የተለያዩ የስትሪንግ አርት ስራውችን እኛ ዘንድ ያገኛሉ ይምጡ ይጎብኙ ያሻዎት ይሽምቱ
0992584860 ያገኙናል
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አታላይ!
~
"አንቱን መዘከሬ ከሆነ ስህተቴ፣
እኔ አንቱን ዘክሬ ይቅርብኝ ጀነቴ!"
~
"ጀነትን አልፈልግም" ማለት የራሳችሁ ምርጫ ነው። ነብዩ ﷺ "ሁሉም ህዝቦቼ ጀነትን ይገባሉ፣ እምቢ ያለ ሲቀር" ብለዋል። እምቢታ ማለት ትእዛዝን አለመቀበል ነው።

"አንቱን መዘከሬ ከሆነ ስህተቴ" የሚለው ግን ቀንዳም ውሸት ነው። በዚህ ቅጥፈት መሰረት:–

~ መውሊድ የማይጨፍር ሰው ነብዩን ﷺ በሶለዋት አያወሳም ማለት ነው። አይን ያወጣ ቅጥፈት!
~ እሳቸውን ማውሳት ማለት በመውሊድ መጨፈር ከሆነ አመቱን ሙሉ ረስታችኋቸው የምታወሷቸው በመውሊድ ቀን ብቻ ነው ማለት ነው።
~ ድግስ ካልተደገሰ፣ ጭፈራ ካልተጨፈረ ነብዩን ﷺ ማውሳት አይቻልም ማለት ነው።
~ በርካታ የመውሊድ ደጋፊዎች ቢድዐ መሆኑን ያምናሉ። የአሕባሽ ቲቪም ሰሞኑን ይህንኑ አረጋግጧል። መውሊድ ከጊዜ በኋላ የመጣ መጤ ፈሊጥ በመሆኑ ላይ ከተስማማችሁ፣ እሳቸውን ማውሳት ማለት መውሊድ መጨፈር ከሆነ ይሄ መውሊድ ከመጀመሩ በፊት ያለፉት ሶሐቦች፣ ታቢዒዮች፣ አትባዑ ታቢዒን፣ አኢማዎች ሁሉ ነብዩን ﷺ አውስተው አያውቁም ማለት ነው። ከዚህ በላይ ቅጥፈት አለ?!
~ እነዚህ ሰዎች ዘንድ ነብዩን ﷺ ማውሳት ማለት አመት ጠብቆ መደለቅ፣ መደነስ ነው። ሎጂካችሁ ጭፈራቸውና ዝላያቸው እየሱስን ከመውደድ የተነሳ እንደሆነ ከሚሞግቱት ጴንጤዎች ጋር ያመሳስላችኋል። እንዲያውም ቅጥፈት ከመሆኑም ጋር የነሱ ሎጂክ ከናንተ ሎጂክ ይሻላል። የሚያዘልላችሁ ፍቅር ከሆነ በአመት አንድ ጊዜ ከሚጨፍረው ይልቅ በየሳምንቱ የሚጨፍረው የበለጠ ያፈቅራል ማለት ነው። ይልቅ እሳቸውን በመውደድ እያመሃኘ ከፊሉ እንጀራውን የሚያበስል፣ ከፊሉ የጭፈራ ሱሱን የሚያስተነፍስ፣ ሌላው ለብልግና አጋጣሚውን የሚጠቀም፣ ሌላው ደግሞ ምኑም ሳይገባው "ሲሉ ሰማሁ ብዬ፣ እላለሁ ነብዬ" የሚል የደመቀ አጫፋሪ ነው።

~
ኢብኑ ሙነወር
የቴሌግራም ቻናል፦

https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
2024/06/29 05:29:22
Back to Top
HTML Embed Code: