Telegram Web Link
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥቆማ

" የ2024 ESP ማመልከቻ ማስገባት ይቻላል " - የአሜሪካ ኤምባሲ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የEducation USA Scholars Program (#ESP) 2024 ማመልከቻ ክፍት መሆኑን አሳውቋል።

ESP በአካዳሚክ ጠንካራ የሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ወደ አሜሪካ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች #እንዲያመለክቱ የሚረዳ የአራት ሳምንታት የሥልጠና መርሃ ግብር ነው።

ዓላማውም ደግሞ የነገዋን ኢትዮጵያ ለመገንባት የሰለጠኑ እና ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅት ያላቸውን መሪዎችን ማፍራት እንደሆነ ኤምባሲው አመልክቷል።

ከአመልካቾች 20 ከፍተኛ የአካዳሚክ ብቃት ያላቸውን ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በኤምባሲው ይለያሉ። ተማሪዎቹ በአካዳሚክ ሪከርዳቸው፣ እንዲሁም በኢንተርቪው እንዲለዩ ይደረጋል።

ከጠቅላላው 20 የመጨረሻ እጩዎች መካከል፣ 15 ከፍተኛ ብቃት ያላቸው፣ በኢኮኖሚ የተቸገሩ ተማሪዎች ከመደበኛ ፈተናዎች፣ ከአሜሪካ ቪዛ ክፍያ ጋር የተያያዙ ወጪዎችን በሚሸፍነው የOpportunity Program Fund (#OPF) ፕሮግራም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይመረጣሉ።

የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ስኬታማ ዕጩዎች ወደ አሜሪካ የራውንድ ትሪፕ ትኬት ያገኛሉ።

ቀሪዎቹ 5 ተማሪዎች በስልጠና ፕሮግራሙ ላይ #በነጻ ይሳተፋሉ ነገር ግን የዝግጅት ወጪን ከራሳቸው ምንጭ ይሸፍናሉ። የሞባይል ዳታ ወጪዎች ለሁለቱም የፕሮግራም ተሳታፊዎች በኤምባሲው ይሸፈናሉ።

ማመልከቻ እስከ ሚያዚያ 10/2024 (5:00 pm EAT) ማስገባት ይችላል ተብሏል።

ለማመልከት አስፈላጊ መስፈርቶች ምንድናቸው ?

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩና ትምህርታቸውንም እዚሁ ኢትዮጵያ እየተከታተሉ ያሉ።

ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ/ች #ኢትዮጵያዊ ተማሪ፣

በዚህ የትምህርት አመት መጨረሻ 11ኛ ክፍልን ያጠናቅቁ እና ከመስከረም 2024 ጀምሮ 12ኛ ክፍል የሚማሩ፣

በጠቅላላ 4 ሳምንታት የESP መርሃግብር ለመሳተፍ ቃል መግባት የሚችሉ መሆን አለባቸው።

ስታመለክቱ የሚያስፈልጉ ፦
1ኛ. የሁለተኛ ደረጃ ትራንስክሪፕት (9፣ 10፣ 11)
2ኛ. ከትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ
3ኛ. የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸውና ለOpportunity Fund Program (OFP) የሚያመለክቱ ከትምህርት ቤት ወይም ከቀበሌ የቤተሰብን #ዝቅተኛ የኢኮኖሚያ ሁኔታ የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ ያስፈልጋል።

የማመልከቻ ሊንክ እና ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ በዚህ ይመልከቱ ፦ https://sites.google.com/amspaceseth.net/educationusa-esp2024

@tikvahethiopia
🇺🇸 Application for the U.S. Embassy’s Education USA Scholars Program (ESP) 2024 is now open!
Deadline: April 10 - ሚያዝያ 2
ESP is a four-week training program that helps academically strong high school students apply to U.S. colleges and universities, with the goal of producing skilled and well-educated leaders to build tomorrow’s Ethiopia.
Visit this link for more about ESP and to submit your application:
👀ካነበብነው:-

✍️✍️ ጉንዳን✍️✍️

✍️ ጉንዳን የክብደቱ 50 እጥፍ መሸከም እና 30 እጥፍ መጎተት ይችላል::አንድ ጉንዳን 250,000 የአንጎል ህዋሳት አሉት:: ከአካላቸው ክብደት አንፃር ትልቅ አንጎል ያላቸው ፍጥረታት ጉንዳኖች ናቸው::

✍️ ጉንዳኖች በምድር ጥልቀት ውስጥ ያለን ውሀ በማሽተት ለይተው ያውቃሉ:: ንግስቲቱ ጉንዳን እስከ 15 አመት እድሜ ትቆያለች:: ጉንዳኖች ውሀ ውስጥ እንደሰመጡ አየር ሳያገኙ ለሁለት ቀናት መቆየት ይችላሉ::

✍️ጉንዳን ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ እስከሚሞትበት ሰአት ድረስ በፍፁም አያንቀላፋም:: በ 1 የጉንዳን መንጋ ውስጥ ግማሽ ሚሊዮን ጉንዳኖች ሊኖሩ ይችላሉ::

✍️ በምድር ላይ  ያሉ ጉንዳኖች በሙሉ ተሰብስበው ክብደታቸው ቢለካ ከአለም ህዝብ አጠቃላይ ክብደት ይበልጣል::

ምንጭ:-

የካ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በመጠኑ ተሻሽሎ የቀረበ
Our Dear Kids and Parents,

On behalf of Safari Academy, I extend warm wishes to you and your families on the occasion of EID-AL-FITR.

As we mark the end of Ramadan, I extend my heartfelt wishes to you and your families for a blessed and joyous Eid al-Fitr.

May this special occasion be filled with love, peace, and happiness.

Eid Mubarak to all!

Warm regards,
Eyob Ayele
The School President
Forwarded from Safari Academy Grade 2
ይህ ልጅ ካሌብ ይባላል። ዛሬ ጠዋት ሰሚት ኮንዶሚኒየም ከመኖሪያ ቤት ወጥቶ ጠፍቶ ወላጆቹ ፍለጋ ላይ ናቸው።

ልዩ ፍላጎት ስላለው ነገሮችን በቀላሉ ስለማያገናዝብ አደጋ ላይ ነውና ካያችሁት ወይም መረጃ ከደረሳችሁ እባካችሁ ከታች ባሉት ስልክ ቁጥሮች ደውላችሁ በማሳወቅ ተባበሩን።
         0923814703
         0924909305
ውድ ቤተሰቦች:-

ከሰዓታት በፊት አፋልጉን ብለን የጠየቅናችሁ ልጃችን ህፃን ካሌብ ገ/ህይወት የተገኘ መሆኑን ስናሳውቃችሁ በታላቅ ደስታ ነው።

ሁላችሁም ባላችሁበት መረጃው እንዲዳረስ ላደረጋችሁት ታላቅ አስተዋፅኦ ምስጋናችን ከልብ ነው።🙏
2024/09/27 21:29:42
Back to Top
HTML Embed Code: