Telegram Web Link
† ምንኩስና ምንድነው? †

★ ሰሞኑን መንኩሻለው ብለህ ለፌስቡክ ፎቶ ልብስ እየቀያየርክ ተርእዮ ፍለጋ(Show) ብዙ የደከምከውና ድራማዊ አክት ያበዛኽው ወንድም ይህንን በደንብ አንብብ

★ ለቤተክርስቲያን ፈተና የሚሆኑባት እንዲህ ለታይታ፣ለገንዘብና ለሥልጣን ፍለጋ ምንኩስናን መረማመጃ የሚያደርጉ ወገበ ነጮች ናቸው ።★

«መጽሐፈ አበው» እንዲህ ይናገራል።
መነኮስ ከሀገሩ ወደሌላ ሀገር ይሂድ። በዚያም በዋሻ፤ በኮረብታው፤ በተራራው ይንቀሳቀስ። በረሃብ፤ በብርድ፤ በጥም፤ በመራቆት፤ በድካም፤ በትጋት ይኑር። ልብሱ የከብት ቁርበት፤ የፍየል ቆዳና ለምድ ይሁን። ሥጋ በሕይወት ዘመኑ አይብላ። የዘወትር ምግቡ የበረሃ ጎመን፤ ቅጠልና የዛፎች ፍሬ ብቻ ይሁን። ካገር አገር አይዙር። ወደሠርግ፤ ወደ ድግስ አይግባ። በሕዝብ መካከል የሚኖር መነኮስ ቢኖር እርሱ ውሸታም ነው። የአጋንንት ረድእ፤ አገልጋይ ነው። ወንድ መነኩሴና ሴት መነኩሲት በአንድ ላይ አይኑር፤ ይራቁ። በአንድ ላይ እየኖሩ፤ በአንድ አጸድ እያደሩ ንጽህ እንጠብቃለን ቢሉ ውሸት ነው። ነብርና ፍየል አንድነት ይኖሩ ዘንድ እንዴት ይቻላል? መነኩሴ ማንንም አይማ። ሃሜተኛ ጸሎተኛ አይደለም። አብዝቶ የሚበላ መነኩሴ የትም እንደሚፈነጭ ፈረስ ነው። መነኩሴ በፀሀይ ግባት አንድ ጊዜ ብቻ ይብላ። ወፎች መብል አይተው በወጥመድ ይያዛሉ። ትልቁ አንበሳ በመብል ምክንያት ወጥመድ ውስጥ ይወድቃል። አዳም በመብል ወደቀ። ይሁዳ ከወጡ አጥልቆ በበላ ጊዜ ሰይጣን ገባበት። ሠይጣን መነኮሳትን በመብል ፤በመጠጥ፤ በሃሜት፤ በሳቅና በስካር ያድናቸዋል። ልቅ፤ ልቅ እየጎረሱ፤ የላመ የጣመ እያግበሰበሱ መነኮስ መባል አይገባቸውም። በእንቅልፍ ተውጠው፤ ከጸሎት ተለይተው እንደአዞ ተገልብጠው እንዲተኙ ያደርጋቸዋል። ዘማውያንም ይሆናሉ። ያኔም አጋንንቱ በመነኮሳቱ ላይ ይዘፍናሉ። በእጃቸውም ይጨበጭባሉ። እንደፈረሶች ሰኮና ሆነው ይረግጡአቸዋል። የዓለምን ጣዕም የቀመሱ፤ የወደዱ መነኮሳት የነፍሳቸውን ደዌ ያያሉ። የነፍሳቸውንም መድኃኒት ይተዋሉ። በሕዝባውያን መካከል የሚመላስ መነኮስ ከቅዱሳን ክብር መድረሻ የለውም። መነኮስ ወደዓለማዊ ችሎት፤ ሸንጎና ፍር አይሂድ። ምሥክር አይሁን። መነኩሴ ማለት ምዉት ማለት ነውና አይቻለሁ፤ ሰምቻለሁ፤ ዳኝነት አውጡልኝ አይበል። ለሕዝባውያን አበ ነፍስ አይሁን። መነኮስ የሞተ ነውና የሚሰማ ጆሮ፤ የሚናገር አፍ የለውም። ዓለም ውስጥ እየኖረ ዓለምን አሸንፋለሁ ቢል ውሸታም ነው። አትመነው። አፉን፤ ጆሮውንና ዓይኑን የማይጠብቅ መነኩሴ ነፍሱን አያድናትም። መነኮስ እነዚህን ሦስት ሰይፎች ካልታጠቀ መነኮስ አይባልም። የዋህነት፤ ትህትናና ድህነት ናቸው። የዋህነት ከቂም፤ ከበቀል ከጥላቻና ከስጋዊ ነገር ሁሉ መራቅ ነው። ትህትና ራስን ዝቅ ማድረግ ሲሆን ድህነት የኔ የሚለው ሀብትና ገንዘብን ሁሉ መናቅ ናቸው። መነኮስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል። በሕይወት ዘመኑ በእንደዚህ ያልተጠበቀ መነኮስ፤ መነኮስ አይደለም።

መ/ር ታሪኩ አበራ

@ortodoxtewahedo
“ምንም እንኳ የመከራ ድሀ ባንሆንም ይህ መከራ ለነጋሪውም ለሰሚውም ከባድ መሆኑን እንገነዘባለን ። “

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

@ortodoxtewahedo
አባታዊ የማጽናኛ መልእክት

በጎፋ ዞን፣ በገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት ናዳ እጅግ ብዙ የሚሆኑ ወገኖቻችን በመሞታቸው ታላቅ ኀዘን ተሰምቶናል ። ምንም እንኳ የመከራ ድሀ ባንሆንም ይህ መከራ ለነጋሪውም ለሰሚውም ከባድ መሆኑን እንገነዘባለን ።

ይሁን እንጂ ጭንቀታችን ብዙ ቢሆንም እግዚአብሔር መልካም የምንሰማበትን ዘመን እንደሚያመጣ ተስፋ እናደርጋለን ።

በተለይም ደግሞ እኛ ክርስቲያኖች በወገኖቻችን መጎዳት ብናዝንም በትንሣኤ ሙታን ስለምናምን የምጽናና በመሆኑ የሞቱት ልጆቻችን ዕረፍተ ነፍስ እንዲያገኙ እየጸለይን፤ የመከራው ገፈት ቀማሽ ለሆኑት የአካባቢው ማኅበረሰብእ ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግ ሁሉም አቅሙ በፈቀደው መጠን እንዲደርስላቸው ስንል አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን።

እግዚአብሔር አምላክ ለቤተሰቦቻቸውና ለሕዝቡ መጽናናትን ይስጥልን፤ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
አሜን።

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ሐምሌ 17 ቀን 2016 ዓ.ም.
ዋሽንግተን ዲሲ አሜሪካ

@ortodoxtewahedo
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ (💠 ✞ SAMI ✞ 💠) via @like
ቅዱሳኑን ያዳነ ቅዱስ መልአክ እኛንም ያድነን ዘንድ እንደ አባቶቻችን "አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ በአክናፊከ ምንትው:: አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ሠለስቱ እደው::" እያልን እንለምነው::

(መልክዐ ገብርኤል)

"በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን: ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም ." †

(ዳን. ፱፥፳)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †

ለመቀላቀል👉@weludebirhane

#አቤቱ የሆነብንን አስብ

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
ገብርኤል ሆይ፤ ከሰው ወገን ጠዋትና ማታ ከቶ እንደ እኔ ኀዘንና ትካዜ የሚበዛበት የለም፣
ከመላእክትም ወገን እንደ አንተ ያዘኑትን የሚያረጋጋ የለም፣
ገብርኤል ሆይ፤ ስለዚህ እኔም አውቄና አንተን አምኜ ያቀረብኩትን ይህን ጸሎት እንደ ትልቅ ዋጋ ቆጥረህ የሚያረጋጋ ቃልህን አሰማኝ።

መልክአ ገብርኤል

እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን።

@ortodoxtewahedoo
‹‹በእሳትና በውኃ መኻከል አሳለፍኸን›› (መዝ.፷፭፥፲፪)

ሐምሌ ፲፰፤፳፻፲፮ ዓመተ ምሕረት

ሥራው ግሩም የሆነ አምላካችን እግዚአብሔር ማዳንም መግደልም የሚችል የባሕርይ አምላክ ነው፡፡ (መዝ.፷፭፥፫) በእርሱ የሚታመኑት ቅዱሳን ሰማዕታት የሚደርስባቸውን መከራና ፈተና ሁሉ በጽናት፣ በልበ ሙሉነት የሚያልፉት ለዚህ ነው፡፡

እሳት ለቅዱሳን ሰማዕታት ጌጣቸው ነው፡፡ በመልክአ ሥላሴ ‹‹የሰማይ ግምጃ ብርሃን ሸማኖች የሆናችሁ ሥላሴ ሆይ ልብሰ ምሕረታችሁ የሰማዕትነት ልብስን ይሁነኝ፤ የእስጢፋኖስ ልብስ ደንጊያ በእኔ ላይ የለምና፤ የሕፃኑ ቂርቆስ ጌጡ የሚሆን እሳትም በእኔ ላይ የለምና›› ብለን የምንጸልየውም ለዚህ ነው፡፡ (መልክአ ሥላሴ፡- ለአያጺክሙ)

ወርቅና ብር በእሳት ተፈትነው እንደሚጠሩ ቅዱሳን ሰማዕታትም በመከራ ውስጥ ተፈትነው እግዚአብሔርን አስደስተው ለእኛም የጽናት ምልክት ሆነው የክብር አክሊልን በመቀዳጀት ከገቡ መውጣት፣ ካገኙ ማጣት እና መከራ ወደ ሌለበት ዘለዓለማዊ ማረፊያቸው ይሄዳሉ፡፡
ቅዱሳን ሰማዕታት በመከራ ነፍስ ከመፈተን በመከራ ሥጋ መፈተንን መርጠው፣ ነፍሳቸውን በእሳተ ገሃነም ከመፈተን በምድራዊው ሰው ሠራሹ እሳት ውስጥ ሥጋቸውን ሳይሰቅቁ በመጨመር በመፈተን ዘለዓማዊ ዕረፍት ማግኘትን መርጠዋል፡፡

ሰው በባሕርዩ እንዲራባ በክፉ ግብር የሚራቡ አጋንንት እያደሩባቸው ዓላውያን ነገሥታት ቅዱሳን ሰማዕታት ላይ በጠላትነት እየተነሡ ያልፈፀሙት ክፉ ሥራ የለም፡፡ በሐምሌ ፲፱ ቀን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነትን ያገኙት ልጅ እና እናት ቅዱስ ቂርቆስ እና ቅድስት ኢየሉጣም ስለ ንጽሕት ሃይማኖታቸው ለመመስከር ፈተናቸው የመጣውም ከዓላውያን ነገሥታት አንዱ በሆነው በእለ እስክንድሮስ ነው፡፡

ይህ ከሓዲ መኮንን ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስን ይዞ ‹‹ስምህ ማነው›› ብሎ በጠየቀው ጊዜ ‹‹ነቅዕ ዘእምዐዘቅት ንጸሕ ወእማይ ዘኢይማስን ክርስቲያን ስምየ፤ ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውኃ የተገኘ ስሜ ክርስቲያን ነው›› በማለት መልሶለታል፡፡

ሹሙ እለ እስክንድሮስ በቅዱስ ቂርቆስና በቅድስት ኢየሉጣ ብዛት ያላቸውን መከራ አድርሶም ስላልረካ ጭፍሮቹን በብረት ጋን ውስጥ ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ ሙጫ፣ የዶሮ ማር እና እርሳስ ብረትን በማስጨመር ሊያሠቃያቸው ፈለገ፡፡ ከጋኑ የሚወጣው ድምፅም እንደ ነጎድጓድ የሚሰማና ወላፈኑም እንደ ፀሐይ የሚያንጸባርቅ ነበር፡፡

ይህ የጋኑ ፍላት ግርማው እጅግ ያስፈራ ነበርና ቅድስት ኢየሉጣ ተሸበረች፡፡ ልጇ ቅዱስ ቂርቆስ ግን ይህን ፍርሃት ለማራቅ እግዚአብሔር ከእነርሱ በፊት በነበሩት ቅዱሳን በአናንያ፣ በአዛርያ እና በሚሳኤል፣ በሶስና እና በዳንኤል ሕይወት ሥራ ውስጥ የነበረውን የማዳን ችሎታ (ከሃሊነት) እያነሣ ሊያበረታት ሞከረ፡፡ ‹‹እናቴ ሆይ፥ ከሚያልፈው ዓለም ጭንቅና መከራ ለማምለጥ ስትዪ በማያልፈው ዘለዓለማዊ እሳት መቀጣት አይገባሽምና ጽኚ›› አላት፡፡ እንዲሁም ዓይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ ወደ እግዚአብሔር እጅግ ልብን የሚነካ ጸሎት አደረሰ፡፡

‹‹ባርያህ የሆነች እናቴ የሌለችበት ለእኔ ያዘጋጀሃት ርስት ውስጥ ከምገባ ከሕይወት መጽሐፍ ፋቀኝ፤ እርሻውን ልታቃጥል ፍሬውን ልትባርክ፣ ዕንጨቱን ቁረጡና አንድዱት፤ ቅጠሉን ጠብቁት፤ ልትል አይገባም፤ ጠላት ዲያብሎስ የአንተ የሆነውን ቅዱሳኑን ድል ነሳኋቸው ብሎ እንዳይመካና ከመንጋውም አንድ በግ ቀማሁ እንዳይል አቤቱ የኃይል መንፈስ ለእናቴ በመስጠት አበርታት›› በማለት ጸለየ ፡፡ የዚህ ሕፃን ሲሆን በመንግሥተ ሰማያት ለእናቱ አባት የሆነ ቅዱስ ጸሎት ከእግዚአብሔር ደርሶ እናቱን አጽንቶ ጭራሽ የብረት ጋኑን ውኃ በምንጭ ላይ በዝቶ እንደሚወርድ ጠል ሁኖ አሳያት፤ ወዲያውም ሁለቱንም ከብረት ጋን ውስጥ ጨመሯቸው፡፡

እሳቱ ዓርባ ክንድ ወደላይ ተመዝዞ ወጥቷል (ወተለዓለ ነበልባል መጠነ አርብዓ በእመት) ፣ የሁለቱ ቅዱሳን ሰማዕታት አምላክም ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤልን ከሰማይ ልኮ በብርሃን በትር ቢመታው እንዳደረ ውርጭ ሆኗል፡፡ የብረት ጋኑም እሳት ጠፍቶ አንዳች ሳይጎዱ ምስክርነታቸውን ፈፀሙ፡፡ በዚህም አስቀድሞ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ የዘመረው ቃል ተፈፀመ፡፡ ይህም፡- ‹‹አኅለፍከነ ማዕከለ እሳት ወማይ፤ በእሳትና በውኃ መካከል አሳለፍኸን፡፡›› በቀደመ ግብሩ እሳት የነበረ በኋላ ግብሩ ውኃ ሆነ፡፡ (መዝ.፷፭፥፲፪)

ቃሉ የማይታበል ልዑል እግዚአብሔር አስቀድሞ በነቢየ ልዑል ቅዱስ ኢሳይያስ የተናገረውን ቃልም በሁለቱ ቅዱሳን ሰማዕታት ተፈፅሞ አገኘነው፡፡ ‹‹ወእመኒ ዐደውከ ማየ አነ: ሀሎኩ ምስሌከ: ወአፍላግኒ ኢያሰጥሙከ ወእመኒ ዐደውከ እሳተ ነበልባል ኢያውዕየከ፤ በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም፡፡›› (ኢሳ.፵፪፥፪)

እኛ እንደነ ቅዱስ ቂርቆስ እና ቅድስት ኢየሉጣ ከእሳት እና ከፈላ ውኃ ውስጥ ጨክኖ በመግባት በእምነት መውጣት የምንችልበት አቅምም ሆነ የጸሎት ኃይል ባይኖረንም በልባችን ጋን ውስጥ እየነደደ ለሀገራችን ኢትዮጵያም የተረፈው በፍቅርና በአንድነት እንዳንኖር ያስቸገረንን ክፉ እሳት አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ እንዲያጠፋልን መለመን ይገባል፡፡ ለዚህም የአምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ቸርነት፣ የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት አይለየን!

ምንጭ ፡-
• መጽሐፍ ቅዱስ
• ድርሳነ ቅዱስ ገብርኤል ዘሐምሌ
• የመዝሙረ ዳዊት ትርጓሜ
• መጽሐፈ ስንክሳር
• መልክአ ሥላሴ

@ortodoxtewahedoo
Audio
ቅዱስ ገብርኤል ሆይ የተሰጠህ ክብር ታላቅ ነው 
                                                  
Size:- 29.3MB
Length:-1:24:12
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedoo
2024/09/29 23:17:16
Back to Top
HTML Embed Code: