Telegram Web Link
✍️...ቅዱስ እስጢፋኖስ !!

ስለ ክርስቶስ መስክሮ በአይሁድ በድንጋይ ተወግሮ በክብር በሰማዕትነት ያለፈውን ቅዱስ እስጢፋኖስ ዛሬም ቅድስት ቤተክርስቲያን ትፈለጋለች ።

የወጣትነት ዘመኑን ኢየሱስን በመስበኩ በዚህም ምክንያት ቀናተኞች አይሁድ እንዲሞት የወገሩት ቅዱስ እስጢፋኖስ ለብዙ ወጣቶች ምሳሌ ነው።

ወጣትነትን ለእግዚአብሔር በመስጠት ክብር ማግኘት ኢየሱስ ክርስቶስን በመስበክ ዘላለማዊ ህይወት ማግኘት መታደል ነው።

ብዙዎች ጊዜአችንን በአልባሌ ነገር በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ ወሬ ከማውራት ከማጋደል የማይሆን ነገር ከማውራት ጥሩ ክርስቲያን ወጣት ለመሆን የተለወጠ ህይወት ይኑረን። ያልታደሰ ህይወት ይዘን ክርስቲያን ነን ብንል ሀሰት ነው።

ክርስቲያን ለመባል በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን እርሱን መምሰል ያስፈልጋል ።ያለበለዚያ በእናቴ በአባቴ ሃይማኖት በማለት መዳን አይችልም ። ለመዳን መለወጥ ለመዳን ክርስቶስን መከተል ያስፈልጋል ። ዛሬም ቅዱስ እስጢፋኖስን እንድንመስል ያስፈልጋል ። የተለወጠ ወጣትነትን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንስጥ።

የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱስ እስጢፋኖስ በረከት አይለየን።

@ortodoxtewahedo
እንዲቀጥል እንፈልጋለን!
(ዳር እስከ ዳር ሼር ይደረግ)
ቅዳሜ ጥር 4/ 2016 ዓ.ም በዶንኪ ቲዮብ ቀጥታ ስርጭት የአእላፋት ዝማሬ አንድ ሳምንት እናስታውሳለን።

@ortodoxtewahedo
ጥር-፪፦ ጻድቁ አቤል የሙታን በኩር ዕረፍቱ

@ortodoxtewahedo
እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል ።
ብጱዕ አቡነ ጴጥሮስ በረከቶ አትለየን ።

@ortodoxtewahedo
ይህን መረጃ ሼር የማያረግ አርቶዶክሳዊ እንዳይኖር ።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ከሀገር ውጪ ኮብልለው ተሰደዋል ተብሎ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተነዛው ወሬ ሐሰት ነው
***

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ከሀገር ኮብልለው ተሰደዋል ተብሎ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው ዘገባ ፍጹም ሐሰት ነው።

ብፁኡነታቸው የ2016 ዓ. ም የከተራ እና ጥምቀት በዓልን ለማክበር በቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ሀገረ ስብከታቸው ወደሆነው ኒወርክ እና አከባቢ መጓዛቸው ታውቋል።

ከከተራ እና ጥምቀት ክብረ በዓል መልስ ባሉ ጊዚያት ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ይሆናሉ።

ሊቀነ ጳጳሳት ወደ መንበራቸው ሲጓዙ ተሰደዋል የሚል ወሬ የሚነዛ መንጋ ልጅነቱ ለዲያቢሎስ ነው።

የውሸት ሙሽሮች !!!

Kune Demelash kassaye -Arba Minch

@ortodoxtewahedo
#የእውነት አባት በረከቶ አትለየን

ኀበ መኑ ነሐውር - ከአንተ ወደ ማን እንሔዳለን?

ይኽ በቀዳማዊ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ የተነገረ ቃል ነው። ያኹሉ ሕዝብ ሲሸሽ የተመለከተው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመከተል ጸንተው የቀሩትን ቅዱሳን ሐዋርያት "እናንተስ ልትሔዱ ትወድዳላችሁን?" አላቸው።

ቅዱስ ጴጥሮስ ፈጠን ብሎ [የሐዋርያት አፈ ጉባኤያቸው] "አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደ ኾንህ እናምናለን። ከአንተ ወደ ማን እንሔዳለን?" በማለት መለሰለት። ዮሐ ፮: ፷፰።

አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ [አፈ ጉባኤ] ናቸው። እንደ ሊቀ ሐዋርያቱ እርሳቸውም ከኢትዮጵያ ሊሔዱ ይወድዳሉን? ቢባሉ የአባታቸውን የሊቀ ሐዋርያቱን ቃል ከሚደግሙት በቀር ሌላ የላቸውም።

ወደ ኒው ዮርክ የሚመጡት በ፪ ምክንያት ነው።

፩. መጻኢው የጥምቀት በዓል ነው። ሀገረ ስብከት ያላቸው ሊቃነ ጳጳሳት የተለየ ምክንያት ካልገጠማቸው በቀር በዓሉን በሀገረ ስብከታቸው እንዲያከብሩ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ያዝዛል። እርሳቸው የኒው ዮርክና አካባቢው ሊቀ ጳጳስ ናቸው። ስለዚህ ወደ ሀገረ ስብከታቸው መሔዳቸው ይጠበቃል።

፪. የፊታችን ቅዳሜ በኒው ዮርክ ከተማ በመንበረ ጵጵስናቸው የጥር ሥላሴ በዓል ይከበራል። ለዚያ ለመድረስ ዛሬ መነሣታቸው የሚገርም አይደለም።

የሚወሸክቱ ሰዎች ፍላጎታቸው ግልጽ ነው። በላይ ቤት በታች ቤት ቢመላለሱ የጴጥሮስ ቁልፍ ተከርችሞ አልከፈት አላቸው። ስለዚህ ይለፋልፋሉ።

👉 ዲ/ን አባይነህ ካሴ


@ortodoxtewahedo
"ከሃይማኖቴ ጋር የእኔ ነፍስ ትወጣለች። በሃይማኖት አንደራደርም" አቡነ አብርሃም

ትናንት ከቆሙበት የመስቀል ዐደባባይ ዛሬም ያልወረዱ አባት። ቤተ ክርስቲያን የሕልውና አደጋ ስለደረሰባት ለመጨረሻው ጸዋትወ መከራ እንዘጋጅ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በመግለጫቸው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች

+ + + + +

፩. ቤተ ክርስቲያን የራሷ ነፃነት አላት

፪. ያም ይኽንን አድርጊ ይሄም ይኽንን አድርጊ ስላላት እየተጎተተች የተባለችውን የምታስተናግድ አትኾንም አይደለችምም።

፫. ማንም ይኽን አድርጊ እያለ ሊጎትታት አይችልም። ነገር ይኽንን በሉ ይኽንን ካላደረጋችሁ የሚባል መያዣ ነገር ቤተ ክርስቲያን አስተናግዳም አታውቅም። ወደፊትም አታስተናግድም። ወደፊትም የመጣውን በጸጋ ከምትቀበል ውጭ። ይኽንን አድርጊ ስልሽ ብቻ ነው የምታደርጊው የሚለው አስተሳሰብ ጨርሶ የቤተ ክርስቲያንን ሕልውና ይነካል።

፬. መንግሥት በዓለ ጥምቀትን ለማክበር ቅድመ ኹኔታ ማስቀመጡን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ በመግለጫቸው ጠቁመዋል። [የአቡነ ቄርሎስን እና የአቡነ ሉቃስን] አቋም በበዓሉ እንድታወግዝ መንግሥት አቋም ይዟል።

፭. መንግሥት አኩራፊ ሊኾን አይገባውም። ይኼንን ካላልሽ እንዲህ አላደርግም ማለት አይገባም።

፮. ሱሪ በአንገት አውጣው የሚባል ነገር ቤተ ክርስቲያን አትሸከምም

፯. መኪና ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ሲገባ የማይፈትሹ ሲወጣ የሚፈትሹ የመንግሥት ጥበቃዎች አሉ። የሚገባ መኪና አይፈተሽም የሚወጣ መኪና ይፈተሻል። ምንድን ነው የተፈለገው? ከቤተ ክርስቲያንስ ምንድን ነው የሚወጣው? መድፍ ነው? መሣሪያ ነው?

እኛ መሪዎቹ የማናውቀው ፈታሽ አቁሞ መፈተሽ ድፍረት ነው። የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕልውና መፈታተን ነው።

፰. መደፋፈሩ በዝቷል። መንግሥት ቤተ ክርስቲያኒቱን ደፍሯታል። አልፎ ይሔዳል። ቤተ ክርስቲያንን መድፈር አደጋ ነው። ለሃይማኖቱ የማይሞት የለም።

አዛዣችን በዝቷል። ላዘዘን ኹሉ አጎንብሰን እንችላለን እንዴ? ሃይማኖታችን ከሚፈቅደው ውጭ። በሉ የተባልነውን ኹሉ ማለት እንችላለን እንዴ? ለእኔ አድርግ የሚለኝ ሃይማኖቴ ብቻ ነው። ማስፈራሪያ አይገዛንም። ዘጠኝ ሞት መጣ ቢሉት አንዱን ግባ በለው።

፱. በየሔድንበት በየቢሮው ደሞ ለኦርቶዶክስ? እየተባልን ነው። ቢያንስ አይኾንም እንኳ [የአባት ነው] አትቁም ያሉት ለማኝ አትቁም ነው። ያንን ያንን ያርሙ።

እዚህ እኛው ቤት አድር ብዬው ቅጥረኛው ስለሚበዛ ነው። የድፍረት ኃጢአት በዝቷል። ድፍረት የቤቱን ሰው ገዝቷል የውጭውንም ሰው ገዝቷል። የማትደፈረውንም ቤተ ክርስቲያን እያስደፈረ ይመጣል። አኹን የቀረው በሉ ውጡ ብሎ የመረካከብ ሥራ ነው ይኽች ቤተ ክርስቲያን የቀራት። ይኽንን ደግሞ ቆሞ የሚያይ የለም።

የጎጠኝነቱ ምንጩ ቤተ ክህነቱ ኾኗል። ከሃይማኖቴ ቋንቋዬ ይበልጣል የሚሉ ሰዎች የተነሡበት ጊዜ ነው። ስወለድ ቋንቋዬን ይዤ ነው የተወለድኹት ሃይማኖት በኋላ ነው የመጣ ነው የሚሉ ካህናት የተፈጠሩበት ወቅት ነው።

፲. ከሃይማኖቴ ጋር የእኔ ነፍስ ትወጣለች። በሃይማኖት አንደራደርም።

አንበርክኬ ልግዛ የሚለው ይቁም

ለመጨረሻው ጸዋትወ መከራ ራሳችንን እናዘጋጅ!

በተጨማሪም ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን በተመለከተ የተናፈሰውን ወሬ በጸና ቃል እስከሞት በሚደርስ ትምምን በመግለጽ በትነውታል።

@ortodoxtewahedo
ብፁዕ አባታችን ቡራኬዎ ይድረሰን

እግዚአብሔር ያገልግሎት ዘመኖን በቅድስት ቤተክርስቲያን ያርዝምልን፤ በእድሜ በጸጋ ይጠብቅልን !

@ortodoxtewahedo
የፈለገ የሚያዛት ፣ የፈለገ የሚያሽከረክራት ፣ ያልወደደ እንደ ወደደ ፍላጎቱን ምኞቱን እንድትፈፅምለት የሚጎትታት ቤተክርስቲያንን ኖራም አታውቅም ወደፊትም ልትኖር አይገባም!!!

በሀይማኖታችን አንደራደርም ! ከ ሃይማኖቴ ጋር ነፍሴ ትወጣለች ።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በረከትዎ ይደርብን ።

@ortodoxtewahedo
2024/11/18 17:52:22
Back to Top
HTML Embed Code: