Telegram Web Link
ዜኖኩ ጽድቀከ
♡የመዝሙር ግጥሞች♡
ዜኖኩ ጽድቀከ ወነገርኩ አድኅኖተከ
ከሠትኩ ቃላቲከ ለሕዝብከ ኢትዮጵያ(፪)
በጸጋሁ ለመንፈስ ቅዱስ ወመሀርክዎሙ
አነ ይቤ ያሬድ ካህን(፪)

ጽድቅህን ነገርኩ አዳኝነትህን አስተማርኩ(፪)
ቃላትህን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ገለጥኩ
እኔም በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ አስተማርኩአቸው አለ ያሬድ ካህን(፪)

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
#ነሀሴ 11

#የዕለቱ_ምስባክ "ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ። ወትሠይም(ሚ)ዮሙ መላእክተ በኵሉ ምድር። ወይዘክሩ ስመኪ በኵሉ ትውልደ ትውልድ።" (መዝ 44፥16-17)

የሚነበቡት መልዕክታት
📌 1ኛ ቆሮ 5፥11-ፍ.ም.
📌 1ኛ ዮሐ 2፥14-20
📌 የሐዋ ሥራ 12፥18-ፍ.ም.

የሚነበበው ወንጌል
📌 ሉቃ 6፥20-24

የሚቀደሰው ቅዳሴ፦ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው፡፡
@m2vbot
Convert To Voice
ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ

ክፍል ፲፩

   < ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

     #መልካም ቀን

  #ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

✞በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡✞
✞✞✞ እንኩዋን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ደብረ ታቦር በሰላም
አደረሳችሁ ✞✞✞
✞✞✞ ደብረ ታቦር ✞✞✞
=>ደብረ ታቦር በቁሙ እሥራኤል ውስጥ ከሚገኙ ተራሮች አንዱ ነው:: ተራራው
ብዙ ታሪካዊ ዳራዎች ቢኖሩትም ክብሩ ከፍ ከፍ ያለው ግን ጌታችን ብርሃነ
መለኮቱን ስለ ገለጸበት ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
+አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደባት በዚያች በተወደደች
ጊዜ: ደቀ መዛሙርቱ ስለ እግዚአብሔር መንግስት ምሥጢርን ይማሩ ነበር::
በጊዜው ግን አበው ሐዋርያት ምሥጢር ባይገባቸው: አንድም ገና መንፈስ
ቅዱስ በእነርሱ ላይ አልወረደም ነበርና እምነታቸው ሙሉ አልነበረም::
+ጌታም አምላክነቱን በየጊዜው በቃልም: በተግባርም ይገልጥላቸው ነበር::
በርግጥ ያንን ነደ እሳት: ሰማያት የማይቸሉትን ግሩማዊ አምላክ በትሑት ሰብዕና
መመልከቱ ሊከብድ እንደሚችል መገመት አያዳግትም::
+ጌታችን ብዙ ተአምራትን በአምላካዊ ጥበቡ ሠርቷል:: እጅግ ድንቅ ከሆኑት
መካከል ደግሞ ቅድሚያውን ደብረ ታቦር ይይዛል:: ጌታ ስለ ምን መለኮታዊ
ክብሩን በደብረ ታቦር ገለጸ ቢሉ:-
1.ትንቢቱ ሊፈጸም (መዝ. 88:12)
2.ምሳሌው ሊፈጸም (ባርቅና ዲቦራ በሢሣራ ላይ ድልን ተቀዳጅተዋልና)
3.ሊቀ ነቢያት ሙሴ "ልይህ" ብሎ ከ1,500 ዓመታት በፊት ጠይቆ ነበርና
እርሱን ለመፈጸም
4.አንድነቱን: ሦስትነቱን ለመግለጽ
5.ቤተ ክርስቲያንን በምሳሌ ለማሳየት
6.ተራራውን ለመቀደስ
7.የሐዋርያቱን ልብ ለማጽናት . . . ወዘተ ነው::
+ነሐሴ 7 ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቂሣርያ ፊልዾስ
ወስዶ "የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?" ብሎ ጠይቁዋቸው ነበር:: እነርሱም
የራሳቸውን ሐሳብ የሌላ እያስመሰሉ "አንዳንዶቹ ኤልያስ: አንዳንዶቹም ሙሴ:
ሌሎቹም ከነቢያት አንዱ ነው ይሉሃል" አሉት::
+ኩላሊትን የሚመረምር ፈጣሪ ነውና "እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?" ቢላቸው
ደንግጠው ዝም አሉ:: የሃይማኖት አባት: ባለ በጐ ሽምግልና ቅዱስ ዼጥሮስ
ግን በመካከላቸው ቆሞ "አንተ ውዕቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው -
የሕያው እግዚአብሔር አንድያ የባሕርይ ልጁ ክርስቶስ አንተ ነህ" አለው:: በዚያን
ጊዜ ቃለ-ብጽዓን እና የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ተሰጠው:: (ማቴ. 16:13)
+መጽሐፍ እንደሚል ደግሞ እንዲህ ከሆነ ከ6ኛው ቀን በሁዋላ ጌታችን 12ቱን
ደቀ መዛሙርቱን ወደ ደብረ ታቦር ወሰዳቸው:: ዘጠኙን በእግረ ደብር (ከተራራው
ሥር) ትቶ 3ቱን (ዼጥሮስን: ዮሐንስንና ያዕቆብን) ይዟቸው ወጣ:: እኒሕ
ሐዋርያት "አዕማድ: አርዕስት: ሐዋርያተ ምሥጢርም" ይባላሉ::
+በተራራው ላይ ሳሉም ድንገት የጌታችን መልኩ ከፀሐይ 7 እጅ አበራ:
ከመብረቅም 7 እጅ አበረቀ:: "ወኮነ ልብሱ ጸዐዳ ከመ በረድ" እንዲል ከታቦር
የተነሳው ብርሃነ ገጹ አርሞንኤም ደርሷል:: ያንን ተመልክተው መቆም ያልቻሉት
ሐዋርያቱ ፈጥነው መሬት ላይ እንደ ሻሽ ተነጠፉ::
+በዚያች ሰዓት ሙሴ ከመቃብር: ኤልያስም ከብሔረ ሕያዋን መጡ:: አንዳንዶቹ
ጌታን 'ነቢይ' (ሎቱ ስብሐት) ብለውታልና ሙሴና ኤልያስ ተናገሩ:- "ስለ ምን
አንተን ነቢይ ይሉሃል: እግዚአ ነቢያት - የነቢያት ፈጣሪ ነህ እንጂ" እያሉ
ተገዙለት: አመሰገኑት::
+ነገር ግን በቦታው ጸንተው መቆየት አልቻሉም:: መለኮታዊ ብርሃኑ ቢበዘብዛቸው
ቅዱስ ሙሴም ወደ መቃብሩ: ቅዱስ ኤልያስም ወደ ማደሪያው በድንጋጤ
ሩጠዋል::
+በዚያች ሰዓት ሊቀ ሐዋርያት ጌታን "ሠናይ ለነ ኀልዎ ዝየ: ንግበር ሠለስተ
ማሕደረ: አሐደ ለከ: ወአሐደ ለሙሴ: ወአሐደ ለኤልያስ - ጌታ ሆይ! በዚህ መኖር
ለኛ መልካም ነው:: በዚህም 3 ዳስ እንሥራ:: አንዱን ላንተ: አንዱንም ለሙሴ:
አንዱን ለኤልያስ" ብሎታል::
+ቅዱስ ዼጥሮስ ለራሱ ሳያስብ ለጌታና ለቅዱሳን ነቢያቱ "ቤት እንሥራ"
በማለቱ ሲመሰገን ጌታን የመጣበትን የማዳን ሥራ የሚያስተው ጥያቄ
በማቅረቡ ከድካም ተቆጥሮበታል:: ለሁሉም ግን ሐሳቡ ድንቅና መንፈሳዊ ነው::
+እርሱ ይሕንን ሲናገር መንፈስ ቅዱስ በደመና አምሳል ወረደና ከበባቸው:: አብ
ከሰማይ ሆኖ "ዝንቱ ውዕቱ ወልድየ ዘአፈቅር: ወሎቱ ስምዕዎ - የምወደው:
የምወልደው: ሕልው ሆኘ የምመለክበት የባሕርይ ልጄ እርሱ ነውና ስሙት" ሲል
ተናገረ::
+ደቀ መዛሙርቱም ከፍርሃት የተነሳ በዚያች ሰዓት እንደ በድን ሁነው ነበርና
ጌታችን ቀርቦ ቀሰቀሳቸው:: በተነሱ ጊዜ ግን ሁሉም ነገር ወደ ነበረበት ተመልሶ
ነበር:: (ማቴ. ማር. ሉቃ. )
+በደብረ ታቦር የጌታችን ብርሃነ መለኮት ያዩ 3ቱ ሐዋርያት ብቻ አይደሉም:: እመ
ብርሃን ካለችበት ሆና ስትመለከት 12ቱ ሐዋርያት ደግሞ በተራራው ሥር ሆነው
በተደሞ ተመልክተዋል::
+ይሕንን ድንቅ ብርሃነ መለኮት ያላየ ይሁዳ ብቻ ሲሆን እርሱም ስለ ክፋቱ
የኢሳይያስ ትንቢት ተፈጽሞበታል:: ኃጢአተኛው የእግዚአብሔርን ክብር
እንደማያይ ተነግሮበታልና:: "ያአትትዎ ለኃጥእ ከመ ኢይርዐይ ስብሐተ
እግዚአብሔር" እንዲል:: (ኢሳ.)
ሊቁም የደብረ ታቦርን ምሥጢር ሲያደንቅ እንዲህ ብሏል:-
"ጸርሐ አብ ኪያከ በውዳሴ:
ወበርእስከ ጸለለ መንፈሰ ቅዳሴ:
አመ ገበርከ እግዚኦ በታቦር ምስለ ሐዋርያት ክናሴ:
መንገለ ሀሎ ኤልያስ ወኀበ ሐለወ ሙሴ:
ዘመለኮትከ ወልድ ከሠትከ ሥላሴ::"
=>ለወዳጆቹ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠ ጌታ የእኛንም ዐይነ ልቡናችንን
ያብራልን:: ከበዓሉ በረከትም ያሳትፈን::
=>ነሐሴ 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ደብረ ታቦር / ደብረ ምሥጢር / ደብረ በረከት
2.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት (ልደቱ)
3.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
4.ቅዱሳን አበው ሐዋርያት
5.አባ ጋልዮን መስተጋድል
6.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ (ልደታቸው)
7.ቅድስት ኦፍራ ሰማዕት
=>ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3."99ኙ" ነገደ መላዕክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5."13ቱ" ግኁሳን አባቶች
6.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
7.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ
=>+"+ ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል::
ክንድህ ከኃይልህ ጋር ነው::
እጅህ በረታች: ቀኝህም ከፍ ከፍ አለች:: +"+ (መዝ. 88:12)
=>+"+ ከስድስት ቀንም በሁዋላ ጌታ ኢየሱስ ዼጥሮስን: ያዕቆብንና ወንድሙን
ዮሐንስን ይዞ ወደ ረዥም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው:: በፊታቸውም ተለወጠ::
ፊቱም እንደ ፀሐይ አበራ:: ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ:: እነሆም ሙሴና
ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው:: ዼጥሮስም መልሶ ጌታ ኢየሱስን:- "ጌታ
ሆይ! በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው:: ብትወድስ በዚህ ሦስት ዳስ: አንዱን
ለአንተ: አንዱንም ለሙሴ: አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ" አለ:: እርሱም ገና
ሲናገር እነሆ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው:: እነሆም ከደመናው:- "በእርሱ ደስ የሚለኝ
የምወደው ልጄ ይህ ነው: እርሱን ስሙት" የሚል ድምጽ መጣ:: ደቀ
መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ:: +"+ (ማቴ. 17:1)
✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞

በዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

[ደብረ ታቦር]

ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

❖ ይኽ በዓል ከጌታችን 9ኙ ዐበይት በዓላት አንደኛው ሲኾን በዓሉ በየዓመቱ ነሐሴ 13 ላይ በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ታሪኩ በ3ቱ ወንጌላት ላይ የተጻፈ ሲኾን ክብር ይግባውና ጌታችን አምላችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስምንቱን ሐዋርያትን ከእግረ ደብር (ከተራራው ሥር) ትቶ ሦስቱን (ጴጥሮን፣ ያዕቆብን፣ ዮሐንስን) ይዟቸው ወደ ታቦር ተራራ በመውጣት የሞተውን ሙሴን ከ1644 ዓመታት በኋላ አሥነስቶ የተሰወረውን ኤልያስንም ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ የሕያዋን አምላክና የሙታን አሥነሺያቸው ርሱ መኾኑን ብርሃኑ የገለጸበት ታላቅ ምስጢር የተከናወነበት ነው፡፡ (ማቴ 17፡1-9)
❖ ጌታ 8ቱን ሐዋርያት ይዟቸው ያልወጣበት በይሁዳ ምክንያት ነው ምክያቱም ከምሥጢረ መንግሥቱ ቢለየኝ ከሞቱ ገባኹበት ባለ ነበርና ነው፤ ነገር ግን በተራራው ላይ ለ3ቱ የተገለጸው ምስጢር ከተራራው ሥር ላሉት ከይሁዳ በስተቀር ተገልጾላቸዋል፤ ለእኛም እንደ ሐዋርያት ምስጢሩን ጥበቡን ይግለጽልን፡፡
❖ ብዙ ተራሮች ሳሉ የታቦር ተራራን የመረጠበት
1)አስቀድሞ የጌትነት ክብሩ በዚያ ተራራ ላይ እንደሚገልጽ ነቢዩ ዳዊት በመዝ 88፡12 ላይ “ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚኣከ ይትፌሥሑ” (ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ይደሰታሉ) በማለት ጌታ በዚያ ተራራ ላይ ብርሃኑን ሲገልጽ የብርሃኑ ነጸብራቅ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ እንደሚታይ የተናገረውን ትንቢት ለመፈጸም ነው፡፡
❖ ሌላው ታቦር በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ 12 ጊዜያት ሲጠቀስ በተለይ በመሳ 4 እና 5 ላይ እንደተጻፈው አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን የእስራኤል ጠላት የነበረው ሲሳራን መስፍኑ ባርቅ በተራራው ላይ ድል ነሥቶበት ነቢይቱ ዲቦራም በተራራው ላይ በደስታ አመስግናበታለች ዘምራበታለች፤ በተመሳሳይ መልኩ የእስራኤል ዘነፍስ የክርስቲያኖችን ጠላት የኾነውን ዲያብሎስን የኹላችን ፈጣሪ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነቱን ገልጦ ድል ስለነሣው ነቢያት ሐዋርያት ምእመናን የሚያመሰግኑት ስለኾነ ለምሳሌነቱ ተስማሚነት ያለውን የታቦርን ተራራን መርጦታል፡፡
❖ ለምን ሙሴንና ኤልያስን ከነቢያት መኻከል መረጠ? ቢሉ
ሀ) በማቴ 16፡13 ላይ ሐዋርያትን ስለማንነቱ እንደጠያቃቸው እንደመለሱለት ኹሉ በእውነት የሙሴና የኤልያስ ፈጣሪ መኾኑን ሲገልጽላቸው ሲኾን ሙሴና ኤልያስም ጌታቸው ፈጣሪያቸው ርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ መኾኑን በተራራው ላይ መስክረዋል፡፡
ለ) በዘፀ 33፡17-23 ላይ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ካለው ጥልቅ ግንኙነት የተነሣ “እባክኽ ክብርኽን አሳየኝ” ብሎ ልመናን አቀረበ፤ እግዚአብሔርም "ወአነብረከ ውስተ ስቊረተ ኰኲሕ ወእከድን እዴየ በላዕሌከ እስከ አኃልፍ" (በሰንጣቃው ዐለት አኖርሃለኍ፤ እስካልፍ ድረስ እጄን በላይኽ እጋርዳለኍ፤ ካለፍኍ በኋላ እጄን አንሥቼልኽ ጀርባዬን ታያለኽ፤ ፊቴ ግን አይታይም) ብሎታል (ዘፀ ፴፫፥፲፯-፳፫)፡፡
❖ ይኸውም ጀርባ በስተኋላ እንደሚገኝ ኹሉ በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በታቦር ተራራ ላይ እንደሚገለጽለት ሲያመለክተው ነው።
❖ ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብም ስለ ታቦር በሚተነትነው መጽሐፉ ሙሴ በቃዴስ ባለው በመሪባ ውሃ ከእስራኤል ጋር በበደለው በደል ምክንያት ምድረ ርስት ኢየሩሳሌም እንዳይገባ አይቷት ብቻ በናባው ተራራ ላይ እንዲያርፍ ኾኗል (ዘፀ ፴፪፥፶፪፤ ዘፀ ፴፬፥፩-፰)፡፡
❖ ይኽ ለሙሴ አሳዛኝ ቢኾንም በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሙሴ በፊት በሩቁ ያያት ግን ያልገባባት በምድረ ርስት በኢየሩሳሌም ያለች ታቦር ተራራ ላይ አምጥቶት በዘመነ ብሉይ በአካለ ሥጋ ያልገባባትን ርስት እንዲገባባት አድርጎታል፤ ይኸውም አዳምና ልጆቹ በአካለ ሥጋ ያጡትን ርስታቸው ገነትን በአካለ ነፍሳቸው ዳግመኛ ሊያገባቸው እንደመጣ የሚያመለክት መኾኑን በስፋት አስተምሯል፡፡
❖ ጌታችን በብሉይ ኪዳን ከነበሩት ከነቢያት ሙሴንና ኤልያስን በሐዲስ ኪዳን ከነበሩት ከሐዋርያት ሦስቱን በታቦር ተራራ ላይ ማውጣቱ፦
1) የታቦር ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ በመኾኗ ሲኾን በቤተ ክርስቲያናችን ብሉይ ኪዳንና ሐዲስ ኪዳን እንደሚነገሩ ለማመልከት
2) ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት በማመን የነቢያትንና የሐዋርያትን ክብርና ምልጃ እንደምታስተምር ለማሳየት ነው፡፡
3) ሌላው የታቦር ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ስትኾን ይኸውም ጌታ ነቢያትንና ሐዋርያትን በተራራዋ ላይ መሰብሰቡ
4) መንግሥተ ሰማያትን ነቢያትም ሐዋርያትም እንደሚወርሷን ለማመልከት
5) ሙሴ ያገባ ሲኾን ኤልያስ ድንግል ነውና መንግሥተ ሰማያትን ደናግልም ያገቡም እንደሚወርሷት ለማጠየቅ ነው፡፡
6) ሙሴ ኦሪት ዘፍጥረትን ሲጽፍ “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” (ዘፍ 1፡1) እንዳለ፤ ዮሐንስም “በመጀመሪያ ቃል ነበር” (ዮሐ 1፡1) ብሎ እንደ ሙሴ አምላክነቱን የሚመሰክር ነውና ሙሴ አስቀድሞ የጻፈልኝ፤ አኹንም ዮሐንስ አምላክነቴን የሚጽፍልኝ እኔ ነኝ ሲል ነው፡፡
7) ሙሴና ኤልያስ ይመሳሰላሉ፤ ይኸውም በሲና ተራራ 40 ቀንና ሌሊት እንደጾመ ኤልያስም በደብረ ኮሬብ 40 ቀንና ሌሊት የጾመ ነውና፨
8) ሙሴ ንጉሡ ፈርዖንን የገሠፀ እንደነበር ኤልያስም ንጉሡ አክዐብን የገሠፀ ነውና፨
9) ዳግመኛም ሰማይኑን ዝናብ እንዳያዘንም በተሰጠው ሥልጣን ባሰረውና ከ3 ዓመት ከ6ወር ቆይታ በኋላ እንዲዘንብ በፈታው ኤልያስን እንዳመጣ ኹሉ የማሰር የመፍታት ሥልጣን ሥልጣነ ተሰጥቶት “እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል” (ማቴ 16፡18-19) ላለው ለጴጥሮስን ታላቅ ሰማያዊ ሥልጣን መስጠቱን ለማመልከት አምጥቷቸዋል፡፡
❖ በቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን ያለው መንፈሳዊ አከባበር ደማቅ ነው፤ ይኽ በዓል በቤተ ክርስቲያን በማሕሌት በቅዳሴ በትምህርት የሚከበር በዓል ሲኾን በሀገርኛ የቡሄ በዓል ይባላል፤ ቡሔ ማለት ሊቁ ደስታ ተክለ ወልድ በመዝገበ ቃላት ላይ ሲገልጹት ቧ ብሎ በደብረ ታቦር የተገለጠው የጌታችንን የፊቱን ብርሃን ጸዳል የልብሱን እንደ በረዶ ነጭ መኾን ያስረዳል ስለዚኽ የብርሃን፣ ብርሃናዊ ማለት ነው፡፡
❖ ሌላው “ብሑዕ” ማለት የቦካ ማለትን ሲያመላክት በዚኽ ቀን የሚጋገረውን ሙሉሙል ዳቦ የሚያመለከክት ነው፡፡
❖ በዚህ በዓል የብርሃኑ ምሳሌ የሚሆን ችቦ ነሐሴ 12 ማታ ይበራል፤ ሌላው በዚኽ በዓል ሰሞን በገጠር ከተራራ ላይ እረኞች ሕጻናት ዥራፍ እየገመዱ ማስጮኻቸው ጌታ በተራራ ላይ ብርሃኑን በገለጸ ጊዜ አብ በደመና ኾኖ “እርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” ባለ ጊዜ ሐዋርያት በድምፁ ደንግጸው መውደቃቸውን ለማመለክት ነው፡፡
❖ ሌላው ሙሉሙሉ ዳቦ መጋገሩ በትውፊት እንደምንረዳው ጌታ ብርሃኑን ሲገልጽ ብርሃኑ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ ያበራ ስለነበር እረኞች ሌሊቱ ኹሉ ቀን መስሏቸው እዛው ስለዋሉ ቤተሰቦቻቸው “ኅብስት” ይዘውላቸው ሄደዋልና የዚያ ምሳሌ ነው፡፡
[በደብረ ታቦር ላይ ብርሃኑን የገለጠው አምላካችን ክርስቶስ ምስጋና ይግባው]፡፡
[መልካም በዓል]
መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

#አቤቱ ህዝብህን አድን
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

📖 ሰላም ለልሳንከ በደብረ ታቦር ዘአልኆሰሰ ለብርሃን ዓቢይ እስከ ጽላሎቱ ተሐውሰ ነበልባለ እሳት ክርስቶስ ዘተዋሐድከ ጳጦሰ በዋዕየ ፍቅርከ ከመ ሥርወ አዕዋም የብሰ ውሳጤ ሕሊናየ ነደ ወልብየ ጤሰ


ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ በታቦር ተራራ ምሥጢር መለኮትህን ለመግለፅ ለተንቀሳቀሰው አንደበትህ ሰላምታ ይገባል ከድምፅህ ግርማ የተነሳ የታላቁ ብርሃን ዓምድ ተነዋውጿልና

ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ ያለማቃጠል የሲናን ዕፅ የተዋሐደው የእሳት ነበልባል አንተ ነህ የዛፎች ግንድ በእሳት እንደሚቃጠል ሁሉ በፍቅርህ ነበልባል ልቦናዬ ጤሰ ኅሊናዬም ነደደ

💠(መልክአ ኢየሱስ)💠


🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

እንኳን አደረሳችሁ መልካም በአል

💠እስቲ ቡሄ እንበል💠

ቡሄ በሉ......ሆ (2)
ሰዎች ሀሉ.....ሆ
የኛማ ጌታ......ሆ የአለም ፈጣሪ.....ሆ
የሰላም አምላክ.....ሆ ትሁት መሀሪ...ሆ
በደብረ ታቦር........ሆ የተገለጠው ...ሆ
ፊቱ እንደፀሀይ...ሆ በርቶ የታየው....ሆ
ልብሱ እንደብርሃን....ሆ ያንፀባረቀው...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛም በራልን(2)
........
ያዕቆብ ዩሀንስ...ሆ እንዲሁም ጴጥሮስ...ሆ አምላክን
አዩ....ሆ ሙሴ ኤልያስ...ሆ
አባቱም አለ ....ሆ ልጄን ስሙት....ሆ
ቃሌ ነውና .....ሆ የወለድኩት...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና (2)
የቡሄው ብርሃን ለኛም በራልን(2)
.......
ታቦር አርሞንኤም...ሆ ብርሃን ታየባቸው ........ሆ
ከቅዱስ ተራራ...ሆ እጅግ ደስ አላቸው....ሆ
ሰላም ሰለም.....ሆ የታቦር ተራራ....ሆ
ብርሃነ መለኮት......ሆ ባንቺ ላይ አበራ....ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛ በራልን(2)
.....
በአባቴም ቤት ....ሆ አለኝ ለከት.....ሆ
በእናቴም ቤት....ሆ አለኝ ለከት...ሆ
በአጎቴም ቤት ....ሆ አለኝ ለከት...ሆ
በአክስቴም ቤት....ሆ አለኝ ለከት...ሆ
ተከምሯል...ሆ እንደኩበት....ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2(
የቡሄው ብርሃን ለኛ በራልን (2)
.......
የአመት ልምዳችን...ሆ ከጥንት የመጣ...ሆ
ከተከመረው ....ሆ ከመሶቡ ይምጣ
በደብረ ታቦር ...ሆ ጌታ ስለመጣ...ሆ
የተጋገረው ....ሆሙልሙሉ ይምጣ...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛ በራልን(2)
.......
በተዋህዶ...ሆ ወልድ ያከበረው....ሆ
የእግዚአብሔር አብ ልጅ....ሆ ወልደ ማርያም ነው...ሆ
ቡሄ በሉ ...ሆ ቡሄ በሉ .....ሆ
የአዳም ልጆች...ሆ ብርሃንን ...ሆ ተቀበሉ...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛም በራልን(2)
........
ኢትዮጽያውያን....ሆ ታሪክ ያላችሁ...ሆ
ባህላችሁን....ሆ ያዙ አጥብቃችሁ...ሆ
ችቦውን አብሩ..ሆ እንደአባቶቻችሁ...ሆ
ሚስጥር ስላለው...ሆ ደስ ይበላችሁ...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛም በራልን(2)
......
ለድንግል ማርያም...ሆ አስራት የሆንሽ...ሆ
ቅዱሳን ፃድቃን ....ሆ የሞሉብሽ ...ሆ
በረከታቸው ያደረብሽ...ሆ ሁሌም እንግዶች ...ሆ
የሚያርፉብሽ....ሆ
ሀገረ እግዚአብሔር ....ሆ ኢትዪጵያ ነሽ...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛምበራልን(2)
........
ለሀዋርያት ...ሆ የላከው መንፈስ ...ሆ
ዛሬም ለኢትዮጵያ ...ሆ ፀጋውን ያፍስስ ....ሆ
በበጎ ምግባር ...ሆ እንድንታደስ ...ሆ
በቅን ልቦና ...ሆ በጥሩ መንፈስ...ሆ
በረከተ ቡሄ...ሆ ለሁላችን ይድረስ....ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛም በራልን (2)
አመት አውደ አመት ድገምና አመት ድገምና...........
..............እንኳን አደረሳችሁ መልካም በአል
ይሁንላችሁ

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
(የማቴዎስ ወንጌል  17)
----------
1፤ ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው።

2፤ በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።

3፤ እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው።

4፤ ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን። ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ።

5፤ እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።

6፤ ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር።

7፤ ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና። ተነሡ አትፍሩም አላቸው።

8፤ ዓይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም።

----------
9፤ ከተራራውም በወረዱ ጊዜ ኢየሱስ። የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያያችሁትን ለማንም አትንገሩ ብሎ አዘዛቸው።

10፤ ደቀ መዛሙርቱም። እንግዲህ ጻፎች። ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ ይገባዋል ስለ ምን ይላሉ? ብለው ጠየቁት።

11፤ ኢየሱስም መልሶ። ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤

12፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ኤልያስ ከዚህ በፊት መጣ፤ የወደዱትንም ሁሉ አደረጉበት እንጂ አላወቁትም፤ እንዲሁም ደግሞ የሰው ልጅ ከእነርሱ መከራ ይቀበል ዘንድ አለው አላቸው።

13፤ በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለ መጥምቁ ስለ ዮሐንስ እንደ ነገራቸው አስተዋሉ።

14፤ ወደ ሕዝቡም ሲደርሱ አንድ ሰው ወደ እርሱ ቀረበና ተንበርክኮ። ጌታ ሆይ፥ ልጄን ማርልኝ፥ በጨረቃ እየተነሣበት ክፉኛ ይሣቀያልና፤

15፤ ብዙ ጊዜ በእሳት ብዙ ጊዜም በውኃ ይወድቃልና።
.
16፤ ወደ ደቀ መዛሙርትህም አመጣሁት ሊፈውሱትም አቃታቸው አለው።
----------
17፤ ኢየሱስም መልሶ። የማታምን ጠማማ ትውልድ ሆይ፥ እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደዚህ ወደ እኔ አምጡት አለ።

18፤ ኢየሱስም ገሠጸው ጋኔኑም ከእርሱ ወጣ፥ ብላቴናውም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ተፈወሰ።

19፤ ከዚህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ብቻቸውን ወደ ኢየሱስ ቀረቡና። እኛ ልናወጣው ያልቻልን ስለ ምን ነው? አሉት።

20፤ ኢየሱስም። ስለ እምነታችሁ ማነስ ነው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ። ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም።

21፤ ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም አላቸው።

📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

ሰው ሁሉ ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን !
(ያዕቆብ 1፥19)

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
(የማርቆስ ወንጌል  9)
----------
2፤ ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ልብሱም አንጸባረቀ፤

3፤ አጣቢም በምድር ላይ እንደዚያ ሊያነጣው እስከማይችል በጣም ነጭ ሆነ።

4፤ ኤልያስና ሙሴም ታዩአቸው፥ ከኢየሱስም ጋር ይነጋገሩ ነበር።

5፤ ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን። መምህር ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ አለው።

6፤ እጅግ ስለ ፈሩ የሚለውን አያውቅም ነበር።

7፤ ደመናም መጥቶ ጋረዳቸው፥ ከደመናውም። የምወደው ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።

8፤ ድንገትም ዞረው ሲመለከቱ ከእነርሱ ጋር ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም።

9፤ ከተራራውም ሲወርዱ የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያዩትን ለማንም እንዳይነግሩ አዘዛቸው።

10፤ ቃሉንም ይዘው። ከሙታን መነሣት ምንድር ነው? እያሉ እርስ በርሳቸው ተጠያየቁ።

11፤ እነርሱም። ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ እንዲገባው ጻፎች ስለ ምን ይላሉ? ብለው ጠየቁት።

12፤ እርሱም መልሶ። ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናናል፤ ስለ ሰው ልጅም እንዴት ተብሎ ተጽፎአል? ብዙ መከራ እንዲቀበል እንዲናቅም።

13፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ኤልያስ ደግሞ መጥቶአል፥ ስለ እርሱም እንደ ተጸፈ የወደዱትን ሁሉ አደረጉበት አላቸው።


📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

ሰው ሁሉ ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን !
(ያዕቆብ 1፥19)

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
(የሉቃስ ወንጌል  9:28:36)
----------
28፤ ከዚህም ቃል በኋላ ስምንት ቀን ያህል ቈይቶ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ያዕቆብንም ይዞ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ።

29፤ ሲጸልይም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም ተብለጭልጮ ነጭ ሆነ።

30፤ እነሆም፥ ሁለት ሰዎች እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤

31፤ በክብርም ታይተው በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ስለ መውጣቱ ይናገሩ ነበር።

32፤ ነገር ግን ጴጥሮስንና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንቅልፍ ከበደባቸው፤ ነቅተው ግን ክብሩንና ከእርሱ ጋር ቆመው የነበሩትን ሁለት ሰዎች አዩ።

33፤ ከእርሱም ሲለዩ ጴጥሮስ ኢየሱስን። አቤቱ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ አለው፤ የሚለውንም አያውቅም ነበር።

34፤ ይህንም ሲናገር ደመና መጣና ጋረዳቸው፤ ወደ ደመናውም ሲገቡ ሳሉ ፈሩ።

35፤ ከደመናውም። የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።

36፤ ድምፁም ከመጣ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ሆኖ ተገኘ። እነርሱም ዝም አሉ ካዩትም ነገር በዚያ ወራት ምንም ለማንም አላወሩም።


📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

ሰው ሁሉ ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን !
(ያዕቆብ 1፥19)

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
Audio
በእለተ እሁድ የሚነበብ የሚተረጎም የሚጸለይ የእመቤታችን ምስጋና ይህ ነው።

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
አሐደ ለከ
ዝማሬ ዳዊት
የደብረ ታቦር መዝሙር

#አሐደ_ለከ

አሐደ ለከ ወአሐደ ለሙሴ /2/
ወአሐደ ለኤልያስ ንግበር ማይደረ /4/

📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
ዜኖኩ ጽድቀከ
♡የመዝሙር ግጥሞች♡
ዜኖኩ ጽድቀከ ወነገርኩ አድኅኖተከ
ከሠትኩ ቃላቲከ ለሕዝብከ ኢትዮጵያ(፪)
በጸጋሁ ለመንፈስ ቅዱስ ወመሀርክዎሙ
አነ ይቤ ያሬድ ካህን(፪)

ጽድቅህን ነገርኩ አዳኝነትህን አስተማርኩ(፪)
ቃላትህን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ገለጥኩ
እኔም በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ አስተማርኩአቸው አለ ያሬድ ካህን(፪)

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
❍ አምላካችን ናና
❍ የቡሄ መዝሙር
#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

🔔 ነሐሴ 12 🔔

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

👉ዲያቆን
📖1ኛ ቆሮ 9÷17....
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ይሁዳ 1÷8-14
👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረ ሐዋርያያ 24÷1-22

👉ምስባክ
📖መዝ 71፥1-3

እግዚኦ ኩነኔከ ሀቦ ለንጉስ
ወጽድቀከኒ ለወልደ ንጉሥ
ከመ ይኮንኖሙ ለሕዝብከ በጽድቅ

👉ትርጉም
አቤቱ ፍርድህን ለንጉስ ስጥ
ጽድቅክንም ለንጉስ ልጅ
ሕዝብክን በጽድቅ ችግረኛዎችክንም
በፍርድ ይዳኝ ዘንድ

📖ወንጌል
ማቴ 22÷1-15

📣ቅዳሴ
ዘእግዝእትነ

🔰 @ortodoxtewahedo

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ
ወይሴብሑ ለስምከ መዝራዕትከ ምስለ ኀይል

መዝ 88፥12-14

ለመቀላቀል👉 @ortodoxtewahedo

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
Audio
ዋዜማ ዘደብረ ታቦር

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
ቡሄ በሉ 16k
ዝማሬ ዳዊት
#ቡሄ_በሉ

📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
"ከስድስት ቀንም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ጴጥሮስን ያዕቆብንና ወንድሙ ዮሐንስን ይዞ ለብቻቸው ወደ ረዥም ተራራ አወጣቸው ..... ከዚህም በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ እንደ ነገራቸው ዐወቁ"

ማቴዎስ 17፥1-14

ለመቀላቀል👉 @ortodoxtewahedo

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
#አማን በአማን
ተሰብሐ በደብረ ታቦር

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
2024/11/18 11:35:33
Back to Top
HTML Embed Code: