Telegram Web Link
#ጎንደር
ይህ ቤተ ክርስትያን ጎንደር ደብረ - ብርሐን ቅድስት ሥላሴ ይባላል። በውስጡ በያዛቸው የስዕል ጥበባት በምድሪቱ ላይ ከሚገኙ ታላላቅ ቅርሶች አንዱ ነው። ደብረ ብርሐን ስላሴ በ17ኛው እና በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ ታላላቅ ነገስታት በነበሩት አባት እና ልጅ አማካይነት በቅብብሎሽ እየጎመራ የመጣ ነው። አፄ ዳዊት እና አዲያም ሰገድ ኢያሱ ዘመናቸውን ያበለፀጉበት ኪነ ሕንጻ ነው።

በደብረ ብርሃን ሥላሴ ውስጥ ጣሪያው እና ግድግዳው በሙሉ ስዕሎች ናቸው። አፍሪካዊ ኢትዮጵያዊ ስዕሎች። ኢየሱስ ክርስቶስን ኢትዮጵያዊ መልክ ሰጥተውት ስለውታል። እናቱ ማርያም ኢትዮጵያዊ ንቅሳት አላት። ፈትልም ትፈትላለች። መላዕክት ጭንቅላት እና ክንፍ ተሰርቶላቸው ይታያሉ። መላዕክት ጦር ጎራዴ ታጥው ኢትዮጵያን ይጠብቃሉ። ስዕሎቹ ዘላለም እንዳበሩ እንዳብረቀረቁ ዛሬም አሉ። ቀለማቱ የተላቆጡት በነጭ ሽንኩርት እና በዕንቁላል በነጩ ፈሳሽ ነው። እናም ያበራሉ።

የሥነ-ስዕል ተመራማሪዎች First Gonderian Art እና Second Gonderian Art እያሉ በአለም የስነ ጥበባት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያስተምሩባቸዋል።

ታሪካቸው ተወስቶ አያልቅም። በሐገሬ ታሪክ በእጅጉ እንድኮራ ከሚያደርጉኝ የሰው ልጅ የአዕምሮ እና የመንፈስ ግኝቶች መካከል ዋነኛው ደብረብርሐን ሥላሴ - ጎንደር ነው።

ምንጭ :- ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ

@orthodoxtewahedo
እንኳን እግዚዕ ዓለማት ቅድስት"ሥላሴ" እና "ደብረብርሃን ቅድስት ሥላሴ (ጎንደር) የቅዳሴ ቤት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+" ቅዳሴ ቤት "+

=>ልክ የዛሬ 324 ዓመት: አድያም ሰገድ ኢያሱ በኢትዮዽያ በነገሡ በ10ኛው ዓመት: (በ1684 ዓ/ም) በጐንደር ከተማ ንግሥተ አድባራት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተሰርታ ተጠናቃለች::

+ጥር 7 ቀንም ሊቁ ክፍለ ዮሐንስን ጨምሮ በርካታ ምዕመናን: ሠራዊት: መሣፍንትና ሊቃውንት ባሉበት ቅዳሴ ቤታቸው ተከብሯል:: በዕለቱም ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: ኢያሱ አድያም ሰገድ ኃያል: ደግ: ጥበበኛ: አስተዋይ: መናኝ ንጉሥ ነውና::

+ቤተ ሥላሴን አስጊጿታልና ከዚህ ቀን ጀምሮ ጥር ሥላሴ በድምቀት የሚከበር ሆኗል:: ነገር ግን በተሠራች በ16 ዓመቷ ደጉ ኢያሱ ከተገደለ በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ በአደጋ ፈርሷል:: ዛሬ የምናየው በ1708 ዓ/ም በልጁ በአፄ ዳዊት ሣልሳዊ የታነጸውን ነው::

ምንጭ:-Dn Yordanos Abebe

✍️አርከ ሥሉስ

@orthodoxtewahedo
"በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች እየተላለፉ ያሉት የበዓል አከባበር ክልከላን የሚገልጹ የሐሰት ዜናዎች ቤተክርስቲያንን የማይወክሉና ቤተክርስቲያናችን በዓሉን በሰላም ለማክበር ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር እያደረገች ያለውን ጥረት ከግንዛቤ ያላስገባ ነው።"

ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣
የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ


@orthodoxtewahedo
ጥር 8

✞ልደተ ካህን ወነቢይ ዘካርያስ ወልደ በራክዩ ✞

"ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ እስራኤል . . .
ይቅር ያለን : ለወገኖቹም ድኅነትን ያደረገ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን::"

(ሉቃ. 1:68)

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
      
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

@orthodoxtewahedo
"የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦትና ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ ከሰፈራ ተነስታችሁ ተከተሉት"

ኢያ ፫፣፫

❤️ መልካም ጥምቀት 💛

ለመቀላቀል

👉 @ortodoxtewahedo
አዲስ አበባ ፈረንሳይ ለጋሲዮን አቦ ማዞሪያ አደባባይ የጥምቀት ዝግጅት ::

@ortodoxtewahedo
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አደረሰን።

ወልቂጤ።

ፎቶ፦ ከማኅበራዊ ሚዲያ

@ortodoxtewahedo
"የእግዚአብሔርን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ ::"

-ማቴ 3÷3

"እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሏቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለም።"

-ዕብራውያን 6፥10

💚💛❤️

@ortodoxtewahedo
#ጥምቀትን የት ለማክበር አስበዋል ።


(‹‹የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦትን ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ ከሰፈራችሁ ተነሥታችሁ ተከተሉት፡፡›› ኢያሱ ፫፥፫)


( በ2016 ዓ.ም የተቀየሩ አሉ መረጃው ከዚኽ ዓመት ውጪ ያሉትን ያጠቃለለ ነው ። )
#ጥምቀትን_በአዲስ_አበባ__በየትኛው_ጥምቀተ_ባሕር_ያከብራሉ_
#በአዲስ_አበባ_በ10ሩም #ክፍለ_ከተሞች_የሚገኙ
#76ት #የጥምቀተ_ባሕር_ቦታዎችና_ወደ_ጥምቀተ_ባሕሩ_የሚወርዱትን_179 #ገዳማትና_አድባራት_እነሆ_ጽፈንላችኋል፡፡
(እኛ በአ.አ. ከሚገኙ 76ት ጥምቀት ባሕር መካከል፤ ብዙ ታቦታት የሚወርዱበትን የጃንሜዳን ፎቶ ለጥፈንላችኋል፤ እናንተም በየአካባቢያችሁ ያሉትን በ‹ኮሜንት› መጻፊያ ላይ ለጥፉልን፡፡)
      #share
፠ ፠ ፠ #በአራዳና_ጉለሌ_ክፍለ_ከተማ_ (7ት ጥምቀተ ባሕር)
#፩ኛ) #በጃንሆይ_ሜዳ_ (በጃንሜዳ)፤ /በአዲስ አበባ ትልቁና የ12 አብያተ ክርስቲያናት ታቦታት የሚያድሩበት)
1ኛ. መንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤ.ክ.፤
2ኛ. ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም፤
3ኛ. መንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም፤
4ኛ. መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ.፤
5ኛ. ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ.፤ (የምስካየ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም ታቦተ ወደ ጥምቀተ ባሕር ስለማይወጣ ሕዝቡና ሰ/ት/ቤቱ አብሮ ነው የሚያከብረው)
6ኛ. መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም
7ኛ. ደብረ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ.ክ.፤
8ኛ. መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ (አብሮም ቅዱስ ሚካኤል ይወርዳል)፤
9ኛ. ቀበና መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤ.ክ.፤
10ኛ. ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ.ክ.፤
11ኛ. አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ.፤
12ኛ.  ፈለገ ሰላም ቤላ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እና አቡተ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ (ቀበና 18 ፓርክ አጠገብ)፡፡
#፪ኛ) #እንጦጦ_ኀሙስ_ገበያ_ሜዳ
1ኛ. እንጦጦ ደብረ ኀይል ቅዱስ ራጕኤል ወኤልያስ ቤ.ክ.
2ኛ. እንጦጦ ደብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም
#፫ኛ) #ሽሮ_ሜዳ_ወረዳ_01#ቀበሌ_02_
1ኛ. ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት
2ኛ. መንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ
#፬ኛ) #አዲሱ_ገበያ_
1ኛ. ደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ
2ኛ. መንበረ ክብር ቅዱስ ሚካኤልና አቡነ ተክለሃይማኖት
#፭ኛ) #ወረዳ_3ና_4 (19 ቀበሌ)
1ኛ. መንበረ ንግሥት ቊስቋም ማርያም
#፮ኛ) #ሸጎሌ_መንገድ_
1ኛ. ጉለሌ(ሸጎሌ) ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
2ኛ. ድልበር መድኀኔ ዓለም
#፯ኛ) #ወረዳ_7_ቀበሌ_15(ቤልኤር፤ ኳስ ሜዳ)
1ኛ. ቀበና ምሥራቀ ፀሐይ መድኀኔ ዓለም

፠ ፠ ፠ #በየካ_ክፍለ_ከተማ_ (14ት ጥምቀተ ባሕር)
#፰ኛ) #ወረዳ_8(22 አካባቢ፤ ባልደራስ አጠገብ)
1ኛ. የካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል
2ኛ. ደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑር(ራ)ኤል
3ኛ. ቀበና ቤዛዊተ ዓለም ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
#፱ኛ) #ወንድይራድ_ትምህርት_ቤት_አካባቢ_(ኮተቤ)
1ኛ. ኮተቤ ደብረ ልዑል ዳግማዊ ቅዱስ ገብርኤል
2ኛ. ኮተቤ (ኋላ ሲ.ኤም.ሲ.) ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል
3ኛ. መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
4ኛ. ሲ.ኤም.ሲ. አቡነ ተክለ ሃይማኖት
5ኛ. ደብረ አራራት ቅዱስ አማኑኤል
6ኛ. ሀገረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ
7ኛ. ኮተቤ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ
#፲ኛ) #ዋሻ_ተክለ_ሃይማኖት_ጠበል_ቦታ
1ኛ. ዋሻ ደብረ መንክራት አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2ኛ. አንቆርጫ መንበረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል
#፲፩ኛ) #በግ_ተራ
1ኛ. ኮተቤ ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
#፲፪ኛ) #ላምበረት_ቤተ_ክርስቲያኑ_አካባቢ
1ኛ. ላምበረት ደብረ ፀሐይ አቡነ አረጋዊ
#፲፫ኛ) #ጉራራ_አካባቢ
1ኛ. ጉራራ ምሥራቀ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
2ኛ. ፈረንሳይ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ
#፲፬ኛ) #ወረዳ_10 #ከጉራራ_ከፍ_ብሎ_ፖሊስ_ሴንተር_አጠገብ
1ኛ. ደብረ መድሐኒት ዳንሴ መድኀኔዓለም
2ኛ. ምሥራቀ ፀሐይ ዳንሴ ቅዱስ ሚካኤል
#፲፬ኛ) #ሎቄ_ቤተ_ክርስቲያን_አካባቢ
1ኛ. ሎቄ መ.ጸ. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
#፲፭ኛ) #ኬንያ_ኤምባሲ_ጀርባ_(በግ ተራ)
1ኛ. ደብረ ዕንቊ ልደታ ለማርያም
#፲፮ኛ) #መሪ_አደባባይ
1ኛ. መሪ ምሥራቀ ፀሐይ ቅድስት ሥላሴ
2ኛ. መሪ ደብረ ታቦር ቅዱስ ፋኑኤል
#፲፯ኛ) #አባዶና_ካራ_አሎ_አርሴማ_ጠበል_አካባቢ_(ገበያው መሐል)
1ኛ. ካራ አሎ ደብረ ቀርሜሎስ መድኀኔ ዓለምና አቡነ ገሪማ
2ኛ. ካራ አሎ ቅድስት ሥላሴ
3ኛ. አባዶ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤልና ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ
4ኛ. ኮተቤ ደብረ ልዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ
#፲፰ኛ) #አባዶ_አካባቢ
1ኛ. አባዶ ገ/አ/ ቅዱስ ሚካኤል
#፲፱ኛ) #አያት_አካባቢ
1ኛ. ጣፎ መ/ብ/ ቅዱስ ገብርኤል
2ኛ. አያት ደ/ክ ቅድስት ማርያም
#፳ኛ) #አባዶ_ኮንዶሚንየም
1ኛ. አባዶ ጽርሐ አርያም ቅድስት ማርያም
2ኛ) ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሩፋኤል
3ኛ) ደብረ ልዕልና ቅድስት አርሴማ
4ኛ) ደብረ መንግሥት መድኀኔ ዓለም
5ኛ) አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
6ኛ. ቅዱስ ሚካኤልና ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ
7ኛ. ኢያሪኮ ቅዱስ ገብርኤል
፠ ፠ ፠ #ልደታ_አዲስ_ከተማና_ቂርቆስ_ክፍላተ_ከተማ_ (5ት ጥምቀተ ባሕር)
#፳፩ኛ) #ቂርቆስ_አካባቢ
1ኛ. ደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ
#፳፪ኛ) #ኦሎምፒያ_ቦሌ_ማተሚያ_ቤት_አካባቢ
1ኛ. ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ
2ኛ. ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ
#፳፫ኛ) #ልደታ_ክፍለ_ከተማ_ሜትሮሎጂ_ጀርባ
1ኛ. ደብረ አሚን ዳግሚት ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2ኛ. ጎላ ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ቅዱስ ሚካኤል
#፳፬ኛ) #ሳር_ቤት_ኮንዶሚንየም
1ኛ. ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኀኒት መድኀኔ ዓለም
#፳፭ኛ) #ቄራ_አካባቢ
1ኛ. አፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል
፠ ፠ ፠ #ኮልፌ_ቀራንዮ_ክፍለ_ከተማ_(9ኝ ጥምቀተ ባሕር)
#፳፮ኛ) #መድኀኔ_ዓለም_ከፍተኛ_መሠናዶ_ትምህርት_ቤት_(ራስ ኀይሉ ሜዳ)
1ኛ. መርካቶ ደብረ ኀይል ቅዱስ ራጕኤል
2ኛ. ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል
3ኛ. ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል
4ኛ. ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ
5ኛ. ጠሮ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ
#፳፯ኛ) #ሳንሱሲ_መናፈሻ_አጠገብ
1ኛ. አስኮ ደብረ ገነት ቅዱስ ገብርኤል
2ኛ. አስኮ ደብረ መንክራት ቅዱስ ጊዮርጊስ
3ኛ. መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
4ኛ. ፍኖተ ሎዛ ብርጭቆ ማርያም
#፳፰ኛ) #ወረዳ_15_(አርሴማ ጠበል /አወልያ ትምህርት ቤት ጋር/)
1ኛ. ቃሎ ተራራ አቡነ ሀብተ ማርያም
#፳፱ኛ) #ገዳመ_ኢየሱስ_ቤተ_ክርስቲያን_ቅጽር_ግቢ_ውስጥ
1ኛ. ደብረ ቀራንዮ መድኀኔ ዓለም
2ኛ. ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ
3ኛ. ደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ፊልጶስ
4ኛ. ወይብላ ደብረ ጽዮን ማርያም
5ኛ. ፊሊዶሮ ደብረ ፀሐይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
6ኛ. መርካቶ ደብረ ገሊላ አማኑኤል
7ኛ. ገዳመ ኢየሱስ
#፴ኛ) #ወረዳ_5_ #ጻድቃኔ_አካባቢ_ታቦት_ማደርያ
1ኛ. ደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊና ገብረ ክርስቶስ
2ኛ. ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ
3ኛ. አውግስታ ደብረ ጽዮን ማርያም
4ኛ. ጻድቃኔ ማርያም
5ኛ. ፈለገ ሕይወት ኪዳነ ምሕረት
6ኛ. ወይራ ገነተ ሰማይ ቅድስት አርሴማና ዕጨጌ ዮሐንስ
#፴፩ኛ) #ወረዳ_4_ #አየር_ጤና_ኪዳነ_ምሕረት_ቤተ_ክርስቲያን_አጠገብ
1ኛ. አየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
2ኛ. ጀሞ ፈለገ ኮሬብ ቅድስት ሥላሴና ቅድስት ማርያም
3ኛ. ዓለም ባንክ ደብረ ራማ ቅዱስ ገብርኤል
#፴፪ኛ) #ወረዳ_1_ #በቴል_አጠገብ_(ኳስ ሜዳ)
1ኛ. ቤቴል ደብረ ኢዮር ቅዱስ ሚካኤል
2ኛ. አንፎ መንበረ ብርሃን ቅዱስ ዑር(ራ)ኤል
#፴፫ኛ) #በላፍቶ_ክፍለ_ከተማ_ወረዳ_4 #ገብርኤል_ጠበል
1ኛ. ሰፈረ ገነት ቅድስት ሥላሴ
#፴፬ኛ) #ወረዳ_2_ #ሮል_ሳሙና_ፋብሪካ_ፊት_ለፊት
1ኛ. ረጲ ደብረ ጎልጎታ መድኀኔ ዓለም
2ኛ. ካራ ቆሬ ቅዱስ ሩፋኤል
3ኛ. ደብረ በረከት ቅዱስ ገብርኤል
4ኛ. ግራር ደ/አ/ቅድስት አርሴማ
5ኛ. ወይብላ ደብረ ጽዮን ማርያም

፠ ፠ ፠ #ነፋስ_ስልክ_ላፍቶ_ክፍለ_ከተማ_ (13ት ጥምቀተ ባሕር)
#፴፭ኛ) #ደብረ_ኢያሪኮ_መድኀኔ_ዓለም_ቤተ_ክርስቲያን_አጠገብ
1ኛ. ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል
2ኛ. ፉሪ ጽርሐ ንግሥት ቅድስት ሐና ማርያም
3ኛ. ደብረ ኢያሪኮ መድኀኔ ዓለም
4ኛ. ደብረ ወርቅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
5ኛ. ፈለገ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ
6ኛ. ፉሪ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል
#፴፮ኛ) #ጎፋ_ሠፈር
1ኛ. ጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል
2ኛ. ቤዛ ብዙኃን ኪዳነ ምሕረት
3ኛ. ቄራ መብራት ኀይል ደብረ መዊዕ ቅዱስ መርቆሬዎስና ዮሐንስ መጥምቅ
#፴፯ኛ) #ጀሞ_መድኀኔ_ዓለም
1ኛ. ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2ኛ. ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስና ቅዱስ ሚካኤል
#፴፰ኛ) #ቻይና_ካምፕ
1ኛ. ፈለገ ዮርዳኖስ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስና ቅድስት ማርያም
#፴፱ኛ) #ጀሞ_ቊጥር_3_አደባባይ
1ኛ. ጀሞ ቊጥር 3 ቅዱስ ገብርኤል
#፵ኛ) #ቶታል_አደባባይ
1ኛ. ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል
2ኛ. መካኒሳ ምዕራፈ ጻድቃን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
#፵፩ኛ) #መካኒሳ_ኮንዶሚንየም
1ኛ. መካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል
#፵፪ኛ) #ዮሴፍ_አካባቢ
1ኛ. ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
2ኛ. ደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ
3ኛ. ብሔረ ጽጌ ቅድስት ማርያም
4ኛ. አዲስ አምባ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
5ኛ. ሐመረ ወርቅ ቅድስት ማርያም
#፵፫ኛ) #ብሥራተ_ወንጌል
1ኛ. ደብረ ቢ/ያ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
#፵፬ኛ) #ደብረ_ዕንቊ_ቅዱስ_ገብርኤል
1ኛ. ደብረ ዕንቊ ቅዱስ ገብርኤል
#፵፭ኛ) #ፉሪ_ኆኅተ_ብርሃን_ቅድስት_ማርያም
1ኛ. ፉሪ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም
#፵፮ኛ) #ፉሪ_ደብረ_ገነት_ቅዱስ_ዑር(ራ)ኤል
1ኛ. ፉሪ ደብረ ገነት ቅዱስ ዑርኤል
#፵፯ኛ) #ቡልቡላ_ ኤምባሲ_አጠገብ
1ኛ. ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል
2ኛ. ለቡ በዓለ ወልድ
፠ ፠ ፠ #አቃቂ_ቃሊቲ_ክፍለ_ከተማ_ (9ኝ ጥምቀተ ባሕር)
#፵፰ኛ) #ወረዳ_1 #አቃቂ_በሰቃ_ወንዝ
1ኛ. ቃሊቲ መካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል
2ኛ. ሣሎ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ
3ኛ. ጃቲ ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
4ኛ. ሰርጢ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም
5ኛ. አቃቂ መንበረ ሕይወት መድኀኔ ዓለም
6ኛ. ቱሉ ዲምቱ ደብረ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ሚካኤል
7ኛ. ፈንታ ደ/ጽ/ቅዱስ ሩፋኤልና ቅድስት አርሴማ
8ኛ. ቀርሣ ፈለገ ብርሃን ቅድስት ልደታ ለማርያም
#፵፱ኛ) #ወረዳ_5 #ከቤተ_ክርስቲያኑ_አጠገብ
1ኛ. ቃሊቲ ደብረ ቊስቋም ማርያምና ቅዱስ ሚካኤል
#፶ኛ) #ወረዳ_4 #ሰርቲ_መድኀኔ_ዓለም_ቤተ_ክርስቲያኑ_አጠገብ
1ኛ. ሰርቲ ደብረ መድኀኒት መድኀኔ ዓለም
#፶፩ኛ) #ወረዳ_9 #ገብረ_መንፈስ ቅዱስ_ቤተ_ክርስቲያኑ_አጠገብ
1ኛ. ኮዬ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
#፶፪ኛ) #ቃሊቲ_አካባቢ
1ኛ. ሠፈረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል
#፶፫ኛ) #ወረዳ_9 #ሥላሴ_ቤተ_ክርስቲያኑ_አጠገብ
1ኛ. ቂሊንጦ ቅድስት ሥላሴ
#፶፬ኛ) #ወረዳ_10 #ገላን_ጉራራ_ገብርኤል_ቤተ_ክርስቲያኑ_አጠገብ
1ኛ. ገላን ጉራራ ፈለገ ግዮን ቅዱስ ገብርኤል
#፶፭ኛ) #ወረዳ_11 #ገላን_ኢዶሮ_ገብርኤል_ቤተ_ክርስቲያኑ_አጠገብ
1ኛ. ገላን ኢዶሮ ቅዱስ ገብርኤል
#፶፮ኛ) #መጠሊ_ገብርኤል_ቤተ_ክርስቲያኑ_አጠገብ
1ኛ. መጠሊ ደ/አ/ቅዱስ ገብርኤል
፠ ፠ ፠ #ቦሌ_ክፍለ_ከተማ_ (19ኝ ጥምቀተ ባሕር)
#፶፯ኛ) #ጉምሩክ_ወረዳ_3
1ኛ. ቦሌ ደብረ ሳሌም መድኀኔ ዓለም ወመጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ወአቡነ አረጋዊ
#፶፰ኛ) #ወረዳ_23 #አየር_መንገድ
1ኛ. ደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያምና ክርስቶስ ሰምራ
#፶፱ኛ) #ወረዳ_06 #መገናኛ
1ኛ. መገናኛ መንበረ ብርሃን ቅዱስ እግዚአብሔር አብ
#፷ኛ) #ወረዳ_02 #ሩዋንዳ_አካባቢ
1ኛ. ቦሌ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል
2ኛ. ቦሌ አየር ማረፊያ መንበረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ
#፷፩ኛ) #ወረዳ_13 #አድዋ_ፓርክ
1ኛ. ቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም
2ኛ. ገርጂ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ
3ኛ. ኤ(የ)ረር ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ዑርኤል
#፷፪ኛ) #ወረዳ_9 #ሰሚት_አደባባይ
1ኛ. ቦሌ ሰሚት መካነ ሰላም መድኀኔ ዓለም
2ኛ. ቦሌ ሰሚት ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ
3ኛ. ቦሌ ሰሚት ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
4ኛ. በሻሌ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ማርያም
#፷፫ኛ) #ወረዳ_12 #ቡልቡላ
1ኛ. ቦሌ ቡልቡላ ደብረ መድኀኒት መድኀኔ ዓለም
2ኛ. ቦሌ ቡልቡላ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ሳሙኤል ወቅዱ አማኑኤል
3ኛ. ቦሌ ቡልቡላ ፍኖተ ሕይወት ቅድስት ማርያም
#፷፬ኛ) #ወረዳ_9 #ጎሮ_ሰፈር_ባሕረ_ጥምቀት
1ኛ. ጎሮ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብኤል
2ኛ. ኤረር ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ
3ኛ. ኤረር መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል
#፷፭ኛ) #ወረዳ_13 #አያት_አደባባይ_ #4_ኪሎ_ሰፈር
1ኛ. አያት መ/ሕ/መድኀኔ ዓለም
#፷፮ኛ) #ወረዳ_13 #መሪ_አያት
1ኛ. መሪ ምሥራቀ ፀሐይ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
2ኛ. አያት ጌቴ ሴማኒ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት
3ኛ. መሪ ቅዱስ ፋኑኤል
4ኛ. መሪ ቅድስት ሥላሴ
#፷፯ኛ) #በሻሌ
1ኛ. ቦሌ በሻሌ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ እስጢፋኖስ
2ኛ. የቃጥላ ደብረ ፀሐይ ቅድሰት ማርያም
#፷፰ኛ) #ወቄ_አካባቢ
1ኛ. ወረገኑ ቅዱስ ሚካኤል
#፷፱ኛ) #አያት_ጨፌ
1ኛ. አያት ጨፌ ደብረ ኢያሪኮ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ
#፸ኛ) #ወረዳ_11 #ለሚ_ኮንዶሚኒየም
1ኛ. ቦሌ ሰሚት ቅዱስ ሩፋኤልና ኤዎስጣቴዎስ
#፸፩ኛ) #ወረዳ_11 #አራብሳ
1ኛ. አራብሳ ቅዱስ ገብርኤል
2ኛ. ዋሻው አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
#፸፪ኛ) #ለሚ
1ኛ. ቦሌ ለሚ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2ኛ. ቦሌ ለሚ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
#፸፫ኛ) #አያት_ኮንዶሚኒየም
1ኛ. አያት ጨፌ ቅዱስ ገብርኤል
2ኛ. አያት ፈለገ ሕይወት ቅዱስ ዮሐንስ
#፸፬ኛ) #ቦሌ_ቡኒ
1ኛ. ቦሌ ቡኒ ደብረ ቤቴል ቅዱስ እግዚአብሔር አብ
#፸፮ኛ) #ሪፈንቲ
1ኛ. ሪፈንቲ ቅዱስ ገብርኤል
2ኛ. ቦሌ ሰሚት መካነ ሕያዋን ዋሻው ቅዱስ ገብርኤል

መልካም የጥምቀት በዓል ይሁንልን!!!

@ortodoxtewahedo
2024/09/30 15:26:09
Back to Top
HTML Embed Code: