Telegram Web Link
የእረኝነታቸውን ብኩርናቸውን በምስር ያልሸጡ አባት..
***

አሸርጋጅ አጎብዳጅ በበዛበት በእዚህ በእሾህ ዘመን ያለአንዳች አባት ያልተወን ቅድስት ሥላሴ የተመሰገነ ይሁን።

እረኛ ያልነው አካል አስብቶ ለአራጅ የሚሰጥ ሻጫ አጋፋሪ ሆኖ በተገለጠበት በእዚህ ትውልድ እንደ አብርሐም አባትነትን ያልናቀ እረኛ መኖሩ ተመስገን ያስብላል።

ብጹዕ አቡነ አብርሐም

በረከትዎ ትድረሰን !!!


@ortodoxtewahedo
"ይህ ዘመን ለቤተክርስቲያን ምቹ ጊዜ ነው "የሚሉ ሆድ አደሮች የበዙበት ጊዜ ስለሆነ ይህ ዘመን ለቤተክርስቲያን ፈታኝ ጊዜ ነው ፡ስለዚ ከምንጊዜውም በላይ ጠንካራ አንድነት ያስፈልገናል ። የቤተ ክርስትያንን ደሞዝ እየበሉ ለመንግስት የሚሰሩ ሆድ አደሮች በዝተዋል ።

@ortodoxtewahedo
ክብረ ክህነት ላይ ማመጽን እንደ ጸጋ የተያያዙ
***

ካህናት የመላእክትን አገልግሎት የተጋሩ የእግዚአብሔር አይኖች ናቸው። የእግዚአብሔር ምህረትን እና ቸርነት የሚመላለስባቸው ነው።

ያለክህነት እና ካህናት ምስጢራት መፈጸም አይቻልም። ያለክህነት እና ካህናት ቤተክርስቲያንንም ጭምር ማሰብ አይቻልም።

በትረ ክህነት የጨበጡ እጆች አጋንንትን እየቀጡ ኀጢአትን የሚያቀልጡ ናቸው፡፡ በዓለም ኖረው ዓለምን የሚያክሙ ሀኪሞች ጭምር ናቸው። ዳሩ ግን እነርሱ እየታመሙ ጤነኛዎችን የሚያመረቅዙ ሆኑ እንጅ።

ካህናት ህዝብ እና አህዛብን ወደ እግዚአብሔር እና ወደ መንግስቱ ያቀርባሉ፤ የመንፈስ ልጆቻቸውን በርህራሄ ይጠብቃሉ፡፡ በለመለመ መስክ፣ በጠራ ውኃ በንጽሁ የዕረፍት ስፍራ ያሠማራሉ፡፡

የኤልያስ መንፈስ በኤልሳዕ እንደሰራ ፣የሙሴ ጸጋ በኢያሱ እንደጸና ዛሬም የሐዋርያት መንፈስ በሀዲስ ኪዳን ካህናት ላይ ይሰራ ዘንድ የታመነ ጸጋ ነው።

በአንብሮተ እድ ፣ በንፍሐት እፍታ መንፈስ ቅዱስ የጸጋዎች ሁሉ ቁንጮን ለሰው ልጆች እያቀበለ ርህራሄውን በክህነት ጸጋ ተመልክተናል

ይህን ጊዜ በምድርም በሰማይም ያስሩ ይፈቱ ዘንድ ስልጣንን ይጨብጣሉ።የአምላክ ሥጋና ደምን በመሰዊው ላይ ያቀርባሉ።

ይህ የክህነት ጸጋ በትውልድ መሃል እንዲረክስ ቆብ ያጠለቁት በትጋት እየሰሩ ነው። እረኞች ጭካኔን ከተኩላ በላይ ገልጠው ክህነት እና ካህናትን አምርረው እንዲጠሉ እየተደረጉ ነው።

በአጭሩ የቅድስት ቤተክርስቲያን አይተኬ ጸጋ ተከርሽሮ እንዲነቀል ቀሚስ ባደረጉ ቆብ ባጠለቁ የስም እንጅ የግብር ካህነት በነጠፈባቸው ሰዎች እየተሰራ ነው።

ይህ ዘመን ግዙፍ የእግዚአብሔር ቸርነት ካልታከበት የሚመጣው ነገር እጅግኑ ያስፈራል።

መሰረት መናድ ላይ ከቤተክህነትም ከቤተመንግስትም እየተሰራ ይገኛል
ደገኛው መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ሆይ ስምህን ውሰድ

ምን ጉድ ነው የገጠመን.. .!!
ለመንጋው የማይራራ የቤተክርስቲያን መከራ የማይታየው እንዴት አባት ሊባል ይችላል ::

በሰሜን በደቡብም በምስራቅም በሁሉም አቅጣጫ የሚገደል ኦርቶዶክስ ዘመኑ ምቹ ነው እያላቹ የመንጋው ጠባቂነቱ ዝም ያላቹ አባቶች ታሪክ ይፋረዳቹዋል ። የዝቋላ አባቶች የቆሉ ተማሪዎች ደም ሳይደርቅ በየሰከንዱ ጉድ ምንሰማበት ዘመን ቤተ ክርስትያን በታሪክ ጥቁር በለበሰችበት ዘመን ።

" በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።

ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ። "

ሐዋርያት 20 : 28

@ortodoxtewahedo
Forwarded from LikeBot
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !!!

እንኳን ለቅድስት ሥላሴ በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

የአብርሐምን ቤት የባረኩ ሥላሴ እኛንም በህይወታችን በኑሮዋጭን በአገልግሎታችን በትዳርአችን በትምርታችን በሥራችን ይባርኩን ።

ሥሉስ ቅዱስ ለሚታምን ሁሉ እምነትን በረከትን ሀገራችን ኢትዮጽያን ሰላም ያድርጉልን አሜን ::

#መልካም እለተ ይሁንልን

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
.
ሆድ አምላካቸው የሁኑ የምእመናን ሰቆቃና መከራ የማይገዳቸው
ክህነታቸውን በምስር ወጥ የሸጡ ከሰማዩ ንጉስ ይልቅ ለምድራዊው
ንጉስ ያስበለጡ ። በምእመናና ገንዘብ እየኖሩ የምእመናን ሞት እንባ ስቃይ ሀዘን የማይገዳቸው የሀሰት ካህን ።

በነገራችን ላይ!
ይሁዳም ጌታውን አሳልፎ ለመስጠት
ምቹ ጊዜን ይጠባበቅ ነበረ🤔🤔🤔
''ማቴ 26:16''


@ortodoxtewahedo
💒 ለምልጃ የማይመች በደል - የክህነት ድፍረት

አባ ለትጹን በነበረበት ገዳም አንድ ቀን አበ ምኔቱ ታሞ ለሞት ደርሶ አገኘው፡፡ መነኮሳትም ዙሪያውን ከበውት ሲያለቅሱት አገኛቸው፡፡ እንዲሁም የሰይጣን ሠራዊትም አበ ምኔቱን ከበውት ደስ ሲሰኙ አያቸውና ደንግጦ

      ‹‹አባት ሆይ በአንተ ላይ የሆነው ምንድነው?›› ብሎ አበ ምኔቱን ጠየቀው፡፡ እርሱም መነኮሳቱን ከእርሱ እንዲርቁ ካደረገ በኋላ የሠራውን በደሉን እንዲህ ብሎ ነገረው፡-

‹‹እኔ ካሁን በፊት ማንም ያልሠራውን ኃጢአት ሠርቻለሁና አባቴ ሆይ በጸሎትህ አትርሳኝ፡፡ እኔ ቅስና ልሾም ፈልጌ ባልሾሙኝ ጊዜ ወደ ሌላ ሀገር ሄድኩ፡፡ ‹‹ኤጲስቆጶሱም ቅስና ሹሞኛል›› ብዬ በድፍረት በቁርባን ላይ የምቀድስ ሆንኩ፡፡ ለጠላሁትም በቁርባኑ መሥዋዕት ውስጥ መርዝ አድርጌ እሰጠዋለሁ እርሱም ይሞታል፡፡ ከእናቴም ጋራ ዓሥር ጊዜ ተኝቻለሁ፣ ከእኔም ፀንሳ ለመውለድ በደረሰች ጊዜ ሥራይ አጠጥቼ ሕፃኑን በሆዷ ውስጥ ገደልኩት፡፡

ኃጢአቴ ብዙ ነውና ተነግሮ አያልቅም፡፡ ከበጎ ሥራም ምንም ምን የሠራሁት የለም፡፡ ነገር ግን በጸሎትህ አትርሳኝ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም መውጫዬ ደርሷልና›› ብሎ ለአባ ለትጹን ነገረው፡፡ ወዲያውም በክፉ አሟሟት ሞተ፤ ነፍሱንም አጋንንት ሲቀበሏትና በየራሱ በሆነ ሥቃይ ሲያሠቃዩዋት አባ ለትጹን ተመለከታት፡፡ በዚህም አባ ለትጹን የመረረ ልቅሶን አለቀሰ፡፡

       አባ ለትጹንም ወደ ፈጣሪ ማርልኝ ብሎ ጸለየለት ተማጸነለት
‹የመጥኩህ ለትጹን ሆይ ኃጢአቱ እጅግ ብዙ ስለሆነ በደሉም ከኃጢአተኞች ሁሉ በደል ስለሚከፋ ምሕረት ስለማይገባው ስለዚያ ኃጢአተኛ ሰው ብዙጊዜ ነፍስህን ለምን ትገድላለህ?›› አለው፡፡ አባ ለትጹንም ‹‹መሐሪና ይቅር ባይ ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ ያን ኃጢአተኛ ትምረው ዘንድ እለምንሃለሁ ያለዚያ ግን የእኔንም ነፍሴን ከእርሱ ጋራ ወደ ሥቃይ ውሰዳት›› ብሎ ጌታችንን ለመነው

     ጌታችንም "ስለ ጽድቅህ በጎነትህ ስል እንዳልተፈጠረ አድርጌልሀለሁ" አለው ! እንዳልተፈጠረ ሆነለት 
      ዛሬም በኤጲስቆጶስነት ላይ የሚበድሉ ሰዎች ቢያንስ እንዳልተፈጠረ የመሆን እድላቸውን አያበላሹ ቢያንስ ቢያንስ ለምልጃ የሚመች ሀጢአት ይኑረን ክርስቶስ  ሊቀካህን በሆነበት ክህነት ላይ እንደመዳፈር ለምልጃ የሚደፋፈር በደል የለም
           // ኢዮብ ዘገነተ ጽጌ //

በነገራችን ላይ!
ይሁዳም ጌታውን አሳልፎ ለመስጠት
ምቹ ጊዜን ይጠባበቅ ነበረ🤔🤔🤔
''ማቴ 26:16''

@ortodoxtewahedo
† ቤተክርስቲያንን የምትወዱ ምዕመናን አስቡበት †

የግብጽ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን እንደ አሁኗ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሙስና እና ለዓለም በሚያደሉ አባቶች ታጭቃ መንፈሣዊ አገልግሎቷ ወደ መቅመቅ ሲወርድ የግብጽ ወጣቶች አንድ የድፍረት መላ ዘየዱ።

በነውጥ የቤተክርስቲያኒቷ የበላይ እረኛ የሆኑትን አባት ቅዱስ ፓትርያሪኩን ከመንበራቸው በጉልበት አንስተው በገዳም እንዲወሰኑ ማድረግ እና ቤተክርስቲያኒቷ ዳግም በአዲስ እረኛ እንድታብብ ማድረግ።

ይህንንም ነውጥ አደረጉ። ሞት ከፍለው ተሳካላቸው። እንደ እነ አቡነ ሺኖዳን(በረከታቸው ይደርብን) የመሰሉ ታላቅ አባት ከድኅረ ነውጥ እንቅስቃሴ በኃላ አፈሩ። ዛሬ ላይ ከ6 እህት አብያተክርስቲያናት መሃከል በተፈሪነቷም በተጽዕኖዋም ግንባር ቀደም ቤተክርስቲያን ሆነች።
**"
የህንድ ማላክራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሐዋርያዊ አገልግሎት እጅግኑ ተዳክማ ከህንድ ምድር ልትጠፋ ስትደርስ ምዕመናንን እና ቅን የሆኑ ካህናቱ አንድ ዘዴ ዘየዱ።

ቤተክርስቲያንን ለካህናት አባቶች ብቻ አሳልፎ ከመስጠት ይልቅ ጊዜውን የዋጀ የምዕመናንን እና የካህናት አባቶችን ፓርላማ መስርተው ለኤጴስ ቆጶስነት ጭምር የሚመረጡ መኖኮሳት በእዚህ የመንፈሣዊ ፓርላማ ግምገማ እንዲያልፍ አደረጉ።

ይህ ስርዓት ካህናትን ፈላጭ ቆራጭ ሳይሆን ትሁት አደረገ። ሁሉም ቤተክርስቲያን ውስጥ ገደብ እና መብት እንዳለው ተሰመረለት።

ዛሬ ላይ የህንድ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አንድም ተመጽዋች ምዕመን የሌላት በኢኮኖሚ እና በመንፈሣዊነት ለህዝብ እና አህዛብ አርዓያ የሆነች ቤተክርስቲያን ሆነች።
***
የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተ*ድሶ እንቅስቃሴ ቁምስቅሏን አይታ ስትዝል ብዙዋን አገልጋዮች ለእንቅስቃሴው አርምሞን አሳዩ።

ስርዓተ ቅዳሴ እየተካሄደ በቅጥረ ቤተክርስቲያን ድንኳን ተክለው የሚጮኹ ተሃድ*ች እስከመፈጠር ተደረሰ ።

ይህን ጊዜ የኤርትራ እናቶች በዛለው ጉልበታቸው አንድ ነገር ወሰኑ። የተሃድሶን እንቅስቃሴ በጉልበት የማስቆም ነውጥ ጠሩ። ድንኳን ሰባሪዎች የሚል ቅጽል ስምም ተሰጣቸው። በቅጥረ ቤተክርስቲያን የተተከሉ ድንኳኖችን ከእነአንቀሳቃሾች ሊያጠፉ ቻሉ።
***
ዛሬ ላይ የኢ/ኦ/ተ/ ቤተክርስቲያን ገዳማት በቅባት እና ጸጋ ተወርሰዋል። መና*fiqan በዘር ማልያ ተሰግስገው ያለከልካይ መሰረቷን እየቦረቦሩ ነው።ዛሬ ላይ አገልጋይን በአስተምሮት ስትከሰው በዘር ፊሽካ የሚያሰልፈው ነገድ ፈጥሯል ።
የታጠቀ ኃይል ሁሉ ቃታ መሳቢያ አድርጓታል።

ስለዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቱን መንገድ ትምረጥ? እንደ ግብጽ ወጣቶች፣እንደ ኤርትራ እናቶች ወይንስ እንደ ህንድ ምዕመናንን እና ካህናት።

አሁን ላይ ቤተክህነቱ እረኛ የሚል ስም በያዙ ነጋዴዎች ተሞልቷል።ከጠቅላይ ቤተክህነት እስከ ወረዳ ቤተክህነት ድረስ ሙስና እና ዘረኝነት ከዓለም በላይ ገኖ ጠንብቶ ይሸታል።

በሙሴ ብትር ለፈርዖን የሚያገለግሉ ግለሰቦች በኩራት ተገልጠዋል። ቤተክርስቲያን አይናችን እያየ እየመነመነችብን ነው።

መንፈስቅዱስ የሚሰራብን ነልጆች ወይም ለመንፈስ ቅዱስ የምንመች ምዕመን መሆን አቅቶናል።

ለሌሎችም አጋሩት

@ortodoxtewahedo
መንግሥት መስቀል አደባባይ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች እንዳይዘምሩ ከለከለ ለመስቀሉ እሮጣለው የአእላፍ ዝማሬ የመሳሰሉትን ፣አባቶችን የሚከፋፍል አጀንዳ ፈጠረና ኦርቶዶክሳውያንን አዘናግቶ በጎን መ*ና*ፍ*ቃ*ን መስቀል አደባባይ እንዲፈነጩበት ፈቀደ ሕዝቡ ለጥ ያልነቃህ ንቃ ።

ቤተ ከርስትያን ስደት ላይ ነች በአገዛዙ ።

@ortodoxtewahedo
ስለ ድንግል ብሎ
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
#ስለ_ድንግል_ብሎ

ስለ ድንግል ብሎ ኢትዮጵያን ይጎብኛት
ድሮስ ከአምላክ በቀር ይህች አገር ምን አላት
በሠራዊት ብዛት መች ትጠበቃለች
በቅዱሳን ጸሎት እሳት ካልታጠረች(፪)

ዓለም ሸምቆባት አህዛብ ይስቃል
በልጆችሽ ዕንባ አውሬው ይቀልዳል
ታልቅ ሕዝብ መሆኑን ማን በነገራቸው
ከዘመናት በፊት አምላክ የጎበኘው(፪)
#አዝ
እውነተኛ ዕንባ ፈለቀ ከምድር
በፍጡራን ዋይታ ፍጹም ብትማረር
ዕንባና ደማችን ተደባልቆ ፈሷል
አምላክ ቅጣት ይብቃን አሁን ይቅር በለን(፪)
#አዝ
ቅዱሳንን መንቀፍ ወገኔ ተውና
ይልቅ ስለነሱ የጽድቅ ጎዳና
በረድኤታቸው በክብራቸው ጥላ
እንከተላቸው ከፍቅራቸው ኋላ(፪)

ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ

"ኢትዮጵያ እጆቿን
ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች"
መዝ ፷፯፥፴፩

✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥

@ortodoxtewahedo

✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥
2024/09/30 15:39:03
Back to Top
HTML Embed Code: