Telegram Web Link
ሜሎሪና ቁጥር 3 "ሜሎሪና-ሕይወቴ"ን በኹሉም መደብሮች ማግኘት ትችላላችሁ።
ሜሎሪና መጽሐፍ በጃዕፈር መጸሐፍ መደብር (ለገሀር፣ 4ኪሎና ሳሪስ አደይ አበባ) ፣ በእነሆ መደብር 4 ኪሎ፣ በየኔነህ መደብር ቃሊቲ መናሀሪያ፣ በሱመያ መደብር መርካቶ እና በሌሎችም መደብሮች ይገኛል። በሌሎችም መደብሮች እየተሰራጨ ስለኾነ የቀረውን የክረምት ቀናት ዳጎስ ያሉ (የሥነልቦናና የመሪነት) ሀሳቦችን ከልብወለድ ታሪክ ጋር በማንበብ እንድታሳልፉ እጋብዛለሁ።


በሚቀጥሉት ቀናት ከመጽሐፉ የተወሰዱ ሀሳቦችን አካፍላችኋለሁ።
@psychoet
እግዚአብሔር ይመስገን!
ያለፉትን 13 ዓመታት የወሰዱት የሜሎሪና ተከታታይ የመጀመሪያ ክፍሎች ተጠናቀዋል። ሦስቱም የሜሎሪና ክፍሎች በየመደብሮቹ ስለሚገኙ እንድታነቡ እጋብዛለሁ። ለምትወዷቸው ደግሞ ለዐዲሱ ዓመት በስጦታ መልክ አበርክቱላቸው።

ፎቷችሁንና ምልከታችሁን ደግሞ በታላቅ አክብሮት ስለምቀበል በውስጥ ላኩልኝ።
ሜሎሪና - ስውር ጥበብ
ሜሎሪና - ቴሎስ
ሜሎሪና - ሕይወቴ
💚💛❤️
@psychoet
‹‹ትልቁ ብቸኝነት ሰውን ማጣት ሳይኾን ራስን ማጣት ነው። በምድር ላይ ራሱን እንዳጣ ሰው ብቸኛ የለም።  ራስን ማጣት፥ በኛ ውስጥ ያሉ ችሎታዎቻችንን አቅማችንንና ስሜቶቻችንን ማጣት ነው፡፡  እራሱን ያጣ ሰው በዙሪያው እልፍ ሰዎች ቢሰበስብ እሱ ግን ዘወትር ብቸኛ ነው።››

            ሜሎሪና ሕይወቴ ገጽ 44

"ሜሎሪና - ሕይወቴን" አንብባችሁ አስተያየታችሁንና የወደዳችሁትን ሀሳብ ከፎቶ ጋር ብትልኩልን ደስ ይለናል።
ሜሎሪና 💚💛❤️
ሜሎሪና ቁጥር 3 (ሜሎሪና ሕይወቴ) እየተነበበ ነው። ፎቶና የወደዳችሁትን ሀሳብ እያካፈላችሁን ስላለ አመሠግናለሁ።

ሜሎሪና መጽሐፍ በጃዕፈር መጸሐፍ መደብር (ለገሀር፣ 4ኪሎና ሳሪስ አደይ አበባ) ፣ በእነሆ መደብር 4 ኪሎ፣ በየኔነህ መደብር ቃሊቲ መናሀሪያ፣ በሱመያ መደብር መርካቶ፣ በባህርዳር ጎንደርና ላሊበላ አካባቢ አዳነ መደብር እና በሌሎችም መደብሮች ይገኛል። በሌሎችም መደብሮች እየተሰራጨ ስለኾነ የቀረውን የክረምት ቀናት ዳጎስ ያሉ (የሥነልቦናና የመሪነት) ሀሳቦችን ከልብወለድ ታሪክ ጋር በማንበብ እንድታሳልፉ እንጋብዛለሁ።
‹‹ኹላችን በምድር ስንኖር ይስፋም ይጥበብም፣ ይብዛም ይነስም  በውስጣችን የፈጠርነው የራሳችን ብቻ የኾነ ዓለም አለን። በዚህ ዓለም ውስጥ ትልቁ የሰውነት ውቅራችን ደግሞ ትዝታ ነው። ትዝታ ለብዙ ሰው የዕድሜ ዘመን እስር ቤት ነው። ብዙ ሠዎችም ወደፊት መራመድ እየፈለጉ አስሮ የሚይዛቸው በገዛ አዕምሮአቸው ውስጥ ያስቀመጡት የትናንት ታዝታቸው ነው። ከትዝታው መፋታትና ትዝታውን ማሸነፍ የቻለ ሰው ግን የትም መድረስ ይችላል።››

ሜሎሪና ሕይወቴ ገጽ - 79


አብርሆት ቤተመጻሕፍት አጠገብ በሚገኘው ሀሁ መጻሕፍት መደብር "ሜሎሪና ሕይወቴ"ን ማግኘት ይቻላል።
@psychoet
‹‹ትልቁ ብቸኝነት ሰውን ማጣት ሳይኾን ራስን ማጣት ነው። በምድር ላይ ራሱን እንዳጣ ሰው ብቸኛ የለም። ራስን ማጣት፥ በኛ ውስጥ ያሉ ችሎታዎቻችንን አቅማችንንና ስሜቶቻችንን ማጣት ነው፡፡ እራሱን ያጣ ሰው በዙሪያው እልፍ ሰዎች ቢሰበስብ እሱ ግን ዘወትር ብቸኛ ነው።››


#ሜሎሪና _ሕይወቴ 💚💛❤️
ፎቷችሁን እየላካችሁልን ስለኾነ እናመሠግናለን።
በሕይወታችን ለማግኘትና ለማሳካት የምንፈልጋቸውን ‹ትልልቅ› የሚባሉ ነገሮች ለማሳካት መክፈል ያለብን ብዙ መሥዋዕትነቶች አሉ፡፡ አንዳንዴ፣ መድረስ ወደ ምንፈልግበት ቦታ ለመድረስ ራሳችንን አዋርደን፣ ዝቅ ብለን፣ ማንነታችንን ደብቀን ነው፡፡ ብዙ ጊዜ የምንፈልገው ቦታ ለመድረስ መሸጥ ያለብን ማንነት እና መጣል ያለብን ክብር ይኖራል።

ሜሎሪና ሕይወቴ
...እነዚህ ሰዎች ሲቸግራቸው፣ ሲከፋቸው እና መውጫ ቀዳዳ ሲጠፋቸው ይስታውሱሃል እንጂ በደስታቸውና በስኬታቸው ጊዜ አትታያቸውም፤ የተቸገሩ ጊዜ ከአንተ እርዳታ ለመጠየቅ ፣ የጨነቃቸው ሰሞን ባንተ ለመጽናናት ፣ ዝቅ ያሉ ሲመስላቸው ባንተ ተጠቅመው ወደ ከፍታ ስፍራቸው ለመውጣት ዘወትር ከደጅህ ናቸው። ያገኙ ቀን፣ ያማረባቸው ዕለት፣ በሰዎች በተከበቡ ጊዜ ግን አንተን አያውቁኽም፣ ካጠገባቸው ኾነኽ አያዩህም ፣ እያወራሃቸው አይሰሙኽም፣ እየጠየቅሃቸው አይመልሱልኽም።...

ሜሎሪና ሕይወቴ


እያነበባችሁ ነው?
ሜሎሪና ቁጥር 3 (ሜሎሪና - ሕይወቴ) ለአንባቢያን ቀርቧል

“ሜሎሪና” ታሪካዊ የሥነልቡና ልብወለድ የሰው ልጅ ሞትን ለማሸነፍ በሚያረገው ትግል ውስጥ የኢትዮጵያውያንን ቀደምት ጥበብ ሚና የሚተርክና ስለ ኢትዮጵያ ትንሣኤ የሚያወራ ልብወለድ መጽሐፍ ነው ፡፡ በአቀራረቡም #የሥነልቡና_ምክሮችንና ሀሳቦችን
#የሥነ_አመራር ጥበቦችን #ከታሪካዊ_ክስተቶች ጋር አጣምሮ ይዟል ፡፡

ከ"ሜሎሪና" መጽሐፍ የተወሰዱ የሕይወት ምክሮችና እውነታዎች

📕 ‹‹ትልቁ ብቸኝነት ሰውን ማጣት ሳይኾን ራስን ማጣት ነው። በምድር ላይ ራሱን እንዳጣ ሰው ብቸኛ የለም።  ራስን ማጣት፥ በኛ ውስጥ ያሉ ችሎታዎቻችንን አቅማችንንና ስሜቶቻችንን ማጣት ነው፡፡  እራሱን ያጣ ሰው በዙሪያው እልፍ ሰዎች ቢሰበስብ እሱ ግን ዘወትር ብቸኛ ነው።››


📕‹‹...ትዝታ ለብዙ ሰው የዕድሜ ዘመን እስር ቤት ነው። ብዙ ሠዎችም ወደፊት መራመድ እየፈለጉ አስሮ የሚይዛቸው በገዛ አዕምሮአቸው ውስጥ ያስቀመጡት የትናንት ታዝታቸው ነው።››

📕‹‹አፍሪካ ውስጥ  ‹ሕዝቡ› እንደሚለው ቃል በመሪዎች የተነገደበት ቃል የለም። አንዳንዱ መሪ ሕዝቡ የሚለው የገዛ ራሱን እሳቤ ነው። ሌላው ደግሞ ቤተሰቦቹንና ዘመዶቹ ብቻ ነው ሕዝቡ ብሎ የሚቆጥረው።››


📕‹‹ሰው የሚሞተው ሥጋው ነፍሱን መሸከም ሲያቅተው ነው፡፡ ሥጋችን ደግሞ የሚያረጅም የሚበላሽም ነው፡፡ ነፍስ ልትሞት ካልቻለችና የሚሞተው ሥጋችን ከኾነ፣ለምን ለነፍሳችን የማያረጅና የማይሞት ሥጋ አንሠራላትም››


📕‹‹በህይወት ስትኖር መቼም ቢሆን ኹሉንም ሰው ማስደሰት አትችልም፤ ማወቅና መጠንቀቅ ያለብህ ዋናው ቁም ነገር ማስከፋት የሌለብህን ሰው ለይተህ ማወቁ ላይ ነው።››
  
ሜሎሪና ሕይወቴ
@psychoet
መልካም አዲስ ዓመት ይኹንላችሁ
#2017
ሜሎሪና መጽሐፍ
🌼🌼🌼🌼🌼
ትላንት ምሳ ሰአት ነው…ሶስት ናቸው… ትልቅ ሮቶ ይዘዋል …ላዳ አስቆሙና ሮቶውን ጫኑና ገቡ…

ከዛ ሩቅ መንገድ ይዘውት ሄዱ…ብዙ ጉራንጉር አስገቡትና የሆነ ቤት ጋር ላይ ሲደርሱ እዚህ ጋር ነን ብለው አስቆሙት
እቃቸውንም ተሸክሞ አወረደና

…ሂሳብ ሲል ...

የለንም አሉት…

ወርዶ ቢለምን ምን ቢል ዝምብለህ ንካው አሉት…

ጭራሽ እንድንከፍልህ ከፈለክ ዝፈንልን አሉት… ዘፈን አልችልም አለ…

በቃ እሺ #እልል በልና እንሰጥሃለን አሉት …ሰርቼ እኮ ነው ለምን ታንገላቱኛላቹ ይህን የሚያክል ሮቶ ጭኜ መኪናዬን ኮሮኮንች ውስጥ ጎድቼ ምንም አትከፍሉኝም ?ቢልም

ጮክ ብለህ #እልልል ካላልክ አንሰጥህም አሉት…

ተናደደና ተውት በቃ ከላይ አገኘዋለው ብሎ እየተሳሳቁበት ሳይቀበላቸው ጥሏቸው ሄደ…

ትንሽ እንደሄደ ከኋላው ስልክ ጠራ… ዞር ሲል Sumsung Not 8+ የተባለ ስልክ አንሱኝ አንሱኝ እያለ እየጮኅ ነው…

መኪናውን ዳር አስያዘና ስልኩን አንስቶት ሃሎ አለ…

ይቅርታ ወንድሜ አንተ ታክሲ ውስጥ ስልክ ጥለን ነበር የሚል ድምፅ ተከተለ…

ማን ልበል? አላቸው … አሁን ያወረድከን ሮቶውን የጫነው ልጆች ነን… እባክህን ስልክ ጥለን ነው

ይሄኔ ይሄ ላዳ ሹፌር ምን ቢል ጥሩ ነው… …
,

,

,

,

,

,

,

አሁን ነዋ #እልልልልል ማለት ብሎ

ጮክ ብሎ ስልክ ጆሮአቸው ላይ

እልልልልልልልል, ልልልልልልልልልል, እልልልልልልልልልል, እልልልልልልል

😂😂

መልካም የስራ ቀን
መመለስ ነበረበት የሚል #ሼር

እርሶ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ ?!

©Fb
ሜሎሪናን እያነበባችሁና አስተያየቶቻችሁኝ እየሰጣችሁን ስላለ እናመሠግናለን። 🙏
‹‹..ምቀኝነት በመጀመሪያ የሚገለጸው በቀልድ ውስጥ ነው። ስለዚህ ሰዎች በቀልድ የሚሉህን ኹሉ ከመረዳትና ራስህን ከአደጋ ለመጠበቅ ቸል እንዳትል። … ሰው በውስጡ የሌለን ወይም ያልመሰለውን ነገር በአፉ አይተነፍስም።››

ሜሎሪና - ሕይወቴ
"ይቺ ዓለም የምትፈልግህ ጠቃሚ ነገር አንተ ጋር እንዳለ ስታምን ብቻ ነው፡፡ ባጠቃላይ ዓለም ራስ ወዳድ ናት - ነዋሪዎቿም እንደዛው። ይሳካልህ ብለው መርቀውህ ሲሳካልህ የማይወዱ፣ ሰላም ሁን ብለው ሸኝተውኽ ጥልን የሚመኙልህ፣ ይከናወንልህ ብለው ውድቀትን የሚያስቡልኽ፣ ራሳቸውን ለመጥቀም አንተን የሚጎዱ ሰዎች ብዙዎች ናቸው።"

መስፍን እንዳለው

ሜሎሪና - ሕይወቴ
ከቻናሉ ቤተሰቦች ምን ያህሎቻችሁ "ሜሎሪና-ሕይወቴ" ን እያነበባችሁ ነው? የመጀመሪያው ዕትም ጥቂት ስለቀረ በሚቀርባችሁ መደብር በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት ትችላላችሁ።
@psychoet
2024/11/06 01:27:33
Back to Top
HTML Embed Code: