Telegram Web Link
Forwarded from Арбитражница dooradas (የሆነ ቦታ የሚኖር ሰው)
እውነት … እኔኮ ብዙ ጊዜ ደስ አይለኝም … ብዙ ጊዜ ደስ አይለኝም … አብዝቶ ቅር ይለኛል … በሃገሬ በኑሮዬ በህይወቴ በእጣፈንታዬ በእድለቢስነቴ በቤተሰቤ አብዝቶ ቅር ይለኛል … ስጠጋው የሸሸኝ አይኑን ያዞረብኝ አምላኬን ካኮረፍኩት ብዙ ጊዜ ሆኖኛል …
ብዙ ጊዜ ፀልዬ ጆሮ-ዳባ ልበስ ስላለኝ … የምወዳቸውን ከቀማኝ … ቀምቶም ልቤን እያሳዘነኝ አብዝቼ አኮረፍኩት … “የለህማ!” አልኩት …
ብዙ ጊዜ ስለእናቴ ህመም ወተወትኩትና “እሷን ተውልኝ እኔን እንዳሻህ !” ስለው አልሰማህ አለኝና “ብትኖርማ …!” አልኩት
ስስቅ ጊዜ ኩርፊያየን ረስቼ ገና “ተመስገን …!” ብዬ ሳልጨርስ ካሳቀኝ በላይ እያስለቀሰኝ አኮረፍኩት …
የእድሌ መምረር ቢበዘብኝ … ለኤሊው እኔ ከፊቴ የደቀነብኝ የመከራ ተራራ ግማሹ ጋር ሳልደርስ ተንሸራትቼ ከጀመርኩበት ወዲያ ስወድቅ … ትክት አለኝና ለእምነቴ ያሰርኩትን ማህተብ በጥሼ “የለህም በቃ!” ብዬ አኮረፍኩት …
ለመሮጥ ሳልሰንፍ … አቅም ሳያጥረኝ … ደረስኩ ያልኩበት ሲርቀኝ …. ድካሜ ሁሉ መና ሲቀር ክፉኛ አኮረፍኩትና “ትቼሃለሁ ተወኝ!” አልኩት …
ግን … ሰው አይደለሁ ደግሞ !...
በትንሽ ነገር እናቴ ስትበረታ … በልጇ ሳቅ ስትበራ … ለምስጋና ከከፈተችው አንደበቷ ተሸቀዳድሜ ደግሞ “ተመስገን !” እለዋለሁ … ኩርፊያዬን ረስቼ ነውኮ … ከዛ በፊት ስንት ለሊት በብርድልብሴ አፌን አፍኜ አለቀስኩ … ስንቴ እናቱ ድንግል ማርያምን “ልጅሽን ተው በይልኝ !” እያልኩ ተማፀንኳት … የትኛው ለሌቴ ያለእንባ ነጋልኝ… “ቅንጦት አይደለም የምለምንህኮ…. “ እያልኩ ጥርሴን ያልነከስኩበት እለት አልነበረም !...
ደስ ብሎኝ የዋልኩበትን ቀን ረሳሁ … ሳላለቅስ የነጋብኝ ቀን አጣሁ … የህይወቴን ሽንቁር ልደፍን ተስፋ ሰንቄ ላይ ታች ብዬ ስባትል ደግሞ ሌላው ጎኔ ይቦረደሳል … ሞቴን እስኪያስመኘኝ … እረፍት እስኪናፍቀኝ … “ሰበሰብኩ!” ያልኩት ነፋስ እንዳገኘው ዱቄት ይበተናል !... ድክም አለኝ
ድክም አለኝና “የለህም “ አልኩት “ ካለህ ግን በቃ የማትሰጠኝን አሳይተህ አታጓጓኝ … !”
እና ብዙ ጊዜ ደስ አይለኝም ! … አብዝቶ ይከፋኛል ….በራሴ በእድሌ በሃገሬ በቤተሰቤ በፈጣሪዬ አብዝቶ ቅር እያለኝ ይከፋኛል አየህ!
በዚህ ሁሉ የመከፋት እሳት ተለብልቦ ነው ልቤ የጠቆረው !🖤


ዘምሽ የአልግዬ
🖤የጠቆረ ልብ🖤

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
ሰኔ 7 ወይም ሐምሌ 7… ወይም ነሐሴ 7 …ወይም …››
(አሌክስ አብርሃም)
‹‹ግንቦት ሰባት ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ያየኋት !ውስጥ ያለው ጫጫታ
የመጠጥና ሲጋራ ሽታ ስላፈነኝ አየር ለመውሰድ ስወጣ ……በሞቃታማው ምሽት አስረኛ
ፎቅ ላይ ካለው የሆቴሉ ‹ቴራስ › ከፈፍ ላይ ደገፍ ብላ ቁልቁቁል በብርሃን
የተጥለቀለቀችውን ከተማ እየተመለከተች ቁማለች ! …የለበሰችው ቀይ የእራት ልብስ
ጠይምና የተራቆተ ጀርባዋን በግልፅ ያሳያል … ተዓምረኛ ቀራፂ ቀርፆ ጨለማው ውስጥ
ያቆማት ውብ ቅርፅ ትመስል ነበር .....››
ይላል ልቦለዱ ሲጀምር ! 2005 ዓ/ም በአንድ የሬዲዮ ጣቢያ የስነፅሁፍ ፕሮግራም ላይ
እንዲቀርብ የላኩት ልብወለድ … ሊቀርብ አንድ ቀን ሲቀረው አቅራቢው ልጅ ደወለና
…‹‹ግንቦት ሰባት የሚለውን ቀን ካልቀየራችሁት አይቀርብም ብለዋል ለምን
አንቀይረውም ?…. ሰኔ 7 ወይም ሐምሌ 7… ወይም ነሐሴ 7 …ወይም …››
‹‹አይ በቃ ተወው ሌላ ነገር አቅርብ አይቀየርም ›› በቃ ሳይቀርብ ቀረ !
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
የፍፄ ግጥሞች pinned «ሰኔ 7 ወይም ሐምሌ 7… ወይም ነሐሴ 7 …ወይም …›› (አሌክስ አብርሃም) ‹‹ግንቦት ሰባት ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ያየኋት !ውስጥ ያለው ጫጫታ የመጠጥና ሲጋራ ሽታ ስላፈነኝ አየር ለመውሰድ ስወጣ ……በሞቃታማው ምሽት አስረኛ ፎቅ ላይ ካለው የሆቴሉ ‹ቴራስ › ከፈፍ ላይ ደገፍ ብላ ቁልቁቁል በብርሃን የተጥለቀለቀችውን ከተማ እየተመለከተች ቁማለች ! …የለበሰችው ቀይ የእራት ልብስ ጠይምና…»
Audio
አልቦ መጋት


ፀሀፊ ና አንባቢ

✍️ቅዱስ ዓርዮስ✍️
🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋
www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋
www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋
www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
#nomore #ethiopia
ይገርማል!
የነጭ አታላይ ቀማኛ ሀበሻን ሊቀራመተው።
አልገዛም ያለን ጫንቃ
ዘመናዊነት አስታኮ በትርኪምርኪ ሊሰብረው።
ሲያሴር ሲያብር ለዘመናት
የየመንን መራር ፅዋ አፉን ለጉሞ ሊግተው።
ዝም አለ ሀበሻ ታጋሽ ሊታዘብ የማሰብ ጥጉን።
የመራቀቁን ከፍታ የሀያልነት ድንበሩን።
እሱ ግን አርምሞ አልገባው ቁማሩን በኛ ቀመረ።
በይፋ እውነትን ቀብሮ ለሀሰት ቆሞ ዘመረ።
ድህነትን ተንተርሶ ህልውናን መዘበረ።
ምናለ...
ምናለ ታሪክን ቢቃኝ የኋሊት ሄዶ ተጉዞ።
ነጭነት እንደማይሰራ በሀበሻ አፈሙዝ መዞ።
ፋሽሽትን ጠይቅ ይንገርህ የማይጨው ገድል ይናገር።
ደመ ሞቃት ቁጡ ናቸው ሲመጡባቸው በሀገር።
ይናገር ቀስተ ደመናው የሰማይ ማህተም ፊርማ።
ኢትዮጵያ ያነባች እንደው ፀባኦት እንደሚሰማ።
ቃላችን እውነት አዘል ነው ጣልቃ ገብነት ይበቃል።
ሀበሻ ለሆዱ ብሎ ሀገሩን መቼ ይሸጣል?
ይበቃል!!!!
ከ ፍፁም ጥበበ
ለአስተያየት 👉 @ft2194
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
ደሞ እንኩ ዜማ

አንቺማ ለኔ ብርሀኔ


🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
Forwarded from Арбитражница dooradas (የሆነ ቦታ የሚኖር ሰው)
የልጅ ነገር
ቶሎ በስሎ ለመጋገር፣




ሏ.....

ጥሬነቷን አላወቀች
በሀሳብ ላይ
ቡኮ ሀሳብ ለቀለቀች፣

ልምሻ አእምሮ
ልምሻ እጅ እግሯ
ቢደነድን ቢጠነክር
የእናቷን ጡት መጋተሯ፣

እሷነቷስ ወተት
መጋት ተጠይፋ
ጥሬ ስጋ ትሸጣለች
በዓደባባይ ተሰልፋ።

የአፍላ ነገር.........
ቶሎ በስሎ ለመበላት
ተበልቶ አልቆ ለመጋገር።

*******
አዝጎ : የብስል : መሀል : ጥሬ : መሆን። የበሰለው : ወርቀዘቦን :ሲጎናፀፍ: ያልበሰለው :ትድግና : ልብስና ትራሱ የሱ እንደሆኑ : ለመገመት : አያዳግትም።

እህልን: በማጭድ : ገዝግዞ : ጎተራ የሚከምር : ገበሬ : ይመስል አገቦአተውን
እንደህል : ለሚወቁ ወፈሰማይ አንበጦች
ሽቅብ : አንጋጠን : ብናይ : ማጠጣተው
ቁልጭ : ብሎ : ይታይ : ነበር።

እሷም : አንገቷን : ቀና አድርጋ ብታማትር
ቢራቢሮ : በአክናፉ : ነፋስን ሰንጥቆ ሲቀዝፍ : ተመለከተችና: በቀለሙ ተሳበች
የመጣበትን : መንገድም : ቢያሳያት : አባጨጓሬነቱ : ኮሰኮሳት። ህመሙንም : በወርቅ ቅብ ደጉሶት ነበርና... ደመመራራነቱ : ገዘፈባት።
መች :እሱ ቆዳውን : ሊያስወድዳት :ሻተና

እሱ ቋንጣ
እሷ ለንቋንጣ

ሆነው እንጂ!!

✍️ቅዱስ አርዮስ✍️
🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗

🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
ሁሉም ሰው ጂኒየስ ነው!
Super Effect Edited
🎤መክሊት የ16ቷ

#የግጥም_ቃና
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ
Forwarded from Арбитражница dooradas (የሆነ ቦታ የሚኖር ሰው)
ኣሳርፈኝ ወደ ልብህ
ኣ(ሳ)ፍረኝ ወደ ውስጥህ!
ብቅቅንናዬን ግታ .፣ ጥራዝ ነጠቄን ኣጨንግፍ
:
ልቤን በእግሬ ልክ ኣርዝመው
ነፍሴን በቃልህ ዘምዝመው
ነፋስ ወንጭፍህ ያሹረኝ፣የብክነት በለሴን ላርግፍ
:
አውቃለሁ ግብሬን ጠንቅቄ
እንዳይጎድል_ አለማወቄ
ልጠራው እንዳንስ ስምህን
ዐይኔ እንዳይሰማ ስራህን
ጆሮዬ እንዳያይ ድምጽህን!

:
አውቃለሁ ግብሬን ጠንቅቄ
አውቃለሁ ልቤን ጠልቄ¡
እንዳይጎድል አለማወቄ

ማዳንህ ተዐምር ብቻ ነው?
ፍቅርህስ ልኩ ፍቅር ነው?
ድምጽህስ ተስፋ ያክለው?
ብርሃንህን ዐይን ይከልለው?

:
ኣውቃለሁ ኣይሰማም ዐይኔ
ኣምናለሁ ጆሮዬ ኣይይም
በማይጎድል ኣለማወቄ...
መሆንህን መድረሴ ኣይለይም
:
አውቃለሁ ...አውቃለ(ሁ)
ልደርስህ ....
ልቤ ልብ .....የለው!!!
:
:
ቢሆንም......
አለማወቄ ባይጎድልም....
ልጠራህ ከንፈር ሳላቅቅ
ሐሳብ ሳበጥር ስሰልቅ
ቃሌ ከብናኝ ቢቀልም...

ሳልገፋው ያ'ሳብህን ዳገት
ሳልቃኘው የቃልህን ኣንገት
መሳቴን ላ’ርም ስጣደፍ፣ ኩነኔ ቢያርገደግደኝ
ኣውቃለሁ ላይህ ስለፋ
ብቀባህ ቅንጭብ ኣንተርፋ
በደሌ ሲገዘግዝህ፣ ኣብልጠህ እንደምትወደኝ

:
ብቻ ውሰደኝ.....!!!
:

..... ኣሳ’ርፈኝ
ልቤን በልብህ
ነፍሴን በነፍስህ.... እቀፈኝ

ብቻ ኣሳፍረኝ
ብቻ ኣሳ’ፍረኝ.....

:
:
[ቻዎ_ሲኞር....

ዎ....

ዎ ....

ዎ.... ...
(((ግጥም))
©. GI®A

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
Forwarded from Арбитражница dooradas (የሆነ ቦታ የሚኖር ሰው)
««እነሆ_ ሦስት (አራት)_ነጠላ ሐረጋትን_ በኣንድ መርፌ _ ለብዙ ጋቢዎች_...........ዝምዘማ ቁጥር ፪)»»
__________ _________ ____

(፩)

(መስሎን!)
ፉርሻችን ላይ መራቀቁ
ከኩርፊያ ጋር መጣበቁ
ሙላት ላያውቅ
ጸድቶ ላያልቅ -
ዝለት እልፍኝ _መሳት ሳሎን
ሽክርክሮሽ....
ማወቅ ኪሮሽ
ስክርክሮሽ....
ሞት ላይፈታው ፍቅር ብሎን...!!!

(መስሎን!)
ግብብ _ጥል
ስምም_ ግንጥል
ግልብ _ ግ'ምን
ጭምት ዝም'ን_
ዳዴ ክህደት _ልጅ ባቢሎን...!!!

አዎ መስሎን!



(፪)

(ተይ አይበጅም!)

በአድማስ ዘመን
በቃል ተመን
ባለ እድሜው ሰው ኣይዋጅም!

(ተይ አይበጅም!)

ፍቅርሽ ፍቅሬ
የእምነት ቤትሽ ያሳብ ቅጥሬ
በቀን ጉልበት አይደረጅም_በቀን ዝለት አያረጅም

(ተይ አይበጅም!)

ይቅር ይቅር ደማም ጋሜ
የልቤ ኣደስ _ ዝባድ ጣሜ
የክት ቃሌ
ኣመት ‘ባሌ
ጥልፍ አለላ _ ኩል ቀለሜ
ሽቅር_ቅሬ ነፍስ ዓለሜ

ተይ አይበጅም!)
በትናንትሽ በትናንቴ
በቅናትሽ በቅናቴ
ያልተኖረ ነገ ጥሪት የተስፋ ቀን ኣይፈጅም!!!

አዎ አይበጅም!!




(፫)

(ጓደ‘ኝነት!
ጓደኝነት!)

ሁለት መሳይ _...
በአኩል ፊደል
በአቻ ኣጻጻፍ..)
ቋሚ ትርጉም ተመሳሳይ!
ፍጹም ጥምረት
ፍጹም ስምረት
ልበ ዝማድ _ኪዳን ፈታይ!

(፫.1)_(ጓደ‘ኝነት!

በኩር ጀጋን
ደም አፍሶ ቆርጦ ሥጋን
አጋር ማቆም
አገር ማከም
የወቶ' አደር ጀብደኝነት

ጓደ'ኝነት!

አብሮ ዘማች
አፍቅሮ ሟች
ለሰው ላገር
ዋልታ ማገር
ማተብ ኪዳን_ ድጉስ እምነት

ጓድ ወታደር..!

መውደድ ልኩ
ግብር መልኩ
ከአምላክ ተርታ የሚሰደር


፫.2)_ጓደ_ኝነት!

ነውር ከታች
እንባን አባሽ
ውበት አልባሽ
መታያ ጌጥ ከላይ ከታች

ስቆ ኣሳቂ
ባዘን ባሴት ልብ አዋቂ
ምስጢር ሙዳይ ቃል ጠባቂ

ጓደ_ኝነት...!
«ልብህ ልቤ...
ውስጥሽ ውስጤ»
አንቺ በእኔ ባንቺ እኔነት!

በወርቁም ቀን በደንበሾም
ገመና ላይ እስከመሾም
ረቂቅ ስልጣን ታማኝነት

.....እንደሆነ ሲያምን ልቤ...
.....እንደሆነ ልብሽ ሲያውቀው
መታመኔ መታመንሽን
ውጥን ቀኔ ተስፋ ቀንሽን
በእውር ስጋት
ጭፍን ትጋት
ከሞት ባህር ፣ ኣ _ን _ዝ _ፈ _ቀ _ው!!!




፬)==(፩+፪+፫)

መስሎን እንጂ
ልተው እንተው
ተይ አይበጅም

ፉርሻችን ላይ መራቀቁ
ባልኖርነው ቀን
ተ ወ ሽ ቀን
ዛሬን ሳይሄድ መናፈቁ

ለዐይን ኣይጥም
አይዋጥም
ለልብ ኣያምር ኣይጎመጅም!

ተይ አይበጅም!
ልተው እንተው
ጓደ'ኝነት ካልከበረ
ጓደ_ኝነት ካልታፈረ

ልብሽ ልቤን ካላሞቀው
ስሜ ስምሽን ካልናፈቀው
ወፍ እግራችን
የፍቅራችን
በእምነት ዝምዝም ካልታሰረ
የልቤ ኩል
የልብሽ ማይ
ከነፍስ አምባ ካልታቆረ!!!


ካፒቴን (ሕዳር ፳ ፳፻፲፬ ዓ.ም)

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
Audio
እጠብቅሻለው

ኤልያስ ሽታሁን

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
Forwarded from Арбитражница dooradas (የሆነ ቦታ የሚኖር ሰው)
አትየኝ ከፊቷ
ልሽሽ ከሒወቷ

ፍላጎቷ ይስመር
ልውጣ ከሷ መስመር

ልራቅ ከሷ
ጨካኝ ነው ነብሷ
ልራቅ ካንቺ
ከአይሁድ ምትበረቺ ።

ልሽሽ ደሞ
የግራዬ አጥንት
ከወጋኝ ተጋድሞ


ልጓዝ ደሞ
ያቀፍሽኝ ያቀፍኩሽ
ትዝታው ታለፈ
ነፍስን አለምልሞ

ልሙት ደሞ
ቁርባን ንስሀዬን
ባንቺ ተፈትቼ
ነፍስያዬ ፀድቶ
ረጅሙን ብርሀን
ጃሎ አገልድሞ
ላንቺ ልሙት ደሞ

እግዜሩን ጠይቄ

ዕፀ በለሷን ዋጥ

እናማ


አብረን ሙትት



ጆጆ አሌክስ ና ቅዱስ አርዮስ
ፃፉት


።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
Forwarded from Арбитражница dooradas (የሆነ ቦታ የሚኖር ሰው)
ልራቅ ካንቺ
ከአይሁድ ምትበረቺ

ልሽሽ ደሞ
የግራዬ አጥንት ከወጋኝ ተጋድሞ

ተፃፈ
ቅዱስ አርዮስ እና ጆጆ አሌክስ

።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
Forwarded from Арбитражница dooradas (የሆነ ቦታ የሚኖር ሰው)
ሰው እንዴት
በውሸት ይዋባል?

ከቅጥፈት ተጣብቆ
አይን አይኑን ይዃላል?

ነጠብጣብ እንባውን
ድብቅ ገፅታውን
በጣቱ ይቀልማል
ህልሙን ይተልማል፣

ለምን? ቢሉ

እውነት የውሸት ፀበኛ
ውሸት የእውነት'ጓደኛ።

ሆናለችና

እኔስ እውነት አለኝ!
ያንቺን ግን እንጃ......


ጆጆ አሌክስ

ቅዱስ አርዮስ

እንደፃፉት


።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
Forwarded from Арбитражница dooradas (የሆነ ቦታ የሚኖር ሰው)
* እስያ*

አስያ ጨብራሬ
አሰያ ጨብራሪት
ፈንገል ፈንገልጋሊት፣
የዛራማ ጉሪት
የቅኔ ዥንጉርጉሪት፤
የዳመና ቅሪት
ውሽል ውሽልሽሊት፣
በዝናብ ምትመጣ
ዘመን ዘመንማኒት።

ሽው ~ንጥፍ
ንጥፍ ~ሽው ፣
ምታስከጎነብሽው
ከነፍስ የምትደርሽው፣

የሌለሽ ~አምሳያ

እስያ..~.አስያ
ከወዲህና ፣ ወዲያ
አካልሽን ~እየናጥሽው
እያንቀጠቀጥሽው

እየተንጎማለልሽ
እየተፍገመገምሽ
ጅብ ለማይበላው ሰው
ብቻ የተገለጥሽ፣

እየተንጎማለልሽ
ወደፊት ምጭና
ድፍቅ እንደገና፣
ወደኃላ መለስ
ጉሪቱን ማስታወስ፣
ዛርና ፣ ርቢን
ውቃቤን ማወደስ
አስያም እንድትነግስ

ከወገብ ማጎብደድ
ማጎብደድ
ማጎብደድ
ከዛም መንጎራደድ፣
ከቀኝ ወደግራ
አንገት ማንገዳገድ
ከቀልብ ያላረፈ
በእሳት ሊማገድ።

ማጫጫስ~ ሉባንጃ
በከሰል~ ምድጃ፣

ቡንን ~ቡንንንንን
እቴ ባንችው መጀን

ቦለል ~ ቦለለለለል......
ምረቃት ~ልቀበል
ከራማው~ ቁጭ ይበል

ሀዬ ና ተነሳ
ቄጠማ ነስንሳ
ሰንደሉን አጢሳ፣

አቦ! አብሽር መርሀባ
እስያ እንድትገባ
በወረብ ሽብሸባ፣
በጌታው ሙሀባ

ጀማው ~ተሰይሞ
አባ ሊቁም ቆሞ፣

እሱስ የኔ መውደድ
እሱስ የኔ መላ
እሷስ አትጠጣ
እሷስ አትበላ፣
ለነፍስ ነው እንጅ
ለአይንስ አትሞላ

የነፍስያ ~ዘምዘም
ለጥንቡ ~ስጋ ደም!

የምታፍለቀልቅ!
የምታስረቀርቅ!

እስያ....... አስያ.......

ሲደቦሩ ሜዳ
ሱገኙ በጋራ ፣
ሙጋድ ሆና ቀረች
የሱስ ገረገራ።

እምቡር
እምቡር
እምቡር
ከነፍስ ተጣብቆ
ልብ ላይ ለመኖር።

እስያ..... አስያ....

አስያ ጨብራሬ
አሰያ ጨብራሪት
ፈንገል ፈንገልጋሊት፣
የዛራማ ጉሪት
የቅኔ ዥንጉርጉሪት፤
የዳመና ቅሪት
ውሽል ውሽልሽሊት፣
በዝናብ ምትመጣ
ዘመን ዘመንማኒት

እስያ አስያ
እስያ ጨብራሬ
እስያ ጨብራሪት



✍️ቅዱስ አርዮስ✍️
🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗

🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
Forwarded from Арбитражница dooradas (የሆነ ቦታ የሚኖር ሰው)
ነበርኩ እሆናለሁ

ያኔ ራሴን ሳውቀው ነበርኩ በጣም ምለይ
ከጨለማ መሀል ብቻዬን የማበራ ትንሽዬ ፀሀይ
እንደው እሱም ባይሆን ሻማ ነበርኩኝ
ነፋስ መሀል ያለሁ በእኔ ለመጠቀም ሁሉ ሚሻማብኝ
ባይቀለኝም እንኳን እንደውሀ ዝናቡ ባያባራ
የራሴን መንገድ ለመቀየስ ፍፁም የማልፈራ
ጠንካራ እንደደ አንበሳ ግን የማላጓራ
ዛሬ ግን አልቻልኩም ብቻነት በዛና
እሱን ምሰል ተብሎ የተፈጠረው ሰው ወደኔ እስኪያቀና
የተኛው አንበሳ ከተቀበረበት እስከሚል ቀና
ብርድ ብርድ ብሎኛል በቃ እናጫጭሰው በል ወደ ምርቃና

ምሽት 1:35
ህዳር_24/2014 ዓ.ም
ተጻፈ በሰምሀር

🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
🦋🦋 @sufafel 🦋🦋
2025/02/05 22:58:47
Back to Top
HTML Embed Code: