Telegram Web Link
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (Becky Alexander)
ጥቂት ነው ምኞቴ
(በእውቀቱ ስዩም)

እኔ በህይወቴ
ጥቂት ነው ምኞቴ
ከድፍና ከግፍ
የጠዳ
በረንዳ
እዚያ ላይ መቆየት ፥
ከሚደምን ዛፍ ላይ ፥ ቅጠል ሲዘንብ ማየት፤

አኔ በህይወቴ
ጢኖ ነው ምኞቴ
ለከርስ ጤፍ እንጀራ
ለነፍስ ባለንጀራ
ድክመቴን ስናዘዝ ፥ተግቶ ሚያዳምጠኝ
በደሌን መዝኖ ፥ ቀኖና እማይሰጠኝ፤

እኔ በህይወቴ
ጥቂት ነው ምኞቴ
ሊሞላ የቃጣው፥ ደርበብ ያለ ኑሮ
በስዊዝ ቤተ-ንዋይ፥ ሶስት መቶ ሺህ ዩሮ
ደሞ ከተቻለ፥ ቆንጆ ሚስት ወይዘሮ
እግዜርና ሰይጣን ፥ተጋግዘው የሳሏት
ቢቻል ትንሽ ቪላ ፥አስር ክፍሎች ያሏት
ግና ምኞቴ ሆይ ፥ እንዲያው ለመሆኑ
ጥቂት ብሎ ነገር ፥ስንት ነው መጠኑ?

@getem
@getem
@beckyalexander
(ከማለዳ ድባብ)
#ከእንጃ_ባሻገር

ተራራ የሚያህል ፥ ግዙፍ እምነት አለኝ
ለምንድነው ታዲያ
የሰናፍኝን ቅንጣት ፥ በመግፋት ያልተቻለኝ?
እንጃ!

ክሀሳብ የሰነፉ
ሰፊ መንገድ ኖሮኝ ፊቴ የተሰጣ
ከቶ ለመንድን ነው
ለመሔድ መጋፋው ፥ መርገጫ እስከማጣ ?
እንጃ!

በብርሐን ፍጥነት ፥ መፍጠን የምችል ሰው
ለወንድነው ታዲያ
ቀድሜ ወጥቼ ፥ አርፍጄ ምደርሰው ?
ከቶ ለምንድ ነው
ለጥያቄዬ መልስ ፣ እንጃ የማበዛው?
እንጃ !

ከቶ ለምንድን ነው
ለጥያቄዬ መልስ እንጃ የማበዛው?
እንጃ!

እሺ ለምንድነው ?
ነፃ ያደልኩትን ፣ በውድ የምገዛው ?
እንጃ!
ታድያ ለምን ይሆን
መልስ አልባ ጥያቄ የምፈለፍለው?
እንጃ !
እንጃ!
እንጃ!
ብቻ አንድ እውነት አለኝ እንጃ የማልለው
ከሙሉ ነገር ላይ መጉደል ነው ሚጎድለው።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
Forwarded from የፍፄ ግጥሞች (𝘖𝘧𝘧𝘪𝘤𝘪𝘢𝘭 𝘬𝘪𝘥𝘶𝘴 𝘥𝘦𝘳𝘦𝘫𝘦)
መተሽብኝ ነበር :
ለሊት ላይ በህልሜ፣
አቤት ብዬም ነበር :
ስምሽ መስሎኝ ስሜ፣
ግና ሳልጨርሰው :
ፍቅርን አጣጥሜ፣
ፍጥን እንደ ንፋስ :
እጥር እንደ #ጳጉሜ
..............አልሽብኝ አለሜ ።

Yibest Belay
@kidapoim
Forwarded from Hanita 💜
ተጓዡ ልቤ
በየሱስራ ተፅፎ
🎙በሀና አዲስ የቀረበ
ሴት ልጅ እናትህ ህይወትህ ናት መናገርን ባሥተማረችህ አንደበትህ ክፉ ቃል አትናገራት።!!!!!!!!
ፍቅርን ስታነቢ 😭
🎤 አብዲ ዳና
km_20211225-2_360p
<unknown>
ሀገሬን አትንኳት!

ሚካኤል አስጨናቂ

🎙በማርሸት ቀረበ
maal taate
Your recordings
Here is ur Christmas gift
በሒወታችን ውስጥ ትልቁ ፈተና የማንነታችንን ጥያቄ ለራሳችን መመለስ ነው።ብዙዎች እኔ ማነኝ?ብሎ መጠየቅ ያስፈራቸዋል።የማንነታቸውን ጥያቄ አንተውስጥ ያገኙት ይመስል አንተ ማነህ ብለው መጠየቅ ይቀናቸዋል።እኔ ማነኝ ብለህ ጠይቀህ መመለስ በማትችልበት ሁኔታውስጥ እየኖርክ ከሆነ መንቃት አለብህ! አንቺ ማነሽ? ካላቹኝ እኔ ተፈጣሪ ነኝ።

የትኑ ተገኔ
@poemers
መቆያ

ደርግ ከእግዚአብሔር - ሊያጣላን ጥሮ፣
ወያኔ በክልል - በዘር ጠብን ጭሮ።
ለሥልጣን መቆያ - ባዘጋጁት መንገድ፣
የበሉ ነበሩ - በሕዝብ በመነገድ።
አዲሶቹ ደግሞ - ስልጣን ሲጨብጡ፣
መቆያ የሚሆን - ድንቅ ሀሳብ ሲያጡ፣
በሃይማኖት ቢላ - ሊያባሉን ወጡ።

መክብብ
January 11, 2022
🔹ከሀብት ሁሉ ትልቁ ሀብት ልብን መስጠት ነው።

🔹ለሰው የምትሰጠው ትልቁ ስጦታ ራስህን ነው።

🔹ሀገር እንዳትጠፍ ትልቅ ነገርን አታጥፍ።

🔸ሕይወት ሁለት ጎን አላት ማግኘት እና ማጣት ፣ማጣትም በራሱ ሁለት ጎን አለው የምታገኘውን ነገር ማጣት እና የማታገኘውን ነገር ማጣት።

🔹 ሀብታሞች የተፈጥሮን ሕግ ሰብራችኃል። በሚሰራበት ሰዓት ትሰራላችሁ በሚተኛበትም ሰዓት ትሰራላችሁ። ምነው ስትባሉ ድህነትን ለማጥፍት 24 ሰዓት እንሰራለን ትላላችሁ ። ድህነትንስ ታሸንፉታላችሁ ሳታውቁት ግን ለውስጣችሁ ሰላምና እና ደስታ ትሸነፉላችሁ።

🔹ጭቃው በሸክላ ሰሪው እጅ ላይ ነው ሰው በአምላኩ እጅ ላይ ነው እንደወደደ አድርጎ የሚሰራው ፈጣሪ ነው።እኛ ማድረግ ያልቻልነውን ፈጣሪ ያደርግልናል ።

🔸ይቅርታ ልጠይቃት ይገባል እኛኮ ምንም አላደረግንም. እሷን መሰላታ..።

🔹ሠማይና ምድር የቆመው በቃል ነው።ያ ቃል ለኛ ጥበብን ይሰጠናል ልክ ለነዚህ እጆች እንደተሰጡት.አብዬ ከዚህ በኅላ ጥበብ ከሰጠህ ጋር አትታገል እርሱ እራሱ አንድያ ልጁን ሰጥቶናልና።

🔹 ትክክለኛ ማሸነፍ በሰው ዘንድ የእራስን አመለካከት ማጋባት ነው። ከተጣላህ ወይም ከሸሸህ አንተ ተሸንፈሀል ከራስህም ከሰውም ጋር ተጣልተኃል ።አንተ እራስህን ለፍቅር ብታዋርድ አንተ ከፍ ከፍ ትላለህ ስለዚህ ትንሽ አቀርቅር።

🔸 ጥሩ በልክ አይመዘንም ፣ ልክ ነው በጥሩ የሚመዘነው።

🔹ተፈጥሮን በተቃውምን ቁጥር፣ ስልጣኔ ባበዛን ቁጥር፣ ችግራችን ይበዛል ችግራችን ደግሞ የምንወዳቸውን ነገሮች ያሳጣናል።

🔸አምላክህን ደስታህን በቅንነት ብትጠይቀው ይሰጥሀል። ብቻ በቤትህ በሀቀኝነት ኑር።

🔹ተስፍን የሰጠ የታመነ ነው።

ከረቡኒ ፊልም

ውብ አሁን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
efrem
<unknown>
┄┉┉✽̶»̶̥🎶••✿••🎶»̶̥✽̶┉┉┄
መረዋ ድምፆች
@poemers
┄┉┉✽̶»̶̥🎶••✿••🎶»̶̥✽̶┉┉┄
ዘር ትሁን!
""""""""""""""
አንድ የራስህ ምስል...
በእልፍ የሴት ማህፀን ቢራባ ቢባዛ፣
ምን ይሰራል መውለድ?
የተፈጥሮ ሳቅ ላይ መከራ ካዋዛ?

የተዘራው ሁሉ ለመብል አይበቅልም፣
ከተኛኻት ሁሉ ሰው አይታነፅም!

ፍቅር ሲነካው ነው የሴት ልጅ ገላዋ፣
ዘርህ የሚበዛ እንደ ምድር አሸዋ!


አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)
ቀረሽ እንደዋዛ
•┈┈•✦•┈┈•
ትመጫለሽ ብዬ ደቂቃ ስ ቆጥር
ትመጫለሽ ብዬ ሰዓቱን ስቆጥር
ትመጫለሽ ብዬ ባዝን ባንጎራጉር
ትወጫለሽ ብዬ በበራፍሽ ብዞር
ብርድ አቆራመደኝ
የመንገድ መብራቶች አይተው አፌዙብኝ
ውርጩ ቀለደብኝ
ጨለማው ሳቀብኝ።
አለመምጣትሽን
አውቀዋል ያውቃሉ
መስኮቶች ጨልመው
ቤቶች ተቆልፈው
ከተማው ሲተኛ
አይተዋል ያያሉ
አለመምጣትሽን
አውቀዋል ያውቃሉ።
-------------------------------

©ገብረክርስቶስ ደስታ
@yegxmrizort
@yegxmrizort
የክፋትህ ብዛት የበደልህ ጥጉ
ማንም የማይተካው ማይገጥም ወጉ፤
ከከፍታ በላይ ከልቤ ጫፍ ጥጉ
ከነፍሴ አስበልጬ ስወድህ ስወድህ፤
አንተ ግን የዳኘችን ጨረቃን ረስተህ ተገኘህ
ባንተ መራቅ መሄድ መከፍቴን ሲያውቀው፤
አይኔም የእምባ ናዳ ጎርፉን አዘነበው፤
ባንተ መራቅ መሄድ አእዋፍ አዝነዋል፤
አንበርም በሰማይ አንታይ ብለዋል
ባንተ መራቅ መሄድ ጨረቃም በሽቃለች ከበፊት ውበትዋ አሁን ደብዝዛለች፤
ባንተ መራቅ መሄድ ፀሀይም በሽቃለች ከበፊት ጉልበቷ አሁን ጠንክራለች፤
እሷ ካለችበት አልበርድም ብላለች
አሁን ግን ያዘነው ትልቁ ሰማይ ነው
ያንተን መራቅ መሔድ መከፋቴን ሲያዉቀዉ ፤
እኔን ያሳርፈኝ ትልቁን እምባውን ዝናቡን ሲጥል ነው።
አትምጪ…
ደስ አይልም ሰፈሩ
ደማም የነበረ ደም ለምዷል አፈሩ።

ምን አሳይሻለሁ?
እንባ የጀመረው ቀን ተገፍቶ አለቀ
"ፀሐይ ስጠልቅ አየሽ"
ብዬ አላሳይሽም ሰው እየጠለቀ።

አትምጪ…
መንገዱ እንደ ድሮው አያረማምድም
አስቦ አያመጣም አስቦ ቢወስድም።
(ይኼው መቼለታ
ይኼን ግጥም ላንቺ ለመላክ ወጥቼ
አንዳች መንገድ ላይ ነኝ መመለሻ አጥቼ።)

አትምጪ…
ብትመጪስ የት ብለሽ? ብትመጪስ ምን አለ?
የሚታይ አይኖርም የሚታይ ላከለ።
ብትመጪስ እማን ጋር? ብትመጪስ ማን አምነሽ?
ምታልፊውን ኹሉ
ታሳንሺው የለ እንኳን ተሽሞንሙነሽ!?
ሽሙንሙን ሽሙንሙን
ራስ ተሰውሮ
አትምጪ ማለትን ምን ይሉታል ስሙን?

ግዴለም አትምጪ…
ምን እነግርሻለሁ?
ምነግርሽስ ቢኖር እንባ ላይ ይቀራል
ይጓዙታል እንጂ መንገድ መች ይወራል።
(መድረስ አደከመኝ
ብርቱ የነበረው ጉልበቴ ደቀቀ
ሩቅ የሚያስጉዘው አፍ ላይ እያለቀ።)

ምን እነግርሻለሁ?
ንግግሬ ሟሟ ልሳኔ ኮሰሰ
የዙሪያዬ መልኩ
እንኳንስ ለጆሮሽ ለምላሴ አነሰ።
ቃል ጠፋኝ መስፈሪያ
ድምፅ አጣሁ መንገሪያ
እንኳን አንቺ መተሽ ሀሳቤ ሊረዝም
አሁን ለብቻዬ እኔም ዝም ልቤም ዝም!

ግዴለም አትምጪ…
ግፊያ ነው ሰፈሩ
ኹሉ እየተጋዘ ወዳለማፈሩ።
(የቀዬው የሀገሩ
ውበትና መልኩ በቃል ቢሰፈርም
የሚነገር ማጣት
የሚያሳዩት ማጣት ይኼ አያሳፍርም? )

ምን አሳይሻለሁ?
ወፍ መዝሙር ተነጥቆ
ወፎቹ መንቆር ላይ ሙሾ በቀለበት
"ፀሐይ ስትወጣ አየሽ"
ብዬ አላሳይሽም
(የመሬቱን ተዪው)
የጋራ መኖሪያ ሰማይ በሌለበት።

ደግሞ ብትመጪስ…
የሚወጣ ጮራ የሚጠልቅ ጀምበር
ምን አሳይሻለሁ ከራስሽ በስተቀር።

(ያዴል ትዕዛዙ)

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
በ1971 አንድ ዕለት ሻ/ል አፈወርቅ ዮሐንስ “ውበትሽ ይደነቃል” በሚል ርዕስ የጻፉትን ግጥም እንደ ልጃቸው ለሚያዩት ለጥላሁን ሰጡት፡፡ ግጥሙን ሲሰጡት በግጥሙ ውስጥ ያሠፈሩትን እምቅ ስሜት ጥላሁን እንዳይስተው በመሻት፣ “ለኢትዮጵያችን ነው የጻፍሁት" ብለው ነገሩት፡፡ ጥላሁን በሻምበል ግጥም ውስጥ ያለውን የቁጭት፣ የቁጣ እና የእልህ ስሜት ከደሙ ጋር አዋህዶ የተሰጥዖውን ጫፍ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ አስገራሚ ዜማ ሠርቶለት በፍቅር ተጫወተው፡፡

'ፍቅሬ ሆይ ልንገርሽ ... ምንም ይሁን ምንም
እዚህ ቦታ ቀራት ... ቢሉኝ እኔ አላምንም፤
የልቤን ልግለፀው ... ዕውነት በሆነ ቃል
ተፈጥሮሽ ፍፁም ነው ... ውበትሽ ይደነቃል፡፡
ፍቅሬ ሆይ ልንገርሽ፣ እኔ እምፈልገው
በክፉ የሚያይሽን፣ እንዳያይ ያድርገው
እንደጠፋ እሳት ነው እንደተዳፈነ
ውበትሽን እያየ፣ ዓይኑን የጨፈነ፡፡
ቁም ነገርሽን ዓይቶ፣ የማያደንቅ ሰው
በግልፅ ያስታውቃል፣ ችሎታ እንዳነሰው
የጠላሽ ይጠላ፣ ብድሩ ይድረሰው
የጎዳሽ ይጎዳ፣ ተፈጥሮ ትውቀሰው፡፡
በከንቱ የሚያማሽ፣ ስምሽን የሚያነሳ
ክፉ በመሆኑ፣ አለበት ወቀሳ፤
መንገድሽን የዘጋ፣ በቅናት ተውጦ
ፀፀት ያንብግበው፣ ይኑር ተበጥብጦ፡፡'

የጥላሁን አድናቂዎችና የሙዚቃ ባለሙያዎችም ጭምር፣ ጥላሁን ካዜማቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ዘፈኖች “በላጩ የትኛው ነው?” ሲባሉ አንድ ብቻ ዘፈን ለመምረጥ ይቸገራሉ፡፡ አብዛኞቹ ግን ቢያንስ በአንድ ነጥብ ላይ ይስማማሉ - የምርጦች ምርጥ ከሚሰኙ የጥላሁን ዘፈኖች አንዱ “ውበትሽ ይደነቃል” ነው፡፡ የግጥሙ ደራሲ ሻምበል አፈወርቅ ግን “ውበትሽ ይደነቃል” እንዲያ በሚያስደንቅ የድምጽ አወጣጥ ጥበብ በጥላሁን ሲዜም ለማዳመጥ አልታደሉም፡፡

© ጥላሁን ገሠሠ የሕይወቱ ታሪክና ምሥጢር በዘከሪያ መሐመድ ገፅ፥ 147

@poemers
Audio
" ጥልቅ ሀዘን ማለት ማዘን ሲያቅት ነው።ማዘን መልካም ነው፣መኖር ነው፣የህይወት ምልክት ነው። ህይወት ያለው ሁሉ ያዝናል። ማዘን አለመቻል ግን ከሞት ይከፋል።ሰው በመጀመሪያ ስሜት ነው፣ሌላው ሁሉ ተከታይ ነው።ሰው ስሜቱን ካጣ ጎዶሎ ነው።"

አለማወቅ
ዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝ
ጥያቄ
"""""""""""""""
ለሰላም መዘመር
እምነቴ ነው ላለኝ
ለዛ ባለ ጦማር
ጥያቄ ነበረኝ።
የተናገርከው ቃል
ፅንፍ እውነት ካለበት
ብዕር ይጣላል ወይ
ጠመንጃ ለማንገት

ብላችሁ በሉልኝ።

ቤተልሔም አባይ(ሰንፔር)ፋና ብዕር
2024/06/18 12:16:22
Back to Top
HTML Embed Code: