Telegram Web Link
የቦሌ የመንገድ አበባ መጥፋት የሚያሳስበው መሪ የዜጎች ህይወት መጥፋት እና ንብረት መውደም ስለምን አያሳስበውም?!(አልሰማም ይሆናል )

እባካችሁ እስኪ ሼር አድርጉት
#ሼርርርርር
@belaybekeleweyaa
@poemers
Audio
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
Share plzzz🙏🙏
@yehangetem
@poemers
እንኳን አደረሳቹ - ሆሳዕና በአርያም

𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐔𝐬 @poemers
#ህማማት(፪)

ሰኞ የተገረፉት ለአርብ ቂም አዝለው
ሲሉ ተሰምተዋል ስቀለው ስቀለው

ብላቴናው

@poemers
የሐሙስን-ቅኔ



ሲያሳሳቸው ጊዜ ነገውን ሊሰቅሉት
ሮብ ርቧቸው አስቀድመው በሉት
ስቀለው ስቀለው ስቀለው ይላሉ
ጠርጴዛ ከበው ከጁ እንዳልበሉ

አጠገበው ህብስት አሰከረው ወይኑ?
በ3ተኛው ጩኸት ተገለጠን አይኑ
የፋሲካ ቂጣ ስንዴው ምን ምን አለክ?
ሰው ሰው ይላልን ወይስ አምላክ አምላክ?

ከየት በላህ ስጋ ደምስ ከምኑላይ
ከ'ኔ ትለፍ ብሎ በጽኑ ሲጸልይ
ጽዋ ነበረ ወይ የተራራው ድንጋይ
የወዝ ደም የሞላው የጠጣችሁት ማይ

የፋሲካው ወይን ምን ምን አለክ ደሙ?
የልጅ የልጅ ነውን? ያባት ያባት ጣ'ሙ
ስትቀባበሉት ስትቆርሱ ያየች ለታ
ልጄን ልጄን ነውን? አባቴን አባቴን
የናቲቱ ዋይታ?

ሃሙስ ጾሜን ልዋል አልፈልግም ንፍሮ
አርብ ስጋ አለልኝ ህዝብ ያልበላው አፍሮ
እጅ እጅ ይላል ምነ እማ ያነፈርሽው
የአይሁድን ሞያ መቼ በቀመስሽው

ምንአስቦ ይሆን በ ባዶ እሚለፋ
ቅጭጭት ከግራቸው ባጠባ ላይጠፋ።
አለም ለረገጣት እድፍ ነው ምንጣፏ
ላዘላት ነው እንጂ የሚበራ ጧፏ።



°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
መልካም ምሴተ ሃሙስ ይሁንልን
******************
tomi

(Toma's tigistu)

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poemers
@poemers
እንኳን ለ ብርነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳቹ በዓሉን የሰላም የፍቅር የመተሳሰብ እንዲሁም ከሌላቸው ጋር የምንካፈልበት ያድርግልን።

@poemers
"""""አይገባሽም ወይ"""""

በፍቅርሽ መምከኔ እንዲህ መንገብገቤ
ሳቶጂኝ ወድጄሽ ሳይገባሽ ክቤ
ሳላይሽ ከዋልኩኝ እኔን አደለሁም
ላንቺ ማዳላቴን እኔም አላመንኩም
እባክሽን ፍቅሬ...
እባክሽን ፍቅሬ ልንገርሽ አድምጪኝ
ባትመልሽልኝም ላፍታ ጆሮ ስጪኝ
ይኸውልሽ ፍቅሬ...
እኔን ለመረዳት አንዴ እንኳን ሞክሪ
ፍቅርን አስተማሪ ላይገኝ መካሪ
ቃላት ካልተመቸሽ በምልክት አውሪ
ዝምታሽ አወከኝ
ጤናዬን አስረሳኝ
እባክሽን አውሪ
አጠብቂ ጥሪ
እኔ ያንቺን ባላቅም
ምላሽ አልጠብቅም
ፍቅሬን ሳልገልፅልሽ
የውስጤን ሳልነግርሽ
እሺ ይሄን ስሚኝ...
አ-አፍሬ ባላይሽ
ፈ-ፈርቼ ብርቅሽ
ቅ-ቅናት አሸነፈኝ
ር-ርዕስም ጠፍብኝ
ሻ-ሻማውን አጥፍቼ
ለ-ለውጥ ለማምጣቴ
ው-ውዬ ለማደሬ
ምክንያቴ አንቺው ነሽ
ብቻ አላብዛብሽ
አንቺን አረብሽሽ
ግጥሙም ይቅርብኝ
ቤቱ ላይመታልኝ
ብቻ ምን ልበልሽ..
ላቶጂኝ ወደድኩሽ
ላትመጪም ጠበኩሽ
ላትረጂኝ ነገር ዝም ብዬ አፈቀርኩሽ❤️



ግጥም -በፍቅርተ
ቀን-25/08/2013
ከዝዋይ
@poemers
@poemers
"""""ተውኩት """""
አስቢበት ብዬ ብዙ ቀን ነገርኩሽ
እንደማይሆን ሳውቀው ቀድሜ ሸሸሁሽ

ቀድመሽ_ሳታስቢው
ቀድሜሽ_አስቤው
አስቤ_አስቤ...
አስቤ ሲደክመኝ
ካንቺ የተሻለች ቆንጆዋን መረጥኩኝ
በሚገርም ሁኔታ ካንቺ ትበልጣለች
በፀባይ በመልክም ቁመት ትረዝማለች
ፀጉሯ ልስላሴው ሀርንም ያስንቃል
የአይኗ ትልቀትም ከፖውዛ ይበልጣል
የወገቧ ቅጥነት ከስምንት ይብሳል
ዳሌዋም ሰፊ ነው ሁሉን አድሏታል
ታዲያ ምን ያደርጋል ፀባዩን ነስቷታል

ብቻ ብዙ ነገር...
አንቺ ምትለይው
ከውበትሽ ይልቅ ፀባይሽ ይደንቃል
እሷ ፀባይ የላት ውበት በዝቶባታል

ሁሉን ነገር ተይው
አስቢው ያልኩሽን እኔ አስቤዋለው
አሰብሽ አላሰብሽም እኔ ትቼዋለሁ 🙈


ግጥም_በፍቅርተ
ቀን_25/08/2013
@poemers
@poemers
ክብር ሊሞቱልን ቀርቶ ሊታመሙልን ለማይገባን ለእኛ ውድ ህይወታቸውን ገብረው ሀገር ላቆዩልን ሁሉ!!! መልካም የአርበኞች ቀን!

#ሼርርርርርርርርር

@belaybekeleweyaa
@poemers
#ግጥም

በናፍቆትሽ እሳት ነድጄ ሳልከስም
በዓይንሽ በጠረንሽ መልሼ እንዳገግም፤
ዛሬም እኖራለሁ ስኖር ስደጋግም
ካለሁበት ድረስ እግርሸ እንዲረዝም፤
ልምጣ ያልሽ እንደሆን ቀና ነዉ ጎዳናዉ
ልቤ ተመላልሶ ደልድሎታልና!

ምኞቱ የማይደክመዉ ልቤ ልበ ብርቱ
ትዝታም አይደለም ተስፋ ነዉ ቅኝቱ።

ትመጪ እንደሁ?🤔

••●◉Join us share◉●••
@poemers @poemers
የነገረሽ ሳይኖር
"እና እንደነገርኩሽ"
ብሎ የሚጀምር-ዝርክርክ ገጣሚ
ውዴ --እንዳትሰሚ።

ዝንጋኤ አነባሮት፣
መርሳት ተጠናውቶት፣
"ምን ልልሽ ነበረ?"
ብሎ ከቀጠለ፣
ቀድሞም ዉል አጥቷል-አሁን ነገር አለ።

እቴ እኔ ልንገርሽ!
ዘመንሽን አትፍጂ-በሆነዉ ባልሆነው፣
ነይ ሁሉንም ትተሽ-እገጥምልሻለሁ።😂😂

ዘነበ--ሞላ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@poemers
አባቶች እናቶች
በፍቅር ተጋግዘው ፣ ያቆሙልን እውነት
በዘመን ጠልሽቶ...
ለእኛ ለልጆች ፣ ይመስለናል ተረት፡፡
።።።።።።
የኛ ትልቅ ችግር ፣ የኛ ትልቅ ህመም
"ተረት ተረት"ሲባል
መሰረት ሳንይዝ
"የመሰረት" ብሎ ፣" እሺ" እያሉ ማዝገም፡፡
።።።።።።፣
ተረት ተረት
"የመሰረት"
አንድ ሀገር ነበረች
"እሺ"
እምነትን ከፍቅር ፣ ገምዳ ያስተማረች፡፡
"እሺ"
አናም በዚች ሀገር...
ሙስሊሞች በእምነት ፣ መስጅድ ሲገነቡ
ክርስቲያኖች በፍቅር...
ይታዩ ነበረ ፣ ምሶሶ ሲያቀርቡ፡፡
"እሺ"
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እናም በዚች ሀገር...
ክርስቲያኖች በምነት ፣ ቤተስኪያን ሲያንፁ
ሙስሊሞች በፍቅር...
ይታዩ ነበረ ፣ ጉልላት ሲቀርፁ፡፡
"እሺ"
እናም በዚ መልኩ ፣ ሲኖሩ ሰኖሩ
እንደተዋደዱ እንደተፋቀሩ
እንደተጋገዙ እንደተባበሩ
መሰረት እንድናይ...
አንዋር ከራጉኤል ፣ ተጎራብተው ቀሩ
"እሺ"
"እሺ" ማለት ጥሩ
መሰረት ሳይዙ ...
የመሰረት ብሎ ፣ መኖር ነው ችግሩ!!!
#ሼርርርርርርርርር
#በላይ በቀለ ወያ

@poemers
@poemers @poemers
"""የኔንም ፍችልኝ"""

ፆም ትፈቻለሽ አሉ : እኔን እያሰርሽኝ ፣
እውነት ጿሚ ከሆንሽ : ከፆማቹ በፊት፣
በሂጃብ ቀሚስሽ : ተገምዶ የቀረውን፣
ቀን ተቆጥሮለት የማይፈታውን፣
ፍቅርሽን ፍችልኝ☺️

ሀይልአብ

@poemers @poemers
@poemers
ሮፍናን_-_ሦሥት_III_ROPHNAN_-_SOST(128k)
<unknown>
New: Rophnan
የነሱን አድዋ ብናሸንፍም
የኛን አድዋ ተሸንፈናል

@poemers @poemers
ዋስ ያጣ ዝምታ
ገጣሚ እና አቅራቢ ሀና አዲስ
@yehangetem
ክፉም ንጉስ መጣ
ደግም ንጉስ መጣ
ብቻ ግን ያልፋሉ ፣ ሁሉም እንደመልኩ
ይብላኝ ከህዝብ ጋር
ለሚጣሉ ህዝቦች ፣ መሪ እያመለኩ !!!


በላይ በቀለ ወያ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poemers
ኤፍሬም ስዩም
አቅራቢ ሀይልአብ

@poemers @poemers
ግጥም-በእኛ 💌 pinned «ክፉም ንጉስ መጣ ደግም ንጉስ መጣ ብቻ ግን ያልፋሉ ፣ ሁሉም እንደመልኩ ይብላኝ ከህዝብ ጋር ለሚጣሉ ህዝቦች ፣ መሪ እያመለኩ !!! በላይ በቀለ ወያ ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ @poemers»
ሳይሽ ደስ ዪለኛል
ተርቦ እንደመብላት ሰው ናፍቆ እንደማግኘት ሳይሽ ደስ ዪለኛል
አምናና ታች አምና ያፈቀረሽ ልቤ እንዲህ በል ዪለኛል
ሂድና ጥራልኝ ፍቅሬን ግለጽልኝ፣ ባታወራት እንኳን አይን አይኗን እይልኝ፣
ብሎ ቢያስጨንቀኝ...
አንችኑ ወዳጁን ፍለጋ ደጅ ደጁን ማተርኩኝ፤
በለስ ቀንቶኝ ሀባሲያው ዘልቄ ቋጥኝ ተሸሽጌ ፣
ስመለከት ኖሮ ሀተራራው ግርጌ፣
ባባትሽ አሽከሮች ዙሪያሽን ትጅበሽ ስትዘልቂ አየሁሽ።

በኔ አይን ስትታዪ፤ የዉበትሽ ፍካት ጨረቃን ያስንቃል
የ ፈገግታሽ ብርሃን ከጸሃይ ዪሞቃል፣ እዉር ያስቦርቃል፣
የተከዝሽ ጊዜ ጋሞራ ዪበርዳል፣ ጸሃይ ትጠፋለች፣
ጨረቃም ከማጀት ገብታ ትቀራለች።
አዎ ዉዴ ያላየሁሽ ጊዜ ዪጠናወተኛል
ልቤ አላፊ አግዳሚውን ፍጥረቱን በሞላ ባንቺነት ዪመኛል
እያንዳንዷን ኮቴ የሷ ነው ዪለኛል
አንቺን በመማተር ሺህ ዜማ ዪቀኛል።
ባንጻሩ ስትመጪ፣ አፌ ምን ቢለግም
የልቤን ፈንጠዝያ የሚገዳደረው አንዳች ስሜት የለም
እናልሽ አለሜ ሃዘንሽ ሃዘኔ፤ ሳቅሽ ሳቄ ሁኖ ዪተናነቀኛል
ሁልጊዜ ሳቂልኝ ደስ ብሎሽ ሳይሽ ዪበልጥ ደስ ዪለኛል።

ገጣሚ : የሱፍ

@poemers @poemers
2024/06/29 12:22:29
Back to Top
HTML Embed Code: