Telegram Web Link
#ጳጕሜን_3

#ሩፋኤል_ሊቀ_መላእክት_ወመልከጼዴቅ_ካህን

‹‹#ርኅወተ_ሰማይ_/ሰማይ የሚከፍትባት እለት››፤::

#እንኳን_ለቅዱስ_ሩፋኤል_በዓለ_ሢመትና_ለቅዳሴ_ቤቱ_በ4ኛው_መቶ_ክ_ዘመን_በቅዱስ_ቴዎፍሎስ_ዘእስክንድርያ_አማካኝነት_በሚደንቅ_ተዓምራት_በአሣ_አንበሪ_ጀርባ_ደሴት_ላይ_ለታነጸው_ቅዳሴ_ቤት

#እንዲሁም_ለካህኑ_መልከጼዴቅ_ዓመታዊ_ክብረ_በዓል_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ_አደረሰን_፡፡

# ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው። ሣልሳይ ሊቀ መላእክት ነው። (“ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሩፋኤል እኔ ነኝ” እናዳለ /ጦቢ ፲፪፥፲፭/፡፡

✤ ሄኖክም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ይለዋል (መጽሐፈ ሄኖክ 6፥3)::
✤ ለሄኖክ ወልደ ያሬድ 6 ዓመት በእግረ ገነት ወድቆ ሳለ ኅበዓቱን ክሡታቱን አሳይቶታል። መ.ሄኖክ 8፡5

ቅዱስ ሩፋኤል ሰማያውያን መዛግብትን በእጁ የሚጠበቁ በመሆናቸው "ዐቃቤ ኖኅቱ ለአምላክ" ይባላል፡፡ እግዘአብሔር እንዳዘዘው የሚዘጋቸው የሚከፍታችው እርሱ ነው፡፡

✤✤✤ ቅዱስ ሩፋኤል ሰውን በመርዳት ሲኖር የነበረውን የጦቢትን ዓይን ያበራና፤ ሣራ ወለተ ራጕኤልን ተቆራኝቷት ከነበረው አስማንድዮስ ጋኔን (ያገባችውን ባል የሚገድል) አላቅቆ የጦቢት ልጅ ጦብያ እንዲያገባት ያደረገ በመኾኑ “ፈታሔ ማሕፀን (መወልድ/አዋላጅ፥ ምጥን የሚያቀል) ይባላል::

” ና ‹‹መልአከ ከብካብ›› ተብሏል (ዛሬም ድረስ የእናቶች ሐኪም ነው)፤ በኋላም ወደ ጦቢት በመኼድ ረዥም ዘመን የታወረ ዐይኑን አብርቶለት ቤቱንም በበረከት ሞልቶታል፤ በዚህም ፈዋሴ ቊስል (ድውያን)፥ ዐቃቤ ሥራይ (ባለ መድኃኒት ፈዋሽ) ተብሎ ይጠራል፡፡
#ጦቢት ልጁን ወደ ሜዶን ክፍል ወደ ምትሆነውና ራጌስ ወደ ምትባለው ሀገር ወደ ገባኤል ቤት ሲልከው መንገዱን የመራው አዛርያስ /ቅዱስ ሩፋኤል/ ነው፤ በዚህም ቅዱስ ሩፋኤል ‹መራኄ ፍኖት› /መንገድ መሪ/ ይባላል፡፡

#ቅዱስ ሩፋኤል በራማ ሰማይ ሁለተኛ ክፍል ላይ የሰፈሩትንና መናብርት በመባል የሚጠሩትን 10ሩን ነገደ መላእክት የሚመራቸው ነው፤ በዚህም ‹‹ሊቀ መናብርት›› ተብሎ ይጠራል፤ መናብርት የሚባሉት መላእክት ረቂቅ የኾነ የመብረቅ ጋሻ፥ የእሳት ጦር ይዘው፤ ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ፤ ከእነዚኽ 10ር ነገደ መላእክት 24ቱ ካህናተ ሰማይ ወጥተዋል፡፡

በኢትዮጵያ በቅዱስ #ሩፋኤል ስም ከተሰየሙት ቤተ ክርስቲያን መካከል፤

1,ጎንደር ደብረ ሣሕል ቅዱስ ሩፋኤል ወአቡነ ሐራ ድንግል ወቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን (ጐንደር)፤ በአፄ በካፋ የተመሠረተና ዚቅ እንደተጀመረባቸው ከሚነገርላቸው ቦታዎች አንዱና ታላቁ ደብር፡፡

2,አዲስ አበባ ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል፤ በ1878 ዓ.ም. በዳግማዊ አፄ ምኒልክ የተመሠረተና ባላ አንድ ጣሪያ ያለው ቀደምት የአዲስ አበባ ደብር፡፡
3,ደብረ ዘይት (አየር ኃይል) ቅዱስ ሩፋኤል ቤ.ክ.

4,ወላይታ ዳሞት ፑላስ ቅዱስ ሩፋኤል ቤ.ክ.

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo

በ facbook ይቀላቀሉን

https://www.facebook.com/profile.php?id=100050228150764
#ጳጉሜ

#የካህናት ቀን

#ቀኑን ካህናትን በማክበር ስጦታን በመስጠት እናክብረዉ።

ባለ ማህተቦችን ወደዚህ ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉@ortodoxtewahedo
4_5902366013483123710.pdf
5 MB
#ስንክሳር የወርሃ ጳጉሜን

ሰው ሁሉ ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን !

(ያዕቆብ 1፥19)

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
እኔስ ምን ልተውልህ?

ጴጥሮስ መረቡን ተወልህ : ማቴዎስም ቀረጡን በርተሎሜዎስም ግብርናውን ሌላውም ሽመናውን ተዉልህ እኔስ ምን ልተውልህ? ምን ልጣልልህ?

ኒቆዲሞስ ትዕቢቱን ሳምራዊቷም እንስራዋን ዘኬዎስም ዛፉን ማርያም ዘናይን ዝሙቷን ተዉልህ እኔ ባሪያህ ምን እተውልህ ይሆን? ከኔ የሚጣልና የሚወድቅ ሀጢአት እጅግ ብዙ ነው ቤቴ የከረፋ በደለኛ ልጅን ምን እጥልልህ ይሆን?

ቤቴ እንደሆን ከጣሪያው የማያስገባህ ላንተ የማይገባ አደፍ ቤት ለዘመናት የተዘጋ ቤት ድር እንደሚበዛው ልቤም አንተን አጥቶ ሀጢአት ደርቶበታል ...እናም ሁሉን ክፋት ጥዬ ልከተልህ በዕውቀት ሳይሆን በሕይወት ልከተልህ ስለ አንተ ሳይሆን አንተን ልወቅህ ልቅረብህና ሰው አርገኝ ......ብቻ ካንተ ያለያዩን ልጣልና ልከተልህ

/ኢዮብ ዘገነተ ጽጌ/


ሰው ሁሉ ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን !

   (ያዕቆብ 1፥19)

   < ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

     #መልካም ቀን

  #ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
#ጳጉሜ

የቅዱስ ሩፋኤል እና የፊደል ቀን

ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
#​​ፈታሔ ማሕፀን

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ " የዘለዓለም ሕይወትን እንዲወርሱ ቅዱሳን መላእክት ምእመናን ለመርዳት ለማገልገል ከእግዚአብሔር የሚላኩ ረቂቃን ፍጥረታት አይደሉምን? ( ዕብ ፩÷፲፬) ብሏል። ቅዱስ ዮሐንስም "የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ"( ራእዩ ለዮሐንስ ፰÷፬) በማለት ተናግሯል።

ቅዱሳን መላእክት ያለማያቋረጥ ለፈጣሪያቸው ምስጋና የሚያቀርቡ ረቂቃን ፍጥረታት ናቸው። በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ለተልእኮ ይፋጠናሉ። የሰውን ጸሎትና ልመና ወደ እግዚአብሔር ያደርሳሉ፤ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ምሕረት ወደ ሰው አድርሰው በእምነት ያጸናሉ። "በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፥ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው" (ራእ. ፰÷፪) የሚለው የሚያስረዳን ለተልእኮ መፋጠናቸውን ነው። ሄኖክም “በሰው ሰውነት ላይ የተሾሙ ከከበሩ ፯ቱ ሊቃነ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል አንዱ ነው” (ሄኖ.፮÷፩-፵፪) ብሏል።

የሰዎችን ልመና ወደ እግዚአብሔር፣ የእግዚአብሔርን ምሕረት እና በረከት ወደ ሰው የሚወርድባት ዕለት"ነው።

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo

በ facbook ይቀላቀሉን

https://www.facebook.com/profile.php?id=100050228150764
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እንኳን ደህና መጡ

የቅዱስነትዎ ቡራኬ አይለየን !

Galateeffamoo fii Eebbifamoo Qulqulluu Abunaa Maatiyaas Paatriyaarikii Jalqabaa Hangafa Phaaphaasota Kan Itiyoophiyaa

Baga Nagayaan Dhuftan

Eebbi Qulqullummaan Keesaan Nu-Wajjiin Haa-Ta'u
እንኳን ለፈታሄ ማህፀን ለሊቀ መናብርት ቅዱስ ሩፋኤል መልአክ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን!
#ቅዱስ_ሩፋኤል

#መስተፍስሒ (ልቡናን ደስ የሚያሰኝ)
#ዐቃቤ_ሥራይ (ባለ መድኃኒት ፈዋሽ)
#መዝገበ_ጸሎት (የጸሎት መዝገብ መክፈቻ የተሰጠው)
#ሊቀ_መናብርት (በዙፋን ላይ በክብር የሚቀመጡ መላእክት መሪ)
#ፈታሔ_ማኅጸን (የሰውንም ሆነ የእንስሳትን ማኅጸን የሚፈታ)
#መወልድ (አዋላጅ: ምጥን የሚያቀል) ይባላል::
<<በምልጃው ይጠብቀን::>>

ጷጒሜን ፫ ጉለሌ ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ።

የአመት ሰው ይበለን!

@ortodoxtewahedo
#ጳጉሜ

የቤተክርስቲያን እና የሰንደቅ አላማ ቀን

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ቤተ ክርስትያን ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ
ባላስብሽም ምላሴ በጉሮሮየ ይጣበቅ


🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
4_5902366013483123697.pdf
33.3 MB
#ስንክሳር ዘወርሃ መስከረም

ሰው ሁሉ ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን !
(ያዕቆብ 1፥19)

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
እየጀመሩ ያለመቋጨት ልምድና ፣የሌብነትና የዝርፊያ ሥርዓት እየተፈጠረ በመሆኑ ከመሞጋገስ ወጥተን የቤተ ክርስቲያንን ክብር ልንመልስ ይገባል ሲሉ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ገለጹ፡፡

ብፁዕነታቸው ይህንን ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሀገረ አሜሪካ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት አጠናቅቀው ወደ መንበራቸው መመለሳቸውን ተከትሎ በተደረገው የአቀባበል መርሐ ግብር ላይ ነው፡፡

የቤተ ክርስቲያን መልክ ከዕለት ወደ ዕለት እየጠወለገ ነው ያሉት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የባህርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ግፉ፣ ጦም አዳሪውና ተሳዳጁ በዝቷል፤ ሳይሞቱ ሞተዋል፣ ሳይታመሙ ታመዋል እየተባሉ ከሥራ የተባረሩ አገልጋዮች ተበራክተዋል ብለዋል፡፡

የተራበን የምትመግብ፣ የተጣላን የምታስታርቅ፣ የበደለ እንዲክስ፣የሰረቀ እንዲመልስ የምታስተምር ቤተ ክርሰቲያን አጀንዳ ሁና ማየታቸው እጅጉን እንዳሳዘናቸው የገለጹት ብፁዕ አቡነ አብርሃም በዚህ ወቅት በንግግር ብቻ እየተመጸዳደቅን የምናልፍበት ጊዜ ባለመሆኑ ችግሩ ከሥር መሠረቱ የሚፈታበት መንገድ ሊመቻች ይገባዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ቀዳማዊ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በበኩላቸው ስለአቀባበሉ አመስግነው በዚህ የክረምት ወቅት በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ሁሉ እግዚአብሔር መጽናናትን እንዲሰጣቸው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

ቅዱስነታቸው አክለውም ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ የሚገኘው ጉዳይ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሥም የሚያጎድፍ ተግባር መሆኑን ጠቅሰው እየተፈጠረ ያለው ነገር የሚፈታው በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔና ውይይት ነው ብለዋል፡፡

@ortodoxtewahedo
2024/09/30 11:36:42
Back to Top
HTML Embed Code: