This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
yme yme byalew👌
//ያለ ልብ እንዳልሞት\\
አቧራው ፍቅርሽን
ንፋስ ሲያራግበው፤
እንዴት አይኔን አልፎ
ልቤን አሳደፈው።
ብዙም ሳይቆይ ገና
ልጠራርገው ብል፤
በጡብ ቤት ገንብቶ
አንቺን ሳለሽ ስእል።
ስእሉን ላጠፋው
ቀለም ብደባልቅ፤
ያንቺ ውበት ጎላ
አማረበት ይልቅ።
ጥቁር ቀለም ይዤ
ስእሉን ብቀባው፤
ሊያበላሽሽ ቀርቶ
ጥላሽ ሆኖ አረፈው።
የቤቱ ሳያንሰኝ
ያንቺ ስእል ጎልቶ፤
አፍቃሪ አስባለኝ
ሰዉ ተዘባብቶ፤
ልቤ ጥሎኝ ሄደ
ንግስቱን ለመሾም፤
ፍቃድሽ ከሆነ
ኩራት ቢይዝሽም፤
ይኽንን አርጊልኝ
እንዲያው በፍቅር ስም።
ከቻልሽ፤
ንጉስ እኔን አርገሽ
ልቤን ንገሺበት፤
ካልቻልሽ፤
ልብሽ ተያዥ ሆኖ
ይቀመጥ ከኔ ቤት፤
ድንገት፤
የኔን ካልመለሽው
ያለ ልብ እንዳልሞት።
@abela_black
@getem
@getem
@getem
አቧራው ፍቅርሽን
ንፋስ ሲያራግበው፤
እንዴት አይኔን አልፎ
ልቤን አሳደፈው።
ብዙም ሳይቆይ ገና
ልጠራርገው ብል፤
በጡብ ቤት ገንብቶ
አንቺን ሳለሽ ስእል።
ስእሉን ላጠፋው
ቀለም ብደባልቅ፤
ያንቺ ውበት ጎላ
አማረበት ይልቅ።
ጥቁር ቀለም ይዤ
ስእሉን ብቀባው፤
ሊያበላሽሽ ቀርቶ
ጥላሽ ሆኖ አረፈው።
የቤቱ ሳያንሰኝ
ያንቺ ስእል ጎልቶ፤
አፍቃሪ አስባለኝ
ሰዉ ተዘባብቶ፤
ልቤ ጥሎኝ ሄደ
ንግስቱን ለመሾም፤
ፍቃድሽ ከሆነ
ኩራት ቢይዝሽም፤
ይኽንን አርጊልኝ
እንዲያው በፍቅር ስም።
ከቻልሽ፤
ንጉስ እኔን አርገሽ
ልቤን ንገሺበት፤
ካልቻልሽ፤
ልብሽ ተያዥ ሆኖ
ይቀመጥ ከኔ ቤት፤
ድንገት፤
የኔን ካልመለሽው
ያለ ልብ እንዳልሞት።
@abela_black
@getem
@getem
@getem
ወደድኩሽ .....ጅል እስክሆን
ሄድሽ ደሞ .......ያንን ሰሞን
አንቺዬ
የተነሳሽበት ማልደርስበት መንገድ
ናፍቆትሽን ይዤ ዘላለም ል'ራመድ
ከበደኝ
ቀድሞውንስ መች ቀለለኝ።
ታድያ ይሄን እየሰማሽ
እንደምን ነህ አልሺኝ
እኔማ...
አለው እንደምንም ምንም ባለመሆን
ታውቂው የለ አፍቃሪን ያፈቀረ ሰሞን
አንዲያ ነኝ....
አዎን
የናፍቆቴን መራብ ትውስታ ላይገታው
ዝምብዬ ምኳትን ህመሜን ላይረታው
መጣው ስላልሺኝ ነው አሁንም ምበረታው።
አንቺዬ
ውዬ አድሪያለው እና እስክትመጪ በፆም
ባክሽ ብቅ በዪ እስትንፋሴ እንዳትቆም።
✍️#በረከት_ሐ(@berii34)
@getem
@getem
@getem
ሄድሽ ደሞ .......ያንን ሰሞን
አንቺዬ
የተነሳሽበት ማልደርስበት መንገድ
ናፍቆትሽን ይዤ ዘላለም ል'ራመድ
ከበደኝ
ቀድሞውንስ መች ቀለለኝ።
ታድያ ይሄን እየሰማሽ
እንደምን ነህ አልሺኝ
እኔማ...
አለው እንደምንም ምንም ባለመሆን
ታውቂው የለ አፍቃሪን ያፈቀረ ሰሞን
አንዲያ ነኝ....
አዎን
የናፍቆቴን መራብ ትውስታ ላይገታው
ዝምብዬ ምኳትን ህመሜን ላይረታው
መጣው ስላልሺኝ ነው አሁንም ምበረታው።
አንቺዬ
ውዬ አድሪያለው እና እስክትመጪ በፆም
ባክሽ ብቅ በዪ እስትንፋሴ እንዳትቆም።
✍️#በረከት_ሐ(@berii34)
@getem
@getem
@getem