Telegram Web Link
Forwarded from ዘ-ተዋሕዶ ቦት
🙏 በማርያም ይሄን ቻናል ሳታዩ እንዳታልፉት JOIN የምትለውን ብቻ ይንኳት።🙏
‹‹የጥቁሩን አህያ ራስ ከነጩ የነጩን አህያ ራስ ከጥቁሩ››

አቡነ ቶማስ የመርዓስ ሀገር ኤጲስ ቆጶስ ሲሆኑ ታላቅ ሰማዕትነትን የተቀበሉ ሃይማኖት ምግባራቸው እጅግ የቀና ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስ በነገሠ ጊዜ ክርስቲያኖቹን ሲያሠቃዩ በነበረበት ወቅት ከንጉሡ መኳንንት አንዱ ወደ መርዓስ ሄዶ አቡነ ቶማስን በጭፍሮቹ አሲያዛቸው፡፡ አባታችንን እንደያዟቸው ደብድበው በምድር ላይ እየጎተቱዋቸው ደማቸው እየፈሰሰ ወሰዷቸው፡፡ መኰንኑ ‹‹ለአማልክት ስገድ›› አላቸው፡፡ አቡነ ቶማስም ‹‹ከእግዚአብሔር በቀር የሚሰግዱለት አምላክ የለም›› አሉት፡፡ መኰንኑም እጅግ የበዙ ጽኑ ሥቃዮችን አሠቃያቸው፡፡ የነዳጅ ድፍድፍ አፍልተው በሰውነታቸው ላይ እንዲሁም በአፍና በአፍንጫቸው ጨመሩባቸው፡፡ ቶሎ ብለው እንዲሞቱ ሳይሆን በሥቃይ ሆነው እንዲቆዩ በማድረግ ለ22 ዓመታት በጨለማ ውስጥ እያሰሩ አሠቃዩአቸው፡፡ ከሃዲያኑም በየዓመቱ ወደ እስር ቤቱ እየገቡ አንድ አካላቸውን ይቆርጣሉ፡፡ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በየተራ ቆራረጧቸው፡፡ አፍንጫቸውን፣ ከንፈሮቻቸውን፣ ጆሮዎቻቸውን ሁሉ በየተራ እየቆረጡ ለ22 ዓመትታት ጣዖታቸውን ሲያጥኑበት ኖረዋል፡፡
አንዲት ደግ ክርስቲያን ሴት ግን የተጣሉበትን ጉድጓድ አይታ ስለነበር በድብቅ ሌሊት እየሄደች ትመግባቸው ነበር፡፡ ደገኛውና ጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ በነገሠ ጊዜ ይህች ሴት ሄዳ ስለ አቡነ ቶማስ ነግረችውና አባታችንን ከተጣሉበት ጉድጉድ አወጣቸው፡፡ ቆስጠንጢኖስ የከበሩ 318 ኤጲስ ቆጶሳትን በኒቅያ አገር እንዲሰበሰቡ ሲያደርግ አንዱ አቡነ ቶማስ ነበሩ፡፡ ወደ ጉባዔውም ሲሄዱ ደቀ መዛሙርቶቻቸው በቅርጫት አድርገው በአህያ ጭነው ወደ ጉባኤ ኒቂያ ይዘዋቸው ሄደዋል፡፡ በመንገድም ሳሉ ዐላዊያኑ አግኝተዋቸው አህዮቻቸውን ሌሊት ራስ ራሳቸውን ቆርጠው ጣሉባቸው፡፡ አቡነ ቶማስም ራሳቸው የተቆረጡትን አህዮች አምጡልኝ ብለው የጥቁሩን አህያ ራስ ከነጩ፣ የነጩን አህያ ራስ ከጥቁሩ ገጥመው ቢባርኳቸው ሁሉም አህዮች ከሞት ተነሥተዋል፡፡
ከጉባዔውም ሲደርሱ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጽድቃቸውን ዐውቆ ‹‹አባቴ በረከትዎ ትድረሰኝ›› በማለት በዐላዊያኑ የተቆራረጠ አካላቸውን ዳሶ ተባርኳል፡፡ አቡነ ቶማስ ዘመርዓስም ከሌሎቹ ኤጲስ ቆጶሳት ጋር ሆነው አርዮስን መክረውና አስተምረው እምቢ ቢላቸው አውግዘውት ወደ ሀገራቸው እንደተመለሱ ነሐሴ 24 በሰላም ዐርፈዋል፡፡

የአቡነ ቶማስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን

✞ ✞ ✞

@ortodoxtewahedo
Audio
ከልማድ ኃጢአት እንዴት እንላቀቅ

Size 2.5MB
Length 11:02

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
#22🕯🕯

#ቅዱስ ኡራኤል ሆይ

"ተራዳኢነትህ ሀገርን ከጥፋት ሕዝብን ከስደት ያድናልና ፡ ዑራኤል ሆይ ከፈጣሪ ይቅርታን አስገኝተህ የኃጥአንን ነፍስ የምትጎበኝ ነህና በዚያች የቁርጥ ፍርድ ቀን የሲኦልን ደጃፍ እንዳናይ ስለእመቤታችን ድንግል ማርያምና ስለልጅዋ ስለመድኃኔዓለም በቃል ኪዳንህ እንማጸንሐለን ።

(መልከአ ዑራኤል ቁ.፲፩እና፲፱ )

@ortodoxtewahedo
ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ

እንኳን ለሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን !!!

" የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው።"
ምሳ. ፲፥፯ /10፥7/

✝️ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገና በለጋ ዕድሜው ዓለማዊውን መንግሥት ንቆ ሰማያዊውን መንግሥት በመሻት ለክርስቶስ ታመነ

✝️ በእምነቱም የተነሳ ከጣኦት አምላኪ ነገሥታትና ወታደሮች ብዙ ስቃይና መከራ ደረሰበት

✝️ ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን በፅኑ መከራና ስቃይ ሳይሸነፍ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ

✝️ በክርስትናው ፀንቶ ጣኦት አምላኪዎችን ስለ ክርስቶስ እየሰበከ ደጋግመውም እየገደሉት አምላኩም ከሞት እያስነሳው ብዙ ድንቆችን እያደረገ ኖረ

✝️ ለአምላኩ የታመነው ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጨረሻም በአምላኩ ፍቃድ ሰማያዊ አክሊልን ተቀናጅቶ በሰማዕትነት ዐረፈ

አምላካችን እግዚአብሔር ከቅዱስ ጊዮርጊስ በረከት ያሳትፈን፤ ከሥጋና ነፍስ መከራም ይጠብቀን። አሜን።

@ortodoxtewahedo
2024/09/30 07:35:13
Back to Top
HTML Embed Code: