካት የሊቨርፑል ቀጣይ አሰልጣኝ በመሆን ፊርማቸውን ማኖራቸው ተገልጿል።

አሰልጣኙ በንግግራቸውም " በሚቀጥለው የውድድር አመት የሊቨርፑል አሰልጣኝ ሆኜ መሾሜን አረጋግጣለሁ " ሲሉ በይፋ አሳውቀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መሐመድ ኤልኔኒ ከአርሰናል ጋር እንደሚለያይ አሳወቀ !

ግብፃዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች መሐመድ ኤልኔኒ በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ከሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ጋር እንደሚለያዩ ይፋ አድርጓል።

መሐመድ ኤልኔኒ በአርሰናል ቤት ያለው ኮንትራት በሚቀጥለው ወር የሚጠናቀቅ መሆኑን ተከትሎ በነፃ ክለቡን የሚለቅ ይሆናል።

መሐመድ ኤልኔኒ ለደጋፊዎች ባስተላለፈው መልዕክትም " በልቤ ውስጥ ለዘላለም ትኖራላችሁ ምን ያህል እንደምወዳችሁ እና ለእኔ ስላላችሁ ቦታ ልነግራችሁ እፈልጋለሁ።

ለእኔ ያደረጋችሁትን ድጋፍ መቼም አልረሳውም ፣ እሁድ ኤምሬትስ ስታዲየም በአካል እነሰነባበታለን።"በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማሲሚላኖ አሌግሪ ከሀላፊነታቸው ተሰናበቱ !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ጁቬንቱስ ጣልያናዊውን አሰልጣኝ ማሲሚላኖ አሌግሪ ከሀላፊነት ማሰናበቱ ተገልጿል።

አሰልጣኝ ማስሚላኖ አሌግሪ ከክለቡ ጋር የኮፓ ኢታሊያ ዋንጫን ካሸነፉ ሁለት ቀናት በኋላ ከሀላፊነታቸው ተሰናብተዋል።

ፓውሎ ሞንቴሮ አሰልጣኝ ማስሚላኖ አሌግሪን በመተካት እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ የጁቬንቱስ ጊዜያዊ አሰልጣኝ እንደሚሆን ተገልጿል።

ጁቬንቱስ ለቀጣይ የውድድር አመት የቦሎኛውን አሰልጣኝ ቲያጎ ሞታ በሀላፊነት ለመሾም በመስራት ላይ እንደሚገኙ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ማን ይሆናል ? የዘንድሮ የውድድር ዓመት የ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የአመቱ ምርጥ እና ወጣት ተጫዋች እጩዎች ይፋ ተደርገዋል። በአመቱ ምርጥ ተጫዋች ዝርዝር ውስጥ :- - ፊል ፎደን ፣ ኤርሊንግ ሀላንድ ፣ አሌክሳንደር አይሳክ ፣ ማርቲን ኦዴጋርድ ፣ ኮል ፓልመር ፣ ዴክላን ራይስ ፣ ኦሊ ዋትኪንስ እና ቫን ዳይክ ተካተዋል። በወጣት ምርጥ ተጫዋች እጩ ውስጥ ስምንት ተጫዋቾች…
ኮል ፓልመር የአመቱ ምርጥ ወጣት ተጨዋች ተባለ !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ2023/24 የውድድር አመት የአመቱ ምርጥ ወጣት ተጨዋች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት እንግሊዛዊው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች ኮል ፓልመር የፕርሚየር ሊግ የአመቱ ምርጥ ወጣት ተጨዋች ተብሎ ተመርጧል።

ኮል ፓልመር በዘንድሮው የውድድር አመት በሊጉ ለቼልሲ ሀያ ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ሲችል አስር ለግብ የሆኑ ኳሶችንም አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ መድን ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 5ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ ደረጃቸውን ማሻሻል ችለዋል።

የኢትዮጵያ መድንንን የማሸነፊያ ግቦች አለን ካይዋ 3x ፣ ሀይደር ሸረፋ እና ብሩክ ሙሉጌታ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥረዋል።

ባለፉት ስምንት ጨዋታዎች ሽንፈት ያልገጠመው ኢትዮጵያ መድን አምስተኛ ተከታታይ ድሉን ማስመዝገብ ችሏል።

የኢትዮጵያ መድኑ ተጨዋች አለን ካይዋ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ሀትሪክ መስራት የቻለ #ስድስተኛው ተጨዋች መሆን ችሏል።

በዚህ አመት ሀትሪክ የሰሩ ተጨዋቾች እነማን ናቸው ?

- አለን ካይዋ ( ኢትዮጵያ መድን )

- አሊ ሱሌይማን ( ሀዋሳ ከተማ )

- ሀብታሙ ታደሰ ( ባሕር ዳር ከተማ )

- አቤል ያለው ( ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር )

- አንተነህ ተፈራ ( ኢትዮጵያ ቡና )

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

9️⃣ ድሬዳዋ ከተማ :- 34 ነጥብ

1️⃣1️⃣ ኢትዮጵያ መድን :- 31 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ሐሙስ - ኢትዮጵያ መድን ከ አዳማ ከተማ

ሐሙስ - ወልቂጤ ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኬቨን ዴብሮይን ልምምድ ሰርቷል !

የማንችስተር ሲቲው ቤልጂየማዊ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬቨን ዴብሮይን ከቀናት በፊት ካጋጠመው ጉዳት በማገገም ወደ ልምምድ መመለሱ ተገልጿል።

ማንችስተር ሲቲ በዛሬው ዕለት ከእሁዱ የዌስትሀም ዩናይትድ ወሳኝ የሊግ የመጨረሻ ጨዋታ በፊት በሰሩት መደበኛ ልምምድ ላይ ኬቨን ዴብሮይን መሳተፉ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሪያድ ደርቢ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ !

በሳውዲ አረቢያ ሊግ ሰላሳ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አል ናስር ከአል ሂላል ጋር ያደረጉትን የሪያድ ደርቢ ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችለዋል።

የአል ናስርን ግብ ኦታቪዮ ከመረብ ማሳረፍ ሲችል ሚትሮቪች በጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃ አል ሂላልን አቻ አድርጓል።

የአል ሂላሉ የፊት መስመር ተጨዋች አሌክሳንደር ሚትሮቪች ሀያ ሰባተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዘንድሮው የውድድር አመት በአርባ አራት ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ በማድረግ በሳውዲ አረቢያ ሊግ ታሪክ ቀዳሚው ተጨዋች መሆኑን ችሏል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ አል ሂላል :- 90 ነጥብ

2️⃣ አል ናስር :- 78 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ማክሰኞ - አል ሪያድ ከ አል ናስር

ማክሰኞ - አል ሂላል ከ አል ታኢ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ናፖሊ የጨዋታ ቀን እንዲቀየርለት መጠየቁ ተገለጸ ! የጣልያኑ ክለብ ናፖሊ ፕሬዝዳንት ዲ ላውረንቲስ ክለባቸው የፊታችን አርብ ከፊዮሬንቲና ጋር የሚያደርገው የሊግ መርሐ ግብር ቀን እንዲቀየርላቸው መጠየቃቸው ተገልጿል። ፕሬዝዳንቱ የቀን ይቀየርልን ጥያቄውን ያቀረቡት ጣልያን ውስጥ አርብ እና ቀን 17 ሲገጣጠሙ መጥፎ እድል ያመጣል የሚል እምነት መኖሩን ተከትሎ እንደሆነ ተዘግቧል። አወዳዳሪው አካል…
ናፖሊ ከፊዮሬንቲና ነጥብ ተጋርተዋል !

በጣልያን ሴርያ የሰላሳ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ናፖሊ ከፊዮሬንቲና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የናፖሊን ግቦች ራህማኒ እና ክራቫትሼሊያ ከመረብ ሲያሳርፉ ለፊዮሬንቲና ብራጊ እና ንዞላ አስቆጥረዋል።

የአምናው የሊጉ ሻምፒዮን ናፖሊ ያለፉትን ስድስት የጣልያን ሴርያ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

ናፖሊ በዘንድሮው የውድድር አመት ሀያ አራት የሴርያ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ሳይችል ቀርቷል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

8️⃣ ፊዮሬንቲና :- 54 ነጥብ

9️⃣ ናፖሊ :- 52 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

እሁድ - ናፖሊ ከ ሊቼ

እሁድ - ካግሊያሪ ከ ፊዮሬንቲና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
🔹iPhone 15 Pro Max
🔹iPhone 14 Pro Max

🔹 Samsung S24 Ultra
🔹 Samsung S23 Ultra

♦️ New & Slightly Used Available

Contact us :
0925927457
@Heyonlinemarket
https://heymobile.store/
2024/09/29 12:35:53
Back to Top
HTML Embed Code: