Telegram Web Link
💒 ለምልጃ የማይመች በደል - የክህነት ድፍረት

አባ ለትጹን በነበረበት ገዳም አንድ ቀን አበ ምኔቱ ታሞ ለሞት ደርሶ አገኘው፡፡ መነኮሳትም ዙሪያውን ከበውት ሲያለቅሱት አገኛቸው፡፡ እንዲሁም የሰይጣን ሠራዊትም አበ ምኔቱን ከበውት ደስ ሲሰኙ አያቸውና ደንግጦ

      ‹‹አባት ሆይ በአንተ ላይ የሆነው ምንድነው?›› ብሎ አበ ምኔቱን ጠየቀው፡፡ እርሱም መነኮሳቱን ከእርሱ እንዲርቁ ካደረገ በኋላ የሠራውን በደሉን እንዲህ ብሎ ነገረው፡-

‹‹እኔ ካሁን በፊት ማንም ያልሠራውን ኃጢአት ሠርቻለሁና አባቴ ሆይ በጸሎትህ አትርሳኝ፡፡ እኔ ቅስና ልሾም ፈልጌ ባልሾሙኝ ጊዜ ወደ ሌላ ሀገር ሄድኩ፡፡ ‹‹ኤጲስቆጶሱም ቅስና ሹሞኛል›› ብዬ በድፍረት በቁርባን ላይ የምቀድስ ሆንኩ፡፡ ለጠላሁትም በቁርባኑ መሥዋዕት ውስጥ መርዝ አድርጌ እሰጠዋለሁ እርሱም ይሞታል፡፡ ከእናቴም ጋራ ዓሥር ጊዜ ተኝቻለሁ፣ ከእኔም ፀንሳ ለመውለድ በደረሰች ጊዜ ሥራይ አጠጥቼ ሕፃኑን በሆዷ ውስጥ ገደልኩት፡፡

ኃጢአቴ ብዙ ነውና ተነግሮ አያልቅም፡፡ ከበጎ ሥራም ምንም ምን የሠራሁት የለም፡፡ ነገር ግን በጸሎትህ አትርሳኝ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም መውጫዬ ደርሷልና›› ብሎ ለአባ ለትጹን ነገረው፡፡ ወዲያውም በክፉ አሟሟት ሞተ፤ ነፍሱንም አጋንንት ሲቀበሏትና በየራሱ በሆነ ሥቃይ ሲያሠቃዩዋት አባ ለትጹን ተመለከታት፡፡ በዚህም አባ ለትጹን የመረረ ልቅሶን አለቀሰ፡፡

       አባ ለትጹንም ወደ ፈጣሪ ማርልኝ ብሎ ጸለየለት ተማጸነለት
‹የመጥኩህ ለትጹን ሆይ ኃጢአቱ እጅግ ብዙ ስለሆነ በደሉም ከኃጢአተኞች ሁሉ በደል ስለሚከፋ ምሕረት ስለማይገባው ስለዚያ ኃጢአተኛ ሰው ብዙጊዜ ነፍስህን ለምን ትገድላለህ?›› አለው፡፡ አባ ለትጹንም ‹‹መሐሪና ይቅር ባይ ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ ያን ኃጢአተኛ ትምረው ዘንድ እለምንሃለሁ ያለዚያ ግን የእኔንም ነፍሴን ከእርሱ ጋራ ወደ ሥቃይ ውሰዳት›› ብሎ ጌታችንን ለመነው

     ጌታችንም "ስለ ጽድቅህ በጎነትህ ስል እንዳልተፈጠረ አድርጌልሀለሁ" አለው ! እንዳልተፈጠረ ሆነለት 
      ዛሬም በኤጲስቆጶስነት ላይ የሚበድሉ ሰዎች ቢያንስ እንዳልተፈጠረ የመሆን እድላቸውን አያበላሹ ቢያንስ ቢያንስ ለምልጃ የሚመች ሀጢአት ይኑረን ክርስቶስ  ሊቀካህን በሆነበት ክህነት ላይ እንደመዳፈር ለምልጃ የሚደፋፈር በደል የለም
           // ኢዮብ ዘገነተ ጽጌ //

በነገራችን ላይ!
ይሁዳም ጌታውን አሳልፎ ለመስጠት
ምቹ ጊዜን ይጠባበቅ ነበረ🤔🤔🤔
''ማቴ 26:16''

@ortodoxtewahedo
† ቤተክርስቲያንን የምትወዱ ምዕመናን አስቡበት †

የግብጽ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን እንደ አሁኗ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሙስና እና ለዓለም በሚያደሉ አባቶች ታጭቃ መንፈሣዊ አገልግሎቷ ወደ መቅመቅ ሲወርድ የግብጽ ወጣቶች አንድ የድፍረት መላ ዘየዱ።

በነውጥ የቤተክርስቲያኒቷ የበላይ እረኛ የሆኑትን አባት ቅዱስ ፓትርያሪኩን ከመንበራቸው በጉልበት አንስተው በገዳም እንዲወሰኑ ማድረግ እና ቤተክርስቲያኒቷ ዳግም በአዲስ እረኛ እንድታብብ ማድረግ።

ይህንንም ነውጥ አደረጉ። ሞት ከፍለው ተሳካላቸው። እንደ እነ አቡነ ሺኖዳን(በረከታቸው ይደርብን) የመሰሉ ታላቅ አባት ከድኅረ ነውጥ እንቅስቃሴ በኃላ አፈሩ። ዛሬ ላይ ከ6 እህት አብያተክርስቲያናት መሃከል በተፈሪነቷም በተጽዕኖዋም ግንባር ቀደም ቤተክርስቲያን ሆነች።
**"
የህንድ ማላክራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሐዋርያዊ አገልግሎት እጅግኑ ተዳክማ ከህንድ ምድር ልትጠፋ ስትደርስ ምዕመናንን እና ቅን የሆኑ ካህናቱ አንድ ዘዴ ዘየዱ።

ቤተክርስቲያንን ለካህናት አባቶች ብቻ አሳልፎ ከመስጠት ይልቅ ጊዜውን የዋጀ የምዕመናንን እና የካህናት አባቶችን ፓርላማ መስርተው ለኤጴስ ቆጶስነት ጭምር የሚመረጡ መኖኮሳት በእዚህ የመንፈሣዊ ፓርላማ ግምገማ እንዲያልፍ አደረጉ።

ይህ ስርዓት ካህናትን ፈላጭ ቆራጭ ሳይሆን ትሁት አደረገ። ሁሉም ቤተክርስቲያን ውስጥ ገደብ እና መብት እንዳለው ተሰመረለት።

ዛሬ ላይ የህንድ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አንድም ተመጽዋች ምዕመን የሌላት በኢኮኖሚ እና በመንፈሣዊነት ለህዝብ እና አህዛብ አርዓያ የሆነች ቤተክርስቲያን ሆነች።
***
የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተ*ድሶ እንቅስቃሴ ቁምስቅሏን አይታ ስትዝል ብዙዋን አገልጋዮች ለእንቅስቃሴው አርምሞን አሳዩ።

ስርዓተ ቅዳሴ እየተካሄደ በቅጥረ ቤተክርስቲያን ድንኳን ተክለው የሚጮኹ ተሃድ*ች እስከመፈጠር ተደረሰ ።

ይህን ጊዜ የኤርትራ እናቶች በዛለው ጉልበታቸው አንድ ነገር ወሰኑ። የተሃድሶን እንቅስቃሴ በጉልበት የማስቆም ነውጥ ጠሩ። ድንኳን ሰባሪዎች የሚል ቅጽል ስምም ተሰጣቸው። በቅጥረ ቤተክርስቲያን የተተከሉ ድንኳኖችን ከእነአንቀሳቃሾች ሊያጠፉ ቻሉ።
***
ዛሬ ላይ የኢ/ኦ/ተ/ ቤተክርስቲያን ገዳማት በቅባት እና ጸጋ ተወርሰዋል። መና*fiqan በዘር ማልያ ተሰግስገው ያለከልካይ መሰረቷን እየቦረቦሩ ነው።ዛሬ ላይ አገልጋይን በአስተምሮት ስትከሰው በዘር ፊሽካ የሚያሰልፈው ነገድ ፈጥሯል ።
የታጠቀ ኃይል ሁሉ ቃታ መሳቢያ አድርጓታል።

ስለዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቱን መንገድ ትምረጥ? እንደ ግብጽ ወጣቶች፣እንደ ኤርትራ እናቶች ወይንስ እንደ ህንድ ምዕመናንን እና ካህናት።

አሁን ላይ ቤተክህነቱ እረኛ የሚል ስም በያዙ ነጋዴዎች ተሞልቷል።ከጠቅላይ ቤተክህነት እስከ ወረዳ ቤተክህነት ድረስ ሙስና እና ዘረኝነት ከዓለም በላይ ገኖ ጠንብቶ ይሸታል።

በሙሴ ብትር ለፈርዖን የሚያገለግሉ ግለሰቦች በኩራት ተገልጠዋል። ቤተክርስቲያን አይናችን እያየ እየመነመነችብን ነው።

መንፈስቅዱስ የሚሰራብን ነልጆች ወይም ለመንፈስ ቅዱስ የምንመች ምዕመን መሆን አቅቶናል።

ለሌሎችም አጋሩት

@ortodoxtewahedo
መንግሥት መስቀል አደባባይ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች እንዳይዘምሩ ከለከለ ለመስቀሉ እሮጣለው የአእላፍ ዝማሬ የመሳሰሉትን ፣አባቶችን የሚከፋፍል አጀንዳ ፈጠረና ኦርቶዶክሳውያንን አዘናግቶ በጎን መ*ና*ፍ*ቃ*ን መስቀል አደባባይ እንዲፈነጩበት ፈቀደ ሕዝቡ ለጥ ያልነቃህ ንቃ ።

ቤተ ከርስትያን ስደት ላይ ነች በአገዛዙ ።

@ortodoxtewahedo
ስለ ድንግል ብሎ
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
#ስለ_ድንግል_ብሎ

ስለ ድንግል ብሎ ኢትዮጵያን ይጎብኛት
ድሮስ ከአምላክ በቀር ይህች አገር ምን አላት
በሠራዊት ብዛት መች ትጠበቃለች
በቅዱሳን ጸሎት እሳት ካልታጠረች(፪)

ዓለም ሸምቆባት አህዛብ ይስቃል
በልጆችሽ ዕንባ አውሬው ይቀልዳል
ታልቅ ሕዝብ መሆኑን ማን በነገራቸው
ከዘመናት በፊት አምላክ የጎበኘው(፪)
#አዝ
እውነተኛ ዕንባ ፈለቀ ከምድር
በፍጡራን ዋይታ ፍጹም ብትማረር
ዕንባና ደማችን ተደባልቆ ፈሷል
አምላክ ቅጣት ይብቃን አሁን ይቅር በለን(፪)
#አዝ
ቅዱሳንን መንቀፍ ወገኔ ተውና
ይልቅ ስለነሱ የጽድቅ ጎዳና
በረድኤታቸው በክብራቸው ጥላ
እንከተላቸው ከፍቅራቸው ኋላ(፪)

ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ

"ኢትዮጵያ እጆቿን
ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች"
መዝ ፷፯፥፴፩

✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥

@ortodoxtewahedo

✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለታሪክ ይቀመጥ በልጆቹ ሞት በቤተ ክርሰቲያን ስደት መከራ የሚቀልድ አባት።

@ortodoxtewahedo
​​እንኳን ለቅዱስ ዕፀ መስቀል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †

መጋቢት 10

++ ቅዱስ ዕፀ መስቀል ++

ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ቸር አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማያዊ ክብሩ ወደ ምድር ወርዶ: በማሕጸነ ማርያም እግዝእት በኪነ ጥበቡ ተጸንሶ: በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: በፈቃዱ መከራ መስቀልን ተቀብሎ: ከግራ ቁመት: ከገሃነመ እሳት: ከሰይጣን ባርነት: ከኃጢአት ቁራኝነትም አድኖናል::

☞ "እምእቶነ እሳት ዘይነድድ አንገፈነ" እንዳለ ሊቁ::

+ ምንም መስቀል በብሉይ የወንጀለኞች መቅጫ ሆኖ ቢቆይም እግዚአብሔር ለዓለም መዳኛነት የመረጠው ነውና ሕብረ ትንቢቶች ሲነገሩለት: በብዙ ሕብረ አምሳልም ሲመሰል ኑሯል:: ከተፈጥሯችን ጀምሮ ዓለም ራሷ አርአያ ትዕምርተ መስቀል ናት::

+ እግዚአብሔር ለቃየልን እንዳይገድሉት ከሰጠው ምልክት (ዘፍ. 4:15) ጀምሮ ይስሐቅ ሊሰዋ የተሸከመው እንጨት (ዘፍ. 22:6): ቅዱስ ያዕቆብ ያያት የወርቅ መሰላል (ዘፍ. 28:12):
ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች የባረከበት መንገድ(ዘፍ. 48:14): ባሕረ ኤርትራን የከፈለችው የሙሴ በትር (ዘጸ. 14:15): የናሱ ዕባብ የተሰቀለበት እንጨት (ዘኁ. 21:8) ጨምሮ በርካታ ምሳሌዎች ለቅዱስ መስቀሉ መኖራቸውን መተርጉማን ተናግረዋል::

+ ቅዱስ ዳዊትን የመሰሉ ነቢያት ደግሞ "ለሚፈሩሕ ከቀስት ያመልጡ ዘንድ ምልክትን ሰጠሃቸው" እያሉ መስቀሉን ከርቀት ተመልክተዋል:: (መዝ. 59:4)

+ በሐዲስ ኪዳን ግን ምሳሌው ገሃድ ሆኖ: ጌታ በዕፀ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሥጋውን ቆረሰበት: ደሙን አፈሰሰበት: ዓለምንም አዳነበት:: ስለዚህም "መስቀል ብርሃን ለኩሉ ዓለም: መሠረተ ቤተ ክርስቲያን" ተብሎ የሚመሰገን ሆኗል::

+ ቅዱስ ያሬድ ሊቁ አክሎ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር" ብሎ ጠላትን ማሳፈሪያ መሆኑን ይነግረናል:: ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስም ስለ መስቀሉ አምልቶ አጉልቶ አስተምሯል:: መመኪያችን ነውና:: (1ቆሮ. 1:18, ገላ. 6:14)

+ አንዳንዶቹ እኛን 'የተሰቀለውን ትታቹሃል' ይሉናል:: የተሰቀለውማ የጌቶች ጌታ: የነገሥታት ንጉሥ: የአማልክት አምላክ: ሁሉ በእጁ የተያዘ: ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና ከኦርቶዶክስ በላይ የሚያመልክ በወዴት አለና::

+ ነገር ግን መስቀሉን ንቆ የተሰቀለውን ማክበር አይቻልምና እኛ ለመስቀሉ የጸጋ ስግደትን እንሰግዳለን: እናመሰግነዋለን:
እናከብረዋለን: ቤዛ: ጽንዕ: መድኃኒት: ኃይል እያልንም እንጠራዋለን:: አባቶቻችን በመስቀሉ ምርኩዝነት ማዕበለ ኃጢአትን: ባሕረ እሳትን ተሻግረዋል::

+ በመስቀሉ ቢመኩ አጋንንትን ድል ነስተዋል:: ጠላትንም አሳፍረዋል:: እኛም በመስቀሉ አምነን ከብረን: ገነን እንኖራለን:: ተጠቅመንበታልና ከራሳችን ሕይወት በላይ ምስክርን አንፈልግም::

     
@ortodoxtewahedo
ብሔር ብሔረሰቦች እና የእምነት ህብረት እንለይ
Amani Amani

እያንዳንዱ ቸርች ለተከታዮቻቸው የሚያስተምሯቸውን ትምህርቶች ልዩነት እንመልከት።

1, እግዚአብሔር የሚድኑትን አስቀድሞ መርጧል

2, ህፃናትን ማጥመቅ ያስፈልጋል ፤ ጥምቀትም ለድኀነት አስፈላጊ ነው

3,እግዚአብሔር ለሁሉም የሰው ልጅ ድኀነት በነፃ ፈቃድ ሰጥቷል

4, ጥምቀት ምስክርነት እንጂ ለድኀነት ጥቅም የለውም፤ህፃናትም መጠመቅ የለባቸውም

5, አንዴ የዳኑ ሰዎች ድኀነታቸው አያጡም

6, ጌታ ከድንግል ማርያም ስጋ እና ነፍስን አልነሳም

7, አንዴ የዳነ ሰው ድኀነቱን ሊያጣ ይችላል

8, ጌታ ከድንግል ማርያም ስጋ እና ነፍስን ነስቷል

9,ህብስቱ እና ወይኑ እውነተኛ የጌታ ስጋ እና ደም ነው

10, ህብስቱ እና ወይኑ እውነተኛ የጌታ ስጋ እና ደም ሳይሆን ምሳሌ ነው

አነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው። 😊

ጌታ ግን ምን ብሎ ፀለየ:-

" ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም፤ አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፥ አንተ፥ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 17: 20-21)

አንድ ሳይኮን
አንድ የጌታ ቃል ሳይያዝ
አንድ መረዳት ሳይኖር
ከአንድ መንፈስ ሳይቀዱ
በአንድ ልብ ቃለ እግዚአብሔር ሳይቀበሉ

እንዴት በአንድ ቦታ መሰባሰብ ይቻላል

ጥቅሙስ ምንድንነው
**=-=-=-==_+_+_+_+_+
የኢዩጩፋ ኢየሱስ
የእስራኤል ዳንሳ ኢየሱስ
የጆይ ጭሮ ኢየሱስ
የመካነ ሕይወት ኢየሱስ
የሙሉ ወንጌል ኢየሱስ
የቃለሕይወት ኢየሱስ
የፓስተር ዮናታን ኢየሱስ
ወዘተ ይለያያሉ።

ይህ ፖለቲካ መስሪያ በመንግሥት የተቀነባበረ ሴራ ነው

@ortodoxtewahedo
Audio
አትጥገቡ /ዐቢይ ጾም/ 
                                                  
Size:- 18.3MB
Length:-52:34
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
2024/09/28 23:26:23
Back to Top
HTML Embed Code: