Telegram Web Link
#ሐምሌ_7_የቤተ_ክርስቲያን_ማኅቶት#አፈ_በረከት_ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ#ወልዱ_ለአቡነ_በጸሎተ_ሚካኤል_ልደቱና_እረፍቱ_ነው፡፡
ዕረፍቱ የኾነው በሐምሌ 7 (6,705 ዓመተ ዓለም፥ በ2ት እንድቅትዮን፥ በአልቦ አበቅቴ፥ በ7ት ጥንተ ዮን፥ በወንጌላዊው ማቴዎስ ዘመን በዕለተ ረቡዕ) ነው፡፡ ያረፈውም በአፄ ይስሐቅ ጥያቄ የጋራ መናገሻ መድኀኔ ዓለም ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን ባርኮ ሲመለስ በደብር ቅዱስ ደብረ ጽጌ ማርያም ሲኾን ፤ አርድዕቱ ሥጋውን ይዘው ሂደው በአባቱ መካን በደብረ ጎል (አሁን በደብረ ባሕርይ) አሳርፈውታል፡፡
፠ይህ አባት ከ40 በላይ መጻሕፍትን የደረሰና ብዙ መጻሕፍትን እያጻፈ ለመላው ገዳማት ያዳረሰ፤ ጸሓፊ፥ ቅዱስና ጻድቅ፥ ፈላስፋና ደራሲ፥ መናኝና ባሕታዊ፥ ሊቅና ተመራማሪ፥ ገጣሚና በለቅኔ፥ የመጻሕፍት ተርጓሚና የዘመን አቈጣጠር (የአቡሻህር) ሊቅና ተንታኝ፥ አርክቴክትና መሐንዲስ ነው፤ በዚህም ምክንያት በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል፤
፠ዳግማዊ ቄርሎስ (ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ)፥
፠ ዐምደ ሃይማኖት
፠ ዳግማይ ቅዱስ ያሬድ፤
፠ የወርቃማ ዘመን ወርቃማ ደራሲ፤
፠ የቤተ ክርስቲያን ማኅቶት፥
፠ አፈ በረከት
፠ የከሃድያን ዘላፊ፥ የቅዱሳን ፀሐይ …….ተብሏል

ከ40 በላይ ድርሰቶቹ መካከል በአብዛኞቻችን ዘንድ የሚታወቁት 34ቶቹ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፤
1. ✼ ኆኀተ ብርሃን
2. ✼ መዝሙረ ኢየሱስ (ሰላመ ማርያም)
3. ✼ መዝሙረ ድንግል
4. ✼ የማርያም የምስጋና ሰላምታ
5. ✼ ውዳሴ መላእክት
6. ✼ ውዳሴ ነቢያት
7. ✼ ውዳሴ ሐዋርያት
8. ✼ ውዳሴ ሰማዕታት
9. ✼ ውዳሴ ጻድቃን
10. ✼ መጽሐፈ ብርሃን
11. ✼ መጽሐፈ ምሥጢር
12. ✼ መጽሐፈ ሰዐታት ዘመዓልት ወዘሌሊት
13. ✼ መጽሐፈ አርጋኖን
14. ✼ አርጋኖነ ውዳሴ
15. ✼ መሰንቆ መዝሙር
16. ✼ እንዚራ ስብሐት
17. ✼ ውዳሴ መስቀል
18. ✼ ፍካሬ ሃይማኖት
19. ✼ ፍካሬ ሐዋርያት
20. ✼ መጻሕፍተ ቅዳሴያት
21. ✼ ቅዳሴ እግዚእ ካልዕ
22. ✼ መዐዛ ቅዳሴ
23. ✼ ሕይወታ ለማርያም (ሕይወተ ማርያም)
24. ✼ ውዳሴ ስብሐት
25. ✼ ውዳሴ ማርያም ካልዕ
26. ✼ ውዳሴ ስብሐት ወሰላምታ
27. ✼ ማኅሌት ዘነቢያት ወዘሐዋርያት
28. ✼ የሰባቱ ጊዜያት ጸሎት (መልክአ ሕማማት)
29. ✼ ጸሎተ ፈትቶ (ጸሎተ ማዕድ)
30. ✼ ጸሎት ዘ(ቤት)ውስተ ቤት
31. ✼ መልክአ ቊርባን
32. ✼ ተአምኆ ቅዱሳን
33. ✼ ተአምኆታ ለእግዝእትነ ማርያም
34. ✼ ክብረ ቅዱሳን

(በፎቶ ላይ የምታዩት ገዳም፤ በዓለም ብቸኛው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ገዳም የኾነው ደብረ ባሕርይ ነው፡፡ የቦታው አቀማመጥ እጅግ በጣም ማራኪና እንደ ደብረ ዳሞ ሲሆን የሚወጣው በመሰላል ነው፡፡)፤ ገዳሙ የሚገኘው #በደቡብ_ወሎ_በቦረና_አውራጃ ነው፡፡

(አስተጋባኢ /ይህንን ጽሑፍ ከአባቶች በመጠየቅ ፥ መጻሕፍትን በማንበብ ፥ ከታላቁ ገዳም ደብረ ባሕርይ ጋሥጫ ድረስ ሂዶ ያዘጋጀው የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሰሌዳ መጽሔት ዝግጅት ክፍል ነው/፡፡)
አምላከ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የሀበነ በረከተ ወረድኤወረድኤተ

@ortodoxtewahedo
"+ እንኩዋን ለአጋእዝተ ዓለም #ሥላሴ አመታዊ በዓል አደረሳቹ

"+ #ሥሉስ_ቅዱስ +"

=>በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት)
የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ #እግዚአብሔር ነው:: #አብ : #ወልድ : #መንፈስ_ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::

+ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት " #ቅድስት_ሥላሴ " እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም:: የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው
ያድራሉ::

+ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን #ቅዱስ_አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል:: ሥላሴ አኀዜ ዓለም (ዓለምን በእጁ የያዘ) ነው:: ነገር ግን በፍቅር ለሚሻው በፍቅር ይመጣል::

+አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን አጠበ:: (ወይ መታደል!) በጀርባውም አዘላቸው:: (ድንቅ አባት!) ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት::

#ቅድስት_ሣራ ሳቀች::እንደ ዘንድሮ ወገኖቻችን የማሾፍ አይደለም:: ደስታና ጉጉት የፈጠረው እንጂ:: ሥላሴ "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ" ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት ነው " #ይስሐቅ" የተባለው::

+ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን (ሐይመት) የድንግል እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ #አብ ለአጽንኦ: #መንፈስ_ቅዱስ ለአንጽሖ: #ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና::

=>የሥላሴ ቸርነት: የአብርሃም ደግነት: የአበው አባ ጊዮርጊስና
አባ ሲኖዳ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን::

"+ እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ:- 'በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ:: እያበዛሁም አበዛሃለሁ' ብሎ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ በራሱ ማለ:: እንዲሁም እርሱ ከታገሠ በሁዋላ ተስፋውን አገኘ:: +

"+ (ዕብ.6:13)

"+ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር: የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን:: +"+
(ቆሮ. 13:)


@ortodoxtewahedo
Audio
አንደበቱ ተከፈተ ||የሰው ተከታይ አትሁኑ
        
Size:-22.6MB
Length:-1:04:53

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
Audio
"ጌታችን በመርከብ ውስጥ ሕዝቡ በሐይቅ ውስጥ"

Size:-22.7MB
Length:-1:39:03

👉 ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን

@ortodoxtewahedo
📌 "አስታውስ"

➯ ደካማነትህን አስታውስ፣ ያንጊዜ በጣም ጠንቃቃ ትሆናለህ፣ ሊጎዱህ በሚችሉ በትምክህትና በውዳሴ ከንቱም አትሸነፍም፡፡

➯ የተሰጠህን በፍቅር የተሞላ የእግዚአብሔርን ቸርነት አስታውስ፣ ይህም በምስጋና የተሞላ ሕይወት እንድትመራ ያደርግሃል፤ በእግዚአብሔር ፍቅርና ሥራ ላይ ስትታመን ፍጹም የሆነ እምነት በልብህ እያደገ ይመጣል፤ ከእግዚአብሔር ጋር ያሳለፍከው ጊዜ ደግሞ በእምነት እንድትኖር ያበረታታሃል፡፡

➯ የሰዎችን ፍቅርና ካንተ ጋር ያሳለፉትን መልካም ጊዜ አስታውስ፤ የሰዎችን ቀናነት ትጠራጠር ዘንድ ወይም ያደረጉብህን ክፉ ነገር ታስብ ዘንድ ይገባሃልን? የቀደመ ፍቅራቸው ስለ እነርሱ ይማልዳል ያንተንም ቁጣ ያበርዳል፡፡

➯ ሞት እንዳለ አስታውስ፣ እንዲሁ በዓለም ያለ ፈተናም እንደሚያልፍ
✍️"ሁሉ ከንቱ ነው፣ ነፋስንም እንደመከተል ነው፡፡" ማለትን ትረዳለህ፡፡
📖መኬ 1፥14

➯ በእግዚአብሔርፊት መቆምህንና እርሱም እንደሚመለከትህ አስታውስ፣ ያኔ ኃጢአት አትሰራም እግዚአብሔርን ታየዋለህና፡፡

➯ ስለ አንተ የፈሰሰውን የክርስቶስን ክቡር ደም አስታውስ፤ በዚህም ሕይወትህ ያለውን ዋጋ በእርግጥ ታውቃለህ፤ በዓይኖችህ ፊት የከበረ ይሆናል፣ ስለዚህም በከንቱ በመኖር አታጠፋውም፣
✍️"በዋጋ ተገዝታችኋልና"  እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ፡፡
📖1ኛ ቆሮ 6፥20

➯ በወላጆችህ እምነት በተጠመቅህባት ቦታ ለእግዚአብሔር የገባኸውን ቃል አስታውስ፤ ዲያብሎስን፣ ሥራዎቹን ሁሉ፣ ሐሳቦቹንና ጥበቡን፣ ኃይሉንም ትክድ ዘንድ፡፡

➯ በዚህ ዓለም እንግዳመሆንህንና ወደ ሰማያዊው ቤትህ እንደምትመለስ ዘወትር አስታውስ፤ ያን ጊዜ በዚህ ዓለምና በደስታው ተስፋ ማድረግን ትተዋለህ፡፡

➯ በጠባቡ በር መጓዝ ወደ መንግስተ ሰማያት እንደሚያደርስህ አስታውስ፤ ሰፊው ደጅ ፊት ለፊትህ ተከፍቶ ብታየው፣ አልፈኸው ሂድ ከእሱም ራቅ፣ በእርሱ የሄዱ እንዳሉ አልቀዋልና፤ ዘላለማዊው ሕይወትህን አስታውስ፣ ሁልጊዜም ስለዚህ ትጋ፡፡

➯ የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህንና እርሱን መምሰል እንዳለብህ አስታውስ፤ እውነተኞች ከሆኑት ከእግዚአብሔር ልጆች ጋር አካሄድህን አስተካክል፡፡

➯ የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆንህን አስታውስ፡፡ በውስጥህ ያለውንም ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝን፤ ዘወትርም ቅዱስ የእግዚአብሔር ማደሪያ ሁን፡፡

📌 ምንጭ
✍️አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

@ortodoxtewahedo
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛

ደካማነትህን አስታውስ ያን ግዜ በጣም
ጠንቃቃ ትሆናለህ ሊጉዱህ በሚችሉ
በትምክህትና በውዳሴ ከንቱም አትሸነፍም

ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
Audio
የሕይወት ውሃ
        
Size:-32.3MB
Length:-1:32:43

"በቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም የተሰጠ ትምህርት"
በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
ይቅር ስላልከኝ
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
ይቅር ስላልከኝ ነው

ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ

@ortodoxtewahedo
#በገዳማት_የምሕላ_ጸሎት_ታውጇል

ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ  በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የሚፈጸመውን የምሕላ ጸሎት አስመልክቶ ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ  አሜን

‹‹ተማሕለሉ ወሰአሉ ኃበ አቡክሙ ሰማያዊ እስመ አብ ይሁበክሙ ኵሎ ዘሰአልክሙ…አባታችሁ የምትለምኑትን ሁሉ  ይሰጣችኋልና ወደ ሰማይ አባታችሁ ለምኑ፣ ምሕላንም አውጁ›› ኢዩኤል 1፤14 ቅዱስ ያሬድ
በሀገር አስተማማኝ ሰላም ሲጠፋ  በጾም በጸሎት በመወሰን፣ምሕላን በማወጅ ልባዊ በሆነ ተማሕጽኖ ሁሉን ማድረግ ወደሚችለው አምላካችን አግዚአብሔር ምልጃን ማቅረብ የሚያስፈልግ መሆኑን ከሀገራችን ሊቃውንት መካከል የመጀመሪያ  የሆነው  ቅዱስ ያሬድ ከሰማያውያን ዐውደ ማህሌት ሰምቶ በቀሰመው ጣዕመ ዜማ  አበክሮ ይነግረናል፡፡

በመሆኑም ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷልና በእውነት የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ እግዚአብሔር መተላለፋችንን ይቅር እንዲለን፣ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ፍቅር አንድነት፣ ለሕዝባችን ደኅንነት እንዲሰጥልን ከአንድነት ገዳማት ኅብረት በቀረበው ጥያቄ መነሻነት ምሕላ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በሁሉም የሀገራችን ክፍልና በሌሎችም አህጉራተ ዓለም የምትገኙ መነኰሳትና መነኰሳይያት  ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት የገዳማት ኅብረቱን ጥሪ ተቀብላችሁ የምሕላ ጸሎት እንድታደርሱ፣ በጤና ችግር ምክንያት ካልሆነ በስተቀር እስከ ዕርበተ ፀሐይ በመጾም ሱባኤ እንድትይዙ፣ ቋሚ ሲኖዶስ በኅብረተ መንፈስ ቅዱስ ከአደራ ጋር ያሳስባል፡፡

ሁሉም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮችና  ምእመናን  ሀገራዊ ሰላምን፣  መረጋጋትንና ፍቅር አንድነትን ለማስፈን ጾምና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የምታደርጉትን  ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርጋችሁ መደበኛ ሥራችሁን በያላችሁበት ቦታ እየሠራችሁ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆናችሁ በጾም በጸሎት እንድተጉ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

‹‹እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ››
ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ፎቶ Eotc tv

@ortodoxtewahedo
" መሰልቸት የጭንቀት የልጅ ልጅ ነው ስንፍናም ሴት ልጅ ናት ። እሷን ለመልቀቅ ፣ በትጋት መድከም - በጸሎት አትስነፍ ፣ ያኔ መሰልቸት ያልፋል እና ቅንዓት ይመጣል ። እናም በዚህ ትዕግስት እና ትህትና ላይ ከጨመሩ ፣ ከዚያ እርስዎ  ከብዙ ክፋት ያድናል"

ቅዱስ አምብሮስ

@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖

"ወዮ ይኽች ዕለት አብ የቀደሳት ወልድ የባረካት መንፈስ ቅዱስ ከፍ ከፍ ያደረጋት ናት፡፡

በእርሷ ደስ ይበለን፡፡ በእርሷም ኃሤትን እናድርግ ትከብሩባት ዘንድ አክብሯት!

ዘመን ወር ለመባል በእርሷ የታወቃችኹ ሌሎች ዕለታት ኾይ የበዓላትን በኩር ኑ አመስግኗት ይኽችውም የከበረች ሰንበተ ክርስቲያን ናት፡፡"

ቅዳሴ አትናቴዎስ

ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖
አረሳውም_ያንን_እለት_አልዘነጋም_ያን_ደግነት_ሰማዕቷ_ቅድስት_አርሴማ_ደጓ_እናቴ።_አሮን_ቤቢ_6a5c
<unknown>
አልረሳውም ያንን ዕለት

አልረሳውም ያንን ዕለት
አልዘነጋው ያን ደግነት
እናቴ ሆይ ምልሽ ኪዳነ ምሕረት
እምዬ ሆይ ምልሽ ኪዳነ ምሕረት
ስላለኝ ነው ምክንያት/፪/


ለሠው ተናግሬ ያልተረዳኝ ሰው
ዕንባዬ በምሬት ከዓይኔ የሚፈሰው
የቤቴን ገመና ሁሉን ስነግርሽ
አዛኝ እህት ነሽና እራራልኝ ልብሽ
አረሳው መቼም የአንቺን ደግነት/፪/
ውለታ አለብኝ ኪዳነ ምሕረት

አዝ__

ልቤ በሐዘን ጠቁሮ ውስጤ እየደማ
በቅረዜ ሲጨልም ስጓዝ በጨለማ
በራፌን ዘግቼ ዝምብዬ አለቅሳለሁ
አይኔን አቀርቅሬ እናቴ እልሻለሁ
ዘንበል አልሽልኝ ሠምተሽ ፆሎቴን/፪/
አልተጸየፍሽም ብቸኝነቴን

አዝ__

እናት የለኝ ብዬ ከቶም አልከፋ
እኔስ አይቻለሁ ስትሞይኝ በተስፋ
ምድራዋዊ እናቴ ለጊዜው ነው ፍቅሯ
ያንቺስ ግን ልዩ ነው እረ ስንቱን ላውራ
ማርያም ማርያም ብል አልሠለችሽ/፪/
በልቤ ጽላት ስለ ታተምሽ

አዝ___

ሲረበኝ መጥተሻል ሲጠመኝ ደርሰሻል
ለጎደለው ቤቴ በረከት ሆነሻል
ጭንቄም ቀለለልኝ ሐዘኔም ራቀ
ያስጨነቀኝ ጠላት ራሱ ተጨነቀ
መዳኒት ወልደሽ ዳኩኝ ከመሜ/፪/
ይኸው ዘመርኩኝ በምልጃሽ ቆሜ



ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖
ደጅ ጠናሁ
ዝማሬ ዳዊት
ደጅ_ጠናሁ

ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምህረትን
ተፅናናሁኝ ረሳሁ ሀዘኔን
የአምላክ እናት እመቤታችንን
ሞገስ ሁኚኝ ቀሪው ዘመኔን

የመከራው ዘመን አለፈ እንደዋዛ
አንቺን ተጠግቼ የአለሟን ቤዛ
የልጅሽ ቸርነት የአንቺ ደግነት
ባርያሽን ሰውሪኝ ከአስጨናቂው ሞት
እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያሁሉ መከራ
እምባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንቺ እየታበሰ ሰላም ለኪ

#አዝ

ልቤ ባንቺ ፀና ከፍ ከፍም አለ
በጠላቶቼ ላይ አፌ ተናገረ
በማዳንሽ ስራ ባሪያሽ ደስ ብሎኛል
የኃያላኑን ቀስት ልጅሽ ሰብሮልኛል
እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያሁሉ መከራ
እምባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ ባንቺ የታበሰ ሰላም ለኪ

#አዝ

እጄ ባዶ ሲሆን ወዳጆቼም ሸሹኝ
በመርገም ምክራቸው ሊለያዩን ሲሹ
እርሱ የሰጠኝን እሱ ወሰደ አልኳቸው
እመቤቴ አለችኝ ብዬ አሳፈርኳቸው
እናቴ ስምሽን ሰጠራ አለፈ ያሁሉ መከራ
እምባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንቺ እየታበሰ ሰላም ለኪ

#አዝ

በአውደ ምሕረቱ ሆኜ ስጠራት
ዘንበል ብላ አየችን ኪዳነ ምህረት
ሀሳብሽን ምንም የለም የሚመስለው
እረፍት ያገኘሁት እናቴ ባንቺ ነው
እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያሁሉ መከራ
እምባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ ባንቺ እየታበሰ ሰላም ለኪ



ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

📖📖📖📖📖📖📖📖📖
2024/09/29 11:26:41
Back to Top
HTML Embed Code: