Telegram Web Link
Time መጽሔት በልዩ እትሙ "የአእላፋት ዝማሬ"ን ምስል አወጣ

| ጃንደረባው ሚድያ | ኅዳር 2017 ዓ.ም. |

በአሜሪካን ሀገር ኒውዮርክ የሚታተመውና ከ1923 ዓ.ም. ጀምሮ ኅትመቱ ያልቆመው 105 ሚልዮን አንባቢያን ባሉት ቁጥር አንዱ "Time” መጽሔት የኢትዮጵያን የገና በዓል በማስመልከት በጻፈበት አንቀጽ የአእላፋት ዝማሬን ከፊል ገጽታ በውስጥ ገጹ ላይ አካትቶአል:: "Jesus” በሚል ዐቢይ ርእስ የታተመው የ2024 ዓ.ም. የመጽሔቱ ልዩ ዕትም ላይ "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በታኅሣሥ 27 (January 6, 2024) በገና ቅዳሴ ላይ ሲካፈሉ በማለት የአእላፋት ዝማሬ ላይ ጧፍ ይዘው እየዘመሩ የነበሩ ምእመናንን ይዞ ወጥቶአል::

"መጽሔቱ የአእላፋት ዝማሬን ገጽታ ይዞ መውጣቱ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የቀረበ የሚታይ ማስታወቂያ መሆኑ ደስ ይለናል" ያሉት የአእላፋት ዝማሬ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ወ/ሮ ቤርሳቤሕ ደረጄ "ሆኖም መጽሔቱ ዝማሬውን "ቅዳሴ ሲያስቀድሱ" ብሎ መግለጹ በቅዳሴ ላይ ምእመናን መብራት ይዘው የሚሳተፉበት ሥርዓት የሌለ ከመሆኑ አንጻር ዘግባውን ያጎድለዋል ብለዋል::

በዘገባው ላይ ታይም መጽሔት "የኢትዮጵያ ስድሳ በመቶ የሚሆን ሕዝብ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ነው" ሲል የገለጸ ሲሆን "ከራሽያ ቀጥሎ የዓለም ትልቁ ኦርቶዶክስ ሕዝብ ቁጥር ያለባት ሀገር ናት" ብሎአል:: በ2024 ጃንዋሪ 6 የተካሔደውን የአእላፋት ዝማሬ በመስቀል አደባባይ እንደተካሔደ አድርጎ ቢገልጸውም በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም የተካሔደ መሆኑ ይታወሳል:: የዘንድሮው የአእላፋት ዝማሬ በመሐረነ አብ ዑደት እና በመዝሙር ጥናት ከጾመ ነቢያት ጋር አብሮ እንደሚጀመር የኢጃት ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ኢየሩሳሌም ዳግማዊት ገልጸዋል::

ለመቀላቀል
👉 @ortodoxtewahedo
Audio
ታላላቅ ሥራን አድርጎልኛልና 
                                                  
Size:- 102MB
Length:-1:33:17
       
     በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
እንጦጦ መንበረ ንግስት ቁስቋም ማርያም አዲስ አበባ ።

እንኳን ለእናታችን ለደብረ ቁስቋም ዓመታዊ በዓል በሰላም በጤና አደረሰን!

ዮም ጸለሉ መላእክት ላዕለ ማርያም ወላዕለ ወልዳ
ክርስቶስ በደብረ ቁስቋም(2)
እንዘይብሉ ስብሐት ስብሐት በአርያም ስብሐት በአርያም(2)

#ትርጉም

ዛሬ መላእክት በማርያምና በልጇ በክርስቶስ ላይ በደብረ
ቁስቋም ጸለሉ እንደዚህ አሉ ምስጋና በሰማይ ።

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
#ህዳር 6

#ቁስቋም ማርያም

"አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ፤እናይሽ ዘንድ ተመለሽ" መኋ 7፥1

ጠቢብ ሶሎሞን እመቤታችንን ከጠራበት ከገለፀበት ቃላት አንዱ ሱላማጢስ የሚል ነው ጠቢብ እንደ ነብይነቱ ስለ ንጽሕናዋ፣ስለ ድንግልናዋ፣ስለ ትህትናዋ..... እንደተናገረ ሁሉ ድንግል ማርያም ፍቅር ያላት ፍቅር በቃል ኪዳኗ አማልዳ የምታሰጥ ሰላማዊት መሆኗን ሲገልፅ ሱላማጢስ ብሏታል።

እመቤታችን ብዙ መከራ ካየችበት ብዙ መከራንም ከተቀበለችበት ከዚያ የግብጽ በረሃ የመመለሷን ነገር ሶሎሞን በትንቢት መነፅርነት ተመልክቶ ተመለሽ ሲላት እንመለከታለን የእመቤታችን የመከራዋ ጊዜ ሲፈፀም የህፃኑን ነፍስ የሚሻው ሄሮርስ በሞተ ግዜ (ማቴ 2፥19)እመቤታችን ከስደት ተመልሳለች።

የእመቤታችን የስደት ወቅት ሊቃውንቱ እንደሚነግሩን 3 አመት ከ6ወር ነው ይህ ግዜ ሲፈፀም ህዳር 6 ድንግል ማርያም ስደቷን ጨርሳ ተመልሳለች የነብዪ ሆሴዕ ቃልም ተፈጽሟል (ሆሴ 11፥1)::

አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሙሉ ሰላም ላጣ ለአዳም ሰላም የሆነች "ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር" ተብሎ እንዲመሰገን ምክንያት የሆነች የሰላም እናት የሰላም እመቤት ድንግል ማርያም (ሱላማጢስ) ከስደት ተመልሳለች።

ዛሬ በኋጥያት ስደት ያለን ብዙዎች ነን የሰራነው ኋጢአት ከእግዚአብሔር ፊት ከቤተክርስቲያን ደጅ ያሰደደን ብዙዎች ነን።

ዛሬ በትዕቢት ልብ ተይዘን ትላንት ካስቀደስንባት፣ከቆረብንባት፣ከቀደስንባት፣ከተማርንባት፣ካስተማርንት ደጅ የተሰደድን ብዙዎች ነን ሚጠታችን መቼ ይሆን።

ከስጋወደሙ የተሰደድን ከልጅነት ግዜያችን በኋላ፣ከትዳራችን በኋላ ከአገልግሎታችን በኋላ ሥጋ ወደሙን መቀበል ያቆምን ከሕይወት ምግብ የተሠደድን ሥጋችን እየደለበ ነፍሳችን ከህይወት ምግብ እጥረት የቀጨጨችብን ሚጠታችን መቼ ይሆን???

ከአገልግሎቱ የተሰደድን ትላንት እንዘምር፣ትላንት እንማር ትላንት እናስተባብር የነበርን አገልጋዮች ዛሬ የት ነን??መመለሳችን መቼ ይሆን??

ወዳጄ በቤተክርስቲያን አለሁ እንጂ ነበርኩ አያድንምና ያለነው የነበርንበት ካልሆነ ወደ ነበርንበት እንመለስ በደልን እንጂ በደለኛን ወደ ማይጠላ አምላክ እንሰደድ የት ነህ ስንባል እዚህ ነኝ ለማለት ከምናፍርበት ቦታ እንዳንገኝ ወደ ደገኛይቱ ቤት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንመለስ።

ፍቅር አንድነት ያላት ፍቅር አንድነት የምታሰጥ ሱላማጢስ ድንግል ማርያም ከኋጥያት ስደት ትመልሰን።

👉ዮም ጸለሉ መላእክት ላዕለ ማርያም ወላዕለ ወልዳ

ክርስቶስ በደብረ ቁስቋም(2)
እንዘይብሉ ስብሐት ስብሐት በአርያም ስብሐት በአርያም(2)

#ትርጉም
ዛሬ መላእክት በማርያምና በልጇ በክርስቶስ ላይ በደብረ
ቁስቋም ጸለሉ እንደዚህ አሉ ምስጋና በሰማይ ።

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
ተመየጢ ተመየጢ

   ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ

“አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ ተመለሽ፤ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ ተመለሽ” መኃ 7፥1  በኖኅ መርከብ ውስጥ ሆኖ ዐይኖቹ አሻግሮ ማየት የማይፈልግ ማን አለ? ከዚያ ሁሉ ጥፋት በኋላ ምድርን መልሶ ማየት ያጓጓል። ለዐርባ ቀናት ከሰማይ የወረደውና ከምድር የገነፈለው ትኩስ ውኃ የተራሮችን ራስ ሳይቀር የሚገሽር ትኩሳት የነበረው ውኃ ነው።

ማንም ቢሆን ለአንድ መቶ ሃምሳ ቀናት ምድርን ይዟት የቆየውን ውኃ መጉደል አለመጉደሉን በልቡ ማውጣት ማውረዱ አይቀርም። በዚህ መካከል የምድሪቱን ዕጣ ፋንታ ሊያሳውቅ የሚችል ታማኝ መልዕክተኛ ማግኘት እንዴት መታደል ነው? መዓቱ ቆሟል፤ በመርከቧ ውስጥ የሚኖሩት ሁሉ የምድሩን ፊት ማየት ይፈልጋሉ። በዚህ ጊዜ ነው ኖኅ ርግብን ምድሩን አይታ እንድትመለስ የላካት። መጀመሪያ ሄደች ለእግሯ ማረፊያ ስላላገኘች ተመልሳ መጣች፤ ምድሩ በውኃ ተሞልቶ ነበርና። ዳግመኛ ላካት የውኃውን መድረቅ ለማመልከት የወይራ ዝንጣፊ ይዛ ተመለሰች ከሰባት ቀን በኋላ መልሶ ላካት አልተመለሰችም። ኖኅም ምድር ከጥፋት ውኃ ማረፏን በዚህ አወቀና ከመርከቡ ወጣ።

ርግቢቱን ወደ ዓለም ልኮ ኖኀ ከመርከብ ወጣ። ለጥፋት ውኃ መምጣት ምክንያት የሆነው ኃጢአት መጉደሉን የምትናገረዋ ርግብ እመቤታችን እስከትመጣ ድረስ የዚህችኛዋ ርግብ አገልግሎት እስከዚህ ድረስ ስለነበረ ነው − መመለሷን ሳይጠብቅ ከመርከብ የወጣው። የኖኅ ርግብ ሳትመለስ በዚያው መቅረቷ እንደ ቁራ የምድሩ ነገር ስቧት አይደለም፤ እውነተኛው ሰላም የሚሰበክበት፣ የጥፋት ውኃ በሚጎድልበት ሳይሆን የሰው ልጅ ከኃጢአት የሚያርፍበት ዘመን እስኪመጣ ድረስ ርግቢቱ አትመለስም።

ከዚያ በኋላ የተነሡ ነቢያት ይህንን ስለሚያውቁ ነው እንደ ኖኅ ዘመን ከሚበሩት አእዋፍ መካከል የሆነችውን ርግብ ሳይሆን ከሰዎች መካከል አንዷ የሆነችውን ርግብ ተመየጢ ተመየጢ ሲሉ የኖሩት። ከጥፋት ውኃ ሳይሆን ከኃጢአት መውጫ ጊዜው መድረሱን የምታበሥራቸውን ርግብ በሕይወተ ሥጋ መቆየት እስከቻሉበት ዘመን ድረስ ተመየጢ ተመየጢ እያሉ ደጅ ይጠኗታል። ርግቧ ካልተመለሰች ሰላም በምድር ላይ መታወጁን ማን ይናገራል? ቁራም አልተመለሰም። ሌላ መልዕክተኛም አልተገኘም።

መጥቀው ከሚበሩ ንስሮች ይልቅ ለሰላም አብሣሪነት የተመረጠች ይህች ርግብ እንዴት ያለች የተመረጠች ናት? ይህች ርግብ የእመቤታችን ምሳሌ ናት ብለው ሊቃውንት ተርጉመዋል። በሰሎሞን መኃልይ ላይ “ርግቤ መደምደሚያዬ” መኃ 5፥2 ተብላ የተጠራች እመቤታችንን ቅዱስ ኤፍሬም “ተፈሥሒ ኦ ማርያም ርግብ ሠናይት፤ በጎ ርግብ እመቤታችን ደስ ይበልሽ” ብሎ አመስግኗታል። ከዚህ አያይዞ የመልክአ ውዳሴ ደራሲ ደግሞ “ርግበ ገነት ጽባሓዊ፤ በምሥራቅ በኩል የተተከለችው የገነት ርግብ” ብሏታል። ከእመቤታችን ቀድመው ለእናትነት ቀድመው የተመረጡ ብዙ ቢሆኑም የሰላም አለቃ ክርስቶስን ለመውለድ ግን አልተቻላቸውም። በቅድስና የተመረጡ የታወቁ ሴቶችም ነበሩ የእመቤታችንን ያኽል በሰውና በእግዚአብሔር ዘንድ የታመነ የሰላም መልዕክተኛ ግን አልተገኘም።

በምድር ላይ የሚኖር ፍጥረት ሁሉ መምጣቷን እያሰበ ሲናፍቅ ነው የኖረው። በርግጥም በመጣች ጊዜ ክርስቶስን ይዛ በመገኘቷ መላእክት በምድር ላይ ለሚኖሩ ሁሉ “ለግዚአብሔር ምስጋና በሰማይ ይሁን በምድርም ሰላም” ሉቃ 2፥14 እያሉ አዋጅ ነገሩ። ስትጠበቅ የነበረችው የኖኅ ርግብ መጣችና ሰላምን ወለደችልን። ሰላም ከማንም ዘንድ የሆነችለን አይደለም፤ ሰላምን ተወልዳ ነው ያገኘናት ያውም ከሌላ አይደለም − ከእመቤታችን ነው።

ዛሬም የኖኅ ርግብ ሆይ! ተመየጢ ተመየጢ እንላለን።

ምድር እንደዚያን ጊዜው ሁሉ ሰላም የላትም። የሰላም ወሬ ሊያወራን የሚችል ማንም የለም። በያንዳንዱ ቀን ማለዳ መስኮታችንን ከፍተን የጥፋት ውኃ መጉደሉን የሚነግረን ሰው እንፈልጋለን ነገር ግን እስካሁን የነገረን የለምና ርግቢቱ እመቤታችን ሆይ እባክሽ ተመየጢ?

ይሆናል ብለን የላክነው ቁራ የምድርን በሬሳ መሞላት እንደ መልካም ነገር ሆኖለት ፊቱን ወደ እኛ አልመለሰም። ከኛ ጋር በነበረ ጊዜ በፊታችን ላይ ያየውን ጭንቀት ከኛ ተለይቶ ከወጣ በኋላ ረስቶት ሰላሙን ሊያበሥረን ወደኛ መመለስ አልፈለገም። ዛሬም የኛን ተሰብስቦ በአንድ ስፍራ መቀመጥ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ዓለምን እንደፈለገ ብቻውን ከወዲያ ወዲህ ይመላልስባታል። ነገሮችን ሁሉ ለብቻው ሊጠቀምባቸው ወደደ። የመርከቧ ነዋሪዎች ተጨንቀዋልና ርግቢቱ ድንግል ማርያም ሆይ እባክሽ ተመየጢ?

ወይናችን እንዲያፈራ፤ አበባም በምድራችን ላይ እንዲታይ በመርከቧ ውስጥ ያለን እኛ ልጆችሽ ምድርን እንድንወርሳት ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ።

ሔሮድስ ሞቷል፣ አርኬላዎስ ነግሷል አልልሽም፤ እንዳልሞተ ታውቂአለሽ። አርኬላዎስ ብለን የሾምናቸው ሁሉ ሔሮድስ እየሆኑብን ተቸገርን። በኛ ዘመን በዳዊት ዙፋን የሚቀመጥልን፤ በልቡ እግዚአብሔርን መፈለግ ደስ የሚያሰኘው ንጉሥ እንኳን ባናገኝ በሔሮድስ ፋንታ ለይሁዳ የምንሾመው አርኬላዎስ ብንፈልግ አላገኘንም። የሕጻኑን ነፍስ የሚሿት ዛሬም አሉ አልሞቱም ግን ቢሆንም ተመየጢ!

ምድር የሞላት በግፍ የፈሰሰው የገሊላ አውራጃ ሕጻናት ደም ስለቆመ አይደለም ተመየጢ የምንልሽ ግፋችንን እንድታይልን ነው እንጅ። በኛ ዘንድ ስለልጆቿ የምታለቅስ ራሔል አሁንም እያለቀሰች ነው። ለቅሶም በራማ እየተሰማ ነው። ዋይታ በየደጁ አለ። ከሔሮድስ ቃል ተገብቶላቸው በገደሉት ሰው ልክ ሽልማት ሊቀበሉ የወጡት ገና አልተመለሱም። ግን ምን እናድርግ? ሰለ አባታሽ ስለ ኢያቄም፣ ስለ እናትሽ ስለ ሐና ብለሽ እመቤቴ ሆይ ተመየጢ?

ካልተመለስሽማ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ ደራሲ፤ “ወእቀውም ዮም በትሕትና ወበፍቅር” ብሎ የሚቀድስ፤ እንደ ዘካርያስ የሚያጥን፤ እንደ ሙሴ ቅብዐ ክህነት የሚቀባን ካህን ከወዴት እናገኛለን? ስለዚህ ነው ተመየጢ የምንልሽ። እመቤቴ ሆይ! አባቶቻችንን እንደ ጥንቱ የልብሳቸውን ዘርፍ ዳስሰን መፈወስ አምሮናል፤ ጥላውን ሲጥልብን የሚፈውስ ካህን ያስፈልገናል፤ ጋኔን ማውጣትም በገንዘብ ሆነ፥ እኛን ድሆችሽን ከአጋንንት እስራት ማን ነጻ ያውጣን? ተአምራት ማድረግም ትንቢት መናገርም ለግያዝ ሆነ።

ገንዘብ ሳይቀበሉ ከለምጻችን የሚያነጹን እነ ኤልሳዕ ቢፈለጉ አይገኙም። ስለሌሉ ሳይሆን ቅብዝብዝነታችንና ምልክት ፈላጊነታችን ካጠገባችን አርቋቸው ይኸው ባጠገባችን የሉም። ግሩም በሆነው በቊርባኑ ፊት በቆመ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ “ጎሥዐ” ብሎ የሚያመሰግን ካህን ዐይናችን ፈለገ፤ ልባችን ተመኘ፤ ነገር ግን በምስጋና እና በውዳሴ “ጎሥዐ” ማለትን ትተው በልሳነ ሥጋ “ጎሳ” የሚሉት በዝተውብን እየተጨነቅን ነውና ተመየጢ?


#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
የጴጥሮስ ጥላ የጳውሎስ ሰበኑ እመቤቴ ሆይ ቀራጩ ማቴዎስ ወንጌላዊ ተብሎ የተጠራው፣ ዐሣ አጥማጆቹ ወንድማማቾች ሰውን ወደ ማጥመድ የተለወጡት፣ ገበሬው ታዴዎስ፣ አትክልተኛው በርተሎሜዎስ ለዚህ መዐርግ የበቁት ባንች ነው። ሿሚውን ወለድሽላቸው፤ ታሪካቸውን የሚለውጠውን ወደ ዓለም አመጣሽላቸው። በእኛ ዘንድ ግን ነገሮች ሁሉ ተገለባብጠውብናል። ዓሣ አስጋሪ የነበሩት እነዚያ ወንድማማቾችም እንደገና መረብና መርከባቸውን ይዘው ወደ ገሊላ ባሕር ገብተዋል። ማቴዎስም ወደ ቀራጭነቱ ተመልሷል፤ ታዴዎስም ወንጌልን በገበሬ ዘር መስሎ ያስተምረናል ብለን ስንጠብቅ ዘር ወደ መዝራት ተመልሶ ዘሩን እየዘራ ነው።

በርተሎሜዎሶቻችንም ሰውን ተክለው ያጸድቁታል ብለን ተስፋ ስናደርግ ሰፊ እርሻ ከመንግሥት ተቀብለው አትክልት እየተከሉ እንደሆነ ሰማን እንግዲህ በዚህ ሰዓት የቀረን ብቸኛ ተስፋ ያንች መመለስ ነውና ርግቢቱ ሆይ! እባክሽ ተመየጢ?

ከመጣሽማ እንኳን ሰዎች መላእክት ይወርዳሉ። “ወሰላም በምድር” የሚለው ቅዳሴአችንም እውነት ይሆንልናል። ከመጣሽማ አባ ሕርያቆስም ለከንቱ ውዳሴ ሳይሆን በማብዛት ያይደለ በማሳነስ፤ በማስረዘም ያይደለ በማሳጠር ምስጋናሽን ያቀርባል። አድማጭ ሲኖር ዜማ የሚያስረዝሙ አድማጭ እንደሌለ ካወቁ ምስጋናሽን አስታጉለው የሚወጡ እነዚህን አናገኛቸውም ነበር።

ከመጣሽልንማ እንዚራ ስብሐቱን፣ አርጋኖኑን፣ ሰዓታቱን፣ ኆኅተ ብርሃኑን፣ ማኅሌተ ጽጌውን፣ አንቀጸ ብርሃኑን በስምሽ የሚደርሱልሽ አዲሶቹ አባ ጊዮርጊሶች፣ ቅዱስ ያሬዶች ይነሡልን ነበር። ይሄው አዲስ ድርሰት አዲስ ምስጋና የሚያሰማን አጥተን ስንት ጊዜ ሆነን። የዳዊት የሰሎሞን ርግብ ድንግል ማርያም ሆይ ተመየጢ ተመየጢ? እናይሽ ዘንድ ተመለሺ::

ማስታወሻ:- ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
ደብረ ቁስቋም

ኅዳር ፮ ቀን የአርያም ንግሥት፣ የፍጥረታት ሁሉ እመቤት፣ የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ አረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን አስከትላ ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት የስደት እና የመከራ ዓመታት በኋላ በስተደቡብ የምትገኘው ደብረ ቁስቋም ላይ ያረፉችበት ዕለት ይከበራል፡፡

ደብረ ቁስቋም በደቡብ ግብጽ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ይህ ተራራ የተቀደሰ ተራራ ስለመሆኑ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ታኦፊሎጎስ በድርሳነ ማርያም ‹‹ይህም ከሀገሮቹ ሁሉ ተራሮች የሚበልጥ (የተለየ) ከፍ ያለ ተራራ ነው፡፡ በውስጡ ቅዱስ አግዚአብሔር ያድራል፡፡ ይህንን ተራራ የእግዚአብሔር ልጅ ወዶታል፤ አክብሮታልምና፤ ከዓለም ሀገሮች ሁሉ ከተቀደሰች እናቱ ጋር አድሮባታልና፡፡ ከመላእክት ቤት ያድር ዘንድ አልወደደም፤ ቢታንያንም አልመረጠም፡፡ ከተራራው ላይ ባለች ገዳም ቤት ውስጥ አደረ እንጂ፤ ነቢዩ ዳዊት የጽዮንን ተራራ ወደደ፤ በአርያምም መቅደሱን ሠራ እንዳለ፡፡››

በቅዱስ ወንጌል እንደ ተጻፈ ሄሮድስ ክርስቶስን ለመግደል በፈለገ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለአረጋዊው ዮሴፍ በሕልሙ ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ›› ባለው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ (ማቴ. ፪፥፲፫-፲፭)

በስደቱም ጣዖታተ ግብጽ እየተሰባበሩ ሲወድቁ፤ በእነርሱም አድረው ሰውን ሲያስቱ የነበሩ አጋንንትም ሲሸሹ ታይተዋል፤ ደግሞም ጌታችን ዳግማዊ አዳም ነውና በምክረ ከይሲ (ዲያብሎስ) ምክንያት ተሰዶ የነበረው ቀዳማዊ አዳምን ለመካስ ተሰደደ፤ በዚህም አጋንንትን ከሰው ልቡና አውጥቶ አሳደደ፡፡
እመቤታችን ቅድስት ማርያም ከጌታችን ኢየሱስ ጋር ከመሰደዷ አስቀድሞ ነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹ወይወርድ እግዚእነ ውስተ ምድረ ግብጽ እንዘ ይጼዐን ዲበ ደመና ቀሊል፤ ጌታችን በፈጣን ደመና (በእመቤታችን ጀርባ) ተጭኖ ወደ ግብጽ ይወርዳል›› ተብሎም በተናገረው መሠረት ትንቢቱ ተፈጽሟል፡፡ (ኢሳ. ፲፱፥፩)

ጌታችን ኢየሱስ  በደብረ ቁስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቱን ሰበሰባቸው፤ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንንም አክብሮ የቁርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ሰጥቷቸዋል፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከጌታችን ኢየሱስ ጋር በቁስቋም ተራራ ስድስት ወራትን ያረፈች ሲሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኅዳር ፮  የእነርሱን ስደትና ወደ ሀገራቸው እስራኤል መመለሳቸውን በማስታወስ ታከብራለች፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!!!

ምንጭ፤ ድርሳነ ማርያም (ትርጉም ፳፻፫ ዓ.ም)
              ስንክሳር ዘወርኃ ኅዳር

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
#ኅዳር_7

#ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሊቀ_ሰማዕት

ኅዳር ሰባት በዚህችም ቀን የልዳ ሀገር የሆነ የሰማዕታት አለቃ የታላቁ መስተጋድል የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው ዳግመኛም ጌታችን በውስጧ ላደረገው ድንቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ።

ይህም እንዲህ ነው በውስጧ ድንቆች ተአምራት እንደሚሠሩ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ ሊአፈርሳት አሰበ ስሙ አውህዮስ የሚባለውንም መኰንን ከብዙ ሠራዊት ጋር ላከው፤ ያም መኰንን በደረሰ ጊዜ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥዕል ወዳለበት አዳራሽ በትዕቢት ሆኖ ገባ። በሥዕሉም ፊት በብርጭቆ መቅረዝ መብራት ነበረ በቤተ ክርስቲያኒቱና በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ እየዘበተ በእጁ በያዘው በትር የመብራቱን መቅረዝ መትቶ ሰበረው የመቅረዙም ስባሪ ወደ ከሀዱው ራስ ደርሶ መታው ራሱንም ታመመ ፍርሃትና እንቅጥቅጥም መጣበት ወድቆም ተዘረረ ባልንጀሮቹም ወደ አገሩ ሊወስዱት ተሸከሙት በክፉ አሟሟትም ተጐሳቊሎ ሞተ ወስደውም ከባሕር ጣሉት ወገኖቹም ወደ ሀገራቸው አፍረው ተመለሱ።

ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ በልዳ ሀገር ያለች የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን ያፈርሳት ዘንድ ራሱ ተነሥቶ ሔደ በዚያንም ጊዜ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ መታው ሰባት ዓመት ያህልም ዐይኖቹ ታውረው አእምሮውንም አጥቶ ቁራሽ እንጀራም እየለመነ ኑሮ ሞተ።

ክብር ይግባውና ጌታችንም የቤተ መንግሥቱን ሰዎች አስነሣበት እርሱን አስወግደው ጻድቅ ሰው ቁስጠንጢኖስን በእግዚአብሔር ፈቃድ አነገሡት እርሱም በአዋጅ የጣዖታትን ቤቶች ዘግቶ አብያተ ክርስቲያናትን ከፈተ ለክርስቲያን ወገኖችም በሁሉ ዓለም ተድላ ደስታ ሆነ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘኅዳር)


@ortodoxtewahedo
#ከአሐቲ ድንግል

ድንግል ማርያም እግዚአብሔር ስለመረጣት ነው ንጽሕት የሆነችው ወይስ ንጽሕት ስለሆነች ነው እግዚአብሔር የመረጣት?

አንዳንዶች ስለ ድንግል መመረጥ ሲነገር ሲሰሙ ሲመርጣት ላትመረጥ ነውን? እርሱ ጠበቃት እንጂ እርስዋ ምን አደረገች ሲሉ ይሰማሉ። እግዚአብሔር ሰለመረጣት ነው ንጽሕት የሆነችው የሚለው አደገኛ ክህደት ነው። ለምን ቢሉ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠውን ነፃ ፈቃድ የሚንድ ነውና። ዳግመኛ እርሷ እግዚአብሔር ስለመረጣት ብቻ ከሆነ ንጽሕት የሆነችው እያንዳንዱ ሰው ንጹሕ የማይሆነው እግዚአብሔር ስላልመረጠው ነው ወደሚል የቅድመ ውሳኔ ክህደት የሚያመራ ጠማማ መንገድ ነው።

እንዲህ ከሆነ ደግሞ በዓለም ላይ ለሚሠሩ የርኩሰትና የአመፅ የበደል ውድቀቶች ሁሉ ተጠያቂው እግዚአብሔር እንጂ ሰው አይደለም ብሎ እግዚአብሔርን መሳደብ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር የመረጠው ብቻ ንጹሕ ከሆነ ሁሉም የመንጻት ሥልጣን ካልተሰጠው በበደለኛነት ዘመናቸውን የፈፀሙ ሰዎች ተጠያቂ መሆን የለባቸውም፤ ከኃጢአት ለመንጻት ቢፈልጉ እንኳን አልተመረጡምና አይችሉም ማለት ነዋ! እንዲህ ከሆነ ሰዎች ሁሉ ሊድኑ እና እውነቱን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ የሚወድ እግዚአብሔር (ጢሞ. ፪፥፫) ፈቃዱ ወዴት አለ? እርሱ የመረጣቸው ብቻ የሚነጹ ከሆነ ባልመረጣቸው ላይ ለምን ይፈርድባቸዋል? ፈታሒ በጽድቅነቱስ ወዴት አለ?

ነገር ግን ርቱዕ የሆነው የሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የቀና የጸና አስተምህሮዋ እንዲህ አይደለም። እግዚአብሔር ሰዎችን ፍጻሜያቸውን አስቀድሞ አይቶ ይመርጣል እንጂ ወስኖ መርጦ የፈጠረው ሰው የለም። በወንጌል የእግዚአብሔር መንግስት በመካከላችሁ ናት ማለቱም ሰው ለመዳን የሚያስችለው ለመምረጥ የሚያበቃው ኃይል በእጁ እንዳለ ሲያጠይቅ ነው። በስሙ ለሚያምኑ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው የተባለውም ለዚህ ነው። በስሙ ለሚያምኑ የተሰጣቸው ስልጣን የተባለው ለመዳንም ላለመዳንም የሰው ነፃ ፈቃድና ልጅነት እንደተሰጠ ሲያስረዳ ነው። እግዚአብሔር ወደ አቤልና ወደ መስዕዋቱ ተመለከተ የተባለውም አቤል የልቡን ቅንነት የመስዕዋቱን መበጀት ስሙርነት አይቶ ተመልክቶ አቤልን ተቀበለው እንጂ አቤል እንዲያ እንዲሆን አድርጎ ወሰኖ መርጦ አልፈጠረውም። በአንፃሩ ወደ ቃየልና መስዕዋቱ አልተመለከተም ማለት የቃየልን የልቡን ጥመት አየና የመስዕዋቱን አለመበጀት አይቶ አልተቀበለውም ነገር ግን እግዚአብሔር ለክፋት ወስኖ አልፈጠረውም። እግዚአብሔር ሲኦል የሚገቡ ሰዎች እንዳሉ አውቆ ሲኦልን አዘጋጀ እንጂ ሲኦል በሚገቡ ሰዎች ላይ አስቀድሞ እንዲገቡ አድርጎ ወስኖ አልፈጠረም።

እናቱ ድንግል ማርያምን ከእናቷ ማሕፀን መርገም እንዳይኖርባት የጠበቃት እርሱ ነው ቅድመ ዓለም የአምላክ እናት እንድትሆን የመረጣትም እርሱ ነው። ነገር ግን ፍፃሜዋን በነፍስ በስጋ በአፍኣ ንጽሕት እንድትሆን አውቆ መረጣት እንጂ እርሱ ሰለወሰነ የጠበቃት የመረጣት አይደለችም። በዘመኗ ሁሉ በቅድስናዋ ተሸልማ እንደምትኖር አውቆ ከመርገም አነጻት፥ ኖሮባት አይደለም እንዳይኖርባት ጠበቃት እንጂ!

መንፈስ ቅዱስ ጠበቃት አነፃት መባሉም ፍፃሜዋን አይቶ መርገም እንዳይኖርባት ጠበቃት ማለት ነው እንጂ በዓለም ኃጢአት እንዳትሰራ ከለከላት ማለት አይደለም። ንጹህ ሆኖ መፈጠርማ አዳምም ተፈጥሮ ነበር በተፈጥሮ የተሰጠውን ንጹህ ጠባይ በቅድስና መጠቀም አልተቻለውም እንጂ እርሷ ግን ንጽሕናን ቅድስናን ደራርባ ይዛ ተገኝታለችና በዛው ድንግልናዋ ለአምላክ እናትነት በቃች። የሕይወት ፍሬን አፈራችበት እንዲመርጣት እግዚአብሔርን የሳበ በአምላክ ዘንድ ሞገስን የያዘ ንጽሕና ይዛ ተገኝታለችና እንድትመረጥ ሆና ተገኝታለች። ንጹሃንን ለክብር መምረጥማ ለፈጣሪ ድንቅ አይደለም ከእርስዋ ይልቅ ጠላቶቹን እኛን በደሙ ፈሳሽነት ይቅር ማለቱ አይደንቅምን?.......(ቀጣዩን መጽሐፉን ገዝተው ያንብቡ)

(ከርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ አሐቲ ድንግል ገፅ 272-277 ላይ የተቀነጨበ)

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
Audio
ወፍም ቤትን አገኘች
                         
Size 16.1MB
Length 46:08

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
2024/11/18 14:38:45
Back to Top
HTML Embed Code: