ብሔር ብሔረሰቦች እና የእምነት ህብረት እንለይ❗
Amani Amani
እያንዳንዱ ቸርች ለተከታዮቻቸው የሚያስተምሯቸውን ትምህርቶች ልዩነት እንመልከት።
1, እግዚአብሔር የሚድኑትን አስቀድሞ መርጧል
2, ህፃናትን ማጥመቅ ያስፈልጋል ፤ ጥምቀትም ለድኀነት አስፈላጊ ነው
3,እግዚአብሔር ለሁሉም የሰው ልጅ ድኀነት በነፃ ፈቃድ ሰጥቷል
4, ጥምቀት ምስክርነት እንጂ ለድኀነት ጥቅም የለውም፤ህፃናትም መጠመቅ የለባቸውም
5, አንዴ የዳኑ ሰዎች ድኀነታቸው አያጡም
6, ጌታ ከድንግል ማርያም ስጋ እና ነፍስን አልነሳም
7, አንዴ የዳነ ሰው ድኀነቱን ሊያጣ ይችላል
8, ጌታ ከድንግል ማርያም ስጋ እና ነፍስን ነስቷል
9,ህብስቱ እና ወይኑ እውነተኛ የጌታ ስጋ እና ደም ነው
10, ህብስቱ እና ወይኑ እውነተኛ የጌታ ስጋ እና ደም ሳይሆን ምሳሌ ነው
አነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው። 😊
ጌታ ግን ምን ብሎ ፀለየ❓:-
" ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም፤ አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፥ አንተ፥ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 17: 20-21)
አንድ ሳይኮን❓
አንድ የጌታ ቃል ሳይያዝ❓
አንድ መረዳት ሳይኖር❓
ከአንድ መንፈስ ሳይቀዱ❓
በአንድ ልብ ቃለ እግዚአብሔር ሳይቀበሉ❓
እንዴት በአንድ ቦታ መሰባሰብ ይቻላል❓
ጥቅሙስ ምንድንነው❓
**=-=-=-==_+_+_+_+_+
የኢዩጩፋ ኢየሱስ
የእስራኤል ዳንሳ ኢየሱስ
የጆይ ጭሮ ኢየሱስ
የመካነ ሕይወት ኢየሱስ
የሙሉ ወንጌል ኢየሱስ
የቃለሕይወት ኢየሱስ
የፓስተር ዮናታን ኢየሱስ
ወዘተ ይለያያሉ።
ይህ ፖለቲካ መስሪያ በመንግሥት የተቀነባበረ ሴራ ነው
@ortodoxtewahedo

✝️ኑ! ቸርነትን እናድርግ ✝️
መጋቢት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ፣
+++
ገቢው በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው ማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ የተጎዱ ወገኖቻችንን፣ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ለመደገፍ የሚውል።
የመግቢያ ትኬቱን፡-
1. በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 4ኛ ወለል (ቤተ አብርሃም)
2. በወረዳ ማእከላት ጽ/ቤቶች
3. በማኅበረ ቅዱሳን ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ሱቆች
4. በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ የዕለት ገንዘብ መሰብሰቢያዎች
5. በአሐዱ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች
6. በሰ/ት/ቤት ጽ/ቤቶች
ለበለጠ መረጃ
• 09 44 71 82 82
• 09 42 40 76 60
ማኅበረ ቅዱሳን
👉 @ortodoxtewahedo

ማኅበረ ቅዱሳን "ኑ ቸርነትን እናድርግ" በሚል መሪ ቃል የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ሊያከናውን ነው።
መጋቢት 11 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን "ኑ ቸርነትን እናድርግ" በሚል መሪ ቃል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር መጋቢት 15 ቀን ከቀኑ 7:00 ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ አዘጋጀ።
ማኅበሩ በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ ያገኘና ላለፉት 31 ዓመታት እያገለገለ የሚገኝ ሲሆን ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች የመጀመሪያው የማኅበራዊ ድጋፍ አገልግሎት እንደሆነና በየጊዜው ለሚከሰቱ ችግሮች ድጋፍ እያደረገ እንደነበር አስታውሷል።
በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ከፍተኛ የሆነ የማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን በዋናነት በሁለት ቦታዎች በዋግኽምራ እና ሰሜን ጎንደር ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የተስፋፋ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ ገዳማትና አድባራት ቀጥተኛ ተጎጂ እንደሆኑ በዚህም የአብነት ትምህርት ቤቶች እስከመበተን የደረሱም እንዳሉ ስለታወቀ በዚህ ፕሮጀክት መተካታቸው ተነግሯል።
የገቢ ማሰባሰቢያው በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው ማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ የተጎዱ ወገኖቻችንን፣ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶችን ለመደገፍ የሚውል እንደሆነ ተገልጿል ።
በየጊዜው በሚከሰከቱ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት አስቸጋሪ ቢሆንም ወገን ለወገኑ መርዳት ስላለበት ሌሎች አገልግሎቶችን ለጊዜው በመግታት ኅብረተሰቡን በማስተባበር ትኩረት ተደርጎ እንዲሠራ የተወሰነ ሲሆን በተለይም ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች ላይ በስፋት ድጋፍና እርዳታ እንደሚደረግ በዚህ የጾም ወቅት ደግሞ ምጽዋት ማድረግ አግባብም እንደሆነ የማኅበሩ ሰብሳቢ ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም በመግለጫው ተናግረዋል።
አያይዘውም ሁላችንም የቤተ ክርስቲያን ልጆች በዚህ ወቅት በአንድ ልብ እና ሀሳብ በመሆን ለተቸገሩት መድረስ እንደሚገባ ፤ ብፁዓን አባቶች በማስተማር ፤ ማኅበራት ፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ፣ አጠቃላይ የቤተክርስቲያን ልጅ የሆነ ሁሉ በገንዘብ በዓይነት ሊበላሹ የማይችሉ የታሸጉ ምግቦችን ጨምሮ ድጋፍ እንዲያደርግ ማኅበሩ ጥሪ ያቀርባል ብለዋል።
በዕለቱ ብፁዓን አባቶች ቡራኬና ቃለ ምዕዳን ይሰጣሉ ፤ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን መምህራን ትምህርተ ወንጌል ፤ የመዝሙር አገልግሎት፤ ዶክመንተሪ ቪዲዮ የሚቀርብ ሲሆን በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ የገዳማትና አድባራት አባቶችን ጨምሮ የሚደረግ መርሐ ግብር ይሆናል።
ምዕመናን ክርስቲያናዊ አለባበስ እንዲለብሱ እና የአቅማቸውን ያህል እንዲለግሱ እንዲሁም የተዘጋጀው ገቢ ማሰባሰቢያ እስከ ሚያዝያ 27 ድረስ ለሁለት ወራት በተለያየ መልኩ የሚቀጥል መሆኑንም በመግለጫው አያይዘው ገልጸዋል።
አሁን ባዘጋጀው የማኅበራዊ ድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሩን መሳተፍ ለማይችሉ በተለያዩ በሚዘጋጁ የድጋፍ ማድረጊያዎች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።
የመርሐ ግብሩን የመግቢያ ትኬት :-
1. በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 4ኛ ወለል (ቤተ አብርሃም)
2. በወረዳ ማዕከላት ጽ/ቤቶች

"ከዚህ በፊት የተቃጠሉብንን አብያተ ክርስቲያናት መልሰን ሠርተን ለማክበር ጫፍ ስንደርስ እያፈረሱብን በሀዘን ላይ ሀዘን እየተጨመረብን ይገኛል።"
መጋቤ ሐዲስ ነቅዓጥበብ አባቡ
መጋቢት 11 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ)
የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ፈተና በተመለከተ መግለጫ ሰጡ።
የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ አባቡ (ቀሲስ) በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ፈተና እና ችግር በተመለከተ የሰጡት ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ስለወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ከሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የተሰጠ መግለጫ።
እግዚኦ ቦኡ አሕዛብ ውስተ ርስትከ ወአርኰሱ ጽርሐ መቅደስከ ወረሰይዋ ለኢየሩሳሌም ከመ ልገተ ዓቃቤ ቀምሕ ፤ አቤቱ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ የቅድስናህንም መቅደስ አረከሱ ኢየሩሳሌምንም እንደ መደብ አደረጓት መዝ 78:1
ጥንታዊት ፣ ታሪካዊት ፤ ሐዋርያዊት ፣ ዓለም አቀፋዊት እና ኢትዮጵያዊት ፊተኛዪቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ የሀገረ መንግሥት ግንባታ በታሪክ ፣ በትምህርት ፣ በኪነ ሕንጻ እና በመሳሰሉት ሁለተናዊ ቁልፍ ጉዳዮች ያበረከተችው በጎ አስተዋጽኦ ማንም ሊክደው የማይችል ዓለም ያወቀው ፀሐይ የሞቀው የአደባባይ ምሥጢር ነው።
ይሁን እንጂ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ታላቋ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ለሀገር ክብር ለሕዝቦቿ አንድነት የዋለችው ውለታ ተዘንግቶ ክብሯን በሚነካና መብቷን በሚጋፋ ሁኔታ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንዲሉ አበው ያለ ስሟ ስም በመስጠት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ፣ በአገልጋይ ካህናት ላይ እና በምእመናን ልጆቿ ላይ በርካታ አሳዛኝ እና ልበ ሰባሪ ድርጊቶች ተፈጽመዋል ፣ አሁንም ባላሰለሰ ሁኔታ እየተፈጸሙ ይገኛሉ።
በዚህም መሠረት በሀገረ ስብከታችን ባለፉት ጥቂት ዓመታት በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ቅጥራቸው ተደፍሮ ፈርሰዋል ንዋያተ ቅድሳቶቻቸው ተቃጥለዋል ካህናት አገልጋዮቿ ተገለዋል ምእመናን ልጆቿ ሞተዋል ከሞቀ ቀያቸው ከደመቀ ቤታቸው ተፈናቅለው ለከፋ የሕይወት እንግልት ተዳርገዋል።
ችግሩ ከነገ ዛሬ ይቀላል በማለት በትዕግሥት ለማለፍ በአባቶቻችን መንገድ እና ጥበብ ለማለፍ ብንሞክርም ችግሩ ግን ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ በመምጣቱ በጣም አዝነናል ልባችንም በእጅጉ ተሰብሯል።
አሁን እንኳን በዚህ ታላቅ ጾም ተረጋግተን ፊታችንን ወደ እግዚአብሔር በፍጹም ንስሐ መልሰን ስለሀገራችን ስለ ቤተ ክርስቲያናችን እና ስለሕዝባችን ሰላም በምናለቅስበት ሰዓት ሁልጊዜ የመከራ ገፈት ቀማሽ በሆነው የይፋት ቀጠና ከዚህ በፊት የተቃጠሉብንን አብያተ ክርስቲያናት መልሰን ሠርተን ለማክበር ጫፍ ስንደርስ እያፈረሱብን በሀዘን ላይ ሀዘን እየተጨመረብን ይገኛል።
አሁንም በዚህ ወቅት በኤፍራታ እና ግድም ወረዳ ቤተ ክህነት የካሬ ቆሬ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን በድጋሚ ወድሟል የሞላሌ ቅዱስ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ተጎድቷል።
በተመሳሳይ በቀወት ወረዳ ቤተ ክህነት የኩሪብሪ ቅዱስ ሚካኤል እና የዋጮ ቅዱስ በዓለ ወልድ አብያተ ክርስቲያናት መጎዳታቸውን እና የየለን ቅድስት ማርያም ንዋያተ ቅድሳት መዘረፉ ሀዘናችንን እጽፍ ድርብ አድርጎታል።
ስለዚህ፦
1.ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሰላም ቤት የአንድነት ተምሳሌት የሀገር ባለውለታ ያለ ቋንቋ ፣ ያለዘር እና ያለከለር ልዩነት ለሁሉም በእኩልነት መንፈሳዊ አገልግሎቷን ተደራሽ አድራጊ መሆኗ ታውቆ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚደረገውን ግፍ እና አስነዋሪ ነገር ሁሉ በፅኑዕ እንቃወማለን የሚመለከተው አካልም በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚፈጸውን ድፍረት የተሞላበት በደል እና ነውር ያስቆምልን ዘንድ በአጽንኦንት እንጠይቃለን።
2.የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት ማረጋገጥ የሚገባው አካል የምእመናን ልጆቻችንን በሰላም ወጥቶ በሰላም የመግባት ሰላም እና ደኅንነት በማረጋገጥ ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው በችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን ወደ ቤት ቀያቸው እንዲመለሱ አስፈላጊው ሁሉ ይደረግልን ዘንድ በቤተ ክርስቲያናችን ስም እናሳስባለን።
3.ለወገን ደራሽ ወገን በመሆኑ በይፋት ቀጠና እና በምንጃር ወረዳ ቤተ ክህነት ከአውራ ጎዳና አካባቢ ከቤታቸው እና ከቀያቸው ተፈናቅለው ላሉ ወገኖቻችን ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውን በሙሉ የድጋፍ እጃችሁን ትዘረጉልን ዘንድ በጸሎታችሁም ታስቡን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን።

ፕትርክናን እምቢኝ አሉ 🤔
ዘንድሮ ከምስራቅ ኦርቶዶክስ አብያተክርስቲያናት አባቶች እየተሰማ ያለው ዜና በአግራሞት አፋችንን እያስከፈተ መቀጠሉን ቀጥሏል
ብጹዕ አቡነ ኒኮሎዝ ይባላሉ የፕሎፕዲቭ ሊቀ ጳጳስ ናቸው
ሊቀ ጳጳሱ የቡልጋሪያ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ዕረፍትን ተከትሎ ለቀጣይ ፓትርያርክነት በእጩነት ቢቀርቡም እርሳቸው ግን #እምቢኝ ብለዋል
ከፕትርክናው እጩነትም ራሳቸውን አግለዋል።
አሉ የኛዎቹ ቆብ በጉልበት የሚቀሙ!

#ደጉ እና ሩሩህ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ወርሀዊ በዓል እንኳን አደረሳቹ።
"ቅዱስ ሚካኤል ኾይ"
እንደ ፀሐይ ሥነ ጸዳል የሚያንጸባርቁ በሰማይ ላይ ለሚንበለበሉ አክናፎችኽ ሰላም እላለኹ
የእግዚአብሔር ልዩ መልእክተኛ ሚካኤል ኾይ ከላይ ከሰማይ ተመልክተኽ በምትመጣበት ጊዜ ኹሉ በሲዖል የሚኖሩ ግዞተኞች ሚካኤል ኾይ መጣኽልን ደረስክልን እያሉ ደስታቸውን ይገልጻሉ።"
#መልክአ ቅዱስ ሚካኤል
" የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።"
#መዝሙረ ዳዊት 34:7፤)
"በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ሕዝብም ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤ በዚያም ዘመን በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ እያንዳንዱ ይድናል። "
#ትንቢተ ዳንኤል 12:1
" የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሀያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም፥ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፤ እኔም ከፋርስ ነገሥታት ጋር በዚያ ተውሁት። "
#ትንቢተ ዳንኤል 10:13
" ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም።
"
#ትንቢተ ዳንኤል 10:21፤)ዐ
"የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር። ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።"
#የይሁዳ መልእክት 1:9፤
"ቅዱስ ሚካኤል ኾይ

#መልክአ ቅዱስ ሚካኤል.
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞

#ቅዱስ_ሚካኤል
ሊቀ ኃይላት ቅዱስ ሚካኤል፣ በ "12"ቱም ወራቶች የሚካኤል በዓላቶቹ የግዝት ናቸው፣ ግዝት ማለታችን እንደ ሰንበት የከበረ ስንል ነው! እንግዲህ የመላእክት ቁጥራቸው እልፍ ነው! በእሁድ ሰዓት ሌሊት በ "9" ሰዓት ከእሳትና ከንፋስ ተፈጥረዋል! ሰማልያል ውጉዝ ሁኖ እስከተለየበት ጊዜ ድረስም፣ የነገዶ ቁጥር "100" የአለቆችም ቁጥር "10" ነበረ! እያንዳንዱ አለቃ በውስጡ አስር አስር ነገድን ይይዛል!
ከፊሎቹ በኤረረ: ከፊሎቹ በራማ: ከፊሎቹም በኢዮር ተሰይመዋል! ሁለት ወገንም ናቸው ብርሃናዊያን እና መልአክተ ፅልመት ናቸው: ለእነዚህም አለቃቸው ሰማልያል ነው የአሁኑ ሳጥናኤል! ኪሩቤል በአምሳለ ቀሲስ የሚላገለግሉ የመጀመሪያ ነገዶች ናቸው አለቃቸውም ኪሩብ ሲሆን እንዲሁ ሱራፌል ሁለተኛ ነገዶች ናቸው፣ እኚህም በአምሳለ ዲያቆናት የሚያገለግሉ ሲሆን፣ አለቃቸውም ሱራፊ ይባላል! እያለ...አጋይስጥ...እያለ...መኳንንት... እንዲህ ክእልቅናቸው ጋር ነገዳቸው በተዋረድ ይሄዳል! ግዙፋን: ረቂቃን: ብልህ: አስተዋይ: ልባዊያን: አዋቂና ትሁታንም ናቸው!
. ከዋነኞቹም አለቆች አንዱ ቅዱስ ሚካኤል ነው( ሥዩም በዲበ ኃይላት )! መጋቢ ብሉይ ይሉታል፣ በብሉይ ዘመን ወደ ምድር የሚፋጠን ነበርና! ኃይላት ለተባሉት ለአስሩ ነገዶችም አለቃ ነው! እኚህም ለስላሴ ሰይፍ ጃግሬዎች ናቸው! የምክሩ አበጋዝ፣ መጋቤ ብሉይ፣ መዝገበ ርኅራሄ፣ አይኑ ዘርግብ እና ወዘተ ሌሎች ቅፅል ስሞቹ ናቸው! ቅዱስ ሚካኤል በክንፉ ጥላነት ሁላችንንም ከክፉ ይጠብቀን! በአማላጅነቱም ከፈጣሪ ያስታርቀን።
[ አሜን ] #ቆዩ_በሰናይ//

ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የምሥራቅ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የገዳማት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ለ8 ደቀ መዛሙርት ሥልጣነ ክህነት ሰጡ !
መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
በብፁዕ አቡነ ሉቃስ የምሥራቅ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ አኅጉረ ስብከት እና የገዳማት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ሥልጣነ ክህነት ሰጥተዋል።
ብፁዕነታቸው በዛሬው ዕለት በአውስትራሊያ ሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለቆዩ 8 ደቀ መዛሙርት ነው የዲቁና ሥልጣነ ክህነት የሰጡት።
ዘገባውን ለማሰናዳት የምሥራቅ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ አህጉረ ስብከትን የፌስቡክ ገጽ ተጠቅመናል።