Telegram Web Link
ሀሙስ #8

ራስን የማወቅና የመምራት ክህሎት

የሚከተሉት ነጥቦች አንድ ራሱን የሚያውቅ ሰው ሊኖሩት የሚገባ ባህሪያትን ያሳዩናል::

*ደካማና ጠንካራ ጎኑን ለይቶ ያውቃል

*ለራሱ ህይወት ኃላፊነት ይወስዳል

*ስለራሱ ያለው አመለካከት አዎንታዊ ነው

*በራሱ ይተማመናል

*ራሱን ለማሻሻል ይጥራል (በኢኮኖሚ በማኅበራዊ…)

*የሚሄድበትን መንገድ ያውቃል/ራዕይ አለው

*ለአላማው መሳካት መስዋትነትን ይከፍላል

*ሌሎችን ለመሆን አይጥርም/በራሱ ማንነት ይተማመናል

*ራሱን ያከብራል

*የራስ ህይወት መሪ ለመሆን ደግሞ የሚከተሉት ሶስት ነጥቦች አጋዥነት ይኖራቸዋል

#ሀ. ለራስ ህይወት ኃላፊነት መውሰድ

*ስለኛነታችን ልናውቃቸው የሚገቡ እውነታዎች

*በዓለም ላይ አንተን የሚመስል ማንም እንደሌለ

*በዓለም ላይ መኖራችን ለአንድ አላማ መሆኑ

*ሃሳባችንን፤ ምኞታችንን፤ አመለካከታችንን መቆጣጠር የሚያስችል ሃይል እንዳለን

*የዛሬ አስተሳሰብ ለነገ ህይወታችን መሰረት እንደሆነ

*የራስን ማንነት ለመፈተሽ የሚረዱ ጥያቄዎች

*ጠንካራ ጎኔ ምንድን ነው?

*ደካማ ጎኔ ምንድን ነው?

*ለራሴ ያለኝ አመለካከት ምን ይመስላል?

*ለህይወት ያለኝ አመለካከት ምን ይመስላል?

#ለ. ዓላማ ያለው ህይወት መምራት

*ልንሰራውና ልንሆን የምንፈልገውን ነገር ለይተን እንድናቅ ይረዳና

*የህይወት አስቸጋሪ ሁኔታዎች በድል የምንወጣበትን ኃይል ይሰጠናል

*ጤናማና ውጤታማ ሰዎች እንድንሆን ይረዳናል

#ዓላማ_ያለው_ህይወት_ለመምራት_ምን_ማድረግ_ይጠበቅብናል?

*ዓላማ ያለው ህይወት ለመምራት ራስን ማዘጋጀት

*እየኖርን ካለነው የተሻለ ህይወት መኖር እንዳለብን ማመን

*በመጀመሪያ በቀላሉ ልንተገብረው የምንችለውን ነገር በማቀድና በመተግበር በዕቅድ መመራት/መሄድ

*ከጎጂ ልምዶችና አስተሳሰቦች ራስን ማውጣት

*ለራሳችን የምንገባውን ቃል ማክበር

*ሽንፈትን በጸጋ አለመቀበል ይልቁንም ካለፈው ስህተታችን በመማር የተሻለ ነገርን ማለም

*በዓላማ መመራት ስንጀምር ሊያጋጥሙን የሚችሉ እንቅፋቶች

*ከራሳችን/ከውስጣችን የሚመነጭ

*በአቅራቢያችን ካሉ ሰዎች የሚነሳ

*የአካባቢያዊ ሁኔታዎች አለመመቸት

(በአንቶኒዮ ሙላቱ)©zepsychologist
@Psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
#ክፍል_9
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)
#SHARE አድርጉት ብዙ ሰው ያስተምራል #Like
#Frustration / #ተስፋ_መቁረጥ_ከየት_ይመጣል ?
___

ብዙ ጊዜ ሰዎች በተለያዩ ሁኔታዎች
ሁነው ተስፋ የለኝም ፣ ተስፋዬ ተሟጧል ፣ የመሳሰሉትን ቃላት በቀን ተቀን ሕይወታቸው ይጠቀማሉ ፡፡

ተስፋ መቁረጥ ወደ ግባችን / ፍላጎቶቻችን እንዳንደርስ የሚያረገን ባህሪ ነው ፡፡ በሕይወቱ ብዙ ጊዜ ተስፋ የሚቆርጥ ሰው ወደግቡ/እቅዱ የመድረሱ እድል በጣም አነስተኛ ነው ፡፡ ወደ ጠቃሚ የሕይወት ግባችን አለመድረስ ደግሞ ድብርት ፣ ጭንቀት ፣ ፍርሃት ፣ የበደለኝነት ስሜት ያመጣብናል ፡፡

ሳይኮሎጂ ችግር የመፍቻ ዋና መንገዱ የችግሩን ምክንያት መረዳት እንደሆነ ያትታል ፡፡ስለሆነም የተስፋ መቁረጥ ዋና ዋና ምክንያቶች እንመለከታለን፡፡
___
1.Environmental Factor
(አካባቢያዊ ምክንያት)

በአካባቢያችን ያሉ የተለያዩ ሁኔታዎችና ገጠመኞች ፍላጎቶቻችንንና እቅዳችንን እንዳናሳካ ይከለክሉናል ፡፡
ለምሳሌ ፦ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ማድረግ የምንፈልገውን ነገሮች " አትችለውም ፣ ይከብድሀል ፣ ከዚህ በፊት አልተሞከረም ፣ ሰው ምን ይልሀል" በማለት ተስፋ ሊያስቆርጡን ይችላሉ ፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ያደግንበት ባህል ፣ የምንኖርበት አካባቢ ለማድረግ ያቀድነውን ነገር እንዳናሳካ በራሱ ሊይዘን ይችላል ፡፡ ይሄ በሕይወታችን ተስፋ መቁረጥን ያስከትላል ፡፡

2.Personal inadequency Factor (ግላዊ ብቃት/ክህሎት ማጠር )

ይህ ደግሞ ፍላጎቶቻችንን እንዳናደርግ የሚገድበን አለመሙላት (ብቃት አልባነት) ነው ፡፡ ለምሳሌ ፦ አንድን እቃ በጣም ወደነው ለመግዛት ስንፈልግ ከተወደደብንና ያለን ገንዘብ አነስተኛ ከሆነ ተስፋ ቆርጠን ላንገዛ እንችላለን ፡፡ እዚህ ጋር ነገሩን ለመግዛት በቂ ገንዘብ አለመኖር የራሳችን የሆነ ጉድለት ይሆናል፡፡ ሌላው አንድን ነገር ለመስራት አስበን የግል ችሎታ / ብቃት/ ክህሎት ሲያንሰን እሱ " በቃ አልችልም " በማለት ተስፋ ለመቁረጥ መንስኤ ይሆነናል ፡፡

3. Conflict of interest ( የፍላጎት ግጭት )
የመጨረሻው የግላዊ ፍላጎቶች/ ግቦች እርስ በእርስ ሲፃረሩ ተስፋ ሊያስቆርጠን ይችላል ፡፡ ተስፋ መቁረጡ የሚመጣዎ ሁለቱንም ግቦቻችንን ልናሳካ ባለመቻላችን ነው ፡፡ አንዱን ግብ ብናሳካ ራሱ ሌላውን ስላላሳካን የመወላወል ተስፋ የመቁረጥ ( የማዘን ) ስሜት ይሰማናል፡፡


ከነዚህ ሶስቱ ዎና ዎና ምክንያቶች እግጅ በጣም ብዙ ሰው የሚያጋጥመው የመጨረሻው (.Conflict of Motives / የፍላጎት ግጭት ) እንደሆነ ሳይኮሎጂ ይጠቁማል፡፡
__
እነዚህ Conflict of motives ( የፍላጎ
ት ግጭት ) ደግሞ በ አራት ይከፈላሉ ፡፡
__
ሀ. Approach - Approach Conflict

(ፍላጎት ፥ ፍላጎት ግጭት)

ይህ ግጭት ሁለት ነገሮችን በእኩል ፈልገን ነገር ግን መምረጥ የምንችለው አንዱን ብቻ ሲሆን ማለት ነው ፡፡ ለምሳሌ :- ተማሪዎች ዩኒቨርስቲ ከገቡ በኅላ Department ሲመርጡ ብዙ ተማሪዎች በሁለት ወይም ከዛ በላይ በሆኑ የdepartment ምርጫዎች ይወጠራሉ ነገር ግን መምረጥ የሚችሉት የወደዱትን ሁሉ ሳይሆን አንዱን ብቻ ስለሚሆን ግጭት ውስጥ ይገባሉ ፡፡ ሌላው ገበያ ሂደን ሁለት ሱሪዎች በጣም ወደናቸው ነገር ግን መግዛት የምንችለው አንዱን ብቻ ከሆነ ይህ አይነት ግጭት ከራሳችን ጋር ይገጥመናል፡፡


ለ. Avoidance - Avoidance Conflict (የማስወገድ ፥ የማስወገድ ግጭት)

ይህ ደግሞ ከሁለት የማንፈልጋቸው ነገሮች የግድ አንዱን መምረጥ ግድ ሲለን ነው ፡፡
ለምሳሌ ፦ ልጃችን በሰዎች ታግቶ ብር ካልከፈላችሁ ይገደላል ቢሉን ፤ እዚህ ጋር ልጁ እንዲሞትም አንፈልግም ለአጋቾቹ ብር መክፈልም አንፈልግም ፡፡ ግን አንዱን መምረጥ ግድ ይለናል ፡፡ ሌላ ምሳሌ ፦

ሐ. Approach - Avoidance Conflict (የፍላጎትና ማስወገድ ግጭት)

ይህ ደግሞ በአንድ ግብ ላይ የፍላጎትም የማስወገድም ስሜት ሲሰማን ነው ፡፡

መ. Multiple Approach - Avoidance Conflict (ብዙ የፍላጎት ማስወገድ ግጭት)

ይህ ሁላችንም በሕይወት ቆይታችን የሚያጋጥመን የለት ተለት ግጭት ነው ፡፡ እያንዳንዱ የሚገጥመን ነገር #ብዙ_አወንታዊና_አሉታዊ ነገሮች ይይዝና እሱን #መምረጥና #አለመምረጥ ችግር ይሆናል ፡፡
ለምሳሌ ፦ አንድ ሰው መልኩን ፣ ገቢውን ወደን ፀባዩ አመለካከቱ ካላማረን ይሆነኛል አይሆነኝም ብለን ከራሳችን እንጋጫለን ፡፡ሌላው አንድን ስራ ስንሰራ በዉስጡ ያሉ የተለያዩ ጥሩና መጥፎ ነገሮች ስገፉን ሲስቡን እንደዚህ አይነት ግጭት ውስጥ እንገባለን ፡፡



፠፠__፠፠

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

በቴሌግራም በዚህ ታገኙኛላችሁ 🚙 www.tg-me.com/Psychoet 👍


ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
ቸር ሰንብቱ!
፠፠__፠፠
ሳምንት ሰው ይበለን!
ሀሙስ #9

የግጭት አፈታት ሳይኮሎጂ

#ላለንበት ችግር አንድ መፍትሄ የሆነ ጽሑፍ ስለሆነ ባላችሁበት Facebook ግሩፕ #Share አርጉት

ግጭት ጥልቅ ውስጣዊ ስሜቶች አደባባይ ላይ ወጥተው እንዲሰጡ ያደርግል፡፡ በዚህ ጊዜ በእውናችን ቀርቶ በህልማችን እንኳን አልመን የማናውቀውን ነገር ራሳችንም ሌሎችም ሲያደርጉ አስተውለን ይሆናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ለመስማት የሚከብድ ወንጀል ፈጸመው ወዳጅ ዘመዶቻቸው ስለእነዚሁ ሰዎች ጠባይ ሲጠየቁ “እሱ እኮ ሰውም ቀና ብሎ አይመለከት፣ ታላቁን አክባሪ፤ አንገት ደፊ ወዘተ ነበር” ሲሉ ይደመጣል፡፡ እንደተባለውም እነዚህ ሰዎች ሰው አክባሪ፣ ካልደረሱባቸው ሰው ላይ የማይደርሱ ይሆናሉ፡፡ መስካሪዎቹ ፊት ለፊት ያዩትን ነው የመሰከሩት፡፡ ነገር ግን እነዚህ መስካሪዎች አይተውት የማያውቁት አጥፊ ስሜት እነዚህ ሰዎች ውስጥ ይኖራል፤ ተመልካች ይቅርና ባለቤቱም ራሱ አያውቀው ይሆናል፤ ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው እንዲሉ፡፡ይህ ማለት ግን በስሜት ተገፋፍተን በፈጸምነው ድርጊት ተጠያቂ አንሆንም ማለትም አይደለም፡፡ ዞሮ ዞሮ ስሜቶቻችንም የገዛ ራሳችን ንብረት እንጂ የማንም አይደሉም፡፡

ግጭት የሚያስከትለውን ውድመት የበዛ የሚሆንበት ዋነኛ ምክንያት ከመፈጠሩ በፊት ለመከላከልም ሆነ ከተፈጠረ በኋላ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ዕውቀት እና ክህሎት እጦት ነው፡፡ በትንሽ በትልቁ ብስጭት የሚሉ ሰዎችን ታውቁ ይሆናል፤ ለምን ቀና ብላችሁ በሙሉ ዓይናችሁ ተመለከታችሁኝ ብለው ችግር የሚፈጥሩ እና ችግር ውስጥ የሚገቡ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በምዕራቡ ዓለም ለእንደዚህ ዓይነት ሰዎች ‹ንዴትን መቆጣጠር› የሚችሉበት የተለየ ስልጠና ቁጭ ብለው እንዲወስዱ ይደረጋል፡፡ ልክ እንደዚሁ ሁሉ ግጭትን መከላከልም ሆነ መፍታት በስልጠና ሊደረጅ የሚችል ችሎታ ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ ግጭትን ለመከላከል እና ለመፍታት የሚረዱ ነጥቦችን እንዳስሳለን፡፡

1. ስናዳምጥ ‹ጥቃትን› አናዳምጥ

ጥቃት እየተፈጸመብን ነው ብለን ከአሰብን አጸፋዊ መልስ ለመስጠት አናቅማማም፡፡ ክፉ ደግ መነጋገር ደግሞ ምክንያታዊ ውይይት ድራሹ እንዲጠፋ ያደርጋል፡፡ በተለይ ግጭት ከተፈጠረ በኋላ ማንኛውም ዓይነት ንግግር ሲደረግ ‹ይህ ሰው በትክክል ምን እያለ ነው?›፣ ‹ምን ዓይነት መረጃ ነው በመተላለፍ ላይ የሚገኘው?›፣ ‹ምንድነው የተከፋበት ምክንያት? ለምን ተቆጣ? ለምን ክፉ ተናገረ?› ወዘተ በማለት በስሜት ታጅበው ከሚፈሱት ቃላት ጀርባ ያለውን መልዕክት ለይቶ ማወቅ ጥሩ ነው፡፡ ይህንን ከአደረግን ራስን ለመከላከል ከፍ ሲልም መልሶ ወደ ጥቃት ወደ መሰንዘሩ ከመኬዱ በፊት መግባባት እንዲነግስ ያደርጋል፡፡

2. ደመ ነፍሳዊ ግፊት አደብ እንዲገዛ ማድረግ

የምንፈልገው እንዳልተሟላ፣ ፍትህ እንደጎደለ፣ ውሸት እንደከበረ፣ መስማት የማንፈልገው ጥያቄ እንደቀረበ ወዘተ ስናስብ እጥፍ ድርቡን መልሳችሁ አከናንቡ የሚል ውስጣዊ ደመ ነፍሳዊ ግፊት ይቀሰቀሳል፡፡ እስከ ዶቃ ማሰሪያው፣ አፍንጫው ድረስ፣ ልክ ልኩን ወዘተ ነገረው ዓይነት ፈሊጣዊ አገላለጾቻችን ‹ክፉ ነገርን ልክ የለሽ በሆነ ክፍት መመከትን› እንደምናበረታታ ፍንጭ የሚሰጡ ናቸው፡፡ አጥቂ ምክንያታዊ ይሁንም አይሁንም፣ ደግ ይሁንም አይሁንም አበጀህ የማለት፣ እንደ ጀግና ከፍ አድርጎ የመመልከት ባህል ሊወገድ ይገባል፡፡

በግጭት ወቅት ‹እንዲህ በል፣ እንዲያ በል፣ የት አባቱ ወዘተ› ዓይነት ውስጣችን የሚፈሉ የደመ ነፍስ ግፊቶችን ማቀዛቀዝ ግጭትን ለመፍታት ይረዳል፡፡ ደመ ነፍሳዊ ምሪትን ከአስቆምን በኋላ ተረጋግቶ በማሰብ መናገር የምንፈልገውን ‹እኔ› በማለት መናገርም እንዲሁ ይመከራል፡፡ ለምሳሌ፣ በቤት ውስጥ የትዳር አጋር ስራ አላግዝ ብሎ አስቸግሮ ከሆነ ‹አንተ ድሮም ሰነፍ ነህ፣ ምንትስ ነህ› ከማለት ይልቅ ‹እኔ ስራ ካላገዝከኝ/ካላገዝሽኝ ቅር ይለኛል፤ ተጋግዘን ልንሰራ ይገባል፤ ይኼ እኮ የጋራ ህይወት ነው› ማለት ግጭት ላይ አርቆ ማጠሪያ ስልት ነው፡፡ ስለዚህ በተቻለ መጠን ውስጣችን አሉታዊ ስሜት ሲጸነስ እንደመጣልን ከመናገር እንቆጠብ፡፡ ‹ከአፍ የወጣ አፋፍ› አይደል ከነአባባሉስ፡፡ ንግግር የፈሰሰ ውሃ ነው፡፡ እንደ ደራሽ ውሃ ፈሶ ያለ የሌለውን ጠራርጎ ከሄደ በኋላ ሁኔታዎችን ወደ ነበሩበት መመለስ ፈታኝ ነው፡፡ ስለሆነም ንግግር ሲያደርጉ ማመዛዘን እንዲሁም ከአንደበታችን የሚወጡ ቃላት ግጭቱ ላይ ሄደው ሲያርፍ የቤንዚን ነው ወይስ የውሃ ሚና የሚጫወቱት የሚለውን ቀድሞ ማሰብ ተገቢ ነው፡፡

3. የሰዎችን በጎ ጎን ማነጋገር

100 % አጥፊ፣ ምንም ነገር የማይገባው፤ ውስጡ እንጥፍጣፊ መልካምነት የሌለው ወዘተ ሰው አይኖርም፡፡ የትኛውም ሰው መልካም ማንነት የማንነቱ አካል ነው፡፡ እርስ በእርስ ስንነጋገር አንዳችን የአንዳችንን ይህንን መልካም ጎን ለማነጋገር ጥረት እናድርግ፡፡ ‹ጅኒ› ገለመሌ የሚል አጓጉል ፍረጃ ውስጥ ሳንገባ መልአኩን ማንነት እናወያየው፡፡የሰው የእምነቱ መነሻ ስረ መሰረት የአንድም ይሁን የብዙ የሰው ልጅ ፍቅር ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ አንድ ድፍን ያለ ‹ነጭ› አለያም ደግሞ ድፍን ያለ ‹ጥቁር› ብቻ ሊሆን አይችልም፡፡ ፈረንጆቹ እንዲህ ዓይነቱን ጠርዘኛ አመለካከት ‹‹either/or thinking›› ይሉታል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ራስንም ሆነ ሌሎችን አውዳሚ ነው፡፡ ከ‹ሰይጣን› ሌላ ሙሉ ለሙሉ ‹ሰይጣን› የሆነ ፍጥረት የለም፡፡

4. ለሰዎች ስሜት ቦታ እንስጥ

ስሜቶቻችን ጠቋሚ ምልክት ናቸው፡፡ ለራሳችንም ሆነ ለሌሎች ስሜት ደንታ ቢስ መሆን ተገቢ አይደለም፡፡ የሰዎችን ስሜት መረዳት የተፈጠረው ግጭቱ መንስኤ ምን እንደሆነ ለማወቅ ይረዳል፡፡ ችግር ችግር ሆኖ የሚዘልቀው መንስኤው እስኪታወቅ ድረስ ነው፡፡ የራስንም ሆነ የሌላውን ስሜት አይቶ እንዳላዩ ማለፍ ግን ግጭትን ይወልዳል፤ ያባብሳልም፡፡ ‹ዶርማንት› የሚባል የእሳተ ገሞራ ዓይነት አለ፡፡ መገለጫው ውሎ አድሮ አንድ ይደርሳል ብለን ሳናስበው የደረስንበት ቀን ላይ መፈንዳት ነው፡፡ ያኔ ታዲያ እዚያ አካባቢ ያለን ምንም ነገር አያደርጋችሁ፡፡ የነበረውን እንዳልነበረ ይሆናል፡፡ ሰሚ ጆሮ ተነፍጎ የከረመ ስሜትም እንዲሁ ቋት ሲሞላ አንድ ቀን ያፈነውን ክዳን አሽቀንጥሮ ሲወጣ ብዙ ሳይሰባብር አይበርድም፡፡ ‹አይመጣምን ትተሸ ይመጣልን አስቢ› ትልቅ ቁም ነገር አዘል መልዕክት ነው፡፡ በእንቁላል ዕድሜ ላይ የሚገኙ ስሜቶችን ስራዬ ብሎ መስማት፣ ቦታ መስጠት እና ፍላጎታቸውን ለማሟላት ከሰማይ በታች ማድረግ የሚቻለውን ነገር ሁሉ ማድረግ ግጭትን በሩቅ ያስቀራል፤ ድንገት ቢቀሰቀስ እንኳን ያለ ብዙ ኪሰራ ይቀዘቅዛል፡፡ ሳይኮሎጂቶች ቅጣትን የማያበረታቱት ለዚህ ነው ለጊዜው ቀጪ ዱላውን ጨብጦ ዙሪያቸው ሲገኝ ልጆች ታዛዥ እንዲሆኑ ያደርጋል እንጂ ዘላቂ የሆነ የጠባይ ለውጥ ግን ጨርሶ አያመጣም፡፡ ስለዚህ በግለሰብም ሆነ በማኅበረሰብ ደረጃ ግጭትን አስቀድሞ ለመከላከልም ሆነ አንድ ጊዜ ከተፈጠረ በኋላ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ ለማረጋጋት ለሰዎች ስሜት ቦታ መስጠት፣ እንደተረዳናቸው ማስረዳት፣ ቁስላቸው እንደተሰማን መግለጽ ይመከራል፡፡
5. መስማት እና መስማማት መካከል ያለውን ልዩነት መገንዘብ

የተጋጨን ሰው ቅሬታውን መስማታችንን ማወቅ አለበት፡፡ የሰው ልጅ አለመግባባት ሲፈጠር ቀዳሚ ፍላጎቱ መሰማት ነው፡፡ መስማማት ቀጥሎ የሚመጣ ሌላ ሂደት ነው፡፡ በቂ ጊዜ ሰጥተን ሰምተናል ማለት በተባለው ሁሉ ተስማምተናል ማለት አይደለም፡፡ በሁሉ ነገርም መስማማት አይቻልም፡፡ መደማመጥ ግን ቁልፍ ሚና ሊጫወት

እና በቀላሉ ልንተገብረው የምንችለው የግጭት መፍቻ መመሪያ ነው፡፡ ከሁሉ በፊት ምንአልባትም ከሁሉ በላይም አቁሳዩ ጥይት አድማጭ ማጣት ነው፡፡ ሰውን ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ማለፍ ክብረ ነክ ድርጊት ነው፤ ንቀት ነው፤ ‹ምን ታመጣላችሁ?›፣ ‹የራሳችሁ ጉዳይ› ወዘተ ማለት ነው፡፡ እነዚህ የአመለካከከት እና ድርጊት መስመሮች በራሳቸው ግጭትን ይቀሰቅሳሉም፤ ያባብሳሉም፡፡ አንድን ሰው እህ ብሎ መስማት፣ ሃሳቡን በሚገባ እንዲገልጽ ዕድል መስጠት፣ እየተባለ ያለውን ፍሬ ነገር በገዛ ራስ ትርጉምና ፍረጃ ሳይጀቡኑ ለመረዳት ጥረት ማድረግ፣ ሳይኮሎጂስቶች ‹‹already listening›› የሚሉት አለ (የሚመልሱትን መልስ እያውጠነጠኑ መስማት ማለት ነው)፣ እንደዚህ ካለው የማይበጅ የህሊና ድምጽን ዝም አሰኝቶ የሌላውን ህሊና የቅሬታ ድምጽ መስማት ግጭትን ይቀንሳል፤ ይፈታልም፡፡ ተደማመጥን ማለት ተስማማን ማለት አይደለም፤ ሰሚ ጆሮ መስጠት መሸነፍ አይደለም፡፡ መደማመጥ እስካለ ድረስ በአልተስማሙበት ጉዳይ ላይም በልዩነት መስማማት ይቻላል፤ ‹ላለመስማማት መስማማት› እንዲሉ፡፡

6. ስናዳምጥ አስሬ ጣልቃ እየገባን አስተያየት አንስጥ

ይኼም እንዲሁ ለንግግር አድራጊው ያለንን ዝቅተኛ ክብር አስረጂ ነው፡፡ የሚከባበሩ ሰዎች ግጭት ውስጥ የሚገቡበት ዕድል አነስተኛ ነው፡፡ አይበለውና ግጭት ቢነሳ እንኳን በሰለጠነ መንገድ መፍታት አስቸጋሪ አይሆንም፡፡ አንድ ከዚህ በፊት በሌላ አንድ ጽሑፌ ላይ ያነሳሁት ገጠመኝ አለኝ፡፡ እዚህ ጋርም ቢነሳ አስተማሪነቱ የጎላ ሊሆን ስለሚችል ደግሜ ላንሳው፡፡ በነጋ በጠባ አንድንዴ አገር ጉድ እስኪል ድረስ የሚጣሉ ጥንዶች ቤት በአንድ አጋጣሚ ተገኘሁና አንድ ርዕሰ ጉዳይ ተነስቶ ሃሳብ መቀያየር ጀመርን፤ ይመስለኛል ክርክር ቢጤም ነው፡፡ ሚስት ሃሳቧን ሳትጨርስ ባል ደጋግሞ ያቋርጣል፡፡ ሚስት ታዲያ መሃል ላይ ወደ እኔ አንገቷን አዙራ በቅሬታ ድምጽ ‹ተመልከተው አያዳምጠኝም እኮ› አለችኝ፡፡ ቅሬታዋ ‹ለምን በእኔ ሃሳብ አልተስማማም› አይደለም፡፡ ቅሬታዋ ‹ለምን ስናገር አታዳምጠኝም› ነው፡፡ ስንወያይ ሃሳብ የማስጨረስ ልምድ ይኑረን፡፡ ማንም ‹ዓመት› አያወራም፡፡ የቤተሰብ ውይይት ይባልናም በመመገቢያ ጠረጴዛ ዙሪያ ተሰባስበን የወላጅን የትዕዛዝ ዝርዝር የመስማት ትዕግስት እንዲኖረን እንጂ የራሳችንን ሃሳብ እንድንገልጽ አንበረታታም፡፡ አምባገነኖችን በዚህ መልኩ ነው በየቤቱ የምንፈጥራቸው፡፡ ሳይደመጥ ያደገ ልጅ ነገ አድማጭ መሪ የሚሆንበት ዕድል ጠባብ ነው፡፡ በተቋማት ውስጥም ተመሳሳይ ችግር አለ፡፡ ውይይት ማለት በአንድ አቅጣጫ ብቻ ከአሰሪ ወደ ሰራተኛ የሚዥጎደጎድ ምክር ይመስለናል፡፡ ሃሳብን ማስጨረስ ይልቁንም ‹እንዲህ ለማለት ፈልገህ ነው ወይ?› የሚል ጥያቄ በንግግር መጨረሻ በመጠየቅ በትክክል የተባለውን ለመረዳት መጣር፣ ስንነጋገር ከተናጋሪ ጋር ቀጥታ የዓይን ግንኙነት ማድረግ፣ በየመሃሉ ‹አሃ› ማለት ወዘተ ተናጋሪ እየተደመጠ እንደሆነ ስለሚያስገነዝበው መከባበር የሰፈነበት አየር እንዲኖር ያደርጋል፤ መከባበር ወደ መስማማት የማይወስድበትም ምንም ምክንያት የለም፡፡

7. ግምታችንን ገልጸን ግምታችን ስህተት ከሆነ ለመታረም ፈቃደኛ መሆን

‹ግምቶች ብዙ ጊዜ ከእውነታ የራቁ ናቸው› ይላል አንድ ወዳጄ፡፡ ለእውነት የቆመ ሰው ‹ከአፈርኩ አይመልሰኝ› ከሚል ድርቅና የጸዳ ነው፡፡ ‹በዚህ ሰዓት ነበር አይደል ቤት የገባኸው?› ብለን ‹አይደለም፤ በዚህ ሰዓት ነው› የሚል የተለየ መልስ ከተሰጠን፣ ማረጋገጥም ከቻልን ሃሳባችንን እንቀይር፡፡ አንድ ጊዜ የተናገሩትን ላለመሻር በስህተት ላይ ስህተትን እየከመሩ የመሄድ አዚማችን ራስን እያረሙ፣ ወደ እውነት እየተቃረቡ፣ ከእውነት ጋር በእውነት እየተመሩ ከመኖር ይልቅ ሚዛን ይደፋል፡፡ በታሪክም በአመክንዮም ስህተት ስህተትን አርሞ አያውቅም፡፡ ከሰው ስህተት ከብረት ዝገት አይጠፋም፡፡ መሳሳትን ማመን የመንፈስ ከፍታ ነው፡፡ ራስን ማረም ትልቅነት ነው፡፡ ‹ይቅርታ አድርጉልኝ› ማለት ህይወት ውድድር ነው ብለን ብናምን እንኳን በልጦ መገኘት ነው፡፡ እንደ ግለሰብ ለመታረም ፈቃደኛ ያለመሆን ድርቅና ያጠቃናል፡፡ ይኼንን የስነ ልቡናችንን ጎን አፍርሶ መስራት ጠቃሚ ነው፡፡ በአንድ ወቅት አንድ አባ ወራ ከሚስቱ ጋር ተጋጭቶ ለማስማማት ጥረት በምናደርግበት ወቅት ‹እኔ ምንም ስህተት የለብኝም፤ 100 % ልክ ነኝ› የሚል መልስ ይሰጠናል፡፡ የሰው ልጅ በዚህ ደረጃ ልክ ሆኖ አያውቅም፤ ወደፊትም የሚሆን አይመስለኝም፡፡ የዚህ አባ ወራ ምላሽ ‹ስህተትን ማመን ሞት ነው› የሚል የጸና እምነት እንዳለን፣ ድርቅናችን ጥጉ የት ድረስ እንደሆነ የሚጠቁም ነው፡፡

8. ውስብስብ ነባራዊ ሁኔታዎችን ለመረዳት እንትጋ

አለማወቅ የብዙ ችግር ምንጭ ነው፡፡ ማወቅ ትዕግስትን፣ ጥረትን፣ ተነሳሽትን ወዘተ ይጠይቃል፡፡ ድምዳሜ ላይ ከመድረሳችን በፊት የግጭቱን ቀስቃሽ መንስኤዎች ለመረዳት መጓጓት ግጭትን በመፍታት ሂደት ውስጥ ገንቢ ሚና ይጫወታል፡፡

9. ‹ገንቢ ውይይት ማድረግ ይቻላል› የሚል እምነት ይኑረን

የአትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ የ‹ይቻላል› መርህ በግጭት አፈታት ውስጥም ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡ አስቀድሞ ‹መግባባት አይቻልም› የሚል እምነት ውስጣችንን ከሞላው ለመግባባት ምንም ጥረት አናደርግም፡፡ ጥረት ብናደርግ እንኳን ለይስሙላ ይሆናል፡፡ የተዘጋ የአይቻልም አስተሳሰብ ወደ መቻል የሚወስዱንን መንገዶች ለመስራት መፈንቀል ያለብንን ድንጋይ በሙሉ እንዳንፈነቅል ጋሬጣ ይሆንብናል፡፡ ከአንጀት ካለቀሱ እንባ መቼም ቢሆን አይገድም፡፡

10. ግጭቱ እንዲባባስ እያደረግን ከሆነ ከድርጊታችን እንቆጠብ

ባልና ሚስት ፍቅራቸው ሳይጠፋ አንድ ጣሪያ ስር አብረው የሚኖሩት አንዱ እሳት ሲሆን ሌላኛው አፈር ከሆነ ብቻ ነው ፡፡ እሳትን በእሳት ማጥፋት ፈጽሞ አይቻልም፡፡

11. ጥፋቱ የማን እንደሆነ ሳይሆን መንስኤው ምን እንደሆነ ለማወቅ መሞከር

ጣት መጠቆም የረባ ለውጥ አያመጣም፡፡ ኮሽ ሲል ተወንጃይ ፍላጋ መሯሯጥ ዘላቂ ለውጥ አያመጣም፡፡ ማውገዝ ረጅም መንገድ አያስኬድም፡፡ መወነጃጀል ግጭትን መፍታት የማይችል ቀሽም ስትራቴጂ ነው፡፡ ግጭት ሲቀሰቀስ ጥፋተኛውን ሳይሆን መንስኤውን ለማወቅ መጣር ግጭቱ ዳግም እንዳይፈጠርም ሆነ አንድ ጊዜ ከተፈጠረ በኋላም እንዲበርድ ለማድረግ ያግዛል፡፡ እውነቱን ለመናገር በየትኛውም ዓይነት ግጭት ውስጥ ሁሉም ወገን የሚጫወተው ሚና ይኖራል፡፡ ስለዚህ ‹ይኼ ግጭት እንዲቀሰቀስ እንዲሁም እንዲባባስ ምን ዓይነት ሚና ተጫውቻለሁ?› ብሎ ራስን መጠየቅ እና የራስን ቤት ከሁሉ በፊት መፈተሽ ግጭትን ይከላከላል፤ ያበርዳልም፡፡
12. ስምምነትን ግልጽ ማድረግ

በግልጽ ያልተቀመጡ ስምምነቶች ዛሬም ሆነ ነገ ግጭት እንዲፈጠር በር መክፈታቸው አይቀርም፡፡ ፍላጎትን በቀጥታ በመናገር ሁሉም አሸናፊ የሚሆንበትን አማራጭ ተግባራዊ የሚያደርግ፣ ዳግመኛ ለጥል መጋበዝ እንዳይመጣ የሚያደርግ ግልጽ ስምምነት ላይ መድረስ ብልህነት ነው፡፡ በግለሰቦች ሌላው ቀርቶ በባለ ትዳሮች መካከል እንኳን በተደጋጋሚ ቅራኔ የሚፈጥሩ ጉዳዮች ካሉ በሚገባ ከተነጋገሩ በኋላ የመፍትሄ ስምምነቱን በወረቀት ጭምር አስፍሮ ማስቀመጥ ወደፊት ግጭት ሊፈጠር የሚችልበትን ዕድል ይቀንሳል፡፡ ሰው ሊረሳ፣ ቃሉን ሊያጥፍ፣ ፍላጎቱ ሊለወጥ ወዘተ ይችላል፡፡

13. ግጭት ወደፊትም ሊፈጠር እንደሚችል ማሰብ እና አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ

@psychoet
ዝም ማለትን ብንለምድ!

“ለሰው ልጅ አንደበቱን ከፍቶ መናገርን ለመማር ሁለት አመት ብቻ ነው የሚፈጅበት፣ ይህንን አንደበቱን መዝጋትን ለመማር ግን ከ60 አመታት በላይ ይፈጅበታል” – Ernest Hemingway

1. በተናደድን ጊዜ በረድ እስከምንል ድረስ ዝም ማለትን ብንለምድ፣

2. የአንድን ሁኔታ ሙሉ ታሪክ በማናውቅበት ጊዜ በግምት ከመናገር ይልቅ ዝም ማለትን ብንለምድ፣

3. መናገር የፈለግነውን ነገር ብንናገረው የተፈጠረውን ሁኔታ ለመለወጥ ምንም መዋጮ እንደማይኖረው ሲገባን ዝም ማለትን ብንለምድ፣

4. ስሜታዊነታችን ከምክንያታዊነታችን በልጦ ሲገኝ ዝም ማለትን ብንለምድ፣

5. በተናገርነው ቁጥር የተናገርነውን ነገር በመጠቀም ሁኔታውን የሚያባብስ ሰው ሲያጋጥመን ዝም ማለትን ብንለምድ፣

6. አንዴ የተነገረ ነገር የት ሊደርስ እንደሚች ስለማናውቅ በሰዎቹ ፊት የማናወራውን ነገር ሰዎቹ የሌሉበትን እየጠበቅን ከማውራት ይልቅ ዝም ማለትን ብንለምድ፣

7. በማያገባንና ባልገባን የሰው ነገር ላይ ዝም ማለትን ብንለምድ፣

አብዛኛው ችግራችን ይቀረፍ ይሆን?

©Dr eyob
#ክፍል_10
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ) #SHARE
#LOVE_Styles / #የፍቅር_አይነቶች
___
ዛሬ የሳይኮሎጂ 10 ኛ ትምህር
ታችንን ወጣ ባለ ርዕስ ላይ ነገር ግን ለሁላችን አስፈላጊና ወሳኝ ስለሆነው ስለ ፍቅር እንወያያለን ፡፡

ፍቅር በተለያዩ ሙያዎች አንፃር በተለያየ መንገድ ተተርጉሟል ፡፡ Social psychology (በማህበራዊ ሳይኮሎጂ ) አንዱን ትኩረቱን በዚህ ላይ በማረግ የተለያዩ የፍቅር ትርጉም ፣ አይነት ... ላይ ያተኮሩ ጥናቶችን ያበረክታል ፡፡

በአጠቃላይ ስናየው ወንዶች ከሴቶች ይልቅ ቶሎ በፍቅር ይወድቃሉ ሴቶች ደግሞ ተግባራዊ ጓደኛነትን መሰረት ባደረገ ፍቅር ይሳባሉ ፡፡ ፍቅር በብዙ መንገድ ተተርጉሟል ። ከነዚህ በጥቂቱ

*ለሰው ከዝምድና / ከቅርበት የተነሳ ያለን ጥልቅ ስሜት
*ከፆታዊ ፍላጎት ምክንያት ያለ መሳሳብ ወዘተ ......
___
ይህ ብዙ ትርጓሜ ያሉት ፍቅር
ስድስት አይነት የፍቅር አይነቶች /ዘይቤዎች / እንዳሉት ማህበራዊ ሳይኮሎጂስቶች ይናገራሉ ፡፡ እነዚህም

1.Eros-ኤሮስ ፦ለኛ ልዩ ውበት ያለውን ሰው በማየት የሚፈቀርበት ዘይቤ ነው ።

በዚህ ዘይቤ ወንዶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው፡፡ ገና እንዳዩ የሚሰማ ጥልቅ የፍቅር ስሜት ነው ፡፡

2.Storge-ስቶርጄ :- ይህ ደግሞ ከጓደኛነት የተነሳ የሚፈቀርበት ዘይቤ ነው ፡፡
በዚህ ዘይቤ ሴቶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው፡፡ ይህ ፍቅር የሚመነጨው በመለማመድ ፣ በመቀራረብ ፣ አብሮ ጊዜ በማሳለፍ ነው ፡፡

3. Ludus-ሉደስ ፦ ፍቅርን በጨዋታ መልክ የሚገለፅበት ዘይቤ ነው ፡፡

በዚህ #ዘይቤ ወንዶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው፡፡ ይህ ፍቅር በብዛት በማማለል የሚፈጠር ሲሆን ስራዬ ተብሎ ያልተያዘ ፍቅር ነው ፡፡


4. Mania-ማኒያ ፦ እጅጉን በኔነት ስሜት የሚያፈቅሩና ፍቅራቸውን በብዙ መከራ ራሱ የማይጥሉበት የተወሰነ ጊዜ የተቆጠረበት የፍቅር ግንኙነት ነው ፡፡
በዚህ ዘይቤ #ሴቶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው።


5. Pragma- ፕራግማ ፦ ይሄ ደግሞ በምክንያት የተደገፈ ፍቅር ሲሆን በባሕሪ ፣ ባስተሳሰብ የሚመስለንን ሰው የምናፈቅርበት ዘይቤ ነው ፡፡

በዚህ ዘይቤ #ሴቶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው።

6. Agape- አጋፔ፦ይህ የፍቅር አይነት ያለአንዳች ምክንያት የምናፈቅረውን ሰው ከራሳችን በላይ የምናስቀምጥበት ነው ፡፡
ይህ የፍቅር ብዙ ጊዜ ከእምነት ጋር ይያያዛል ፡፡ እንደዚህ የሚያፈቅሩ ሰዋች ፍቅረኛዬ ከሚጎዳ እኔ ልጎዳ ፣ ከሚቸገር እኔ ልቸገር የሚሉ ናቸው ፡፡

#የሳምንት_ሰው_ይበለን !

__

ቴሌግራም ሊንክ 🚙 www.tg-me.com/Psychoet 👍

፠፠__፠፠

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

በቴሌግራም በዚህ ታገኙኛላችሁ 🚙 www.tg-me.com/Psychoet 👍

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
ቸር ሰንብቱ!
፠፠__፠፠
ማንን እንደምናፈቅር የምናውቅበት መለኪያ ፡፡ ባሉት ክፍት ቦታዎች የሚሆነውን ስም ብቻ ጻፉና ብዙ ስሙን የጻፋችሁትን ሰው ❤️ አለ ማለት ነው ፡፡
እስኪ መልሱልኝ ወዳጆቼ?
🚫
ከጥቂት አመት በፊት በካንሰር ምክኒያት ያረፈች ጓደኛዬ ከመሞቷ በፊት የጻፈችልኝ ነበር።

መኖራችን ለሌሎች ድጋፍ ምክኒያት ሲኾን ደስ ይላል። በቅርብ ከክፍያ ነጻ በአካል የማማከር ጊዜ ስለማመቻች ምክር የምትፈልጉ ወዳጆቼ ወደፊት በማስቀምጠው አድራሻ የምታገኙኝ ይኾናል። ሕይወትን በጋራ በሳቅና በለቅሶ እንታገላለን። ❤️

እወዳችኋለሁ።
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
#ክፍል_11   #SHARE
#በቤተሰብ አባል ውስጥ የሥነ-ልቦና መታወክ ሲያጋጥም ምን እናድርግ?

የስነ-ልቦና ወይም የስነ-ባህሪ መታወክ በሀገራችን ትኩረት ካልተሰጠባቸውና የህክምና ዘዴው (psychotherapy) ካልተስፋፋባቸው ማኅበራዊ ችግሮች ውስጥ ዋንኞቹ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በባህላዊና በሃይማኖታዊ ድጋፎች ማኅበረሰባችን ከዚህ ችግር ጋር እየተጋፈጠ ቢሆንም፣ ዋናው ጫና የዚህ ችግር ተጠቂ ከሆኑ የቤተሰብ አባላት ላይ ነው፤ምክኒያቱም እንደሰለጠነው ዓለም የህክምና ፤ ድጋፍና እንክብካቤ ሰጪ  ቦታዎች ስለሌሉን ነው፡፡ ይህን ችግር ለማቃለል እየተንቀሳቀሱ ካሉት አገር በቀል ድርጅቶች ውስጥ አንዱ መቄዶኒያ ሲሆን በዚህ አጋጣሚ ስለሚሰሩት ስራ ያለኝን አድናቆት ሳልጠቅስ አላልፍም፡፡እናንተም የተቻላችሁን ድጋፍ አድርጉላቸው፡፡

ከዚህ በመቀጠል የስነ-ልቡና መታወክ ችግር ያጋጠማቸው የቤተሰብ አባላት ይህን ተግዳሮት ለመቋቋም ምን ማድረግ አለባቸው የሚለውን በዶ/ር ቤሪ ያኮብስ መጽሐፍ መነሻነት ይጠቅማሉ ያልኳቸውን ነጥቦች አነሳለሁ፡፡ መልካም የንባብ ጊዜ!
___
#ለበሽታው_ያለንን_ግንዛቤ_ማሳደግ ፡-

ስለታመመብን ሰው የስነ-ልቡና መታወክ አይነት፣ መንስኤ፣ ምልክቶች፣ ስለሚያባብሱ ሁኔታዎችና ነገሮች እራስን ማስተማር፡፡ ስለታመመው ሰው የስነ-ልቡና ወይም የስነ-ባህሪ ችግር የተሳሳተ መረጃ ካለን ወይም ስለ ምልክቶቹና ስለሚያባብሱ ጉዳዮች ዝቅተኛ ግንዛቤ ካለን ግለሰቡንና ቤተሰቡን በአጠቃላይ ሊጎዳ የሚችል ተግባር ልንፈጽም እንችላለን፡፡

#ለምሳሌ እስኪዞፍሬኒያ (Schizophrenia) ያለባቸው ግለሰቦች ስለሚታያቸው አስፈሪ ግን በገሃዱ አለም የለለ ምስል (hallucination) ምንም ግንዛቤ ከሌለን፤ በተገቢው ተጠቂዎችን ላንረዳቸውና አግባብነት ያለው ምላሽ ላንሰጥ እንችላለን፡፡

#በለሌላ ምሳሌ በከፍተኛ ድባቴ (Depression) ውስጥ ያሉ ግለሰቦች አጥብቀው እራስን ስለማጥፋት (suicidal ideation) ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ ይህ ሃሳብ በዝርዝር እራሳቸውን እንዴት፣በምን፣የትና እራሳቸውን እነደሚያጠፉና የመሳሰሉትን በዝርዝር ማሰላሰልና ሙከራ ማድረግን ሊያካትት ይችላል፡፡ ስለዚህ እድብታ ወደ እንደዚህ አይነቱ የስነ-ልቡናና የስነ-ባህሪ ዝንባሌ ሊወስድ እንደሚችል በቂ እውቀት ከሌለን፤ በዚህ የሚሰቃይ ቤተሰባችን፣ጓደኛችን፣ፍቅረኛችንን እንዲሁም የስራ ባልደረባችንን በተገቢው መንገድ መርዳት አንችልም፡፡ አንዳንዴም ለምን ስለማይጠቅም ነገር ታስባለህ እና የመሳሰሉትን ትችቶች በመስጠት ግለሰቡን እንኮንናለን፡፡ ስለሆነም በግለሰቡ ላይ የምናያቸው እንግዳ ባህሪያትና አስተሳሰቦች ከግለሰቡ ቁጥጥር ውጭ ስለመሆናቸው መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ስለዚህ ስለ ግለሰቡ የስነ-ልቡና ችግር ያለን ግንዛቤ ለግለሰቡ ለምንሰተጠው እርደታ፣ግለሰቡን የምንረዳበትን እይታ፣እንዲሁም ለራሳችን ደህንነት ወሳኝ ሚና ይጫወታል ምክኒያቱም የቤተሰብ አካል ጓደኛ ወይም ፍቀረኛ የስነ-ልቡና ችግር ሲያጋጥም የኛ ደህንነት ላይም ተጽዕኖ ስለሚያደርስ፡፡

➋ትክክለኛ የመረጃ ምንጮችን ማፈላለግ፡-

ስለ ግለሰቡ የስነ ልቡና ችግር ሳይንሳዊ ግንዛቤ ለመጨበት ትክክለኛ ምንጮችን መከተል ይገባናል፡፡ ምንም እንኳን በሀገራችን ቋንቋንዎች የተጻፉ ሳይንሳዊ መሰረት ያላቸው መጽሀፍት ባይኖሩም፣ የእንግሊዚኛ ችሎታ ካለን በእንግሊዚኛ የተጻፉ ሳይንሳዊ መጽኃፍትን ወይም ታእማኝነት ያለቸውን ድህረ-ገጾች መጠቀም፡፡ እንዲህ ስል በእንግሊዚኛ ስለተጻፈ ብቻ ጠቃሚ ነው ማለቴ ሳይሆን እነደ ዕድል ሆኖ ሳይንሱ በምዕራቡ አለም ስለተስፋፋ ብዙ ሳይነሳዊ የሆኑ መጽሀፍት በእንግሊዚኛ ቋንቋ ስለተጻፉ ነው፡፡ ስለዚህ የሀገራችን ሳይኮሎጂስቶችና ሳይካቲሪስቶች ብዙ የቤት ስራ አለብን፡፡ ምርምር ከመመረቂያ ጽሁፍ በላይ መሆን አለበት፡፡ (እዚህ ጋር ላቋርጣችሁና… የኛ አላማ ይህን ክፍት መሙላት  የሚችል በስነ-ልቡና ችግሮችን፣ ትዳርን፣ ፍቅር፣ የልጅ አስተዳደግን፣ ትምህርት ነክና ለሌች የስነ-ልቡና ጉዳዮችን የሚዳስስ ሳይንሳዊ መሰረት ያለቸውን መረጃዎች ለናንተና በውጭ ሀገር ላሉ አዳማጭ ላጡ ወገኖቻችን አማራጭ ማቅረብ ነው፡፡ ስለዚህ ለወደፊት ስለተለያዩ የስነ-ልቡና ችግሮች መንስኤ፣ምልክት፣የመጀመሪያ እርዳታ እንዲሁም ዕርዳታ እንዴት ማግኘት እነደምትችሉ የተደራጀ መረጃ በዌብሳይታችን እናቀርባልን)፡፡ወደ ወናው ሃሳብ ስመለስ ስለስነ-ልቡና ችግሮችና መፍትሄዎች የተነገሩ ወይም የተጻፉ ነገሮች ሁሉ ትክክል ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ በጋዜጦችና መጽሄቶች የሚነገሩ ነገሮችን በባለሙያተኞች የሚነገሩ ከሆኑ እንደ ግብአት መውሰድ ይቻላል፡፡ በጥቅሉ ሳይንሳዊ ዳራ ያለቸውን ታማኝ ምንጮችን ተጠቀሙ ምክሬ ነው፡፡

➌የእርዳታ ምንጮችን መፈለግ፡-

የስነ-ልቡና ችግርን በሀገራችን ካሉ ሌሎች በሽታዎች ለየት የሚያደርገው የበሽታው ተጠቂዎች ላይ የሚደርሰው አድሎና መገለል አንዱ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ምክኒያት ከማህበረሰቡ ከሚገኙ ድጋፍ ይልቅ አድሎው የሚያመዝንበት ሁኔታ አለ ምንም እንኳ የተለያዩ የሀይማኖት ተቃማት የራሳቸውን ድጋፍና እንክብካቤ ለተጠቂዎች የሚያደርጉ ቢኖሩም፡፡ በዚህም ምክኒያት የስነ-ልቡና ችግር ያለባቸው ሰዎች ስለ በሽታቸው ከሌሎች ግለሰቦች የመወያየትና ድጋፍ የማግኘት እድላቸው ዝቅተኛ ነው፡፡ እናም የስነ-ልቡና ችግር ያለባቸው ግለሶቦች ቤተሰቦች ተመሳሳይ ችግር ያለባቸው ሌሎች ቤተሰቦች ጋር መወያየትና ሀሳብ መለዋወጥ ልምድ ከማካፈል በዘለለ ስለሚደርስባቸው ተግዳሮቶች ማውራታቸው የተወሰነም ቢሆን ስለጉዳዩ የሚሰማቸው ጭንቀት ቅልል ሊልላቸው ይችላል፡፡ ይህ እንግዲህ ፈረንጆቹ support group የሚሉት አይነት ነገር ነው፡፡ እዚህ ጋር ማንኛቸውም ሊጠቅሙ የሚችሉ ባህላዊና፣ ሀይማኖታዊ፣መንግስታዊ እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ ከስነ-ልቡና ችግር ጋር በተገኘ እርዳታ የሚሰጡ ተቋማትን ማፈላለግ፡፡

__
(በአሸናፊ ካሳሁን)
🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀
🎊🎉🎀🎊🎉🎀

ቴሌግራም ሊንክ 🚙 www.tg-me.com/Psychoet

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
#የሳምንት_ሰው_ይበለን !

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም በመንግሥት ከተመደቡለት ተማሪዎች በተጨማሪ ባሉት ክፍት ቦታዎች በተወሰኑ የትምህርት መስኮች #የግል_አመልካቾችን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

አመልካቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፦

1. በ2015 አና 2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ የሚያሟሉ፣

2. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና (UAT) በመውሰድ የሚቀመጥን መቁረጫ ነጥብ የሚያሟሉ፣

3. በ2015 ዓ.ም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተምራችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ፣

4. ዩኒቨርሲቲዉ በ12ኛ ብሔራዊ ፈተና ውጤት መሠረት ድልደላ ሲያካሒድ አመልካቾች በመረጡት የትምህርት ፕሮግራም አማራጮች ውስጥ ለመደልደል ውጤታቸው ካላበቃቸው ዩኒቨርሲቲው ወደፊት በሚያደርገው ድልደላ ከሌሎች ተማሪዎች ጋር ተወዳድረው ለመደልደል ፈቃደኛ የሆኑ፣

5. ለጤና የትምህርት ዘርፎች ዩኒቨርሲቲው የሚጠይቀውን ተጨማሪ ምዘና ማለፍ የሚችሉ፡፡

የማመልከቻ ቀናት፦ ከህዳር 20 እስከ 26/2016 ዓ.ም

የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ፦ ህዳር 28 እና 29/2016 ዓ.ም

የቅድመ-ምረቃ የትምህርት መስኮችን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፦
http://www.aau.edu.et/blog/admission-of-self-sponsored-students-in-the-regular-undergraduate-program-for-the-2023_24-academic-year/

ለተጨማሪ መረጃ፦
http://aau.edu.et or https://portal.aau.edu.et
ሀሙስ #10

የቤት በርዎን መቆለፍና አለመቆለፍዎን ከልክ በላይ ያረጋግጣሉ?

Obsessive compulsive disorder (OCD) ከ anxiety(ጭንቀት) የስነ-ባህሪ መዛባት ክፍል የሚመደብ ሲሆን፤ ከቁጥጥር ውጭ ተደጋግሞ በሚከሰት አስጨናቂ ሀሳብና፤ ይህ ምክኒያታዊ ያልሆነ ሀሳብ የሚፈጥረውን ስጋት ለመከላከል በሚደረግ ድርጊት፣ባህሪ ወይም የአእምሮ ምላሽ ይታወቃል፡፡

ለምሳሌ ከብዙ በትንሹ፤ የዚህ አይነት ዝንባሌ ያለባቸው ግለሰቦች ከልክ በላይ በበሽታ እለከፋለው ብሎ በመስጋት በተደጋጋሚ እጅን መታተጠብ፡፡ በቀን ከ60ና ከዛ በላይ እጃቸውን በሳሙና ሊታጠቡ ይችላሉ፡፡ እዚህ ጋር ንጽኅናቸውን የሚጠብቁ ሰዎች ሁሉ በዚህ መዛባት ውስጥ ይመደባሉ ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን ፍርሀት ወለድ የሆነ ከልክ በላይ የሆነውን ነው፡፡ ከዚህ አይነቱ የስነ-ባህሪ መዛባት ጋር ተዛማጅነት ያለው የስብዕና መዛባት አይነትም አለ፡፡ በጥቅሉ አብዛኞቻቸን መጠኑ አይብዛ እንጅ የዚህ አይነት ባህሪ ሊኖረን ይችላል፡፡ ለምሳሌ የቤት በራችንን መቆለፍና አለመቆለፋችንን በተደጋጋሚ ማረጋገጥ እና የመሳሰሉት ሊሆን ይችላል፡፡

እንዲህ አይነቱ ባህሪ የእለት ተለት ህይዎታችን ላይ ጣልቃ የሚገባ ከሆነ መፍትሄ መፈለግ ይበጃል፡፡ መጠኑ የበዛ ሲሆንና ኑሯችንን በአግባቡ መምራት እንዳንችል ጣልቃ ሲገባ የተላያዩ የህክምና ዘዴዎች አሉት፡፡ በተለይ ሳይኮቴራፒ ይመከራል፡፡ እንደዚህ አይነቱን የባህሪ መዛባት ለመቀልበስ በሳይኮቴራፒ ከሚመከሩ ተግባሮች ውስጥ አንዱና ዋነኛው፤ ከቁጥጥር ውጭ የሆነው አስጨናቂ ሀሳብ በሚመጣ ወቅት፤ ሀሳቡን ከመሸሽ ይልቅ መጋፈጥና ምንም አይነት ምላሽ አለመስጠት መፍትሄ ነው፡፡

ለምሳሌ ፦ ከምግብ በኋላና በፊት ልክ እንደማንኛውም ሰው ከታጠብን እንዲሁም ምንም ለጤና አስጊ ነገር በእጃችን እስካልነካን ድረስ፤ በበሽታ እለከፋለሁ የሚለው ከቁጥጥር ውጭ የሆነው ሀሳብ ሲመጣ፤ በፍጹም አለመታጠብ ማለት ነው፡፡የቤት በራችንንም አንዴ ከቆለፍን እንደዛው ደጋግመን አለማረጋገጥ ማለት ነው፡፡

ጥናቶች እነደሚያሳዩት ይህ በሚሆን ጊዜ ከቁጥጥር ውጭ በሆነው በአስጨናቂው ሀሳብና በምንሰጠው ምላሽ መካከል ያለውን ቁርኝት ይቀንሰዋል ወይም ያላላዋል፡፡ በተጨማሪም ሀሳቡን መጋፈጣችን (exposure) ለሀሳቡ ያለንን ፍራቻ ይቀንሰዋል፡፡ የፍርሃት መጠኑ በሚቀንስበት ጊዜ ሀሳቡ በአምሯችን ላይ ያለው ሀይል ይቀንሳል፡፡ በዚህም ምክኒያት በሀሳቡ ላይ ያለን ትኩረትም በዛው ልክ ይቀንሳል፡፡ አንድ ሀሳብ ለሌላ ሀሳብ መሰረት ሲሆን ፤ የዚህ ቅጥልጥሎሽ አጠቃላይ ስሜታችንን ይወስናል፡፡

©zepsychologist
አሸናፊ ካሳሁን

@Psychoet
#ክፍል_12
(በአሸናፊ ካሳሁንና ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ ) #SHARE
#በቤተሰብ አባል ውስጥ የሥነ-ልቦና መታወክ ሲያጋጥም ምን እናድርግ?

........ከቅዳሜው የቀጠለ
የስነ-ልቡና መታወክ ችግር ያጋጠማቸው የቤተሰብ አባላት ይህን ተግዳሮት ለመቋቋም ምን ማድረግ አለባቸው ፦
___________
➍ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ ተስፋ መሰነቅ
፡-

የስነ-ልቡና ችግር ላለበት ግለሰብ ካለን ፍቀር አንጻር ግለሰቡ በአጭር ጊዜ ውስጥ መልካም ባህሪ አሳይቶ ወደ ጤናማ የዕለት ተለት እንቅስቃሴው ቢመለስ የሁላችንም ፍላጎት ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ፍላጎትና ለግለሰቡ የአእምሮ ጤና መሻሻል ያለንን ተስፋ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያላገናዘበና ከልክ ያለፈ መሆን የለበትም፡፡ ምክኒያቱም የስነ-ልቡና መታወክ በአብዛኛው ቀስ በቀስ እየተሻሻለ የሚሄድ እንጅ እነደ ሌሎች አካላዊ በሽታዎች በቅጽበት ስለማይድን ነው፡፡ ስለዚህ ለግለሰቡ መሻሻል ያለን ጉጉት ከልክ በላይ ከሆነ ግለሰቡ ላይ ሌላ ጫና በማሳደር የማባባስ ሁኔታ ሊኖር ይችላል፡፡ እንደጠበቅነው ሳይሆን ሲቀር ለኛ ለቤተሰቦችና ጓደኞችም ያለው የመንፈስ ስብራት ቀላል አይሆንም፡፡ ስለዚህ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገበናዘበ ከሆነ ለወደፊት ለሚከሰቱ ችግሮች የስነ-ልቡና ዝግጁነት ይኖረናል ማለት ነው፡፡

➎የእራስ ቁጥጥር መንፈስን ለግለሰቡ ማጎናጸፍ፡-

እንደየ ግለሰቡ የስነ-ልቡና ችግር መሰረት ግለሰቡ የእራሱን ህይወት እንዲቆጣጠር መገፋፋት፡፡ ግለሰቡ መፈጸም የሚችላቸውን ተግባራት በተቻለ መጠን እራሱ እንዲያከናውን መገፋፋት፡፡ ከሁሉም በላይ ግለሰቡን በክብርና ሰባዊነት በተመላበት ሁኔታ ማዋራት፡፡ ምንም እንኳን ግለሰቡ የሚያሳያቸው እንግዳ የሆኑ ምልክት ወለድ ባህሪያት ቢኖሩም ለሌሎች ሰዎች የምናሳያቸውን ሰብአዊነት የስነ-ልቡና ችግር ላለባቸው ሰዎችም ማሳየት ይኖርብናል፡፡ አንድ ጥያቄ ለእናንተ… አንድ ሰው የጨጓራ ህመም ቢያመው ትስቁበታላሁ፣ትሳለቁበታላችሁ? ታዳያ ለምን የስነ-ልቡና ችግር ላለባቸው ግለሰቦች ላይ?

➏ገደብ ማበጀት፡-

ምንም እንኳን ግለሰቡ የራሱን ህይወት በተቻለ ቁጥጥር እንዲመራ ቢበረታታም የምንሰጠው ነጻነት እንደየ ግለሰቡ ለማህበረሰቡና ለእራሱ ባለው ስጋት መሰረት ሊወሰን ይገባል፡፡ ግለሰቡ እራሱንና ሌሎች የማህበረሰቡ ክፍሎችን ሊጎዳ የሚችልባቸው ሁኔታዎች ላይ ክብር የተመላበት ገደብ ማበጀት መልካም ነው፡፡

➐ የእኩልነት መንፈስን በቤተሰብ ውስጥ ማዳበር፡-

በቤተሰብ ውስጥ ባሉ ተግባራት ውስጥ ግለሰቡ በሚችል ከሆነ እንዲሳተፍ ማድረግ፡፡ ለምሳሌ የቤተሰብ አባላት ግለሰቡን ለመርዳት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ውስጥ ግለሰቡን ከማግለል ይልቅ አሱም እንዲሳተፍ ማድረግ፡፡

➑እራስን ማረጋገት፡-

እራሳቸንን ካላረጋጋን ሌሎችን መርዳት ስለማንችል በተቻለን መጠን እራሳችንን ማረጋጋት ግድ ይለናል፡፡ የራሳችንን ህይወት በአጠቃላይ መዘንጋት ለምንረዳው ግለሰብና ለቤተሰባችን ጥሩ ውጤት አይኖረውም፡፡ ለዚያም ነው አንዳንዴ የቤተሰብ አባላት ተከታትለው ለዚህ ችግር የሚወድቁት ምንም እንኳን በዘር የሚተላለፉና በጋራ የቤተሰብ ሁኔታ ምክኒየት ሊሆኑ ቢችሉም፡፡ ስለዚህ እውነታወን በመቀበል ልክ እንደ ግለሰቡ ሁሉ ለእራሳችሁም ጊዜ መስጠት፡፡ ምክኒያቱም እናንተ ጤነኛ ካልሆናችሁ ሌሎችን መርዳት አትችሉምና፡፡

ማንኛውም ሃሳብ አስተያየት ጥያቄ #Comment ላይ ጻፉልኝ?
__________

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀
🎊🎉

ቴሌግራም ሊንክ 🚙 www.tg-me.com/Psychoet

ምንጭ ፦ Emotional survival guide for care givers ከሚለው የዶ/ር ቤሪ ያኮብስ መጽኃፍ መነሻነት የቀረቡ

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
#የሳምንት_ሰው_ይበለን !

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀
#መልካም_ታህሳስ_ወር !
T.me/psychoet

ይህ ወር የአዕምሮ ደስታ ፣ ሰላም ፣ እረፍት የምታገኙበት ፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት ፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት ፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት ፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት ፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት ወር ይሁንላችሁ ፡፡

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ፍትህ ፣ ሰላም ፣ ልማት የምንሰማበት ይሁንልን ፡፡

አንድ ቀን ነገር ሁሉ ቀላል ይሆናል ! ሁሌም የማያልቅ ተስፋ አለ ።
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ

ለምትወዱት ጓደኛ #መልዕክቱን አስተላልፉ

@Psychoet
2024/09/28 16:23:53
Back to Top
HTML Embed Code: