Telegram Web Link
የቤተክርስቲያን አባቶች እንዲህ ይላሉ
“ኢትዮጵያ ሥጋችን ቤተ ክርስቲያን ነፍሳችን ናት፤ ነፍስ እና ሥጋ ደግሞ አንድ ነው፡፡ አገር ያለሃይማኖት፣ ሃይማኖት ያለአገር የለም፤ ኢትዮጵያን ያህል አገር ማጣት እግዚአብሔርን ከሚያህል ጌታ መለየት ሞት ነው፡፡ ሃይማኖትን እና ነጻነትን ማጣት ሽንፈት ነው፤ ስለ አገር፣ ሃይማኖት እና ነጻነት መሞት ደግሞ ክብር ነው፡፡”

በአባቶቻችን ዘመን የተነገረላት "

ኢትዮጵያ ታበፅ እደዊሁ ሃበ እግዚአብሔር" እንኳንስ የሰው ቀርቶ የእንጨት ጠማማ እንኳ አይገኝብሽም ያልክላት ዘመን መቼ ነው? ለምለም የነበረች ምድር የደም ምድር ሆናለች! እንግዲህ ደግ ሰው አልቋልና አድነን! ለኢትዮጵያም ዘንበል በልላት🙏
አሜን አሜን አሜን

@ortodoxtewahedo
★ ድራማው አልተሳካም ★

★ ሐሰተኛው ነቢይ ኢዩ ጩፋ ሀሰተኛነቱን ማጭበርበሩን ድራማውን በይፋ እያሳየ ነው።★
ከአሰላ ከተማ የመጣው መነኩሴ ነኝ ያለው አጭበርባሪ የውሸት መነኩሴ የለየለት ወመኔ፣የቤተክርስቲያን ጥልቅ ትምህርትና በቂ የአገልግሎት ሙያ የሌለው ወገበ ነጭ ቤተክርስቲያንን ለማሰደብ ቆብና ቀሚስ ከገበያ ገዝቶ ተመሳስሎ የገባ ተኩላ፣ የምንኩስና የቅድስና ሕይወት የሌለው አለሌ መሆኑ ተረጋግጧል።

ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ለማስነቀፍና የቅድስት ቤተክርስቲያንን አማኞች ለሐሰተኛ ነቢያት ለመገበር የአጋንንት ማደሪያ ከሆነው ከአጭበርባሪው ኢዩ ጩፋ ጋር ተመሳጥረው ይህንን ቀሽም ድራማ ለመስራት ቢንፈራገጡም የቤተክርስቲያን አምላክ በአጭር ሰዓት ውስጥ ድንቁርናቸውን ለሕዝብ ገልጦባቸዋል።

ኦርቶዶክሳውያን በጣም አስተውሉ፣የጠመጠመ ሁሉ ቄስ፣ቆብ የደፋ ሁሉ መነኩሴ፣የአገልግሎት ቀሚስ የለበሰ ሁሉ ሰባኪ አይደለም ብዙ አስመሳይ፣አጭበርባሪ፣ወንበዴ፣አጽራረ ቤተክርስቲያን አሉና ተጠንቀቁ !!

ከዚህ በፊት በአዲስ አበባ ጦርኃይሎች ሙሉ ወንጌል አዳራሽ ውስጥ ፓስተሮቹ ሕዝብን ለማጨበርበር ጳጳስ ነበርኩ ስሜም አቡነ ያሬድ ይባላል ብሎ አንዱን የእነርሱ ቢጤ የልብ እውር መድረክ ላይ አቁመው ሲዘሉ ቢውሉም እግዚአብሔር በአጭር ቀን ውስጥ ለምዳቸውን ገፎ በኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ ፊት ውሸታምነታቸውን አጋልጧቸዋል።« የተኩላው ለምድ ሲገፈፍ» በሚለው የመምህር ዘበነ ስብከት ላይ ሙሉ ቪዲዮውን ታገኙታላችሁ። አሁንም ተመሳሳይ ድራማ መስራታቸው አዕምሯቸው የማይነቃ በድንዛዜ መንፈስ የደነቆሩ የአጋንንት ማደሪዎች መሆናቸውን ማሳያ ነው።

ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እውነተኛ መነኮሳት በጾም፣በጸሎት፣በስግደት፣በማይቋረጥ ስብሐተ እግዚአብሔር ሌሊትና ቀን በየገዳማቱና በየአድባራቱ በገድል በትሩፋት ጸንተው የሚታገሉባት እውነተኛ የክርስቶስ መቅደስ ነች።

ለሌሎችም ሼር አድርጉት

@ortodoxtewahedo
ሀሰተኛ ነብያት ያለ ድራማ መኖር አትችሉም ማለት ነው?

ድሮሮሮሮሮ የቀረ ሙድ ምናለ ቢቀርባችሁ? በድራማ የከበረ የሚከብር ጌታ የለምኮ

@ortodoxtewahedo
#ደጉ እና ሩሩህ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ወርሀዊ በዓል እንኳን አደረሳቹ።

"ቅዱስ ሚካኤል ኾይ"

እንደ ፀሐይ ሥነ ጸዳል የሚያንጸባርቁ በሰማይ ላይ ለሚንበለበሉ አክናፎችኽ ሰላም እላለኹ

የእግዚአብሔር ልዩ መልእክተኛ ሚካኤል ኾይ ከላይ ከሰማይ ተመልክተኽ በምትመጣበት ጊዜ ኹሉ በሲዖል የሚኖሩ ግዞተኞች ሚካኤል ኾይ መጣኽልን ደረስክልን እያሉ ደስታቸውን ይገልጻሉ።"

#መልክአ ቅዱስ ሚካኤል

" የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።"

#መዝሙረ ዳዊት 34:7፤)

"በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ሕዝብም ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤ በዚያም ዘመን በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ እያንዳንዱ ይድናል። "

#ትንቢተ ዳንኤል 12:1

" የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሀያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም፥ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፤ እኔም ከፋርስ ነገሥታት ጋር በዚያ ተውሁት። "

#ትንቢተ ዳንኤል 10:13

" ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም።
"
#ትንቢተ ዳንኤል 10:21፤)ዐ

"የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር። ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።"

#የይሁዳ መልእክት 1:9

✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞

@ortodoxtewahedo
አካፋው ሚካኤል (የሰማዕታት ቀን) በስድስት ኪሎ ሰማዕታት ሐውልት የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ ታስቧል ።

ማክሰኞ የካቲት 12 ቀን 2016 ዓ.ም በየካቲት12 ቀን 1929 የፋሺስት ጣልያን ወታደሮች በአዲስ አበባ ያደረሱት አስከፊ ጭፍጨፋ የሚታሰብበት የሰማዕታት ቀን በመታሰቢያ ሀውልቱ ዙሪያ ታስቧል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን እንዲሁም የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የጀግኖች አርበኞች ቤተሰቦች ታድመዋል።

© ዘገባ አዲስ ማለዳ ; ፎቶ ኢፕድ

@ortodoxtewahedo
መፍትሔው ያለው #በቤተ ክህነት እጅ ነው!

የመነኩሴ ልብስ የለበሰው በፎቶው የሚታየው ጎረምሳ ነው።
የተኩላው_ቆዳ_በዐደባባይ_ተገፏል። ቀሪው ጉዳይ የሕግ አገልግሎት መምሪያው የቤት ሥራ ነው።
በዚህ ዘመን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ የተደቀኑ ብዙ ፈተናዎች አሉ።ከእነዚህም ፈተናዎች መካከል አንዱ አልባሳቷን መርካቶ ገዝቶ ማታለል ነው።
በቅርቡ ንዋያተ ቅድሳቱን ከመርካቶ ገዝተው በማጭበርበር የተደራጁ ግለሰቦችን በየሥፍራው እናያለን።
- ይህ አድገኛ አካሄድ በሃይማኖት ላሉትም ኾነ ላልጸኑት የመሰናክል ዓለት ሆኖባቸዋል።በምግባርና በሃይማኖትም ጸንተው ለሚኖሩት ማፈሪያ ሆናል።
የችግሩ፣መፍትሔው ያለው #በቤተ ክህነት እጅ ነው።
እንዴት ይህን ሕገ ወጥ አሠራሪ ሥርዓት የሚያስዝ የጠቅላይ ቤተ ክህነት #መምሪያ ጠፋ?በእርግጥ አውቆ የተኛ በቀሰቅሱት አይሰማማ ነው ። ችግሩ ብዙ ነው ችግሩንም መናገር በቤተ ክህነት ውስጥ ሌላ ችግር ነው ።
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደ ሃይማኖታዊ ተቋም ርምጃ ብትወስድ በስሟ የሚሰራውን ይህን ሕገ ወጥ ተግባር ለማስቆም ይቻላታል።

@ortodoxtewahedo
አክተሩ
1ኛ ሸሚዝ አልቀየረም
2ኛ ፍሪዝ ነው ጸጉሩ መኖክሴ ፍሪዝ አያረግም
3ኛ የኦርቶዶክስ መምህር አይደለም
4ኛ ፓስተሩ ይህንን ድራማ ሲሰራ ከባድ ስህተት ሰርቶል።

በውሸት የሚነግስ ሴጣን እንጂ ጌታ የለም ።

“ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን ።”
 
— ዮሐንስ 3፥11


@ortodoxtewahedo
ፆመ ነነዌ  ከሰኞ - ዕሮብ (ከየካቲት 18 -20 )

የነነዌን ህዝብ ጸሎት የሰማ አምላክ የኢትዮጵያንም ህዝብ ልመና ለቅሶ ችግር ይሰማ ዘንድ ቅዱስ ፍቃዱ ይሁን አሜን፡፡

           ፆመ ነነዌ

ዮናስ ማለት 'ርግብ: የዋህ' ማለት ሲሆን ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ነው::በሰራፕታ ተወልዶ ያደገው ነቢዩ በልጅነቱ ታሞ ሙቶ ነበር:: ታላቁ ነቢይ ኤልያስ ግን 7 ጊዜ ጸሎት አድርጐ ከሞት አስነስቶታል::እናቱ የሰራፕታዋ መበለትም ደግ ሴት ነበረች::
    ቅዱስ ዮናስ በእድሜው ከፍ ሲል የቅዱስ ኤልያስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: የነ ኤልሳዕና አብድዩም ባልንጀራ ነበረ:: ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስ ካረገ በሁዋላ: ቅ.ል.ክርስቶስ በ፰፻ ዓመት አካባቢ የነነዌ ሰዎች ኃጢአት ከመሥፈርቱ በማለፉ የእግዚአብሔር ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ መጣ::

  ሒድና ለነነዌ ሰዎች ንስሃን ስበክላቸው" አለው:: ከነቢያት ወገን ከሙሴና ከዳዊት ቀጥሎ የዮናስን ያህል የዋህ ገራገር የለምና እንቢ አለ ሰምቶ ዝም አለ:: እግዚአብሔር እየደጋገመ ሲናገረው ግን "እንዲህ የሚዘበዝበኝ ከፊቱ ብቀመጥ አይደል!" ብሎ ወደ ተርሴስ ኮበለለ።
     ወገኖቼ አንድ ነገርን ልብ እንበል:: እንኩዋን ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዮናስ እኛ ክፉዎችም ከጌታ ፊት መሸሽ እንደማይቻል ጠንቅቀን እናውቃለን:: ታዲያ ለምን ሸሸ ቢሉ:- ጥበበ እግዚአብሔር በውስጡ ስለ ነበረበት ነው::

   ምክንያቱም ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ 3 ቀን ሌሊት ኖሮ: ሙስና ጥፋት ሳያገኘው መውጣቱ ለጌታ ትንሳኤ ጥላ ምሳሌ ነው:: ለዚህም ምስክሩ ራሱ ጌታችን ነው:: "ወበከመ ነበረ ዮናስ ውስተ ከርሠ አንበሪ ሠሉሰ ዕለተ ወሠሉሰ ለያልየ: ከማሁ ይነብር ወልደ እጉዋለ እመ ሕያው ውስተ ልበ ምድር ሠሉሰ ዕለተ: ወሠሉሰ ለያልየ" እንዲል:: ማቴ. 12:39

   ቅዱስ ዮናስ በገንዘቡ ዋጅቶ ወደ መርከብ በገባ ጊዜ ታላቅ ማዕበል ሆነ:: የእምነት ሰው ነውና እንዲያ እየተናወጡ እርሱ በእርጋታ ተኝቷል:: እነርሱ ግን ቀስቅሰው ቢጠይቁት እጣ ወድቆበታልና የእኔ ጥፋት ስለ ሆነ ወደ ማዕበሉ ጣሉኝ" አላቸው::
     እያዘኑ ቢጥሉት ታላቅ ጸጥታ ሆነ:: እነዚያ አሕዛብም እግዚአብሔርን በመስዋዕትና በስዕለት አከበሩ:: ዮናስ ግን በማዕበልና በአሣ አንበሪ ሆድ ውስጥ ለ3 ቀናት ጸለየ:: አሣ አንበሪው በ3ኛው ቀን ወደ ነነዌ ተፋው::ቅዱሱም "እስከ ሠሉስ ዕለት ትትገፈታእ ነነዌ ዐባይ ሃገር" እያለ ንስሃን ሰበከ::

የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸውን አምነው ቢጸጸቱ ከሰማይ ወርዶ ከደመና ደርሶ የነበረው የእሳት ማዕበል ተመልሶላቸዋል::
    የነቢዩ ትንቢት ግን አልቀረምና ታላቁዋ ነነዌ ከ፫፻ ዓመታት በኃላ ጠፍታለች:: ቅዱስ ዮናስ ግን በቀሪ ዘመኑ ፈጣሪውን እያገለገለ ኑሯል:: ጠቅላላ እድሜውም 170 ዓመት ነው::

አምላከ ቅዱስ ዮናስ እድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍስሃ አይንሳን:: ከበረከቱም ይክፈለን::
በጾመ ነነዌ ስለ ሃገርና ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት መጸለይ ይገባል::
  ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል:: ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም:: ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ: እንዲሁ የሰው ልጅ(ጌታችንን) በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል:: የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይፈርዱበታል:: በዮናስ ስብከት ንስሃ ገብተዋልና:: እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ::
                    ማቴ. 12:39
ለሀገራችን ሰላም ለምድራችንም በረከትን ያድልልን!!
       ወስብሐት ለእግዚአብሔር
        ወለ ወላዲቱ ድንግል
         ወለመስቀሉ ክብር

@ortodoxtewahedo
አራት የገዳም አባቶች ተገደሉ

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሚገኘው ጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም እራሱን ኦነግ ሸኔ ብሎ በሚጠራው ቡድን የገዳሙን መጋቢ ጨምሮ አራት አባቶችን መግደሉን ገዳሙ አስታውቋል፡፡
ሰኞ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓመተ ምሕረት ታጣቂዎቹ ሦስት አባቶችን አግተው ወደ በረሃ ከወሰዱ በኋላ የታገቱትን ለማስለቀቅ ገዳሙ ጥረት በሚያርግበት ወቅት የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ተጨማሪ አባቶችን በመያዝ
1. የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራት
2. የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን
3. የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ
4. በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም የተባሉት የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች እንደተገደሉና አብረው ከነበሩት አንድ አባት ብቻ ማምለጥ መቻላቸውን እንደተረዱ የገዳሙ ኃላፊዎች ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) ገልጸዋል፡፡
የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች ቡድኑ ከዚህ ቀደም ገዳሙን በመዝረፍ ለከፋ ችግር አጋልጦት መቆየቱን አስታውሰው ገዳሜ ጸጥታውን የሚያስከብረበት መሣሪያች በቡድኑ በመወረሳቸው ለከፋ የጸጥታ ችግር መጋለጡን ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ገዳማውያ በስጋት ላይ መሆናቸውንና የመንግሥት የጸጥታ አካላትን እገዛ እንደሚሹ አስታውቀው መረጃውንም በየደረጃው ለሚገኙ የሀገረ ስብከቱና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ማሳወቃቸውን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያና የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት EOTC TV በክሰተቱ ሕይወታቸው ላጡ ሰማዕታት አባቶች የተሰማውን ኃዘን ይገልጻል፡፡ ጉዳዩ አስመልክቶ ዝርዝር መረጃ እየተከታተለ የሚያቀርብ መሆኑን ያስታውቃል፡፡
EOTC TV

@ortodoxtewahedo
“…ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።”

ሮሜ 8፥36


@ortodoxtewahedo
ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ ስለሚገኘው "መነኩሴ "ነኝ ባይ ግለስብ በሀገረ ስብከቱ የማይታወቅ መሆኑን ሀገረ ስብገቱ ገለጸ።
የአርሲ ሀገረ ስብከት ሰሞኑን በማኅበራዊ ድረ ገጾች ራሱን "መነኩሴ"በማስመሰልና በአርሲ ሀገረ ስብከት አገልጋይ እንደሆነ በመግለጽ የሚንቀሳቀሰውን ግለሰብ የማያውቀውና ሐሰተኛ "መነኩሴ" መሆኑን ለጠቅላይ ቤተክህነት በጻፈው ደብዳቤ አስታወቀ።
ከየካቲት 12 ቀን 20916 ዓ.ም ጀምሮ በማኀበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ የሚገኘው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ተችቶ የማስተቸት ድራማዊ ትዕይንት ላይ የቀረበው አስመሳይ " መነኩሴ "ግለሰብ በሀገረ ስብከታችን በተለይ በአሰላ ከተማ በቅዳሴ መምህርነት በስብከተ ወንጌል እንዳገለ በማስመሰል በሰጠው የሀሰት ምስክርነትን በተመለከተ እውነተኛ ምላሽ መስጠት ማስፈለጉን የጠቀሰው ሀገረ ስብከቱ"መንኩሴ "መሳዩ ግለሱብ በሀገረ ስብከቱ በየተኛውም የከተማና የገጠር ገዳማትና አድባራት የማይታወቅና ምንም ዓይነት አገልግሎት ሲሰጥ ያልነበረ መሆኑን ገልጿል።
በተጨማሪ በሀገረ ስብከቱ የሚገኙት ሁሉንም አገልጋዮች የሚታወቁና የተመዘገቡ መሆኑን የጠቀሰው ሀገረ ስብከቱ ግለሰቡ በሀገረ ስብከቱ ካሉት አገልጋች መካከል የማይታወቅና ያልተመዘገበ ከመሆኑም በላይ ሀገረ ስብከቱ በፍጹም የማያውቀው ቀሳጢ ነው በማለት ሐሰተኛ ማንነትን በመላበስ የቤተክርስቲያንን ስም ለማጠልሸተ የተሰማራ መሆኑን ገልጿል።
ስለሆነም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ግለሰቡ የቤተ ክርስቲያናችንን ዓርማ ወይም አልባሳት በመልበስና የሀገረ ስብከታችንን መልካም ገጽታ በማጉደፉ ግለሰቡንና እዩ ጩፋ የተባለውን አጽራረ ቤተ ክርስቲያን በህግ እንዲጠይቅን ስንል በታላቅ አክብሮት እናሳስባለን፤በማለት ለጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ በጻፈው ደብዳቤ ጨምሮ ገልጿል።

ምንጭ: የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

@ortodoxtewahedo
2024/09/29 15:37:36
Back to Top
HTML Embed Code: