Telegram Web Link
የብፅዕነታቸው በረከት ትድረሰን። ትጠብቀንም። አሜን!!!

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
††† >ግንቦት 24 ቀን እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የስደት
በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††

=>የአርያም ንግሥት: የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ
አምላክ ልጇን አዝላ በዚህች ቀን ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች::

+በወንጌል ላይ (ማቴ. 2:1-18) እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በ2 ዓመቱ
የጥበብ ሰዎች (ሰብአ ሰገል) ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት: ወርቅ
እጣን ከርቤውን ገበሩ: አገቡለት::

+ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ
ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 1 አምላክ ልጇን
አዝላ: በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቁዋጥራ: ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት
ወጣች::

+ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ በመከራ: በረሃብና በጥም: በሐዘንና በድካም:
በላበትና በእንባ ተጉዛ በዚሕች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታለች::

+የአምላክ እናቱ
*እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች::
*ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች::
*የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች::
*የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች::
*የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች::
*እመ አምላክ ተራበች: ተጠማች: ታረዘች: ደከመች: አዘነች: አለቀሰች:
እግሯ ደማ: ተንገላታች::

+ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን
እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት:
ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኩዋ ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ::

+አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅዱስ ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል::
ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን
መርጠዋልና::

=>መድኃኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ?
ለምንስ ስደቱን ወደ ግብፅና ኢትዮዽያ አደረገ?

1.ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ
ተነግሯልና (ኢሳ. 19:1, ዕን. 3:7)

2.ምሳሌውን ለመፈጸም:: የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም: ያዕቆብ (እሥራኤል):
ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና::

3.ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: (ኢሳ. 19:1)

4.የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ::

5.ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: ሰው ባይሆን
ኑሮ አይሰደድም ነበርና:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም::
ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና::

6.ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና

7.የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው::

=>ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግስተ ሰማያት ስደት
ይሠውረን:: ከስደቱ በረከትም ያድለን::

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
"ጉዳይ ከሌለኝ ከሀገረ ስብከቴ ወጥቼ አላድርም"

…እሑድና ሰኞ ዕለት ዲላ ከተማ ነበርን፡፡ ማግሰኞ ጠዋት ብፁዕ አባታችንን ተሰናብተን ለመውጣት ከቢሯቸው ኼድን፤ በብሩህ ገጽ ተቀበሉን፡፡ ጥቂት ተወያይተን ስንወጣ ከመኻላችን አንዱ"ለቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ሲመጡ እናገኝዎታለን" አላቸው፡፡
"ያንጊዜ እንኳ ሰዓት የሚኖረኝ አይመስለኝም። የሲኖዶሱ ስብሰባ ሲጀምር እመጣለሁ፤ ሲያልቅ ወደሀገረ ስብከቴ ቶሎ እመለሳለኹ፤ ጉዳይ ከሌለኝ ከሀገረ ስብከቴ ወጥቼ አላድርም"፡፡ ብለው መለሱ፡፡

በእርግጥ በሀገረ ስብከታቸውም ብዙ ባለ ጉዳይ የለም፡፡ እርሳቸው ናቸው ወደባለጉዳዮች የሚኼዱ፡፡
የንግሥ በዐላትን ብዙ መምህራንና ካህናት ባሉበት ቦታ አይውሉም፡፡
ቀዳሽ በሌለበት፣መምህር በታጣበት፣ ለመኪና ጉዞ በማይመች ሥፍራ በእግር ተጉዘው ቀድሰው አስተምረው ይመለሳሉ፡፡ ሰኞ ዕለት ያደረጉት ይኽንን ነው፡፡ ብዙ አገልጋዮች ያሉበትን የንግሥ በዐል ጥለው፥ ካህናት ወደሌሉበት ገጠራማ ቤተክርስቲያን ነው ኼደው የዋሉ፡፡

አካኼዳቸውም ውዳሴ ከንቱ አይደለም፡፡ ትርፍ ያለው ጉዞ ነው፡፡ የአብነት ትምህርት ቤቶችን ይሠራሉ፤
ሃይማኖታችንን አንተውም በማለታቸው ብዙ መከራ የሚደርስባቸውን ምእመናን በትምህርት ያበርታሉ፤በእያንዳንዱ ጉዟቸው አዳዲስ አማንያንን ወደቅድስት ቤተክርስቲያን ይጨምራሉ፡፡
በዚያ ሀገረ ስብከት ቄስ አይተን እንሙት ያሉ ምእመናን ነበሩ፡፡ እግዚአብሔር በቋንቋቸው የሚያስተምርና የሚቀድስ ጳጳስ ላከላቸው፡፡
ወኢትሜህርዎሙ በውዕየተ ልብ ዳዕሙ በሥላቅ፤ [ስለሃይማኖታችሁ]በዋዛ ፈዛዛ እንጂ ልባችሁ እየነደደ አታስተምሩም"
የሚለው የሠለስቱ ምእት ተግሣጽ ያልነካቸው
ብፁዕ አቡነ ገሪማ የጌዴኦ ቡርጂና አማሮ አህጉረ ስብከት ጳጳስ፡፡

መልካም ዕረኝነትን እነሆ በዚያ አየናት!

እንደ ተቋም፥ እርስ በእርስ ከመናቆር አባዜ ወጥተው፥ ለበጎቻቸው ራሳቸውን ሠጥተው የሚደክሙ ጥቂት ብፁዓን አባቶችን ስናይ ተስፋችን ሕያው ይኾናል፡፡

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
“ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም "

እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም በጤና አደረሰን አደሰችሁ ።

ጽሩይ እምወርቅ ወእምብሩር ንጡፍ ወኅሩይ እምአእላፍ ሀብተ ማርያም መልአክ ዘውገ ኪሩብ ቀሊለ ክንፍ አማን ስሙዐ ዜና እስከ አጽናፍ ፡፡

ሰላም ለፅንሰትከ እማህፀነ ቅድስት ዮስቴና በብሥራተ ጻድቅ ባሕታዊ ሠናየ ዜና ሐብተ ማርያም ጴጥሮስ ሐዋርያ ወልደ ዮና መሐረኒ ምግባረ ጽድቅ ወጸግወኒ ልቦና አፍቅሮ ቢጽ እኃሥሥ ዘምስለ ፍጽምት ትሕትና::

(መልክአ አቡነ ሀብተ ማርያም)

" እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና ::
ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና ::
ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . . ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ :: የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል ::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል ::
የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው :: በእርምጃውም አይሰናከልም:: "
(መዝ 36፥28-31 )

ቅዱስ አባታችን ፅንሰታቸው ነሐሴ 26
ልደታቸው ግንቦት 26
ዕረፍታቸው ኅዳር 26 ነው ፡፡

ኦ አምላከ አቡነ ሀብተ ማርያም ዕቀቦ ወአድኅኖ ወባልሆ እመከራ ሥጋ ወነፍስ ወእምኩሉ ተቃራኒ ወእምኩልነ ክቡር ሀብተ ማርያም ለዓለም ዓለም አሜን ለይኩን ለይኩን ::

ወስብሐት ለእግዚአብሔር !

@ortodoxtewahedo
#ነሀሴ 26 በዓለ ፅንሰቱ ለወላዴ አእላፍ አቡነ ኢየሱስ ሞአ ዘ ሃይቅ እስጢፋኖስ ወ አቡነ ሀብተ ማርያም ጻድቅ

"+ እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና:: ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና:: ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . .
ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ:: የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል:: የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም:: +"+

(መዝ. 36:28-31)

"+ ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማሕበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ:: የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ:: እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ:: ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ:: እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና:: ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል::

+ (1ዼጥ. 5:3)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

@ortodoxtewahedo
መረጃ የአቡነ ጴጥሮስ ጉዳይ

(ግንቦት 26/ 2016 ዓ.ም ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ)

የአቡነ ጴጥሮስን ጉዳይ በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶሱ ዛሬ ዉዉይት ያደረገ ሲሆን በዚህ መሠረት ፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣
አቡነ አብርሃም ፣ አቡነ ኤርምያስ ፣ አቡነ ጎርጎርዮስ
፣ አቡነ ሳዊሮስ ፣ አቡነ ሄኖክ ፣ አቡነ ናትናኤል ዘሚኔንሶታ በመሆን መንግስትን እንዲያናግሩ፣ችግሩ እንዲፈታና ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እንዲደረግ ዛሬ ወስኗል ፣ ይሳካ ይሆን እሱን የምናየው ነው ዝርዝር መረጃውን በመደበኛ ፕሮግራማችን ይጠብቁን ::

@ortodoxtewahedo
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ምስለ ኖኅ
ኪዳነ ዘአቀምከ፤ ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ፤
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ ወሥነ
ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ወከመ
ወሬዛ ኃየል መላትሒሁ ጉርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ
ዘወይጠል፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ሰማየ ወምድረ ዘአንተ
ፈጠርከ፤ ፀሐየ ወወርኀ ዘአስተዋደድከ፤ ወመኑ መሐሪ
ዘከማከ፤ በከዋክብት ሰማየ ዘከለልከ፤ ወመኑ መሐሪ
ዘከማከ፤ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ ወመኑ መሐሪ
ዘከማከ፤ ቀደሳ ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት፤ ወአልዓላ
እምኵሉ ዕለት፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ ወኵሉ ይሴፎ ኪያከ፤
#ትርጉም
ከኖኅ ጋር ቃል ኪዳን የገባህ እንዳንተ ይቅር ባይ ማነው
ለእስራኤል ልጆች መናን ያወረድክ፤ ምድርን በአበቦች
ያስጌጥክ፤ እንዳንተ ይቅር ባይ ማነው ? የምድረ በዳውን
አራዊት ከወዳጆችህ ጋር ያስማማህ እንዳንተ ያለ ይቅር ባይ
ማነው፤ ጉንጮቹ እንደ ዋልያ እንቦሳ ፈጣኖች ናቸው፤
አንደበቱ ጣፋጭ ነው፤ ተወዳጅነቱ እንደ ፌቆ ግልገል ነው፤
ሰማይና ምድርን የፈጠርክ፤ ፀሐይና ጨረቃን ያስማማህ፤
ሰማይን በከዋክብት የሸፈንክ፤ ምድርን በአበቦች ያሸበረቅህ፤
ሰንበትን ያከበርካት ከዕለታትም ለይተህ ከፍከፍያደረግኻት፤
አቤት!! እንዳንተ ይቅር ባይ ማንም የለምና ኹሉም አንተን
ተስፋ ያደርጋሉ።
#እንኳን_ለዓለም_ጌታ_ለፍጥረታት_አምላክ_ለነገስታት_ንጉስ_ልዑለ_ባህሪ_ለሆነው_ለአምላካችን_ለመድሐኒታችን_መድኃኒዓለም_ወርሀዊ_በዓል_አደረሰን !

@ortodoxtewahedo
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔

ኦ አባይ  ሀገር በሀኪ ኢትዮጵያ 
ሀገረ  ነጎድጓድ ሀገረ እግዚአብሔር

ተንስኢ ወልበሲ ሀይለ እግዚአብሔር  እስመ ተንስኡ ፀላእትኪ ወአብቀዋ ኦሙ ላይለ ህዝብኪ

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

#መልካም እለተ ይሁንልን

ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
2024/09/27 13:33:47
Back to Top
HTML Embed Code: