Telegram Web Link
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
#ጥቅምት_21 በዚህች ቀን 'ከይሁዳ ተራሮችና ኮረብቶች ጣፋጭ ሣርና ፀዓዳ ወተት ይፈሳል ይመነጫል ' ብሎ ለእመቤታችንን ትንቢት የተናገረላት የነቢይ ኢዩኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው

« ማዕረረ ትንቢት ማርያም ዘመነ ጽጌ እንግዳ
ወዘመነ ፍሬ ጽጋብ ዘዓመተ ረኃብ ፍዳ
ብኪ ተአምረ ዘይቤ ኢዩኤል ነቢየ ኤልዳ
ያንጸፈጽፍ እምአድባሪሁ ወእም አውግሪሁ ለይሁዳ
ፀቃውዓ መዓር ጥዑም ወሃሊብ ፀዓዳ» [ ማኅሌተ ጽጌ ]

ትርጉም

«በመከር ጊዜ አበባ በአበባ ጊዜ ደግሞ መከር አዝመራ ማጨድና መሰብሰብ የለም፡፡ ምክንያቱም ጊዜያቸው የተለያየ ስለሆነ፡፡ ለምሳሌ በመስከረም ወር የአበባ ጊዜ በመሆኑ አዝመራ መሰብሰብ የለም፡፡»

«የትንቢት መከር መካተቻ የሆንሽ. እንደ ዘመነ ጽጌ የረሃብን ዘመን ያስወገድሽ ማርያም ሆይ የኤልዳ ነቢዩ ኢዩኤል /ከይሁዳ ተራሮች ጣፋጭ ማርና ፀዓዳ ወተት ይፈሳል ብሎ/ የተናገረው ትንቢት በአንቺ ታወቀ፤ ተፈጸመ፡፡»
እመቤታችን ነቢያት የተናገሩት የትንቢት ዘር ተፈጸመባት፡፡ ማለትም ነቢያት የአምላክን ሰው የመሆን ነገር በተለያየ ሁኔታ ተናግረዋል፡፡ ጌታችን ነቢያት የተናገሩት ትንቢት መፈጸሙንና ይህንን ፍጻሜ ለማየት የታደሉት ሐዋርያት መሆናቸውን «አንዱ ይዘራል አንዱም ያጭዳል የሚለው ቃል እውነት ሆኖአል፡፡ እኔም እናንተ ያልደከማችሁበትን ታጭዱ ዘንድ ሰደድኳችሁ፡፡ ሌሎች ደከሙ እናንተም በድካማቸው ገባችሁ» በማለት ተናግሮአል፡፡/ዮሐ.4፡37/፡፡ ይህም ነቢያት የዘሩት ትንቢት በሐዋርያት ዘመን ለአጨዳ /ለፍሬ/ መድረሱን መናገሩ ነው፡፡ ስለሆነም «ማዕረረ ትንቢት፤ የትንቢት መካተቻ» ማርያም አላት፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ፍሬ ክርስቶስን ያስገኘችና «ከእሴይ ስር በትር ትወጣለች» እየተባለ የተነገረላት በመሆንዋ በአበባ ትመሰላለች፡፡

ስለዚህ እመቤታችን በመከር ወራት የምትገኝ አበባ ናት፡፡ በመከር ጊዜ የአበባ መገኘት ያልተለመደ ስለሆነ «ወዘመነ ጽጌ እንግዳ፤ እንግዳ የሆነ አበባ» አላት፡፡

ከዚህ በኋላ
«ብኪ ተአምረ ዘይቤ ነቢየ ኤልዳ፣
ያንጸፍጽፍ እም አድባሪሁ ወእም አውግሪሁ ለይሁዳ፣
ፀቃውዓ መዐር ጥዑም ወሀሊብ ፀዓዳ. . .» በማለት ነቢዩ ኢዩኤል የተናገረውን ትንቢት አፈጻጸም ይናገራል፡፡

ነቢዩ ኢዩኤል በዘመኑ ጽኑ ረኀብ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ሕዝቡን በምሕረት እንደሚጎበኛቸውና ረሀቡ እንደሚጠፋ ይነግራቸው ነበር፡፡ «ብዙ መብል ትበላላችሁ.ትጠግቡማላችሁ ከዚህ በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ ተራሮች በተሃ ጠጅ ያንጠበጥባሉ.ኮረብቶችም ወተትን ያፈስሳሉ.በይሁዳም ያሉት ፈፋዎች ሁሉ ውኃን ያጎርፋሉ » /ኢዩ.3.18፤ 2.26/፡፡

«ብኪ ተአምረ ዘይቤ ኢዩኤል ነቢየ ኤልዳ፤ያንጸፍጽፍ እምአድባሪሁ ወእምእግሪሁ ለይሁዳ ፀቃውዐ መዓር ወሀሊብ ፀዓዳ»፡፡ ይህም ማለት ነቢዩ ኢዩኤል ከይሁዳ ተራሮችና ኮረብቶች ጣፋጭ ሣርና ፀዓዳ ወተት ይፈሳል ይመነጫል ያለው በአንቺ ተፈጸመ ማለት ነው፡፡ ይህም እመቤታችን ክርስቶስን በወለደች ዕለት መሪሩ ጣፍጦ፣ ይቡሱ ለምልሞ ተገኝቷል፡፡ ይህ ለጊዜው ሲሆን ፍጻሜው ደግሞ ከእርሷ በነሣው ሥጋና ደም ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ፣ ከልጅነት ተራቁቶ፣ በረሀበ ነፍስና በጽምዓ ነፍስ ተይዞ የነበረውን የሰው ልጅ ከጎኑ ውኃን ለጥምቀት፤ ሥጋውንና ደሙን ምግበ ነፍስ አድርጎ የአምስት ሺህ አምስት መቶውን ዘመነ ረሀብ እንዳስወገደልን ያስረዳል፡፡

ድንግል ሆይ፤ ክብር የክብር ክብር ካለው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ስርጉት በቅድስና ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን።

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
"ቤተክርስቲያንን የሚያስቀጥሉ ሦስት ሰንሰለቶች አሉ እነርሱም:---
ትዳር ፣ ምንኩስና እና ክህነት ናቸው።

እነዚህ እክል ስለገጠማቸው ነው ቤተክርስቲያን እየተቸገረች ያለቸው እንጂ ሌሎች ሰዎች ወይም አህዛብ ክፉ ስለሆኑ አይደለም። እነሱ ደግ የሚሆኑበት ዘመን ነገም እኔ አልጠብቅም ሰይጣን ባለበት መልካም ነገር አይመጣም።

እኛ ግን የጎደለን ይህ ነው፣ በተከበረ ትዳር ፣በተከበረ ምንኩስና እና በተከበረ ክህነት ቤተክርስቲያን ትቀጥላለች።

ምሳሌ እንዴት ካልን፦
የተከበረ ትዳር:- የተከበረ መነኩሴ ይወልዳል።
የተከበረ መነኩሴ:- የተከበረን ጵጵስናን ያመጣል።
የተከበረ ጳጳስ:- የተከበረን ክህነትን ይሾምና
የተከበረው ክህነት:- የተከበረ ትዳርን ባርኮ ያጋባል። የተከበረው ትዳር መልሶ እንደገና የተከበረ ካህንን ይወልዳል።

በዚህ ዑደት ነው ቤተክርስቲያን ተጠብቃ የምትኖረው። አሁን ግን ምንጩ ደፍርሷል። ለዚህም ሁላችንም መስተካከል አለብን። አሁን እኔ ሁሉም ሥርዓት እየፈረሰ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ! ተምረን ማግባትና፣ተምረን መመንኮስም ሆነ ክህነት መያዝን ማስቀጠል አለብን።"

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
እንኳን መላእኩ ለቅዱስ ኡራኤል ወርሀዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ✙ አደረሰን የመላእኩ አማላጅነት አይለየን ።

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
ይእቲ : ተአቢ : እምአድባራት : ወደብር : ርእሰ : አድባራት : እንጦጦ : መንበረ : ፀሐይ : ቅድስት ማርያም : ቤተ : ክርስትያን : ዘሐነፅዋ : ዳግማዊ ምኒሊክ : ወእቴጌ : ጣይቱ : ብርሃን ዘኢትዮጵያ ::

"፲ ፰ ፻ ፸ : ታነፀች።

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
"ፈጥኖ ደራሹ ጊዮርጊስ ሆይ፤ እንደ ወይን ጠጅ ልብን
ደስ የምታሰኝ ነህ እኮን። ኅዘንን ታስረሳለህና።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ፤ ልመናችንን ፈጥነህ ስማ። በባሕር ላይ የምንንሳፈፈውን በየብስ የምንነጉደውን ሁሉ ፈጥነህ እርዳን እምነታችን በአንተ ላይ አድርገናል።
የእግዚአብሔር እውነተኛ ምስክሩ ፈጥኖ ደራሹ ሰማዕት ኃይሉ ጊዮርጊስ ሆይ፤ በየዕለቱ እርዳታህ አይለየኝ። የዚህ ዓለም ነጋዴ ያለትርፍ መውጣት መውረድ ከንቱ ድካም ነውና።"

(መልክአ ቅዱስ ጊዮርጊስ)

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
ሰው ሲፈጠር እግዚአብሔር በሰጠው ሕይወት በክብር እንዲኖር ነበር፡፡ ኃጢአትን ከሠራና ከፈጣሪው ከተጣላ በኋላ ‹‹አፈር ነህና ወአፈር ትመለሳለህ›› ተባለ፡፡ የተሰጠውንም ሰማያዊ ክብር ብቻ ሳይሆን በምድርም ክብርን አጥቶ ተዋረደ፡፡ ለእንስሳት የነበረውንም እንዲበላ ሆነ፡፡ ሊገዛቸው የተፈጠሩት እንስሳትና አራዊት እንዲያጠቁት ሆነ፡፡ መሬት እንኳ አመፀችበት፡፡
የንስሐ ሕይወት፣ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ ፫ኛ ፣ ትርጉም በቀሲስ እሸቱ ታደሰ ወንድም አገኘሁ ገጽ 61



#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
በስምህ ታምኛለሁ
ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ በቴሌግራም
በስምህ ታምኛለው

👉 ዘማሪት ፅጌሬዳ

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
የንጹሐን ደም የድሆች እንባ ያለማቋረጥ ከመፍሰሱ የተነሣ መሬት ጽናቷን ልትለቅ
በየቀኑ መንቀጥቀጥ ይዟታል።
ሥርዓተ ማኅሌት ዘጽጌ ዘሐምሳይ ሳምንት ወበዓለ ተክለ ሃይማኖት (የአምስተኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌና የተክለ ሃይማኖት በዓል)

ነግሥ

ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

አቤቱ ጽሎቴን ስማኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ጩኸቴም ከፊትህ ይድረስ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ፊትህንም ከእኔ ላይ አታዙርብኝ በጭንቀቴ ዕለት ጆሮዎችህ ያድምጡኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ  በጠራሁህ ዕለት ፈጥነህ ስማኝ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለዘላለሙ ሃሌ ሉያ
ይህም ማለት፡ በልዕልናው ያለውን እግዚአብሔርን እናመስነው ፣ ዓለምን በአንዲት ቃል የመሠረተ እርሱ ፈጽሞ ምስጉን ነው።

ሰላም ለአብ ገባሬ ኩሉ ዓለም፤ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም ፤ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም፤ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም፤ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም።

ዓለምን ለፈጠረ ለአብ ሰላምታ ይገባል፣ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስም ሰላምታ ይገባል ፣ ለማርያም እና ለመላእክት ሰላምታ ይገባል ፣ ለነቢያትና ለሐዋርያትም ሰላምታ ይገባል ፣ ለሰማዕታትና ለጻድቃንም ሰላምታ ይገባል።

ዚቅ

ዛቲ ይእቲ እኅተ ትጉሃን መላእክት፤ ወለተ ኄራን ነቢያት፤ እሞሙ ለሐዋርያት፤ ሞገሶሙ ለጻድቃን ወሰማዕት።

እርሷ የትጉሃን መላእክት እህታቸው ፣ የደጋግ ነቢያት ልጃቸው ፣ ለሐዋርያት እናታቸው ፣ ለጻድቃን እና ሰማዕታት ሞገሳቸው ናት።

ወቦ መልክዓ ሥላሴ(ሌላ)

ሰላም ዕብል ለንዋየ ውስጥ ምሕረትክሙ ትሩፋተ ገድል ኩኑኒ ሥላሴ አምጣነ ትሩፋት አንትሙ፤ሶበ ሖርኩሰ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ፤ጊዮርጊስ ኢወሀበኒ መጠነ ነጥበ ጠል እምደሙ፤ወተክለ ሃይማኖት ከልአኒ ስባረ እምዐጽሙ፡፡

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ከውስጣዊ ባሕርችሁ የሚገኝ ቸርነታችሁን ሰላምታ እላለሁ። ሥሉስ ቅዱስ ሆይ፤ የትሩፋት አበጋዝ እንደመሆችሁ የገድል ትሩፋትን አጎናጽፉኝ። ከድላቸው ገድል እሳተፍ ዘንድ በሄድኩ ጊዜ ጊዮርጊስ ከደሙ ጠብታ ሊሰጠኝ አልፈቀደም። ተክለ ሃይኖትም ከስባረ ዐፅሙ አንዲት ስንጥር እንኳ ከልክሎኛልና።

ዚቅ

ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ንዕዱ ማዕዶተ ንትካፈል ርስተ ኀበ ጽጌ ዘሠምረ ኀበ አስተዳለወ ዓለመ ክቡረ ምስለ ተክለሃይማኖት ንትፈሳሕ ሀገረ

ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ወደአማረው እንሻገር ርስትንም እንካፈል ወደ አማረው አበባ ዓለምን ወደ አዘጋጀው ክቡር ከተክለ ሃይማኖትም ጋር በሃገር ደስ ይበለን።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።

በመንጻት ወራት፣ በተአምርም ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ስትገቢ፤ ነጭ እና ቀይ አበባ የሚባል ልጅሽን ታቅፈሽ፤ ከኀዘኔ ታረጋጊኝ ዘንድ ርግቤ ሆይ ነይ፤ መልካም እናቴ ሆይ ደስ የሚል ዜና ከያዘ ከገብርኤልና፤ እንደ አንቺ ርኅሩኅ ከሆነ ከሚካኤልም ጋራ ነይ።

🌷ወረብ፦

ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል/፪/
ወንዒ ሠናይትየ  ምስለ ገብርኤል ገብርኤል ፍሡሕ ሊቀ መላእክት/፪/

ዚቅ፦

በሰላም ንዒ ማርያም፤ትናዝዝኒ ኃዘነ ልብየ፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ሚካኤል ወገብርኤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ሱራፌል ወኪሩቤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ኲሎሙ ቅዱሳን፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ወልድኪ አማኑኤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ለናዝዞ ኩሉ ዓለም።

ማርያም ሆይ በሰላም ነይ፤ ከልቤ ኃዘን ታጽናኒኝ ዘንድ፤ ማርያም ሆይ በሰላም ነይ ከሚካኤልና ከገብርኤል ጋር፤ማርያም ሆይ በሰላም ነይ ከሱራፌልና ከኪሩቤል ጋር፤ ማርያም ሆይ በሰላም ነይ ከቅዱሳን ኹሉ ጋር፤ ማርያም ሆይ በሰላም ነይ አማኑኤል ከተባለ ልጅሽ ጋር፤ ማርያም ሆይ ዓለምን ለማጽናናት በሰላም ነይ።

🌹ማኅሌተ ጽጌ፦🌹

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቌ ባሕርይ ዘየኀቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።

እመቤቴ! የሞቱ መታሰቢያ፤ የስሙ ምልክት የተጻፈብሽ፤ ከሚያበራ የባሕርይ እንቊ የጠራሽ የራስ ወርቅ ክበብ ነሽ፤
የአበባ ጉንጉን የተሣለብሽየጊዮርጊስ የመንግሥቱ ዘውድ ማርያም ሆይ!!
አንቺ ሁሉን ታሰግጂለታለሽ እሱ ግን ለአንቺ ይሰግዳል።

🌷ወረብ

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘይኀቱ እምዕንቄ ባሕርይ/፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/

ዚቅ

ሰአሊ ለነ ማርያም አክሊለ ንጹሐን ብርሃነ ቅዱሳን።

የንጹሐን አክሊል የቅዱሳን ብርሃን ማርያም ሆይ ለምኚልን።

ዓዲ ዚቅ፦

አክሊሎሙ ለሰማዕት ተስፋ መነኮሳት ሠያሚሆሙ ለካህናት፤ነያ ጽዮን መድኃኒት

የሰማዕት አክሊል የመነኮሳት ተስፋ የካህናት ሿሚ፤ እነኋት ጽዮን መድኃኒት።

🌹ማኅሌተ ጽጌ🌹

ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም በማኅበረ ጻድቃን ተወደሰ፤ ወፈድፋድሰ በላዕለ ኃጥአን ነግሠ፤ እስመ አንሥአ ሙታነ ወሕሙማነ ፈውሰ፤ ቦ ዘይቤ አጽገየ ዘየብሰ፤ ወቦ ዘይቤ አድባረ አፍለሰ።

ማርያም ሆይ! የፍቅርሽ ተአምር በጻድቃን ማኅበር ተመሰገነ፤ ይልቁንም በኃጥኣን ላይ በእጅጉ ነገሠ፤ ሕሙማንን ፈውሷልና፣ ሙታንንም አስነሥቷልና፤ የደረቀውንም አለመለመ የሚል አለ፤ ተራራውንም አፈለሰ የሚል አለ።

🌷ወረብ፦

ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም በማህበረ ጻድቃን ተወደሰ ተአምረ ፍቅርኪ/፪/
ቦ ዘይቤ አጽገየ ዘየብሰ ወቦ ዘይቤ አድባረ አፍለሰ/፪/

ዚቅ፡

ይዌድስዋ ኵሎሙ ወይብልዋ እኅትነ ነያ ካዕበ ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ በሰማያት ኵሎሙ መላእክት

በሰማያት ያሉ መላእክት ኹሉ ያመሰግኗታል እነኋት እኅታችን ይሏታል ዳግመኛም አዲሲቱ እንቦሳ ይሏታል።

🌹ማኅሌተ ፅጌ፦🌹

ለምንት ሊተ ኢትበሊ እምአፈ ኃጥእ ውዳሴ፤ ይበቁዓኒ ዘብየ እምአፈ ጻድቃን ቅዳሴ፤ጽጌ መድኃኒት ማርያም ዘሠረፅኪ እምሥርወ እሴ፤ እመ ተወከፍኪ ኪያየ አባሴ፤ተአምረኪ የአኵት ብናሴ።

ከእሴይ ሥር የተገኘሽ የመድኃኒት አበባ ማርያም ሆይ! ከጻድቃን አንደበት የተገኘ፣ ያለኝ ምስጋና ይበቃኛልና፤ ከኃጢአተኛ አንደበት ውዳሴ አያስፈልገኝም አትበይ፤ እኔን በደለኛውን ከተቀበልሽም፤ ተአምርሽን ጨረቃ ታመሰግናለችና።

🌷ወረብ፦

ለምንት ሊተ ኢትበሊ ድንግል ውዳሴ እምአፈ ኃጥእ/፪/
ይበቁዓኒ ዘብየ ቅዳሴ እምአፈ ጻድቃን/፪/

ዚቅ፦

አዘክሪ ለኃጥአን ወአኮ ለጻድቃን አዘክሪ ለርሱሐን ወአኮ ለንጹሐን

ለጻድቃን አይደለም ለኃጥአን አሳስቢ፤ ለንጹሑን አይደለም ለአደፉት አሳስቢ።

🍂ሰቆቃወ ድንግል🍂

እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ ማርያም ውስተ ምድረ ነኪር ትሔልዊ፤ሀገረኪ ናሁ ገሊላ እትዊ፤ለወልድኪ ሕፃን ዘስሙ ናዝራዊ፤ለክብረ ቅዱሳን በከመ ይቤ ኦዝያን ዜናዊ፤እምግብጽ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ።

እመቤቴ ማርያም ሆይ እስከ መቼ በባዕድ ምድር ትኖሪያለሽ ወደ ሃገርሽ ገሊላ ተመለሽ ፣ ዜናዊው ኦዝያን እንደተናገረው ናዝራዊ የተባለ ሕፃን ልጅሽን ለቅዱሳን ክንብር ይኾን ዘንድ ራማዊ(ሰማያዊ) አባቱ ከግብጽ ይጠራዋልና።



#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
🌷ወረብ
በከመ ይቤ ኦዝያን ኦዝያን ክብረ ቅዱሳን/፪/
እምግብጽ ይጼውዖ ለወልድኪ አቡሁ ራማዊ አቡ/፪/

ዚቅ
ትንቢተ ኢሳይያስ ዘተብህለ እምግብፅ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን ጸዋዕክዎ

የኢሳይያስ ትንቢት እንደሚለው ልጄን ከግብጽ ጠራሁት ለቅዱሳን ክብር ጠራሁት።

መዝሙር በ5-
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ጸገየ ወይን ወፈረየ ሮማን፤ወፈረዩ ኩሉ ዕጽወ ገዳም ቀንሞስ ዕቁረ ማየ ልብን፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ጸገዩ ደንጎላት፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት ተሠርገወት ምድር በስነ ጽጌያት፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ እግዚአ ለሰንበት ወአቡሃ ምሕረት፤ማ፦ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ።

ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ወይን አበበ ሮማንም አፈራ፤ የምድረ በዳ ተክሎች ቀንሞስና የተቋጠረ ማየ ልብን ኹሉ አፈሩ፤ ለዕረፍታችን ሰንበትን ሠራልን፤ የሱፍ አበቦች አበቡ፤ ለዕረፍታችን ሰንበትን ሠራልን ክረምት አለፈ በረከትም ኾነ ምድርም በአበቦች ውበት ተጌጠች፤ የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷ ለዕረፍታችን ሰንበትን ሠራልን፤ (በኅብረት፡- ሰንበትን ለዕረፍታችንሠራልን፤ ሠንበትን ለዕረፍታችን ሠራልን።

አመላለስ፦
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ/፪/
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ወለመድኃኒት/፪/


#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
🕊

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

[  † ጥቅምት ፳፬ [ 24 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት †  ]


† 🕊 ቅዱስ አብላርዮስ ገዳማዊ 🕊 † 

† በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ "ታላቁ / ዓቢይ / THE GREAT" የሚል ስም የሚሰጣቸው አባቶች የተለዩ ናቸው:: አንድም እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን የሠሩ ናቸው:: በሌላ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ስም ከሚጠሩ ሌሎች ቅዱሳን እንለይበታለን::

ታላቁ ቅዱስ አብላርዮስ ደግሞ ካለ ማመን ወደ ማመን: ከማመን ወደ መመንኮስ: ከመመንኮስ ወደ መጋደል: ከመጋደል ወደ ትሕርምት: ከዚያም ወደ ፍጹምነት የደረሰ: በምድረ ሶርያም ገዳማዊ ሕይወትን ያስፋፋ አባት ነው::

ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው:: በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል:: ሕይወቱ በጐላ: በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ: ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው::

ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ: እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም [በበርሃ] ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል::

ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለ40 ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል: አስተምሯል:: በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ [ኤሌዎን ዋሻ] በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት::

ከጌታ ዕርገት በኋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው: አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ:: አኗኗራቸውም በቡድንም: በነጠላም ሊሆን ይችላል::

ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው:: ይሕም ሲያያዝ እስከ ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን ደረሰ:: በዚህ ዘመን ግን አባ ዻውሊ የሚባል አንድ ንጹሕ ክርስቲያን ይሕንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው:: ለ፹ ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ 'የባሕታውያን አባት' ተባለ:: ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ::

ይህ ከሆነ ከ፳ ዓመታት በኋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት:: በቅዱስ ሚካኤል አመንኳሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ:: ስለዚህም አባ እንጦንስ የመነኮሳት አባት ተባሉ::

እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል:: ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው: ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል:: ከእነዚህም አንዱና ዋነኛው ዛሬ የምናከብረው ታላቁ ጻድቅ አባ አብላርዮስ ነው::

ቅዱስ አብላርዮስ ሶርያዊ ሲሆን የተወለደው በ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ነው:: በቀደመ ሕይወቱ ክርስትናን ፈጽሞ የማያውቅ ሰው ነበር:: ለዚህ ምክንያቱ የወላጆቹ ኢ-አማንያን መሆን ነው::

ገና በልጅነቱ ወደ ት/ቤት ገብቶ የግሪክን ፍልስፍና: የዮናናውያንን ጥበብ ተምሮ ፈላስፋ ሁኗል:: በ፲፮ ዓመቱም በምድረ ሶርያ አሉ ከሚባሉ የጥበብ ሰዎች አንዱ ሆነ:: ቅዱሱ ማንበብና መጠየቅን አብዝቶ ይወድ ነበር::

የሚያነበው ነገር በሶርያ ቢያጣ በ፲፯ ዓመቱ ተጨማሪ ጥበብን [እውቀትን] ፍለጋ ወደ ግብጽ [እስክንድርያ] ወረደ:: በዚያ ግን ከሰማቸው ትምሕርቶች አንዱ ልቡን ገዛው:: በወቅቱ በግብጽ ላይ ፓትርያርክ የነበረው ቅዱስ እለ እስክንድሮስ ስለ ምድራዊው ያይደለ ስለ ሰማያዊው ጥበብ ሲያስተምር ሰምቶ ተገረመ::

ቅዱስ አብላርዮስ በዚህ ሰዓት የሰበሰባቸውን የፍልስፍና መጻሕፍት ጥሎ ቅዱሳት መጻሕፍትን ያነብ ጀመረ:: ቅዱስ እለ እስክንድሮስም የሚከብድበትን እያፍታታ ተረጐመለት:: በአጭር ጊዜም ክርስቲያን ሆኖ ተጠመቀ::

በዚያው ዓመትም ከከተማ ወጥቶ ወደ በርሃ ገባ:: ከአባ እንጦንስ የመጀመሪያ ደቀ መዛሙርት አንዱ ሆኖ መነኮሰ:: በዚያም በጾምና በጸሎት: በመታዘዝና በትሕትና ለዓመታት ኖረ:: ቀጥሎም ወሬ ነጋሪ መጥቶ ወላጆቹ ማረፋቸውን ነገረው::

በዚህ ጊዜ ቅዱስ አብላርዮስ ከአባ እንጦንስ ዘንድ ተባርኮ: ማኅበሩንም ተሰናብቶ ሶርያ ገባ:: የወላጆቹን ሃብትና ንብረት በሙሉ መጽውቶ ወደ ሶርያ በርሃ ወጣ:: በወቅቱ በአካባቢው ምንኩስና እየተነቃቃ ነበርና የቅዱሱ መምጣት ይበልጥ አጠናከረው::

ታላቁን ሊቅ ቅዱስ ኤዺፋንዮስን ጨምሮ በርካታ ደቀ መዛሙርትንም አፈራ:: በአካባቢውም ታላቅ መካሪ: ናዛዥ: አጽናኝ: መሪ ሆነ:: ከብዙ ተአምራቱ ባለፈ ሃብተ ትንቢት የተሰጠው አባት ነውና እጅግ ክቡር ነበር::

የገድሉን ነገርማ ማን ተናግሮ ይፈጽመዋል!

እርሱ ከዕለተ ሰንበት በቀር እህልን አይቀምስም:: ለዚያውም እሑድ በነግህ [ጧት] ትንሽ ሳር ነጭቶ ከመብላት በቀር ሌላ የሚበላው አልነበረውም:: እንዲህ ባለ የበርሃ ሕይወት ለ፷፫ ዓመታት ኖረ:: በዓለም የኖረበትን ፲፯ ዓመት ብንደምረው ፹ ይሆናል:: ቅዱሱ በተወለደ በ፹ ዓመቱ በ፬ኛው መቶ ክ/ዘመን በዚህች ቀን ዐርፏል::

አምላከ ቅዱስ አብላርዮስ ጥበቡን: ፈሊጡን: ሕይወቱን ይግለጽልን:: ከበረከቱም አይለየን::

🕊

[   † ጥቅምት ፳፬ [ 24 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ አብላርዮስ ገዳማዊ
፪. ቅድስት ጸበለ ማርያም
፫. ቅድስት አውስያ
፬. አባ ዻውሎስ ሊቀ ዻዻሳት

[  † ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
፪. ቅዱስ አጋቢጦስ [ጻድቅ ኤዺስቆዾስ]
፫. ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
፬. ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
፭. ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም [ኢትዮዽያዊ]
፮. "፳፬ቱ" ካኅናተ ሰማይ [ሱራፌል]
፯. ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
፰. አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን

" ወንድሞች ሆይ ! መጠራታችሁን ተመልከቱ:: እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች: ኃይለኞች የሆኑ ብዙዎች: ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም:: ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝነት መረጠ . . . ሥጋን የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ:: ነገር ግን:- የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ::" [፩ቆሮ.፩፥፳፮]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]



#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
የቀድሞው ፓስተር ወደ ኦርቶዶክሳዊት መቅደስ ተመለሰ።
***

የፀጋው ወንጌል አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን አገልጋይ የነበረው የቀድሞው ፓስተር ናትናኤል ቢተው ከአብራከ መንፈስቅዱስ ከቅድስት ቤተክርስትያን እናትነት ተወልዶ

ወደ አማናዊት ንጽሕት እና አንዲት ወደሆነችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት በረት ልጅ ሆኖ ተቀላቅሏል።

እግዚአብሔር ይመስገን ።

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
‹‹በእንተ አቡነ አቢብ!››
እነሆ ሰማዕቱ አቡነ አቢብ ምእመናን በሚቀምሱት የዕለት ምግብ አማካኝነት በነፍስም በሥጋም እንዲድኑ አስገራሚ የምሕረት ቃልኪዳን እንደተቀበሉ የሚናገር የገድል ተአምራታቸው ይህ ነው፡- ብዙዎች ስማቸውን ጠርተው በሚቀምሱት ምግብ አማካኝነት ከተለያዩ በሽታዎች የተፈወሱ አሉ፡፡ ይህ ቃልኪዳናቸው ለኹላችን ይደረግን ዘንድ ከመመገባችን አስቀድሞ የእግዚአብሔርን ስም እንጥራ (አቡነ ዘበሰማያትን ማለቱ ነው፡፡) ከተመገብን በኋላም የዕለት ምግባችንን ስለሰጠን እግዚአብሔርን እናመስግን፡፡ ዘወትር ከተመገብን በኋላ ሦስት ጊዜ ‹‹ስለ ወዳጅህ ስለ አቡነ አቢብ›› እያልን ሦስት ጊዜ እንቅመስ፡፡ አስቀድሞ ጌታችን መድኃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአቡነ አቢብ ተገልጦላቸው ‹‹…ወዳጄ አቢብ ሆይ! የሰውን ልጅ ለማዳን የተቀበልኩትን ሕማማተ መስቀል እያሰብህ ይህንን ሁሉ ገድል ፈጽመሃልና ምን እንዳደርግልህ ትወዳለህ?›› አላቸው፡፡ ንዑድ ክቡር ቅዱስ አባታችን አቡነ አቢብም ‹‹ጌታዬ አምላኬ መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! መቼም ሰው ሁሉ ሳይመገብ አይውልም አያድርምና በተመገበ ጊዜ ስሜን ጠርቶ የተማጸነውን ማርልኝ›› አሉት፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አባታችን አቡነ አቢብ ለሰው ልጆች ያላቸውን ፍቅር ካደነቀ በኋላ ‹‹…ከማዕድ በኋላ ስብሃት ተብሎ የተረፈውን ‹በእንተ አቢብ› ብሎ ሦስት ጊዜ የተመሰገበውን ሰው ሁሉ እምርልሃለሁ›› በማለት ታላቅ የምሕረት ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡
ያልተጠመቀ አረማዊ አሕዛብም እንኳን ቢሆኖ "ስለ አቡነ አቢብ" ብሎ ከተማጸነ ጌታችንን ያንን ሰው ወደቀናች የእምነት መንገድ ሳይመራወና በንስሓ ሳይጠራው በሞት እንደማይወስደው ለአባታችን ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡
ለማዳን ትንሽ ምክንያትን የሚፈልግ ያለ ምክንያትም የማያድን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ እስከዘላለም ድረስ ይክበር ይመስገን!
ሰው ተመግቦ እንኳን መዳን እንዲችል ይህን ድንቅ ቃልኪዳን ለአባታችን ሰጥቷቸዋልና በየቀኑ በዚህ ቃልኪዳን እንጠቀምበት፡፡ ተመግበን ከጨረስንና ስብሃት ካልን በኋላ ሦስት ጊዜ ‹‹በእንተ አቡነ አቢብ›› ብለን እንቅመስ፡፡

በዛሬዋ ዕለት ጥቅምት 25 ቀን በዓመታዊ የዕረፍት በዓላቸው ታስበው የሚውሉት ጻድቁና ሰማዕቱ አቡነ አቢብ ከቃልኪዳናቸው ረድኤት በረከት ይክፈሉን!

‹‹በእንተ አቡነ አቢብ!››

(ደብረ ሰላም ቃጭልቃ አቡነ አቢብ ገዳም ያሳተመው ገድለ አቡነ አቢብ፣ ገጽ 105)

(በዚኹ አጋጣሚ "ስረይ ኀጢአትየ" ብለን ስንጽፍ ጥንቃቄ እናድርግ!)
ሠረየ= መድኀኒት (ድግምት) አደረገ
ሰረየ= ይቅር አለ።

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
2024/11/06 01:39:59
Back to Top
HTML Embed Code: