Telegram Web Link
ማንችስተር ሲቲ ግብ ጠባቂውን አጥቷል !

ብራዚላዊው የማንችስተር ሲቲ ግብ ጠባቂ ኤደርሰን ማክሰኞ ምሽት ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ከቀሪ ጨዋታዎች ውጪ መሆኑን ክለቡ ይፋ አድርጓል።

ተጨዋቹ በማክሰኞ ምሽቱ የቶተንሀም ጨዋታ ያጋጠመው ግጭት ዐይኑ አካባቢ የመሰበር ጉዳት እንዳደረሰበት ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ኤደርሰን ማንችስተር ሲቲ በሊጉ ከዌስትሀም እና በኤፌ ካፕ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ የሚያመልጠው ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሪነቱን አጠናከረ !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወላይታ ድቻ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 5ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የማሸነፊያ ግቦች ባሲሩ ዑማር ፣ ሳይሞን ፒተር ፣ ኤፍሬም ታምራት ፣ ኪቲካ ጅማ እና ፍፁም ግርማ በራሱ ግብ ላይ ከመረብ አሳርፈዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዘንድሮው የውድድር አመት ከየትኛውም ክለብ በላይ አርባ ስምንት ግቦችን በተጋጣሚው መረብ ላይ አሳርፏል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

1️⃣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ :- 53 ነጥብ

1️⃣3️⃣ ወላይታ ድቻ :- 28 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

አርብ - ባሕርዳር ከተማ ከ ወላይታ ድቻ

ቅዳሜ - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ፋሲል ከነማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሊጉ ሀላፊ የአርሰናልን ጨዋታ ይታደማሉ !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊጉ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሪቻርድ ማስተርስ እሁድ በተመሳሳይ ሰዓት በሚደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች አርሰናል ከኤቨርተን የሚያደርጉትን ጨዋታ ለመታደም መምረጣቸው ተገልጿል።

ሀላፊው በሲቲ ጨዋታ አለመታደማቸው በፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ክስ ላይ ለሚገኘው ማንችስተር ሲቲ አሸናፊ ከሆነ ለሁለተኛ ጊዜ ዋንጫውን በእጃቸው እንዳይሰጡ እንደሚያደርጋቸው ተዘግቧል።

ሪቻርድ ማስተርስ ባለፈው አመት ኢትሀድ ተገኝተው የነበረ ሲሆን በዚህ አመት የማንችስተር ሲቲን ጨዋታ ለመታደም ሌላኛው ሀላፊ አሊሰን ብሪቴን እንደሚያመሩ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ግቡን ባለማስቆጠሬ ሀላፊነት እወስዳለሁ " ሰን

የቶተንሀሙ የፊት መስመር ተጨዋች ሰን ሁንግ ሚን ከቀናት በፊት ከማንችስተር ሲቲ ጋር በነበራቸው ጨዋታ ያገኘውን ጥሩ የግብ እድል ባለመጠቀሙ ሀላፊነት እንደሚወስድ ገልጿል።

የግብ ጠባቂው ውሳኔ የሚደንቅ ነበር ያለው ሰን ሁንግ ሚን " ቢሆንም ግቡን ባለማስቆጠሬ ሙሉ ሀላፊነቱን እወስዳለሁ ፣ ቡድኑ ጥሩ ተጫውቶ ነበር ጥሩ ተዘጋጅተንም ነበር ውጤት ይገባን ነበር።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሉክ ሾው ለኤፌ ካፕ ፍፃሜ ይደርሳል ?

የማንችስተር ዩናይትድ የመስመር ተጨዋች ሉክ ሾው ከአንድ ሳምንት በኋላ ለሚደረገው የኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ የመድረስ እድሉ አነስተኛ መሆኑን አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ገልጸዋል።

እንግሊዛዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሀሪ ማጓየር በበኩሉ በኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ የሚደርስበት እድል የሰፋ መሆኑን አሰልጣኙ አረጋግጠዋል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ አያይዘውም ራፋኤል ቫራን እና ቪክቶር ሊንድሎፍ በእሁዱ የብራይተን ጨዋታ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሲቲ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመሩት የፕርሚየር ሊጉ መሪ ማንችስተር ሲቲዎች የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋች #ሶስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ፊል ፎደን ፣ ሮድሪ እና ኤርሊንግ ሀላንድ የማንችስተር ሲቲ የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል።

የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
አፄዎቹ ድል አድርገዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ከወልቂጤ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የአፄዎቹን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ጌታነህ ከበደ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ወልቂጤ ከተማ ያለፉትን አምስት ተከታታይ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ተሸንፈዋል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

4️⃣ ፋሲል ከነማ :- 40 ነጥብ

1️⃣4️⃣ ወልቂጤ ከተማ :- 16 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ፋሲል ከነማ

ሐሙስ - ወልቂጤ ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አርሰናልን ለመፎካከር ተዘጋጅተናል " ዱኩሬ

የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን ተጨዋች አብዱላይ ዱኩሬ ቡድናቸው በእሁዱ የአርሰናል ጨዋታ ምርጡን አቋም ማሳየት እንደሚፈልግ በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

" ከአርሰናል ጋር የምናደርገውን የመጨረሻ ጨዋታ አለም ሁሉ እንደሚመለከተው ግልፅ ነው ምርጡን አቋማችንን እንጠቀማለን " ያለው ዱኩሬ " በጨዋታው አርሰናልን ለመፎካከር ተዘጋጅተናል " ሲል ተደምጧል።

የሁለቱ ክለቦች ተጠባቂ ጨዋታ እሁድ ምሽት 12:00 በኤምሬትስ ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
ኢትዮጵያን በማራቶን የሚወክሉ አትሌቶች ታወቁ !

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሀገራችን ኢትዮጵያን በ2024ቱ የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በማራቶን በሁለቱም ፆታዎች የሚወክሉ አትሌቶችን ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት :-

- በወንዶች
:- ቀነኒሳ በቀለ ፣ ሲሳይ ለማ ፣ ዴሬሳ ገለታ እንዲሁም ታምራት ቶላ እና ኡሰዲን መሐመድ በተጠባባቂነት መመረጣቸው ተገልጿል።

- በሴቶች :- ትግስት አሰፋ ፣ አማኒ በሪሶ ፣ መገርቱ አለሙ እንዲሁም ጎይተቶም ገብረ ሥላሴ እና ቡዜ ዲሪባ በተጠባባቂነት መመረጣቸው ይፋ ሆኗል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ንጎሎ ካንቴ ለብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ቀረበለት !

በአሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሻምፕ የሚመራው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ከአንድ ወር በኋላ ለሚደረገው የጀርመን የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር የሚጠቀመውን ስብስብ ይፋ አድርጓል።

ለሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ኢትሀድ የሚጫወተው የመሐል ሜዳ ተጨዋቹ ንጎሎ ካንቴ ከሁለት አመት ቆይታ በኋላ ለብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ቀርቦለታል።

በስብስቡ ውስጥ ሚሼል ኦሊሴ ፣ ማሎ ጉትሶ ፣ አሌክሳንደር ላካዜት ፣ አክሴል ዲሳሲ ፣ ጉንዶዚ እና ሙሳ ዲያቢ የመሳሰሉ ተጨዋቾች ሳይካተቱ ቀርተዋል።

ሙሉ የቡድን ስብስቡ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና ድል አድርጓል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ከአልሜሪያ ጋር ያደረገውን የስፔን ላሊጋ ሰላሳ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የባርሴሎናንን የማሸነፊያ ግቦች ፌርሚን ሎፔዝ 2x ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የሁለቱ ክለቦች ደረጃ ምን ይመስላል ?

2️⃣ ባርሴሎና - 79 ነጥብ

2️⃣0️⃣ አልሜርያ  - 17 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

እሁድ - ባርሴሎና ከ ራዮ ቫዬካኖ

እሁድ - ማዮርካ ከ አልሜርያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
Forwarded from HEY Online Market
🔹iPhone 15 Pro Max
🔹iPhone 14 Pro Max

🔹 Samsung S24 Ultra
🔹 Samsung S23 Ultra

♦️ New & Slightly Used Available

Contact us :
0925927457
@Heyonlinemarket
https://heymobile.store/
" ሊጉን ለማሸነፍ ሁሉንም እንሰጣለን " ፊል ፎደን

የማንችስተር ሲቲው የፊት መስመር ተጨዋች ፊል ፎደን ቡድናቸው የሊጉን ዋንጫ ለአራተኛ ተከታታይ ጊዜ ለማሸነፍ በመጨረሻው ጨዋታ ያለውን ሁሉ እንደሚሰጥ ገልጿል።

ፎደን በንግግሩም " በተከታታይ ለአራተኛ ጊዜ ሊጉን ለማሸነፍ እሁድ ሁሉንም ነገር እንሰጣለን " ያለ ሲሆን " ማንም ያላደረገው ትልቅ ስኬት እና ታሪክ ነው ለእኛ ትልቅ ትርጉም አለው ለጨዋታው ጓጉተናል " በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ብራዚል የሴቶች አለም ዋንጫ ታዘጋጃለች !

የአለም እግርኳስ የበላይ ፊፋ 74ኛውን የምክርቤቱ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት በታይላንድ ባንኮክ በማካሄድ ይገኛል።

ፊፋ በስብሰባው ወቅት የ2027 ሴቶች አለም ዋንጫ ውድድርን የደቡብ አሜሪካዋ ሀገር #ብራዚል እንድታዘጋጅ መምረጡን በይፋ አሳውቋል።

ብራዚል የሴቶች አለም ዋንጫ ውድድርን ማዘጋጀት የቻለች የመጀመሪያዋ የደቡብ አሜሪካ ሀገር በመሆንም አዲስ ታሪክ የምታስመዘግብ ይሆናል።

የሴቶች አለም ዋንጫን እስካሁን እነማን አዘጋጁ ?

የሴቶች አለም ዋንጫ ውድድር በ2027 ለአስረኛ ጊዜ ሲካሄድ እስካሁን ቻይና 2x ፣ አሜሪካ 2x ፣ ስዊድን ፣ ጀርመን ፣ ካናዳ ፣ ፈረንሳይ እንዲሁም አውስትራሊያ እና ኒውዝላንድ በጥምረት ያዘጋጁ ሀገራት ናቸው።

አሜሪካ የሴቶች አለም ዋንጫ ውድድርን አራት ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ይዛለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ከተጨዋቹ ጋር እንደሚለያይ አሳወቀ !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ከካሜሮናዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጆኢል ማቲፕ ጋር በውድድር አመቱ መጨረሻ እንደሚለያዩ ይፋ አድርገዋል።

ጆኢል ማቲፕ በሊቨርፑል ቤት በቆየባቸው ስምንት የውድድር አመታት 201 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት ችሏል።

የ 32ዓመቱ ተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጆኢል ማቲፕ በሊቨርፑል ቤት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ላግ የፕርሚየር ሊግ ዋንጫዎችንም ማሳካት ችሏል።

" እዚህ ሊቨርፑል ውስጥ ስምንት አስደናቂ አመታት አሳልፌያለሁ ፣ ከታላቅ አሰልጣኝ እና ድንቅ ቡድን ጋር አስደናቂ ታሪክ ተካፍያለሁ ከደጋፊው ጋር በነበረኝ ቆይታ ደስተኛ ነኝ ትዝታዎች ሁልጊዜ አብረውኝ ይኖራሉ።"ሲል ማቲፕ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቲያጎ በጥር ወር ከሊቨርፑል ጋር ይለያያል ? የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቲያጎ አልካንትራ በጥር ወር የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ሊቨርፑልን እንደማይለቅ ተገልጿል። ስፔናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቲያጎ አልካንትራ በሚቀጥለው ክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ሊቨርፑልን ይለቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል። ቲያጎ አልካንትራ በሊቨርፑል ቤት ያለው ኮንትራት ከስድስት ወራት በኋላ…
ቲያጎ አልካንትራ ከሊቨርፑል ጋር ይለያያል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቲያጎ አልካንትራ በሚቀጥለው ክረምት በክለቡ ያለው ኮንትራት ሲጠናቀቅ ሊቨርፑልን እንደሚለቅ ይፋ ተደርጓል።

ስፔናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቲያጎ አልካንትራ ውሉ የሚጠናቀቅ መሆኑን ተከትሎ በነፃ ዝውውር ሊቨርፑልን እንደሚለቅ ተገልጿል።

ቲያጎ አልካንትራ በሊቨርፑል ቤት በቆየባቸው አመታት ዘጠና ስምንት ጨዋታዎች አድርጎ ስድስት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአሰልጣኝ ዣቪ የባርሴሎና ቆይታ ?

ስፔናዊው የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ዋና አሰልጣኝ ዣቪ ከክለቡ ሊሰናበቱ እንደሚችሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን በመዘገብ ላይ ናቸው።

አሰልጣኝ ዣቪ ከቀናት በፊት ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ የሰጡት አስተያየት ከባርሴሎናው ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ ጋር አለመግባባት ውስጥ ሳይከታቸው እንዳልቀረ ተዘግቧል።

ዣቪ ከቀናት በፊት ቡድናቸው ከሌሎች ክለቦች ጋር ለመፎካከር መጠናከር እንደሚያስፈልገው ገልፀው ይህንን ለማድረግ የክለቡ የፋይናንስ ሁኔታ በሀያ አመታት ውስጥ የከፋ መሆኑን ተናግረው ነበር።

ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ በዣቪ አስተያየት መበሳጨታቸው ሲገለፅ በተጨማሪም አሰልጣኙ ውላቸውን ካደሱ በኋላ በቡድኑ እምነት አለኝ በማለት የተናገሩትን ቃል አፍርሰዋል የሚል እምነት እንዳላቸው ተነግሯል።

አሰልጣኝ ዣቪ ከወራት በፊት በአመቱ መጨረሻ ባርሴሎናን እንደሚለቁ አሳውቀው የነበረ ቢሆንም በቅርቡ ክለቡ ሀሳባቸውን አስቀይሯቸው ለመቆየት ወስነው እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሲቲ የመጫወት ፍላጎትን ይወስዳል " ፔሬራ

የፉልሀሙ የመሐል ሜዳ ተጨዋች አንድሬስ ፔሬራ ማንችስተር ሲቲን መግጠም የመጫወት ፍላጎትን እና ጥንካሬን እንደሚያጠፋ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ከማንችስተር ሲቲ ጋር ስትጫወት ያለህን የመጫወት ፍላጎት እና ጥንካሬ ከውስጥህ ይወስዱታል " የሚለው አንድሬስ ፔሬራ የልጆች እና ትልቅ ሰዎች አይነት ጨዋታ ነው የሚመስለው በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሮቢን ቫንፐርሲ በሀላፊነት ተሾመ !

ኔዘርላዳዊው የቀድሞ የፊት መስመር አጥቂ ሮቢን ቫንፐርሲ የኔዘላንዱ ክለብ ሄረንቬን እግርኳስ ክለብ አሰልጣኝ በመሆን በሀላፊነት መሾሙ ተገልጿል።

የቀድሞ የአርሰናል እና ማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች ሮቢን ቫንፐርሲ የመጀመሪያ ክለቡን በአሰልጣኝነት የሚመራ ይሆናል።

ሄረንቬን ፒኤስቪ አሸናፊ በሆነበት የዘንድሮው የኔዘርላንድ ሊግ አስረኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/29 10:29:01
Back to Top
HTML Embed Code: