Telegram Web Link
የሚሰጡ እጆች የተባረኩ ናቸው!!

ልጆቻችን ከትምህርት ትጋታቸው ባሻገር በማኅበራዊ ሕይወታቸው የሚያከናውኗቸው ተግባራት ዘወትር እንዳስገረሙን ነውና ለልጆቻችን ልገሳን ስላስተማሩልን አብዝተን እናመሰግናለን።🙏🙏🙏
ውድ የልጆቻችን ወላጆች፦

በሀገራችን እየተከሰተ ያለውን ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ በተመለከተ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ምን ማድረግ እንዳለብን የሰጠውን ማብራርያ እናስታዉሳችሁ።

➡️ ከቤት ውጭ ከሆኑ ፦ ከዛፎች ፣ ከሕንፃዎች ፣ ከኤሌትሪክ ምሶሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መቆየት።

➡️ በቤት ውስጥ ከሆኑ ፦ በበር መቃኖች ፣ ኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ። ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች እንዲሁም ከመስኮት አካባቢ መራቅ። የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።

➡️ በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ ፦ ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር ፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።

➡️ መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ ፦ የኤሌትሪክ መተላለፊያ ምሶሶዎችን፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም።

''ፈጣሪ የምንወዳቸው ልጆቻችንን፣ ህዝባችንን እና ሀገራችንን ይጠብቅልን!''
ንግግርን በተግባር 👌

የሁሉ መከታ፣ የሁሉ አለኝታ🥰

ለገና በዓል የተደረገ ድንገቴ ፈንጠዝያ (SURPRISE)

ሺ አመት ኑርልን ሚስተር ኢዮብ🙏

መልካም በዓል

🙏🙏🙏
የምንወዳችሁ ልጆቻችን
የምናከብራችሁ የልጆቻችን ወላጆች፦

እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ቤታችሁ በሰላም፣ በፍቅርና በደስታ ይሞላ። ፈጣሪ ልጆቻችንን በእውቀትና በጥበብ ይባርክልን እያልን፤

በዚህ በዓል ለምንወዳቸው ምርጥ ልጆቻችን የህይወት ስኬት ሳንደክም ቀን ከሌት እንደምንሰራ ቃል እየገባንና ዘወትር የእናንተ ከፍተኛ ክትትል እንዳይለየን አደራችሁን እያልን ስለመረጣችሁንና የሳፋሪ ቤተሰብ ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።


መልካም የገና በዓል ይሁንላችሁ!

ኢዮብ አየለ
ፕሬዝደንት
ሳፋሪ አካዳሚ
Our Dear Kids and Respected Parents,

Merry Christmas! On this special occasion, we want to take a moment to thank you for being an integral part of our Safari family. Your unwavering support, trust, and commitment have been the foundation of our shared journey.

This Christmas, we reaffirm our promise to work tirelessly, day and night, to ensure the success of our Kids. Our mission is to guide them toward a bright and prosperous future. However, we cannot do this alone. We kindly ask for your continued cooperation and partnership in working together for the betterment of our Kids’ lives.

May this holiday season bring joy, love, and peace to your families. Thank you for being part of our journey and for trusting us with the growth and success of our children.

Wishing you a Merry Christmas!

Eyob Ayele
Safari Academy
President
ውድ ልጆቻችን ስለጠፈር ሳይንስ ምን ያህል ታውቃላችሁ?
እስኪ ያነበብነውን እናጋራችሁ🙏
2025/07/09 05:23:43
Back to Top
HTML Embed Code: