Telegram Web Link
#እኩለ ጾም ደብረ ዘይት

#ምስባክ

እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽእ
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ።

ትርጉም፦እግዚአብሔር ግልጥ ኾኖ ይመጣል አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም እሳት እፊቱ ይቃጠላል።

(የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 5)

📜3፤ በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።

📜4፤ የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና።

📜5፤ የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና።

📜6፤ ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና።

📜7፤ የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና።

📜8፤ ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና።

📜9፤ የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።

📜10፤ ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።

📜11፤ ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።

📜12፤ ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።

@ortodoxtewahedo
#በስልጤ ዞን

ልዩ የበዓለ ንግሥ ጉባዔ በጦራ ደብረ ታቦር ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤተክርስቲያን

በዓለ ጽንሰትንና ደብረ ዘይትን ምክንያት በማድረግ ከቀን 28-29 የፊታችን ቅዳሜና እሑድ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ተዘጋጅቷል በዕለቱም መምህራነ ወንጌልና ዘማርያን ተጋብዘዋል። የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ።
ነገ 10:00 ሰዓት ላይ የዋዜማ መርሐግብር ይጀምራል። 11:00 ላይ የበገና የመሰንቆ የዝማሬ አገልግሎትና የወንጌል ትምህርት ይቀጥላል። መቅረት ያስቆጫል።

በአንድነት ሆነን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን ህይወት የሆነውን የቃሉን ማዕድ እንመገባለን።

"የእግዚአብሔር ድምፅ ከተማይቱን ይጠራታል"
ትንቢተ ሚክያስ 6:9

@ortodoxtewahedo
#ሰንበተ ክርስትያን

እሑድ ማለት"አሐደ" ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲኾን ትርጉሙ የመጀመሪያ እንደማለት ነው። ይኽች ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ "ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን " በመባል ትታወቃለች።

ዮሐንስም በራዕዩ "የጌታ ቀን" ያላት ናት
(ራዕይ 1፥10)

ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ "ዕለተ እግዚአብሔር" የሚላት ዕለተ እሑድ ናት።

መልካም ዕለተ ሰንበት ይኹንልን

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
ፍኖተ ጽድቅ አገልግሎቱ ከቤተክርስቲያን አስተምህሮና ቀኖና የተቃረነ እንደነበረ በማመን ይቅርታ መጠየቁ ተሰምቷል፡፡ በአንድ ወቅት ደግሞ የጀርባ አጥንት የነበሩት እነ አቡነ ሳዊሮስ ለፍኖተ ጽድቅ አንገታችንን እስንሰጣለን በማለት ጥብቅና ሲቆሙለት እንደነበረ እናስታውሳለን፡፡ ..........አሁንም ቢሆን ነገሩ ያደቆነ ሰይጣን ...ነውና ነገሩ አውደ ምህረት ላይ መቅረብ የለባቸው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አባል ብቻ ሆነው ነው መቀጠል ያለባቸው ምዕመናን ሐሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን::

@ortodoxtewahedo
††† መጋቢት 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት (እመቤታችንን ያበሠረበት መታሠቢያ)
2.ቅዱስ ሶምሶን (መስፍነ እስራኤል)
3.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ (ፍልሠቱ)
4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘአክሱም (ድርሳነ ሚካኤልን መጻፉ የሚነገርለት አባት)
5.እግዚአብሔር ውሃን ከ3 ከፈለው (ጠፈርን ፈጠረ)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
2.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ (ሐዋርያ)
3.አባ ሣሉሲ ክቡር
4.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
5.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት

††† ". . . በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን: ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም . . ." †††
(ዳን. 9:20)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

@ortodoxtewahedo
#ግሸን ደብረ ከርቤ

" እስከ ማዕዜኑ እግዚኦ ትረስዓኒ ለግሙራ "

@ortodoxtewahedo
(፩)ልደታ ለማርያም እናቴ

#ድንግል ሆይ
የነብያት-ትንቢታቸው
የሐዋርያት-ሞገሳቸው
የሰማዕታት-አክሊላቸው
የመላእክት-እህታቸው
የምንዱባን-እናታቸው
የነዳያን - ምግባቸው
የደካሞች-ምርኩዛቸው
የደናግል-መመኪያቸው
አንቺ ነሽ🌹
እመቤቴ ሆይ ልደትሽ ልደታችን ነው እንኳን አደረሳችሁ🌹🌹

👉 ልደታ ለማርያም

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ለዕውራን ብርሃናቸው ለተጠሙትም የወይን ምንጫቸው ሆይ፤ ወደኔ ፈጥነሽ ነይ፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ ኦ ወዮ ትተይኝ ይሆን? ኦ ወዮ ትንቂኝ ይሆን? እንግዲያ የልቤን ኅዘን ለማን እነግረው ይሆን፡፡

💠መልክአ ኤዶም

የቃል ኪዳኗ እመቤት ምልጃዋ አይለየን ።

@ortodoxtewahedo
2024/09/29 21:26:18
Back to Top
HTML Embed Code: