Telegram Web Link
ኪዳነ ምህረት
Orthodox Mezmur Channel
ኪዳነ ምህረት | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ



ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖
Audio
✤ ኪዳነ ምህረት

ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖
ኪዳነምሕረት ልዩ ነሽ ለእኔ
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
#ኪዳነ_ምህረት_ልዩ_ነሽ_ለኔ

ኪዳነ ምህረት ልዩ ነሽ ለኔ
ሳዝን ስጨነቅ አትራቂኝ ከጎኔ
የችግሬ ደራሽ እመ እግዚአብሔር
ቃል ኪዳንሽ ይርዳኝ ካንቺ ጋር ልኑር(፪)
#አዝ
የአዳም ተስፋው ነሽ የሴት ቸርነቱ
ኪዳነምህረት ነሽ የኖህ ምልክቱ
አዳም ደጅ የጠናሽ ሲገባ ንስሀ
ኖህም ድኖብሻል ከጥፋቱ ውሃ
#አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ
ማርያም አንቺ ነሽ የፈጣሪ እናቱ
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ
እመብርሃን ስሚኝ ልመናየን ሁሉ
#አዝ
የሰሎሞን አክሊል የዳዊት ዝማሬ
ድንግል መሆንሽን ትመስክር ከንፈሬ
ለተጠማው ውሻ የሚራራው ልብሽ
ለኔም እራርቶልኝ አስታርቂኝ ከልጅሽ
#አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ
ማርያም አንች ነሽ የፈጣሪ እናቱ
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ
እመብርሃን ስሚኝ ልመናዬን ሁሉ

ዘማሪት ሲስተር ፋሲካ መኮንን
    



ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖
ኪዳነ ምህረት እመቤት
🌺💠❤️ኪዳነ ምሕረት እመቤት🌺❤️💠

ኪዳነ ምሕረት እመቤት እመቤት/×፪/
ነይልን ነይልን ካለንበት/×፪/



ከሰማያት በላይ ካለው ከማደሪያሽ/፪/
ዝማሬ ከሞላው ከዘለዓለም ቤትሽ
የምድር ፍጥረታት ማርያም ማርያም ሲሉሽ/፪/
የቃል እናት እመቤቴ ነይ በሠረገላሽ/፪/


#አዝማች......................................


ከጸጥታው ወደብ ከፍቅር አውድማ/፪/
ከሰላሙ መንደር ከእውነት ከተማ
ሰአሊለነ ቅድስት ውዳሴሽ ሲሰማ/፪/
ከሚካኤል ከገብርኤል ጋር ነይልን ከራማ/፪/


#አዝማች.......................................

ዘርፋፋው ቀሚስሽ ይውረድ ከሰማያት/፪/
እንባችን ይታበስ በአንቺ አማላጅነት
የጽዮን ዝማሬ ተሞላች ነፍሳችን/፪/
ንዒ ንዒ ንዒ እንበል እንደ አባቶቻችን/፪/


#አዝማች.......................................

ፍጥረታት ሊድኑ በአማላጅነትሽ/፪/
የዘለዓለም ኪዳን አማኑኤል ሰጠሽ
ትውልድ ይህን አምኖ ብጽእት ይልሻል/፪/
እናቴ መመኪያዬ ምርኩዜ ሆነሻል/፪/


#አዝማች........................................

የልብን ሲያዋዩሽ ሰምተሽ ዝም አትይም/፪/
ችግረኛን አይቶ ልብሽ አይጨክንም
ከዓይን ጥቅሻ ፈጥነሽ ትደርሺለታለሽ/፪/
ከሃዘን ከመከራ ታሳርፊዋለሽ/፪/


#አዝማች.......................................


👉 ዘማሪት ለምለም ከበደ



ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖
ኪዳነ ምህረት
Orthodox Mezmur Channel
ኪዳነ ምህረት | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ



ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖
እንወድሻለን ኪዳነ ምሕረት_ _ ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ(360P)
<unknown>
ኪዳነ ምህረት እንወድሻለን

ለግዚአብሔር ታቦቱ መቅደሱ
ቀርበናል ባንቺ ወደ ንጉሱ
የክብራችን ጌጥ ሽልማት
እንወድሻለን ኪዳነምህት

በጨለማው ላለ ብርሃንን አየ
ለርስቱ ተካፋይ እንዲሆን ተለየ
ወደ ቀድሞ ክብሩ ሊመለስ ዳግመኛ
አንቺ ነበርሽ ተስፍው ለአዳም መዳኛ

አዝ===========
ያንን ሁሉ ዘመናት የፈሰሰው ደም
አለምን ከእስራት ሊፈታ አልቻለም
ወደ ሚሻል ኪዳን በደም ሊያሻግረን
ደምሽን ተዋህዶ መዳኃኒ አለም ዋጀን

አዝ===========
አለን ብዙ ምክንያት አንቺን ምንወድበት
ዓለም ያልተረዳው ያላወቀው እውነት
ያወቀ የተረዳ የመዳኑን ሚስጢር
አያፍርም ክብርሽን ቆሞ ለመናገር

አዝ===========
አውቃለሁ እግዚአብሔር የሰጠሽን ክብር
ላመስግንሽ እኔም ሳልጨምር ሳልቀንስ
ሚባርክሽ ብሩክ ነውና እናቴ
ኪዳነ ምህረት ንገሽ እመቤቴ
አዝ===========         



ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖
እናት አለኝ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
እናት አለኝ

እናት አለኝ የምታብስ እንባ
አያታለው ስወጣ ስገባ
ኪዳነ ምህረት /3/ አንባ መጠጊያ ናት

ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ
እራቆቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደ እኔ ቀርበሻል
ደጓ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል

ኪዳነ ምህረት /3/ አንባ መጠጊያ ናት/

አዝ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

ለዘላለም ንጽህይት በመሆኗ
ከኔ ጋር ነው ህያው ቃልኪዳኗ
ደስተኛ ነኝ ሀዘኔን አልፌ
አጽናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ

ኪዳነ ምህረት /3/ አንባ መጠጊያ ናት/

አዝ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

ከጥፋቱ ውሀ ማረፊያዬ
መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ
የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ በህይወት አለው ጥልቁን ተሻግሬ

ኪዳነ ምህረት /3/ አንባ መጠጊያ ናት/

አዝ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

በእናትነት ህይወቴን ጎብኝታ
ልቤ አረፈ ተነቅሎ በሽታ
ሰንሰለቴ ከእጄ ተቆረጠ
መራራዬ በልጅሽ ጣፈጠ



ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖
ሲነግሩሽ ሰሚ ነሽ
@yemezmurgetemoche
ሲነግሩሽ ሰሚ ነሽ

ያለሽ ልዩ ፀጋ ያለሽ ልዩ ክብር
የሁሉ እመቤት በሠማይ በምድር
አቁራሪተ መዓት ምዕራገ ፀሎት
ሲነግሩሽ ሰሚነሽ ኪዳነ ምህረት


በመከራ ላለ ሁኚለት መፅናኛ
ዕንባውን አብሺው አይዘን ዳግመኛ
ጉድለቱን ሙይለት በፈረሰው ቆመሽ
ስለምታስምሪው በልዩ ኪዳንሽ
     ከኪዳንም በላይ ኪዳንሽ ልዩ ነው  
     እናቴ የሚልሽ አምላክሽ ልጅሽ ነው


ይበጠስ ከእጁ የወህኒው ሰንሰለት
የሞቱ ደብዳቤ ይቀየር በህይወት
አዲስ ተስፋ ሞልተሽ አዲስ ሰው አድርጊው
መቅበዝበዙን ይርሳ ድንግል አረጋጊው
     ከኪዳንም በላይ ኪዳንሽ ልዩ ነው  
     እናቴ የሚልሽ አምላክሽ ልጅሽ ነው


በእንባ የመጣው ይመለስ በደስታ
መጠማቱ ይቅር ይሞላ በእርካታ
ስዕለቱ ሰምሮለት ይቁም ለምስጋና
የአብራኩን ክፋይ አሳቅፊዉና
     ከኪዳንም በላይ ኪዳንሽ ልዩ ነው  
     እናቴ የሚልሽ አምላክሽ ልጅሽ ነው


ተይዞ ለሚኖር በአልጋ ቁራኛ
ምቺው እመቤቴ የደዌውን ዳኛ
መንገርስ ላንቺው ነው መማፀን ወዳንቺ
ተስፋን ለምትቀጥይ ሕልምን ለምትፈቺ
     ከኪዳንም በላይ ኪዳንሽ ልዩ ነው  
     እናቴ የሚልሽ አምላክሽ ልጅሽ ነው

            
ኪዳነ ምህረት - አቤል መክብብ - Kidane mihiret - Abel Mekbib
masresham
ኪዳነ ምሕረት የ ረፍቴ እናት

# ዘማሪ አቤል መክብብ

ኪዳነ ምህረት የዕረፍቴ እናት
ሰላም ሆነ ባንች አማላጅነት
ንፅህት ድንኳን በእምነት ያጌጥኩብሽ
ሰላም ሆነ በአማኑኤል ልጅሽ

የብርሀን ዝናር ባይኖረኝም
በንጉስ ፊት ተሸልም ብቆም
በልጅሽ ነው ውበቴ ማማሩ
በምልጃሽ ነው ስሜ መቀየሩ
በልቤ ላይ ተነበበ ልጅሽ
አሁን ስሜ ተጠርቷል በልጅሽ
ከታች በምድር እስከሰማይ ድረስ
ድርሻየ ነው ስምሽን ማወደስ(2)

ኪዳነ ምህረት የእረፍቴ እናት
……………………………………
……………………………………
……………………………………

የከበረ ሁነሽ ንግግሬ
ቅኔ አነሳሁ ለክብርሽ ዘማሬ
እንደ ዝግባ ከፍ ብየ ብታይ
ወጥቶልኝ ነው በሰማይ ፀሀይ
ስለ ምልጃሽ ዘይቱ ፈሰሰ
አንቺን ይዤ ሙሽራው ደረሰ
ቀንዲሌ ነሽ ድንግል አዛኝቱ
በልጅሽ ነው የነፍሴ ፅናቱ

ኪዳነምህረት የእረፍቴ እናት
……………………………………
……………………………………
…………………………………

ከኤልያብ ቢደምቅ ደም ግባቴ
ማን ሊመርጠኝ ያላንች እናቴ
ተዋብኩብሽ ገፄ በአንች አበራ
አንደበቴ ስምሽን ሲጠራ
እንደ ሙሴ እንደ አሮን በትር
ማምለጫየ ከፈርዖን ቀንበር
ከእንግዲማ እኔ እንዴት አዝናለሁ
አማላጀ አንችን ይዠዤሻለሁ

ኪዳነምረት የእረፍቴ እናት
            
#እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የምህረት ቃል ኪዳን የተቀበለችበት ወርሃዊ መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ

#እንጦጦ ሀመረ ኖህ ኪዳነ ምህረት ገዳም

በአዲስ አበባ ከተማ በስተሰሜን ምሥራቅ በጉለሌ ክፍለ ከተማ የምትገኝ ስመጥርና ታሪካዊ ገዳም ስትሆን በተራራ፣በሸለቆና በወንዞች የተከበበች በመሆኑዋ በተፈጥሮ አቀማመጧ አረንጓዴ የተላበሰች ናት፡፡ ይህም ለቤተክርስቲያኗ ውበትና ግርማ ሞገስ ከመስጠት አልፎ በሚያስደስት ፀጥታ የአዕዋፍ ዝማሬ ተሞልታ ጸጋን እንድትላበስ አድርጓታል፡፡
ይህች ቦታ የተቆረቆረችው በ484 ዓ/ም ሲሆን በ500 ዓ.ም በአባ ሊባኖስ የአንድነት ገዳም ሆና ተቋቋመች፡፡ አባ ሊባኖስ ወደ ሌላ መንፈሳዊ ተልእኮ ለመሄድ መነኮሳቱን ሲሰናበቱ እንዲህ የሚል ትንቢት ተናግረው ነበር ‹‹ልጆቼ ሆይ በሉ ይህችን ቅድስት ቦታ አደራ ሰጥቻችኋለሁ በኋላ ዘመን ታላቅ ቦታ ትሆናለች' አጋንንት ይወገዱባታል' የብዙ ቅዱሳን አፅም ያርፍባታል' ነገስታት ጳጳሳት ይሰግዱባታል' ብዙ መናንያን መጠጊያ ያደርጋታል ቤተ መቅደሷም በወርቅ በብር ተጊጣ ትታነጻለች የአንድነቱም ገዳም ተሻሽሎ ይቋቋምባታል››፡፡ በ9ኛ መቶ ክ/ዘመን ዮዲት ጉዲት የአክሱም ጽዮንን ቤተ መቅደስ ለማቃጠል ስትነሳ ንጉሡ አንበሣ ውድም ታቦተጽዮንን በምሥጢር በማስያዝ ወደ ሸዋ መጥተው በእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነምሕረት ገዳም ታቦተ ጽዮንን አሳድረው ወደ ዝዋይ ደሴት ሲሄዱ ለገዳሟ ንዋየ ቅድሰት ስጦታ አበርክተዋል ጸበሏን ተጠምቀው ቦታውን መርቀው ሄደዋል፡፡
በ12ኛው መቶ ክ/ዘመን ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከንጉሥ ላሊበላ ጋር ወደ ዝቋላ አምባ ሲመጡ በዚህች ገዳም በእንግድነት አድረው በጸበሏ ተጠምቀው ቦታውን ባርከዋል፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ለመነኮሳቱ እንዲህ ብለው ነበር ‹‹ይህች ገዳም ታላቅ ስመጥር ገዳም ትሆናለች ከእርሷ በታች የሚታየው ጫካና ዱር መናገሻ ከተማ ይሆናል፡፡››
አፄ ዘርዓ ያዕቆብም ወደዚህች ገዳም መጥተው አቀማመጧንና የጸበሏን ፈዋሽነት ተመልክተዋል ‹‹ዳሯ እሳት መሐሏ ገነት ይሁን›› ብለው ብዙ ስጦታ አበርክተዋል፡፡ አፄ ልብነ ድንግልም ወደ ገዳሟ መጥተው ተማህጽኖ አድርገው በጸበሏ ተጠምቀው ታቦተ ልደታንና ብዙ ንዋየቅድሳት ሰጥተው ሄደዋል፡፡ በንግስት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት ይህች ገዳም ሐመረ ኖኅ ኪዳነምህረት ገዳም ተብላ ተሰይማለች፡፡
ይህች ቦታ እንደተነገረላት ትንቢት ብዙ ቅዱሳንና ነገሥታት መጥተው የሰገዱባት የባረኳት' ጸበሏ የአጋንንት ድል መንሻ' የብዙ መነኮሳት መጠጊያ 'የህሙማን መፈወሻ' የእመቤታችንን ቃል ኪዳን ለማግኘት ብዙን ጊዜ ለሱባኤ ከሚመረጡ ቦታዎች አንዷ ናት፡፡ ይህች ደብር በ1957 ዓ/ም የተመሠረተ ሰንበት ት/ቤት ሲኖራት በ1984 ዓ/ም በብፁዓን ጳጳሳት ‹‹መርሶ ሕይወት›› /የሕይወት ወደብ/ የሚለውን ስያሜ አግኝቷል፡፡ የገዳሟ ስያሜ ሐመረ ኖኅ ( የኖኅ መርከብ ) እንደሆነ ሁሉ መርሶ ሕይወት ( የሕይወት ወደብ ) በመባሉ ሁለቱ ተዛማችነት አላቸው ፡፡ ይህ ሰንበት ት/ቤት ለየት የሚያደርገው በግል መኖሪያ ቤት በጋሞኛ ቋንቋ ይሰጥ የነበረውን ትምህርት ከ1986 ጀምሮ በሰ/ት/ቤቱ ስር በማቀፍ የወንጌል ትምህርቱን ከመማር ባሻገር ለጋሞ ሕዝብ መንፈሳዊ እንቅስቃሴን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

አዘጋጅ፡- እህተ ማርያም

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘለአለም ትኑር!!!

ሰው ሁሉ ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን !
(ያዕቆብ 1፥19)

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@ortodoxtewahedo
† ምንኩስና ምንድነው? †

★ ሰሞኑን መንኩሻለው ብለህ ለፌስቡክ ፎቶ ልብስ እየቀያየርክ ተርእዮ ፍለጋ(Show) ብዙ የደከምከውና ድራማዊ አክት ያበዛኽው ወንድም ይህንን በደንብ አንብብ

★ ለቤተክርስቲያን ፈተና የሚሆኑባት እንዲህ ለታይታ፣ለገንዘብና ለሥልጣን ፍለጋ ምንኩስናን መረማመጃ የሚያደርጉ ወገበ ነጮች ናቸው ።★

«መጽሐፈ አበው» እንዲህ ይናገራል።
መነኮስ ከሀገሩ ወደሌላ ሀገር ይሂድ። በዚያም በዋሻ፤ በኮረብታው፤ በተራራው ይንቀሳቀስ። በረሃብ፤ በብርድ፤ በጥም፤ በመራቆት፤ በድካም፤ በትጋት ይኑር። ልብሱ የከብት ቁርበት፤ የፍየል ቆዳና ለምድ ይሁን። ሥጋ በሕይወት ዘመኑ አይብላ። የዘወትር ምግቡ የበረሃ ጎመን፤ ቅጠልና የዛፎች ፍሬ ብቻ ይሁን። ካገር አገር አይዙር። ወደሠርግ፤ ወደ ድግስ አይግባ። በሕዝብ መካከል የሚኖር መነኮስ ቢኖር እርሱ ውሸታም ነው። የአጋንንት ረድእ፤ አገልጋይ ነው። ወንድ መነኩሴና ሴት መነኩሲት በአንድ ላይ አይኑር፤ ይራቁ። በአንድ ላይ እየኖሩ፤ በአንድ አጸድ እያደሩ ንጽህ እንጠብቃለን ቢሉ ውሸት ነው። ነብርና ፍየል አንድነት ይኖሩ ዘንድ እንዴት ይቻላል? መነኩሴ ማንንም አይማ። ሃሜተኛ ጸሎተኛ አይደለም። አብዝቶ የሚበላ መነኩሴ የትም እንደሚፈነጭ ፈረስ ነው። መነኩሴ በፀሀይ ግባት አንድ ጊዜ ብቻ ይብላ። ወፎች መብል አይተው በወጥመድ ይያዛሉ። ትልቁ አንበሳ በመብል ምክንያት ወጥመድ ውስጥ ይወድቃል። አዳም በመብል ወደቀ። ይሁዳ ከወጡ አጥልቆ በበላ ጊዜ ሰይጣን ገባበት። ሠይጣን መነኮሳትን በመብል ፤በመጠጥ፤ በሃሜት፤ በሳቅና በስካር ያድናቸዋል። ልቅ፤ ልቅ እየጎረሱ፤ የላመ የጣመ እያግበሰበሱ መነኮስ መባል አይገባቸውም። በእንቅልፍ ተውጠው፤ ከጸሎት ተለይተው እንደአዞ ተገልብጠው እንዲተኙ ያደርጋቸዋል። ዘማውያንም ይሆናሉ። ያኔም አጋንንቱ በመነኮሳቱ ላይ ይዘፍናሉ። በእጃቸውም ይጨበጭባሉ። እንደፈረሶች ሰኮና ሆነው ይረግጡአቸዋል። የዓለምን ጣዕም የቀመሱ፤ የወደዱ መነኮሳት የነፍሳቸውን ደዌ ያያሉ። የነፍሳቸውንም መድኃኒት ይተዋሉ። በሕዝባውያን መካከል የሚመላስ መነኮስ ከቅዱሳን ክብር መድረሻ የለውም። መነኮስ ወደዓለማዊ ችሎት፤ ሸንጎና ፍር አይሂድ። ምሥክር አይሁን። መነኩሴ ማለት ምዉት ማለት ነውና አይቻለሁ፤ ሰምቻለሁ፤ ዳኝነት አውጡልኝ አይበል። ለሕዝባውያን አበ ነፍስ አይሁን። መነኮስ የሞተ ነውና የሚሰማ ጆሮ፤ የሚናገር አፍ የለውም። ዓለም ውስጥ እየኖረ ዓለምን አሸንፋለሁ ቢል ውሸታም ነው። አትመነው። አፉን፤ ጆሮውንና ዓይኑን የማይጠብቅ መነኩሴ ነፍሱን አያድናትም። መነኮስ እነዚህን ሦስት ሰይፎች ካልታጠቀ መነኮስ አይባልም። የዋህነት፤ ትህትናና ድህነት ናቸው። የዋህነት ከቂም፤ ከበቀል ከጥላቻና ከስጋዊ ነገር ሁሉ መራቅ ነው። ትህትና ራስን ዝቅ ማድረግ ሲሆን ድህነት የኔ የሚለው ሀብትና ገንዘብን ሁሉ መናቅ ናቸው። መነኮስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል። በሕይወት ዘመኑ በእንደዚህ ያልተጠበቀ መነኮስ፤ መነኮስ አይደለም።

መ/ር ታሪኩ አበራ

@ortodoxtewahedo
“ምንም እንኳ የመከራ ድሀ ባንሆንም ይህ መከራ ለነጋሪውም ለሰሚውም ከባድ መሆኑን እንገነዘባለን ። “

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

@ortodoxtewahedo
2024/09/29 09:33:30
Back to Top
HTML Embed Code: