📌 👉 አደገኛው ስብእና/ Narcissism👈📌
🔥ለትዳር፣ ለጓደኝነትና አብሮ ለመስራት ስንመርጣቸው አብዝተን ልንጠነቀቃቸው የሚገባ አስቸጋሪ ማንነት ያላቸው ሰዎች።🔥
📌👉 ሁል ጊዜ ጥፋተኛ እንደሆናችሁ እንድታስቡ የሚያደርጉትን። ለሚሰጧችሁ መጥፎ ምላሽ ተጠያቂው/ዋ አንተ/አንቺ ነሽ የሚሉትን።
📌👉 የእነሱን ችግር እንጂ ፈፅሞ የእናንተን ማዳመጥና መረዳት የማይፈልጉትን።
📌👉 ለጥፋታቸው ሀላፊነት መውሰድ የማይፈልጉ፣ ሁል ጊዜ ትክክል ነኝ ብለው የሚያስቡና ለተፈጠረው ችግር ሁሉ ምክንያቱ እናንተ እንደሆናችሁ እንዲሰማችሁ የሚያደርጉትን።
📌👉 ጉራቸው ከልክ ያለፈ። ታላቅነታቸውን፣ ችሎታቸውን፣ ተፈላጊነታቸውን እና የበላይነታቸውን ሁሌ የሚናገሩትን። ከእናንተ የወሰዱትን ሀሳብ ጭምር የራሳቸው አድርገው የሚነግሯችሁን።
📌👉 የሰውን ትኩረት ለመሳብ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። በእያንዳንዱ ንግግራቸው እኔ....እኔ....እኔ የሚሉትን።
📌👉 ለሌላ ሰው ችሎታ እውቅና የማይሰጡና የሚቀብሩትን።
📌👉 ሌሎችን በጣም የሚያሳንሱ። የእነሱ ትልቅነት የሚጎላው የሌላውን ውድቀት፣ ድክመትና አለመሳካት ሲያወሩ የሚመስላቸውን።
📌👉 ፈፅሞ አክብሮት የላቸውም። ተሳስቻለሁ....ይቅርታ የሚባል ነገር አይታሰብም። ለጥፋታቸው ሌላውን ተጠያቂ በማድረግ የሚያሸማቅቁትን።
📌👉 እነሱ የሚፈልጉትን ሀሳብ እንድትቀበሉና በነሱ ቁጥጥር ስር እንድትሆኑ የሚያደርጉትን።
📌👉ምንም አይነት ፍቅርና ርህራሄ የሌላቸውን።
📌👉 ክፋታቸውን ነቅታችሁ ስትርቋቸው ስማችሁን የሚያጠፉ። ሚስጥርና ድክመታችሁን ለሰው የሚያወሩተን። በሚችሉት ሁሉ ሊጎዷችሁ የሚሞክሩትን።
🔥ይህንን ካነበቡ በኋላ ግንኙነቶችዎን ደግመው ይመርምሩ። ለሌሎችም እንዲጠቅም ሼር ያድርጉ🔥
👉 ©በመአዛ መንክር - ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት
@Psychoet

ስማኝ ልጄ!!!!!!!
1. ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትውደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትንም ልመድ ማለት እንጂ!!!!
2. ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማት ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!!!!
3. ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰው ሀቅ አትለፍ ማለት እንጂ!!!!
4. አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!!!!
5. ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድህ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!!!!
6. ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ!!!
7. ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ!!!!
8. ስራህን ውደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ስራ ውደድ ማለት እንጂ!!!!
9. ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!!!!
10. ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ስትሰራ አትሙት ማለት እንጂ!!!!
11. ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ግዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ!!!!
12. እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነትተናገር ማለት አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት ማለት እንጂ!!!!
13. አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትኑር ማለት አይደለም ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!!!!
14. ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!!!
15. ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሻልክህ ነህ ማለት አይደለም አምሮብሃል ማለት እንጂ!!!!
16. አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እንጂ!!!
©ከFb የተገኘ
ምክሩ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ባላችሁበት ግሩፕ ሼር አድርጉት
@psychoet

+ሕይወታችንን የሚያበላሹ ነገሮች
www.tg-me.com/psychoet
1. ኢጎ ምንድን ነው? ኢጎ ከህጻንነትሽ ጀምሮ ማህበረሰቡ የፈጠረብሽ የውሸት ማንነት ነው፡፡ይህ እብድ የሆነ አለም እብድ አድርጎ አእምሮሽን ቀርጾታል፡፡መጥላት፣ መቅናት፣ መናቅ፣መፍረድ፣ መከፋፈል፣ ዘረኛ መሆን፣ በሀብት መመካት፣ እኔ እኔ ብቻ ማለት...ወዘተ ነገሮች በውስጥሽ ተሰግስገዋል፡፡አንዳንዴ ጊዜ ፡ "እንዴት እንደዚህ አይነት መጥፎ ሰው ሆንኩኝ?" ትያለሽ፡፡መጥፎ የሆንሽው ግን አንቺ ሳትሆኚ ኢጎሽ ነው፡፡ይህ በማህበረሰቡ ከህጻንነትሽ ጀምሮ በውስጥሽ የተከማቸ ኮተት ነው፡፡አራግፊው፡፡አንቺ ውብ፣ ድንቅ፣ ደግ፣ ተወዳጅ፣ አስገራሚ፣ ባለብዙ በረከት፣ ሰው አክባሪ፣ ርህሩህ፣ የማትነካ፣ የማትዳሰስ even የማትሞትና በፈጣሪ አምሳል የተፈጠረሽ መንፈሳዊ ፍጥረት ነሽ፡፡ይህንን እኔ ልነግርሽ አይገባኝም፡፡ይህንን ስታነቢው ራስሽ ታውቂዋለሽ፡፡ውስጥሽም ይነግርሻል፡፡
+
2. ጓደኞችሽን አሳይኝና ማንነትሽን አሳይሻለው፡፡ከአህያ ጋር የዋለች ጊደር አመድ ቅማ ትመጣለች፡፡አመድ ከሚያስቅሙ ሰዎች ጋር የምትውል ሴትም እንደዛው አመዳም ናት፡፡ምርጥ ከሆኑ ሰዎች ጋር ብቻ ጊዜሽን አሳልፊ፡፡መጥፎ ሴት ብትሆኚም እንኳን በምርጥነታቸው ትሸነፊያለሽ፡፡ጓደኞችሽን በጥንቃቄ ምረጪ፡፡
+
3. ሀሳብሽን ከገንዘብሽ በላይ ተቆጣጠሪው፡፡አእምሮሽ የአሉታዊ ሀሳቦች ጭፈራ ቤት ከሆነ ሙሉ ህይወትሽ ገደል ይገባል፡፡በልብሽ ማዕከል የሚነግሰው ሀሳብ ውሎ አድሮ የህይወትሽ እውነታ ይሆናል፡፡እናም በጥንቃቄ ጠብቂው፡፡ሁልጊዜ አዎንታዊ ሀሳብን ብቻ አስቢ፡፡ለመሆኑ አሁን ምን እያሰብሽ ነው?
+
4. ሰዎችን አፍቅሪ ፣ ከልብሽ አክብሪ ፣ምን ይሉኛል ብለሽ ግን ምንም ነገር አታድርጊ፡፡ሰዎች የሚሉትን ነገር አያጡም፡፡ በውሃ ላይ ብትራመጂ ራሱ ዋና ስለማትችል ነው ማለታቸው አይቀርም፡፡ ራስሽ ላይ ብቻ አተኩሪ፡፡ አጭር ለሆነችው ህይወት ሰው ምን ይለኛል ብሎ መጨነቅ መሸወድ ነው፡፡
+
5. ቁሳቁስ ደስታ አይሰጥሽም፡፡ አሁን ደስታ የራቀሽ ብራንድ ነገር ስሌለሽ ከመሠለሽ ይቅርታ፡፡አለም ውስጥ ያለው ቁሳቁስ ሁሉ የአንቺ ቢሆንም እውነተኛ ደስታን አታገኚምም፡፡አዎ ብራንድ ነገር ስትገዢው ሊያሳብድሽ ይችላል፡፡ግን አንድ ቀን ባደረ ቁጥር የገዛሽው ነገር የሚሰጥሽ ደስታ እየተሸረሸረ ይመጣል፡፡እስቲ ከዚህ ቀደም ቋምጥሽ የገዛሻቸውን ነገሮች አስቢ፡፡እነዛ ተንሰፍስፈሽ የገዛሻቸው ነገሮች ዛሬ ያንን የቀደመ ደስታሽን ይሰጡሻል? በፍጹም፡፡ዛሬም ለመግዛት የምትንሰፈሰፊያቸው ነገሮች እንደዛው ናቸው፡፡ከገዛሻቸው በኋላ ይደብሩሻል፡፡ይህ መጥፎ ጨዋታ ነው፡፡ደስታሽ ያለው በውስጥሽ ነው፡፡ከፍያ የለውም፡፡ነጻ ነው፡፡ጥሩ ሰው መሆን ብቻ ደስታ ይሰጥሻል፡፡አንቺ ሰው እንዲያደርግልሽ የምትፈልጊውን ነገር ለሰው ስታደርጊ ደስታ ወደ አንቺ ይመጣል፡፡
+
6. ሁሉም ነገር ሱስ ነው፡፡ህይወትሽን መጥፎ የሚያደርገው መጥፎ ሱስ ነው፡፡መጥፎ ሱስን ግደይው፡፡መቃም፣ ማጨስ፣ መስከር፣ መዋሸት፣ መቅናት፣ መስነፍ...ማንኛው ወደኋላ የሚጎቱትሽን ነገሮች ከህይወትሽ ነቀለሽ ጣያቸው፡፡በምትካቸው በጎ ሱስ ፈጠሪ፡፡ያ መሄድ ወደ ምትፈልጊበት አለም ይወስድሻል፡፡
+
©ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ
ጠቃሚ ስለሆነ ለሌሎችም #Share እናድርግ

መነሻህን ሳታልም ጉዞ አትጀምር፤ መኖርህን ሳታውቅ አትሙት።
ልክ የዛሬ 20 ዓመት በ"ሜሎሪና" መጽሐፍ ♥♥♥
"ሜሎሪና"ን መጽሐፍ በዐማርኛና በኦሮምኛ ቋንቋዎች በየመደብሩ ያገኙታል፡፡
ታሪካዊ የሳይኮሎጂ ልብወለድ
www.melorinabook.com

የትብብር ጥያቄ!
ይህንን መልዕክትና ጥያቄ ቢያንስ ባላችሁበት አንድ የቴሌግራም ግሩፕና ለአምስት ጓደኞቻችሁ አድርሱልኝ?
😔🙏😔
=======================
፩. በዚህ ምድር ላይ ዛሬ የመጨረሻ ቀን ቢሆን ኑሮ አሁን ምን ታደርጉ ነበር?
፪. በጣም የምትወዱት/ የምታፈቅሩት ሰው ዛሬ የመጨረሻው ቀን ቢሆን ምን ታረጋላችሁ?
=======================
ይህንን ጥያቄ ሳትመልሱ እንዳትተኙ
መልካም አዳር!

15 ወርቃማ #አባባሎች!
------------------------ሼር
1) ምቀኞች መብዛታቸው በስኬት መንገድ ላይ የመሆንህ ምልክት ነው!
…
2) #ወንድ #ልጅ እናቱ በሕይወት እስካለች ድረስ #ሕፃን ነው..ለእናቱ!
…
3) በፈተና ላይ አለመታገስ ሌላ #ፈተና ነው!
…
4) #ፈገግታ ቃላት የሌለው መልካም ንግግር ነው!
…
5) ካንተ የባሰ አለና አመስግን ፈገግ በል!
…
6) ትንሽን ለመስጠት አትፈር ምንም አለመስጠት ከሱ የባሰ ነውና!
…
7) የተሸናፊዉ #ፈገግታ ያሸናፊውን #ደስታ ይቀንሳል!
…
8) የሁሉን #ሰው ውዴታ ማግኘት ሊደረስበት የማይቻል ግብ ነው!
…
9) #ነፍስ በኩራት ስትሞላ ጎደሎ የመሆኗ መገለጫ ነው!
…
10) ኩራተኛ ሰው ተራራ ጫፍ ላይ ሆኖ ሌሎችን ትንሽ አድርጎ እንደሚያይ ነው ነገርግን እሱንም ትንሽ አድርገው እንደሚያዩት አያውቅም!
…
11) ብዙ ጊዜ በጉጉት ከምንጠብቀው ይልቅ ድንገት የምናገኛቸው ነገሮች ውብ ናቸው እኛ ከለፋነው ጌታ የፃፈው መልካም ነውና!
…
12) ግኡዝ የሆኑት ውሃና አፈር ለእፅዋት አግልጋይ ናቸው ፤ እፅዋቶች ደግሞ ለእንስሳት ያገለግላሉ እንስሳት ፣እፅዋትና ግኡዛን ደግሞ የሰውን ልጅ ያገለግላሉ ... በተቃራኒው የሰው ልጅ ወደታች ወርዶ ለግኡዛን አገልጋይ (አምላኪ) መሆን ከጀመረ ያኔ ከነሱ የባሰ ይሆናል።
…
13) ብዙ ሰው ልጅ ለዘለዓለም እንደሚኖር ሆኖ ይለፋል አንድ ቀን ሳያልፍለት ይሞታል!
…
14) በሕይወት ትልቁ ስኬት የሕይወትን ትርጉም ማግኘትና አላማ ያለው ኑሮ መኖር ነው፡፡
…
15) በዚህ ቦታ .... ካነበባችሁት ፣ ከሰማችሁት ፣ ከምትከተሉት እምነት የምትወዱትን አባባል በcomment አሳውቁኝና ሌሎችም ያንብቡት፡፡
Share

በአንድ መድረክ ላይ ቻርሊ ቻፕሊን አንድ ቀልድ ቀልዶ ሁሉንም ታዳሚሚዎች በጣም ይስቃቸዋል።ሁለተኛም ያንኑ ቀልድ ደገመዉ ጥቂት ሰዎች ብቻ ሳቁ።ለሶስተኛ ጊዜ ያንኑ ቀልድ ደገመዉ፤በዚህን ጊዜ ግን ማንም አልሳቀም ነበር።ይህን ያየዉ ቻርሊ ለታዳሚዎቹ እንዲህ አላቸዉ........
"በአንድ ቀልድ ደጋግማችሁ ካልሳቃችሁ ለምን ታዲያ በአንድ ችግር ደጋግማችሁ ትጨነቃላችሁ።" ነበር ያላቸዉ።
በዚህች አለም ላይ ምንም ዘላቂ ነገር የለም ችግራችንም ቢሆን!!!!!!
©ማህበራዊ ሚዲያ
በደስታ #ሼር አድርጉት

📌🔖አዲሱን አመት በብሩህ ተስፉ ይቀላቀሉ!
የ 2013 የመጨረሻ 8ኛ ዙር የሕይወት ክህሎት ስልጠናችን ነሀሴ 25 ጀምሮ ይሰጣል
ይምጡና ለ 2014 ጥሩ የሕይወት ክህሎት ይሰንቁ
የሚሰጡት ስልጠናዎች
📝ሳይኮሎጂን መረዳት
📝የሕይወትን አላማ ማወቅ
📝ለ2014 እቅድና ግብ አዘገጃጀት
📝ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም
📝የስሜት ብልሀት
📝ተግባቦትና ፍርሀትን ማስወገድ
የስልጠና ቀናት ለተከታታይ 4 ቀናት(ያሉን ፈረቃዎች)
📆📆📆 ነሃሴ 25፣26፣27፣28
ማክሰኞ፣ ረዕቡ፣ ሀሙስ ፣ አርብ
4-6 ⏰ወይም 8-10⏰
በኹለት ቀን ለመጨረስ
📆📆📆 ነሃሴ 29 እና 30
ቅዳሜና እሑድ
3-6 ⏰ ወይም 7-10 ⏰
🔔በአንድ ፈረቃ ጥቂት ሰው ብቻ ስለምናሰለጥን ቀድመው በሚያመችዎት ፈረቃ ይመዝገቡ ፡፡
💸ክፍያ (የመመዝገቢያ ፣ የስልጠና ፣ የሰርተፍኬት ጨምሮ)- 500 ብር ብቻ
ስልጠናውን ቢወስዱ ይጠቀማሉ ለሚሏቸው ሌሎች ወዳጅዎ #Share ያድርጉ
0912664084 ይደውሉ ይመዝቡ
በአካል ለመመዝገብ የስልጠና አድራሻ : 4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሃን ህንፃ ቢሮ ቁጥር 219 (Nova Training Center)
ትርፋችን የሰው ህይወት መለወጥ ነው፡፡ 📖

#ክፍል_1
ለሌሎችም እንዲደርስ በየግሩፑ #Share አርጉት !
Psychology - ሥነ ልቡና /Ψ/
ሥነልቡና በታሪኩ ውስጥ የተለያየ ትርጓሜ ይዞ የመጣ ሲሆን አሁን በደረሰበት የዕድገት ደረጃ ግን አብዛኞቹ ተመራማሪዎች የሚስማሙበት ትርጉም ይህን ይመስላል ፡፡
ሳይኮሎጂ ከሁለት የግሪክ ቃላት ሳይኪ እና ሎጎስ (Psyche & logos ) የሚሉ ቃላቶች የተወሰደ ነው ፡፡
❖(Psych )ሳይኪ | Mind (ነፍስ - አዕምሮ - መንፈስ) ሲሆን
❖(Logos) ሎጎስ | Disclosure (ገለፃ /ጥናት) ማለት ነዉ ፡፡
በዚህም መሰረት ሥነልቡና ማለት፦
✔ ስለ #ባህሪይ እና #የአዕምሮ አሰራር ሂደት የሚያጠና #ሳይንስ ነው ፡፡
#ባህሪይ ስንል ማናቸውም የምናረጋቸዉና በአይን የሚታዩ ነገሮች ሲሆኑ
#የአዕምሮ አሰራር ሂደት ደግሞ በአይን የማይታይ ግን በተግባር የሚገለፅ ነዉ ፡፡
#ሳይንስ ስንል ሳይንስ የሚያልፍባቸውን ሂደቶች ስለሚያልፍ ነዉ እነርሱም (Emperical / በሙከራ የተረጋገጠና መመልከት የምንችለው ,
Objective / ከግል ስሜት ጋር ያልተያያዘና ከገሀዱ አለም ጋር የተገናኘ ,
Systematic / በስርአት የተቀረፀና የሚሰራ ,
Replicable / ውጤቱ ሆነ ሂደቱ በሌላ ሰው መደገም የሚችል) ናቸው ፡፡
ሌላው ሥነልቡና ማህበራዊ ወይስ ተፈጥሮአዊ ሳይንስ ነው የሚለው ጥያቄ ነው ፡፡ ምንም እንኳን ባለንበት ሀገር ኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም የትምህርት ተቋም እንደማህበራዊ ሳይንስ የሚታይና የሚሰጥ ሲሆን ባብዛኞቹ ባደጉት ሀገራት ግን ከህክምና ትምህርት ክፍል ስር የሚሰጥ በተፈጥሮአዊ ሳይንስ ስር ያለ ትምህርት ነው ፡፡
Social science is the scientific study of human society and social relationships. Whereas natural science deals with the physical world. By these definitions then psychology would fall under the category of a natural science.
https://www.thestudentroom.co.uk/showthread.php?t=4949812
ሥነ ልቡና አዕምሮን አያጠናም ይልቁንስ ስለ አዕምሮ አሰራር ሂደት እንጂ። (ስለአዕምሮ የሚያጠኑት ኒውሮሎጂስት እና ሳይካትሪስቶች ናቸዉ ፡፡ )
የሥነልቦና ትምህርት ዋና አላማ / ግብ (goal) አራት ናቸው እነርሱም ፦
1.ባህሪን መግለፅ (Describe )
2.ባህሪን ማብራራት (Explain)
3.ባህሪን መተንበይ (predict)
4.ባህሪን መምራት /መቆጣጠር (control )
ሥነልቡና (Psychology ) መገለጫ ምልክት (Symbol) ያለዉ ሲሆን ምልክቱ የግሪኩ 23ኛ ካፒታል ሊተር Ψ ሳይ (Psi ) ነዉ፡፡ የ ሳይ ምልክት የተገለበጠ "ሐ" ይመስላል ፡፡ በዚህ ምልክት ' Ψ ' ላይ ያሉት ሶስት አምዶች አንዳንድ ጠቢባን በነዚህ ሶስት ነገሮች ይመስሏቸዋል
1. ነፍስን #Soul
2. ሀሳብን(አዕምሮ) #Mind
3. መንፈስን #Spirit
❖❖______❖______❖❖
Source:- personal knowledge from d/f text books But If you wish to read to Intro Books I can suggest
ምንጭ ፦ ካለኝ ዕውቀት ማለትም ከዚህ በፊት ከሰማኀቸው ፣ ከተማርኩት እንዲሁም ካነበብኩት ለአንባቢ እንዲቀር አድርጌ በአማረኛ የፃፍኩት ነው ። ጠሩ መጸሐፎች የሚፈልግ መጠቆም እችላለሁ ፡፡
በሚቀጥለው ሳምንት ይቀጥላል፡፡ ማንኛውም ጥያቄ / ተጨማሪ ሀሳብ Comment ማረግ ይቻላል ፡፡
በሚቀጥሉት ሳምንታት እንዚህን እናያለን ፦
1. በሥነልቡና ስር ያሉ ዋና ዋና ሙያዎች (Sub fields )
2. የሥነልቡና ታሪካዊ አመጣጥ ፣ ከፍልስፍና ጋር ያለው ቁርኝትና በዘርፉ ብዙ ሚና ያበረከቱ ሰዎች
3. እንዴት ነገሮችን እንደምናስታውስና እንደምንረሳና ከዚህ ጋር ተያይዞ መርሳት የሚባል ነገር በሥነ ልቡና አለ ወይ
4.ሥነ ልቡና ስለ ህልም ምን ይላል ብለን እንመለከታለን
ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የTelegram ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛
ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
የሳምንት ሰው ይበለን!
Join

ሰዎች ስለእኛ በሚያስቡት ነገር ላይ መጨነቅን ለማቆም ቀላል ዘዴዎች
Telegram www.tg-me.com/psychoet
አንብበው ሲጨርሱ ለሌሎችም #Share ያድርጉ
‘’የማይባል ነገር ተናገርሁ እንዴ? እንዴት እንደዚህ አደርጋለሁ? ሰዎች እኮ መሃይም :ገገማ:የሚያናድድ ሰው ነው/ነች ይሉኝ ይሆናል’’ እያልን ራሳችንን የምናስጨንቅ ስንቶቻችን ነን! ሌሎች ሰዎች ስለእኛ በሚያስቡት ነገር ላይ በመጨነቅ አእምሯችንን በጨለማ ቦታ እንዲንከራተትና ራሳችንን በመጠራጠር የስጋት ስሜት እንዲሰፍንብንና እንዳንረጋጋ እያደረግን መሆኑን ልናውቅ ይገባል:: ለነገሩ ሁላችንም ሰዎች ስለእኛ ያላቸው ሃሳብ/አስተያየት ምን ይሆን ብለን መጨነቅ እንደሌለብን እናውቃለን ወደ ተግባር ለመቀየር ግን ስንቸገር እንታያለን:: ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዘዴዎች ብንጠቀምባቸው ይረዱናል!
1. የሰዎችን አዕምሮ ማንበብ እንደማንችል መረዳት፡- እስኪ ሰዎች ስለእኛ የሚያስቡትን በእርግጠኛነት ማወቅ እንችላለን? ብዙ ጊዜ ነገራትን ሳናጣራ ይሆናል በማለት ብቻ ማወቅ እንደምንችል ነው የምናስበው ይህ አስተሳሰባችን ደግሞ ለህይወታችን ፀር ወደሆኑ ድምዳሜዎች/ዉሳኔዎች ይመራናል::ስለዚህ እነዛ ሰዎች ሃሳባቸውን የሚገልጹበትን ዕድል አግኝተው ሃሳባቸውን እስካልገለጹልን ድረስ ስለምን እንደሚያስቡ ማወቅ በፍጹም አንችልም፡፡
2. በቋሚነት ለሚጠቅመን ነገር መስራት:- ከሌሎች ሰዎች የሚሰነዘሩ የኩነኔ አስተያየቶች በእርግጥም እኛን ይጎዱናል ነገር ግን ከእነዚህ ሰዎች የሚመጣውን አሉታዊ ምላሽ በመፍራት የምናጣቸው/የምናሳልፋቸው መልካም ዕድሎች ጥለውብን ከሚያልፉት የአእምሮ ጠባሳ አይበልጥም፡፡ እነዚህ የኩነኔ/አሉታዊ አስተያየቶች የሚያደርሱብን ጉዳት ቅጽበታዊ ሲሆን ባጣናቸው/ባመለጡን መልካም ዕድሎች ምክንያት የሚደርስብን ጸጸትና ቁጭት ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ስር እየሰደደና እያደገ ነው የሚሄደው፡፡ ስለዚህ በቋሚነት የሚጠቅመንን ነገር ለማግኘት ጊዜያዊ የሆኑ ተቀባይነት ማጣትን ለመቀበል ፈቃደኞች እንሁን::
3. ራስን ከመኮነን/በራስ ላይ ከመፍረድ መቆጠብ:- እስኪ ሰዎች ምን ይሉን ይሆን ብለን የምንጨነቅበትን ሃሳብ ለሰከንድ ቆም ብለን እናስበው! በእርግጠኝነት እኛ ለራሳችን የምናስበውን ነገር ላይ ነው ሌሎችም እንደዚ ያስባሉ ብለን የምንሰጋ፡፡ ስለዚህ በራሳችን ላይ መፍረድን አቁመን(ራስን ከመኮነን ተቆጥበን) እኛነታችንን ከተቀብለነው ወይም ለራሳችን ጥሩ ግምት ከሰጠን ሌሎቹ ስለእኛ ለሚሰጡት/ለሚያስቡት ሃሳብ ፍርሃትና ስጋት አይኖረንም ማለት ነው፡፡
4. ሌሎች ሰዎችን መኮነንን/በሌሎች ላይ መፍረድን ማቆም፡- ሰዎችን እየገመገምን፡እየኮነንና እየፈረድንባቸው የምንኖር ከሆነ እነሱም በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚፈርዱብን ነው የምናስበው፤ ስለዚህ በእነሱ ላይ ከመፍረድ ይልቅ ህይወታችንን ለማሻሻልና ለማደራጀት እንደሚያግዙን ቆጥረን ብናደንቃቸውና ብናበረታታቸው የበለጠ ተጠቃሚዎች መሆን እንችላለን፡፡
5. ስለእኛ አለመሆኑን መረዳት፡- ሰዎች በራሳቸው እይታ ከደረሰባቸው ክስተት፡ ቁስል፡ ፍራቻና እንከን የተነሳ ለነገሮች የተለያዩ አሉታዊ ምላሾችን ይሰጣሉ ነገር ግን የእነሱ ምላሽ ከእኛ ጋር የሚገናኝ እንዳልሆነ ልብ ልንል ይገባናል፡፡ ለምሳሌ የሆነ ቢዝነስ ለመጀመር ብንወስንና አንድ ሰው ”እመነኝ ይህንን ስራ ከጀመርህ በሚቀጥሉት ወራት አሊያም ዓመታት ምንም ዓይነት የእረፍት ጊዜ አይኖርህም” ቢል ሰውዬው የተናገረው ቢዝነስ መጀመር ላይ ያለውን ሃሳብ/አመለካከት እንጂ እኛን በተመለከተ እንዳልሆነ ለይተን መረዳት ይጠበቅብናል::
6. በሚያስደስተን ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ:- ይህን ባደርግ ሰዎች ይፈርዱብኛል በማለት የሚያስደስቱንን ተግባራት ከማድረግ የምንገደብ ከሆነ(የማኅበረሰቡን እሴቶች በጠበቀ መልኩ) ጊዜያችንን ምንም ዓይነት ጥቅም በሌለው ጭንቀት እያባከንነው መሆኑን እናስተውል፡፡ ስለዚህ በህይወታችን ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት የሚችለውን ብርቅ የሆነውን አቅምና ኃይላችንን በመሸርሸር ፈንታ እኛን በሚያስደስቱን ነገራት ላይ ትኩረት ልናደርግ ይገባል፡፡
7. የሚያውኩንን ነገሮች መለየት፡– ሌሎች ሰዎች አሉታዊ በሆነ መልኩ ይገመግሙናል/ይፈርዱብናል ብለን የምንጨነቀው ምናችንን በተመለከተ ነው? በስራችን ሁኔታ: ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት: ምናልባትም በክህሎታችንና ነገሮችን በመመርመር ባለን አቅም ሊሆን ይችላል:: ስለዚህ በውስጣችን መረጋጋት እንዳይኖር የሚቀሰቅሱ ነገሮችን መለየትና ማሻሻል ከቻልን ማሻሻል አሊያም እንዳሉ መቀበል ያስፈልጋል:: ምክንያቱም ከሁኔታዎች ጋር ሰላም መፍጠር ከቻልን የሰዎች አጸፋዊ ምላሽ አያስጨንቀንም ማለት ነው::
8. ራሳችንን መቀበል:– ፍጹም አለመሆናችንን፡ እንከንና ድክመቶች እንዳሉን መቀበል ነገር ግን አቻ የሌለን(ልዩ) በዓለም ላይ እኛን የሚመስል ሰብዕናና ተሰጥኦ የታደለ ሰው እንደሌለና ወደፊትም እንደማይኖር ልናስተውል ይገባል፡፡
9. አጸፋዊ ምላሾችን መጠበቅ/ተስፋ ማድረግ፡- በሰዎች ዘንድ የሚፈጠረውን አጸፋዊ መልስ በመፍራት ፈንታ ያ ምላሽ ሊፈጠር እንደሚችል አስቀድመን ተስፋ ማድረግ አለብን(የሰዎችን ስሜት ለመቀስቀስ መፍራት የለብንም) ምክንያቱም በሰዎች ዘንድ አሉታዊም ይሁን አዎንታዊ ምላሽ መፍጠር ካልቻልን ምናልባትም ራሳችንን የመሆን ድፍረቱን ልናጣ እንችላለንና፡፡
10. እየኮነኑን/እየፈረዱብን ነው ብለን ካሰብናቸው ሰዎች ጋር ማውራት፡- እንዲያው ሁኔታዎች ተመቻችተውልን ስለእኛ መጥፎነት ያስባሉ/እየፈረዱብን ነው ብለን ከምናስባቸው ሰዎቸ ጋር ተቀራርበን ብናወራ እስከምንገረም ድረስ ምንም ባለጠበቅነው ሁኔታ አዕምሯቸው በብዙ ጭንቀቶች እንደተሞላ ልናውቅ እንችላለን፡፡ ማን ያውቃል ልክ እኛ እንደምንጨነቀው እነሱም ሌሎች ሰዎች ስለእነሱ ምን ሊያስቡ/ሊሉ በሚችሉት ሃሳብ እየተጨነቁ ሊሆን ይችላል እኮ፡፡ ስለዚህ ራሳችንን ግልጽ በማድረግ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ተቀራርበን ሃሳብ ማንሸራሸር ያስፈልጋል::
በአጠቃላይ ከላይ የተዘረዘሩትን ሃሳቦች ወደ ተግባረ ከቀየርናቸው እኛም መቀየር እንችላለን!
(በአለበል አዲስ)
©Zepsychologist

ነገ ይጀምራል ! 📌🔖አዲሱን አመት በብሩህ ተስፉ ይቀላቀሉ!
የ 2013 የመጨረሻ 8ኛ ዙር የሕይወት ክህሎት ስልጠናችን ነሀሴ 25 ጀምሮ ይሰጣል
ይምጡና ለ 2014 ጥሩ የሕይወት ክህሎት ይሰንቁ
የሚሰጡት ስልጠናዎች
📝ሳይኮሎጂን መረዳት
📝የሕይወትን አላማ ማወቅ
📝ለ2014 እቅድና ግብ አዘገጃጀት
📝ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም
📝የስሜት ብልሀት
📝ተግባቦትና ፍርሀትን ማስወገድ
የስልጠና ቀናት ለተከታታይ 4 ቀናት(ያሉን ፈረቃዎች)
📆📆📆 ነሃሴ 25፣26፣27፣28
ማክሰኞ፣ ረዕቡ፣ ሀሙስ ፣ አርብ
4-6 ⏰ወይም 8-10⏰
በኹለት ቀን ለመጨረስ
📆📆📆 ነሃሴ 29 እና 30
ቅዳሜና እሑድ
3-6 ⏰ ወይም 7-10 ⏰
🔔በአንድ ፈረቃ ጥቂት ሰው ብቻ ስለምናሰለጥን ቀድመው በሚያመችዎት ፈረቃ ይመዝገቡ ፡፡
💸ክፍያ (የመመዝገቢያ ፣ የስልጠና ፣ የሰርተፍኬት ጨምሮ)- 500 ብር ብቻ
ስልጠናውን ቢወስዱ ይጠቀማሉ ለሚሏቸው ሌሎች ወዳጅዎ #Share ያድርጉ
0912664084 ይደውሉ ይመዝቡ
በአካል ለመመዝገብ የስልጠና አድራሻ : 4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሃን ህንፃ ቢሮ ቁጥር 219 (Nova Training Center)
ትርፋችን የሰው ህይወት መለወጥ ነው፡፡ 📖
@psychoet
የ 2013 የመጨረሻ 8ኛ ዙር የሕይወት ክህሎት ስልጠናችን ነሀሴ 25 ጀምሮ ይሰጣል
ይምጡና ለ 2014 ጥሩ የሕይወት ክህሎት ይሰንቁ
የሚሰጡት ስልጠናዎች
📝ሳይኮሎጂን መረዳት
📝የሕይወትን አላማ ማወቅ
📝ለ2014 እቅድና ግብ አዘገጃጀት
📝ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም
📝የስሜት ብልሀት
📝ተግባቦትና ፍርሀትን ማስወገድ
የስልጠና ቀናት ለተከታታይ 4 ቀናት(ያሉን ፈረቃዎች)
📆📆📆 ነሃሴ 25፣26፣27፣28
ማክሰኞ፣ ረዕቡ፣ ሀሙስ ፣ አርብ
4-6 ⏰ወይም 8-10⏰
በኹለት ቀን ለመጨረስ
📆📆📆 ነሃሴ 29 እና 30
ቅዳሜና እሑድ
3-6 ⏰ ወይም 7-10 ⏰
🔔በአንድ ፈረቃ ጥቂት ሰው ብቻ ስለምናሰለጥን ቀድመው በሚያመችዎት ፈረቃ ይመዝገቡ ፡፡
💸ክፍያ (የመመዝገቢያ ፣ የስልጠና ፣ የሰርተፍኬት ጨምሮ)- 500 ብር ብቻ
ስልጠናውን ቢወስዱ ይጠቀማሉ ለሚሏቸው ሌሎች ወዳጅዎ #Share ያድርጉ
0912664084 ይደውሉ ይመዝቡ
በአካል ለመመዝገብ የስልጠና አድራሻ : 4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሃን ህንፃ ቢሮ ቁጥር 219 (Nova Training Center)
ትርፋችን የሰው ህይወት መለወጥ ነው፡፡ 📖
@psychoet
ከሰዎች ጋር ያለንን ተግባቦት ለማዳበር የሚረዱ ጠባያት
1. ጥሩ አድማጭ መሆን
ተግባቦትን ለማዳበር ከሚረዱ ጠባያት ዋነኛው ጥሩ አድማጭነት ነው፡፡ ሰዎች በሚናገሩበት ሰዓት ተናግረው እስኪጨርሱ አለማቋረጥ፤ ዓይናቸውን መመልከት፤ በንግግር መሃልም መረዳታችሁን ለማመልከት ጭንቅላታችሁን ወደ ላይና ወደ ታች መነቅነቅ፤ ተናግረውም ከጨረሱ በኋላ መናገር የፈለጉትን ሃሳብ በጥቂት ቃላት ማጠቃለል የጥሩ አድማጭነት ምልክቶች ናቸው፡፡
2. የፊት ገጽታችንና የእጅ እንቅስቃሴአችን
በንግግር ወቅት ያለን የፊት እና የእጅ እንቅስቃሴ ስለምንናገረው ሃሳብ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ አለ፡፡ ለምሳሌ አስደሳች ሃሳብ ለመናገር እየሞከርን የፊት ገጽታችንን ማኮሳተር፤ ማጨማደድ እና የዓይን ሽፋሽፍትን መሰብሰብ ለአድማጭችን ተቃራኒ መልዕክት ይልካል፡፡ ስለዚህም ከምንናገረው ሃሳብ ጋር ውህደት ያለው የፊት ገጽታና የእጅ እንቅስቃሴ ሊኖረን ይገባል፡፡
3. ፍሬ ሃሳቡን በተወሰኑ ቃላት መግለጽ
የሰው ልጅ ትኩረትን ሰጥቶ አንድን ድርጊት መከወን የሚችው ለጥቂት ደቂቃዎች ስለሆነ በንግግር ወቅት በጥቂት ቃላት የምንፈልገውን ሃሳብ መግለጽ ይገባል፡፡ የምናናግረውም ሰው በዚያች በሚያናግረን ሰዓት ብዙ የሚያሳስቡት እና ጊዜ ሊሰዋላቸው የሚፈልጋቸው ብዙ ጉዳዮች እንዳሉት በማመን አጭርና በተመረጡ ቃላት የተሟላ ንግግር ብናደርግ ጥሩ ተግባቦት ይኖረናል፡፡
4. ትኩረት የሚያሳጡ ነገሮችን ማራቅ
ተንቀሳቃሽ ስልክ እንዲህ የዕለት ተዕለት ኑሯችን ውስጥ ዘልቆ በገባበት ጊዜ ውስጥ ከሰዎች ጋር በምንነጋገርበት ወቅት የምንጠቀማቸው ከሆነ ተገቢ ያልሆነ ትርጉም ይሰጣል፡፡ ለምናናግረው ሰው ውይም ስሚናገረው ሃሳብ ግድ እንደሌለን ያሳብቃል፡፡ ስለዚህም በንግግር ወቅት ተንቀሳቃሽ ስልካችንን ጨምሮ የምንከውነውን ማንኛውንም ስራ አቁመን ሙሉ ትኩረታችንን በመስጠት ልናዳምጥ እንዲሁም ምላሽ ልንሰጥ ይገባል፡፡
5. አቀማመጥን ማስተካከል
ወደ ጀርባችን ተለጥጦ መቀመጥ፤ ጀርባችንን መስጠት ወይም ፊትን ወደ ተቃራኒው አቅጣጫ ማዞርን የመሳሰሉ አቀማመጦች ተግባቦትን አስቸጋሪ ሊያደርጉ ስለሚችሉ ወደ ምናናግረው ሰው አቅጣጫንን ማስተካከል እንዲሁም ጠጋ በማለት አቀማመጣችንን ማስተካከል ይገባናል፡፡
6. የሚያናግሩትን ሰው ስሜት መረዳት
እጅግ የሚያሳዝን ታሪክ እየተነገረን ስሜታቸውን ከቁብ ሳንቆጥር ቅጭም ባለ አኳኋን “የምተለው ይገባኛል” ብንል ተአማኒነት ያሳጣል፡፡ የተናጋሪውን ስሜት ወደእኛም ዘልቆ እንዲገባ መፍቀድ ከቻልን መልካም ተግባቦት ይኖረናል፡፡
7. ንግግርህ ፍሰት ያለው እና ያልተዘበራረቀ እንዲሆን ማድረግ
ከአንድ ሃሳብ ወደ ሌላ ሃሳብ መዝለል ውልና ማሰሪያ የሌለው ንግግር፤ ውይይትና ክርክር ማድረግ መጨረሻቸው የማያምር ነው፡፡ ስለዚህም ትኩረትን በአንድ ሃሳብ ላይ ብቻ በማድረግ ያልተዘበራረቀ እንዲሁም ፍሰቱን የጠበቀ ንግግር ማድረግ እርሱንም አጠናቆ ወደሌላው መሻገር ተገቢ ነው፡፡
8. በየንግግሩ መሃል የሚገቡ ድምጾችንና የቃላት ድግግሞሽን ማስቀረት
ብዙውን ጊዜ ሰዎች ሃሳባቸውን ከመከታተል ይልቅ ወደዚህ ጽምጸት አትኩረው እንዲያፌዙ ይጋብዛል፡፡ ስለዚህም “አ….. “ “አም….” የሚሉ ድምጸቶችን ማስወገድ ይገባል፡፡ እንዲሁም “እና” ፤ “ማለት ነው” እና “ምናምን” የሚሉ ቃላትን መደጋገም ንግግራችንን አሰልቺ ሊያደርጉት ስለሚችሉ ማስወገድ ይገባል፡፡
9. የድምጻችንን ቃና እንደየሃሳባችን ማቀያየር
በንግግር ወቅት አንድ ቃና ብቻ ያለው ወጥ ንግግር ማድረግ፤ ለሃዘኑም ለደስታውም ለቁጣውም ተመሳሳይ ድምጸት መጠቀም የአድማጭ ትኩረት እንዲበታተን የሚጋብዝ ነውና አንዴ ከፍ አንዴ ዝቅ አንዳንዴም ለጥቂት ሰኮንዶች ዝም እያልን በተለያየ ቃና የታጀበ ንግግር ማድረግ የአድማጭን ትኩረት ለመሳብና እስከ ንግግሩ መጨረሻ ሰብስቦ ለማቆየት ይረዳል፡፡
ቴሌግራም ቻናሌ ፡ www.tg-me.com/psychoet
የቻናሉ ቤተሰቦች በቅርቡ የኅትመት ብርሃን ያየውና በአስገራሚ የታሪክ ፍሰቱና ስነልቦናዊ ምክሮቹ የቀረበው የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ተከታታይ ልብወለድ መጽሐፍ "ሜሎሪና" እንድታነቡ እጠይቃለሁ ፡፡ ያነበቡት ኹሉ ወደውታል ፣ ተምረውበታል ፣ ሕይወትን ዘወር ብለው አይተውበታል ፡፡ መጽሐፉን ( በጃዕፈር ፣ በሀሁ እንዲሁም በሌሎች መደብሮች ያገኙታል ) ።
ለሌሎች #Share በማረግ ተግባቦታችንን እናሳድግ
ቴሌግራም ቻናሌ ፡ www.tg-me.com/psychoet
©Zepsychology

ግጭትን በሰላማዊ መንገድ መፍታት
Telegram www.tg-me.com/psychoet
ግጭት የአንድ ሰው ድርጊት ወይም አመለካከት ሌላውን ሲረብሽ የሚፈጠር ሲሆን ይህም በቤተሰብ ፤ በጓደኛ ፤ በስራ ቦታ፤ በጋብቻ.. ወዘተ መካከል ሊከሰት ይችላል፡፡ የግጭቱ ሁኔታ መክረር ወይም በቀላል መፈታት እንደተጋጪዎቹ ባህርይ ፤ግንኙነትና የግጭቱ ዓይነት ይለያያል፡፡ የተለያዩ የግጭት ዓይነቶችን በአራት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡
✍ከራስ ጋር የሚፈጠር ግጭት (Intra-personal)
ምንም እንኳን የተለያዩ የግጭት ዓይነቶች ቢኖሩም በማኅበረሰባችን ውስጥ የላቀ ትኩረት የሚሰጣቸው ከውጫዊ አካላት ጋር ለሚፈጠሩ ግጭቶች ነው፡፡ ይሁንና ሰው ከራሱ ጋር የሚፈጥረው ግጭት ከሌሎች ግጭቶች በተለየ መልኩ አካላዊ ፤ ስነ-ልቦናዊና ማኅበራዊ ቀውሶችን እንደሚያስከትል ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ከራስ ጋር የሚፈጠር ግጭት በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አብዛኛውን ድርሻ የሚይዘው ሰው በህይወት ዘመኑ በሚፈጽማቸው ስህተቶች ከህሊናው ጋር የሚፈጥረው ግጭት ነው፡፡
✍ከሌላ ሰው ጋር የሚፈጠር ግጭት (Inter-personal)
በሁለተኛ ደረጃ የሚጠቀሰው የግጭት ዓይነት ከሌላ ሰው ጋር የሚፈጠር የግጭት ዓይነት ሲሆን ይህም በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ ከዋነኛዎቹ የዚህ ግጭት መንስኤዎች መካከል በሃሳብ አለመግባባት ፤ ግትርነት ፤ ነገሮችን በትዕግስት አለማሳለፍ ወዘተ ይጠቀሳሉ፡፡
✍በአንድ ቡድን አባላት መካከል የሚፈጠር (Intra-group)
ይህ የግጭት ዓይነት በግለሰቦች ደረጃ የሚፈጠር ሳይሆን ለአንድ ዓላማ በተመሠረተ ቡድን ውስጥ ባሉ አባላት መካከል ምክንያታዊና ምክንያታዊ ባልሆኑ ጉዳዮች የራስን አቋም በማጣት የሌላውን ሃሳብ ተከትሎ በመሄድና የተዛባ መረጃ በመያዝ ከሌሎች የቡድን አባላት ጋር የሚፈጠር የግጭት ዓይነት ነው፡፡
✍በቡድኖች መካከል የሚፈጠር ግጭት (Inter-group)
የተለያዩ ተግባራትን የሚያከናውኑ ሁለትና ከዚያም በላይ የሆኑ ቡድኖች በሚያገናኟቸው ጉዳዮች ላይ ተስማምተው መስራት ሳይችሉ ሲቀር ወይም አንዱ ሌላውን በበላይነት ማስተዳደር ሲፈልግ የሚፈጠር የግጭት ዓይነት ነው፡፡
በአጠቃላይ ከላይ የጠቀስናቸው የግጭት ዓይነቶች በሚከተሉት ምክንያቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡
*የአመለካከት ልዩነት
*የባህል ፤ አስተዳደግ ፤ የባህርይ ልዩነት
*የዓላማ እና የፍላጎት ልዩነት
*የስልጣን/የኃይል ልዩነት
*እውነታና ፍላጎት አለመስማማት
★የግጭት አፈታት ዘዴዎች
ማንኛውም ዓይነት ግጭት ለማኅበራዊና ስነ-ልቦናዊ ቀውስ ሊዳርግ እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ በመሆኑም በማንኛውም ጊዜ የሚያጋጥሙትን ለግጭት የሚዳርጉ ሁኔታዎችን ከግጭት በራቀ መልኩ የመፍታት ክህሎትን ማዳበር ስኬታማ የሆነ ህይወት ለመምራት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡
ግጭትን በሰላማዊ መልኩ ለመፍታት የሚያስችሉ ነጥቦች
1.የግጭቱን መንስኤ ለይቶ ማወቅ፡–
ግጭቶች በሚፈጠሩበት ጊዜ መንስኤያቸውን ለይቶ ማወቅ ግጭቱ እንዳይባባስ ለማድረግና በቀላሉ መፍትሄ ለማፈላለግ ይረዳል፡፡ ለምሳሌ አንድ ግጭት በሃሳብ አለመግባባት ቢፈጠር ይህ ሁኔታ ሊከሰት የቻለው ተጋጪው ካለው የአስተሳሰብ፤ የባህል ፤ የአስተዳደግ ፤ ወይም ከግለሰቡ የግል ባህርይ የተነሳ ሊሆን እንደሚችል መገንዘብ መቻል ግጭቱን በቀላሉ ለመፍታት ይረዳል፡፡
2.አማራጭ መፍትሄዎችን ማየት
ለተከሰተው የሃሳብ ልዩነት ወይም ግጭት እንደመፍትሄ ሊወሰዱ የሚችሉ አማራጭ መንገዶችን ማየት ግጭትን በቀላሉ ለመፍታት ያስችላል፡፡
3.ስሜታዊነትን ማስወገድ
አብዛኛውን ጊዜ በስሜታዊነት የሚወሰዱ እርምጃዎች ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው የጎላ ነው፡፡
በመሆኑም ግጭት በሚነሳበት ወቅት እራስን ለመቆጣጠር እና ከስሜታዊነት የጸዳ ውሳኔ ለመወሰን ይቻል ዘንድ ግጭቱ ከተነሳበት አካባቢ በመራቅ ረጋ ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡
4.ስምምነት መፍጠር
የተፈጠረውን አጋጣሚ አንስቶ ፊት ለፊት በግልጽ በመነጋገር ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር እንደ አስፈላጊነቱ ሌላ ሦስተኛ አካል ገብቶ የሚያነጋግርበትን መንገድ በመፈለግ ከግጭት ይልቅ ስምምነት የሚፈጥርበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይገባል ፡፡
መልካም ቀን ተመኘሁላችሁ ፤ ሰላም!
©zpsychologist

እራስን ማክበር
www.tg-me.com/psychoet #Share
እውነት ነው እኛ ኢትዩጵያውያን ሰው አክባሪዎች ነን፡፡ግና ሰው ማለት ማን ነው? ሌሎች ሰዎች? ወይስ እኔ እራሴ? እርግጥ ነው አምናለሁ እኛ ኢትዩጵያውያን እንግዳ አክባሪዎች ነን ፤በዕድሜ ጠና ያሉ አባቶችን እና እናቶችን እናከብራለን ከመቀመጫጭን ብድግ ብለን “ኖሩ አባቴ” ብለን ወንበራችን እንለቃለን፡፡አሪፍ ባህል! ባህል እንግዲህ አንጻራዊ አይደል… እዚህ ለፈረንጆቹ ብድግ ብላችሁ ተቀመጡ ብትሏቸው ምላሹ ተቃራኒ ነው፡፡ በእኔ እይታ እንደተረዳሁት ከሆነ አረጋውያንን ለመርዳት ብትሞክሩ ውጤቱ እንደ ሀገራቸን “ተባረኩ“ “ክፉ አይንካችሁ” ሳይሆን ግልምጫ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም መረዳታቸውን ከጥገኝነት ጋር ስለሚያይዙት፡፡ ሁሉም ግን እንደዚህ ያስባሉ ማለት አይለደም፡፡ እንዲያው በዚያው ወግ ቢጤ አሰኝቶኝ ነው እንጅ የዛሬ ትኩረቴስ ሌላ ነው… እነሱም ጥገኝነታቸውን ያባሩ እኛም መልካም ባህላችንን እናበለጽግ፡፡ እንከባበር…ተባረኩ!
ሌሎችን ማፍቀር ከእራስ ማፈቀር ይጀምራል እንደሚባለው፤ ሌሎችን ማክበር እራስን ከማክበር ይጀምራል ብየ አምናለሁ፡፡ እራስን ማክበር ከእራስ ጋር ለመስማማት፤ ስለ እራስ መልካም አመለካከትና ስሜት ለማዳበር መሰረታዊ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌጨው ባለዕዳ አይቀበለውም ይሉ አይደል አበው ሲተርቱ፡፡ ብዙ ጊዜ “እራስ” የሚል ጽንሰ ሃሳብ በጽሁፎቼ በተደጋጋሚ እጠቀማለሁ ምክኒያቱም የሁሉም ፀባይና ባህርይ መጀመሪያ እራሳችን ስለሆን፡፡ ደስ የሚለው ነገር እራሳችሁን ሁሌም ታገኙታላችሁ በቁጥጥራችሁ ውስጥ ስለሆነ መልካሙን አሊያም አሉታዊውን ነገር ማስረጽት ችላላቸሁ፡፡ ስለዚህ ለሚሰማን፣ለምናስበው፣ለምንተገብረውና ለአጠቃላይ ማንነታችን የላቀ ሀላፊነት አለን ማለት ነው፡፡ የችግሩ መንስኤ ሌላ ሰው ነው ብለን ምናምን ከሆነ ግን የቁጥጥር መጠናችን አናሳ ነው፡፡ የምንፈልገውን ለመሆን እራሳችን ላይ እንጀምር…
በአጭር አገላለጽ እራሳችን ማክበር እንለማመድ ምክኒያቱም ከሌሎች ግለሰቦች ጋር በሰላም ለመኖር መከባባር እንደሚያስፈልግ ሁሉ ከእራሳችን ጋር መልካም ግንኑነት ለመፍጠር እራሳችን ማክበር ቀዳሚ ጉዳይ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ወዳጃችሁ በሆነ ባልሆነ በእራሱ ጥፋት ከፍቅረኛው ጋር እየተጋጨ እንደሆነ ቢያማክራችሁ… በአብዛኛው እንዴት እንደዚህ አይነት ጥፋት ታጠፋለህ ብላችሁ አትቆጡትም፡፡ በእርጋታና በአክብሮት ትሰሙታላችሁ እንጅ፡፡ እናንተ ይህ ወዳጃችሁ ያጠፋውን ጥፋት ብትፈጽሙ ከእራሳችሁ ጋር እንዴት ባለ መንፈስ ነው የምትነጋገሩት? በአክብሮት ልክ ሌሎች ግለሰቦችን እንደምታዋዩ ? ወይስ በብስጭትና በቁጣ? ስለማንኛውም ጉዳይ ከእራሳችን ጋር በምንነጋገርበት ጊዜ በአክብሮት መንፈስ ከሆነ ለነገሩ ተገቢ መፍትሄ እንዲሁም በጉዳዩ ምክኒያት የሚሰማንን መጥፎ ስሜት ይቀንሰዋል፡፡ ማድረግ የሌለብንን ነገር ስንፈጽም እራሳችንን በትሁት መንፈስ የማውራታችንን ጥቅም ለመረዳት ቆም ብላችሁ “ይህን የፈጸምኩትን ጉዳይ አከሌ ቢፈጽመው እንዴት ብዬ አዳምጠውና ምክር እለግሰው ነበር?” ብላችሁ ጠይቁ፡፡ ይህ ባልንጀራችሁ ብትበሳጩበት እንዴት ነገሩን እንደሚያባብስበት መረዳት ቀላል ነው፡፡ ስለዚህ እራሳችን በሆነ ባልሆነው የምናመናጭቅ ከሆነ እንደዚሁ ለችግሩ መፍትሄ ከስጠት ይልቅ ሚዛናዊ አስተሳሰባችን በማሳት የበለጠ ችግሩን እናባብሳለን፡፡
ሌሎችን ማክበር እራስን ከማክበር ይጀምራል ! ሰላም!
አሸናፊ ካሳሁን
©zepsychologist