Telegram Web Link
††† እንኳን ለታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ዓመታዊ የተዓምር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

"በዛቲ ዕለት #እግዚአብሔር ገብረ: በእደ ባስልዮስ መንክረ::"
(በዚህች ዕለት እግዚአብሔር በባስልዮስ እጅ ድንቅን አደረገ)

††† ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ †††

††† ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ባስልዮስ #አርእስተ_ሊቃውንት ከሚባሉ አባቶች አንዱ ነው:: አባቱ #ኤስድሮስ(ባስልዮስ የሚሉ አሉ): እናቱ ደግሞ #ኤሚሊያ ይባላሉ:: ባልና ሚስት ከተቀደሰ ትዳራቸው 5 ወንድና 1 ሴት ልጅን አፍርተዋል:: የሚገርመው ሴቷ ( #ቅድስት_ማቅሪና) ገዳማዊት ስትሆን 5ቱም ወንዶች ዻዻሳት መሆናቸው ነው::

የሁሉ የበላይ የሆነው ግን ቅዱስ ባስልዮስ ነው:: አባቶቻችን እንዳስተማሩን ቅዱሱ ሊቅ ከ318ቱ ሊቃውንት አንዱ ነው:: #ቅዱስ_ኤፍሬም ሶርያዊንም ያስተማረው እርሱ ነው:: ነገር ግን ቅርብ ጊዜ ከድረ ገጾች (websites) እየገለበጡ የሚጽፉ አንዳንድ ወንድሞች ይህንን የሚያፋልስ ነገር ጽፈው ተመልክተናል::

††† ቅዱስ ባስልዮስ
ገዳማዊ ጻድቅ:
ባለ ብዙ ምሥጢር ሊቅ:
የብዙ ምዕመናን አባት:
የቂሣርያ ሊቀ ዻዻሳት:
ባለ ብዙ ተአምራትና ከከዊነ እሳት (ከፍጹምነት) የደረሰ አባት ነው:: ለመጀመሪያ ጊዜ የነዳያንን ሆስፒታል በ4ኛው መቶ ክ/ዘ ያስገነባ እርሱ ነው::

እጅግ ብዙ ድርሰቶች አሉት:: መጽሐፈ ቅዳሴንም ዛሬ በምናውቀው መንገድ ያሰናሰለው እርሱ ነው:: ለምዕመናን የሚጠቅሙ ብዙ ሥርዓቶችን ሠርቶ: የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ተርጉሟል:: ታዲያ ይህ ሊቅ: ቅዱስና ጻድቅ ሰው ብዙ ድንቆችን ሠርቷል:: ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ዛሬ ይህኛውን ታስባለች::

በዘመኑ እዚያው #ቂሣርያ ውስጥ አንድ አገልጋይ (በዘመኑ አጠራር ባሪያ) ነበር:: የሚሠራው ደግሞ በሃገረ ገዥው ግቢ ውስጥ ነው:: ለሥራ ሲገባ የሰውየውን አንዲት ብቸኛ ልጅ ተመለከታት:: ቆንጆ ነበረችና በፍትወት ተለከፈ:: ጧት ማታ ሥራው እሷን ማየት ሆነ::

እንዳይጠይቃት ደረጃው አይመጥንምና ከባድ ፍርድ ይጠብቀዋል:: ነገሮች ከአቅሙ በላይ ሲሆኑበት በቀደመ ስሕተቱ ላይ ሌላ ከባድ ስሕተትን ጨመረ:: ወደ ጠንቅዋይ (መተተኛ) ቤት ሒዶ ሥራይ እንዲደረግለት ጠየቀ:: መተተኛው ግን "ይህንን ማድረግ የሚችል ሰይጣን ብቻ ስለሆነ ካልፈራህ ወደ እርሱ ልላክህ" አለው::

ያ ከንቱ ሰው "እሺ" አለ:: መተተኛው ቀጠለ "በል! ሌሊት 6 ሰዓት ሲሆን ወደ አሕዛብ መቃብር ሒድና ግራ እጅህን ወደ ላይ ዘርጋ:: ከዛ ይመጣልሃል" ብሎ ላከው:: አገልጋዩም የተባለውን ሲያደርግ ከአጋንንት አንዱ መጥቶ: ነጥቆ ወደ ጥልቁ: የሰይጣኖች አለቃ ወደ ሚገኝበት ወሰደው::

ጋኔኑ ሰውየውን አለው:- "አንተ የፈለከው እንዲፈጸም መጀመሪያ ክርስትናህን ካድ:: በክርታስም ላይ ክህደትህን ጽፈህ በፊርማህ ስጠኝ" አለው:: ያ ልቡ የታወረ ሰው እንደተባለው መጽሐፈ ክህደቱን ለሰይጣን ሰጠ:: ወዲያው ያ ያመጣው ወደ ቤቱ መለሰው::

በማግስቱ ጠዋት በሃገረ ገዥው ቤት ታላቅ ግርግር ሆነ:: ልጃቸው "ያን አገልጋይ ካላጋባችሁኝ ራሴን አጠፋለሁ" አለች:: ቢለምኗትም ልትሰማ አልቻለችም:: ወላጆቿ ግራ ስለተጋቡ ከምትሞት ብለው እያዘኑ ልጃቸውን ከአጋንንት ጋር ለተዛመደ ሰው ሰጡ::

እነርሱ ተጋብተው ኑሯቸውን ቀጠሉ:: ወላጆች ግን የአንድ ልጃቸውን ነገር እንዲህ በዋዛ ሊተውት አልወደዱምና ጾሙ: ጸለዩ: ተማለሉ:: በእንዲህ ሁኔታ ብዙ ዓመታት አለፉ:: ወላጆቿ ግን ተስፋ አልቆረጡምና እግዚአብሔር ሰይጣን የቀማትን ማስተዋል መለሰላት::

አንድ ቀንም ባሏን ጠርታ " #ቤተ_ክርስቲያን ተሳልመህ: ቆርበህ : ስመ እግዚአብሔር ጠርተህ: አማትበህስ ታውቃለህ?" አለችው:: እርሱም "በጭራሽ አላውቅም" አላት:: "ለምን?" ብትለው የሆነውን ነገር ሁሉ ዘርዝሮ ነገራት:: በጣም ከመደንገጧ የተነሳ ምድር ከዳት::

ለረዥም ሰዓት አለቀሰች:: ከሰይጣን ጋር ተጋብታ የኖረች ያህል ስታስበው አንገፈገፋት:: ሰውነቷ ተስፋ ቆረጠ:: ወዲያው ግን በህሊናዋ አንድ ሐሳብ መጣላት:: "ያ ታላቅ የእግዚአብሔር ሰው ከሰይጣን ባርነት ሊገላግለኝ ይቻለዋል" አለች:: ፈጥናም ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ዘንድ ሒዳ ከእግሩ ሥር ወድቃ አለቀሰች::

እርሱም "ልጄ ሆይ! አይዞሽ: በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉ ቀላል ነው:: ሒጂና ባልሺን አምጪው" አላት:: ሒዳ አመጣችው:: ቅዱሱም ያን ሰው "መዳን ትፈልጋለህ?" አለው:: ሰውየው መልሶ "ያቺን ደብዳቤ መመለስ የሚቻል ቢሆንማ እፈልግ ነበር" አለው:: ቅዱስ ባስልዮስም ሴቷን "ሒጂና ጸልይ: ከ40 ቀን በሁዋላ ትመጫለሽ" ብሎ አሰናበታት::

በሰይጣን ባርነት የተያዘውን ያን ሰው ግን ወደ ራሱ በዓት ወስዶ አስገባውና በ4 አቅጣጫ በመስቀል አተመው:: ትንሽ ምግብ ሰጥቶት "ከ3 ቀን በሁዋላ እመጣለሁ" ብሎት ሔደ:: ቅዱሱ ያለ ዕረፍት ይጋደልም ጀመር:: በ3ኛው ቀን መጥቶ "እንዴት ነህ?" አለው:: "አባቴ! አጋንንት አሰቃዩኝ" አለው:: "አይዞህ!" ብሎት ወጣ::

በ6ኛው ቀን መጥቶ "አሁንስ?" አለው:: "አባ! ስቃዩ ቀረልኝ: ግን ደብዳቤዋን እያሳዩ ያስፈራሩኛል" አለው:: "በርታ" ብሎት ሔደ:: በ9ኛው ቀን ተመልሶ "ደግሞ አሁንሳ?" አለው:: "አባቴ! ምስጋና ለፈጣሪህ! ከአካባቢው እየራቁ ነው" አለው::

እንዲህ በ3: በ3 ቀናት እየተመላለሰ ለ13 ጊዜ ጠየቀው:: በ39ኛው ቀን መጥቶ "ዛሬ ምን አየህ" ቢለው "አባ! አጋንንትን ከእግርህ በታች ስትረግጣቸው አየሁ" አለው:: ቅዱስ ባስልዮስ በ40ኛው ቀን ደወል ደውሎ መነኮሳት: ካህናትና ምዕመናንን ሰብስቦ: ያን ሰው ከመሃል አቁሞ: "እግዚኦ በሉ" አላቸው::

ሕዝቡ እግዚኦታውን ሲፈጽሙ ከሰማይ ድምጽ ተሰማ:: ቀና ሲሉ ያቺ የክህደት ደብዳቤ ሁሉ እያዩአት ከመካከላቸው ወደቀች:: በዚያች ቦታም ታላቅ እልልታና ሐሴት ተደረገ:: ቅዱሱ በጸሎቱ ለ40 ቀናት ከእንቅልፍና ከምግብ ተከልክሎ ያቺን ነፍስ ማረከ::

የሕዝቡንም ሃይማኖት አጸና:: በዚያውም ቅዳሴ ቀድሶ ሕዝቡን አቁርቦ አሰናበታቸው:: ባልና ሚስቱንም ባርኮ በፍቅር ይኖሩ ዘንድ አሰናበታቸው:: ታላቁ ሊቅም ተጋድሎውን ፈጽሞ ጥር 6 ቀን ዐርፏል::

††† አምላከ ቅዱስ ባስልዮስ እኛንም ከኃጢአት ማሠሪያ ፈትቶ ከአጋንንት ሤራ ይሰውረን:: ከሊቁም በረከትን ያሳትፈን::

††† መስከረም 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
2.አባ ይስሐቅ ባሕታዊ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3."99ኙ" ነገደ መላዕክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5."13ቱ" ግኁሳን አባቶች
6.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
7.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ

††† "እውነት እውነት እላቹሃለሁ:: በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል:: ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል:: እኔ ወደ አብ እሔዳለሁና:: አብም ስለ #ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ:: ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ::" †††
(ዮሐ. 14:12)

ሰው ሁሉ ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን !
(ያዕቆብ 1፥19)

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼


#ቤተክርስቲያን #ባህረ #ጥበባት

ቤተክርስቲያን ባህረጥበባት(4)
አትመረመርም(2)እጅግ ጥልቅ ናት(2)
በሥጋዊ ጥበብ ለማወቅ ቢቃጣ
የእምነት መነፅሩን ይዞ ስላልመጣ(2)
አንዳንዱ በክህደት(2) ፈጣሪውን አጣ(2)
............
እንመሰክራለን አማኑኤል አለ
እንመሰክራለን ፈጣሪያችን አለ(2)
አንዳንዱ ቢክደው(2)እየተታለለ(2)
.............
ቤተክርስቲያን ባህረጥበባት(4)
አትመረመርም(2)እጅግ ጥልቅ ናት(2)
...............
እንመሰክራለን ድንግል አማላጂ ናት
እንመሰክራለን ማርያም አማላጂ ናት(2)
ወላዲተ አምላክ(2)መሰረተ ሕይወት(2)
..................
ቤተክርስቲያን ባህረጥበባት(4)
አትመረመርም(2)እጅግ ጥልቅ ናት(2

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ የእናንተ አስተያየት ያበረታናልና አስተያየታችሁን በ
@ortodoxtewahedoo ላይ ይለግሱን !

‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ›› ት.ኢሳ 58÷3

ለመቀላቀል

👇👇👇👇👇👇👇👇
http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
††† እንኳን ለጻድቃን ቅዱሳን አባ አጋቶን ወአቡነ ያሳይ ዘመንዳባ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አባ አጋቶን ዘዓምድ †††

††† ታላቁ ጻድቅ በትውልድ ግብጻዊ ሲሆኑ የነበሩበት ዘመንም ከ4ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ እስከ 5ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ አካባቢ ነው:: በእርግጥ 'አጋቶን ' በሚባል ስም የሚጠሩ ብዙ አበው አሉ:: ቅድሚያውን 2ቱ ይወስዳሉ::
አንደኛው አባ አጋቶን ለ30 ዓመታት ድንጋይ ጐርሰው የኖሩት አባት ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ ዛሬ የምናከብራቸው ናቸው:: እኒህኛው 'ዘዓምድ ' ይባላሉ:: ምክንያቱም ለ50 ዓመታት አንድ ምሰሶ ላይ ያለ ዕረፍት ጸልየዋልና ነው::

አባ አጋቶን ገና ከልጅነታቸው መጻሕፍትን የተማሩ ሲሆኑ ምናኔን አጥብቀው ይፈልጓት ነበር:: በዚህም ራሳቸውን በትሕርምት እየገዙ: በዲቁና ማዕርጋቸውም እያገለገሉ እስከ 35ዓመታቸው ቆዩ:: በዚህ ጊዜ ደግሞ 'ይገባሃል' ብለው ቅስናን ሾሟቸው::

የማታ ማታ የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ተምኔተ ልባቸውን ፈጽሞላቸው ወደ በርሃ ሔዱ:: ወቅቱ የግብጽ ገዳማት በቅዱሳን ሕይወት የበሩበት ነውና እዚህም እዚያም አበውና እናቶች ይገኙ ነበር::

አባ አጋቶንም የከዋክብቱ አበው አባ ገዐርጊና አባ አብርሃም ደቀ መዝሙር ሆነው ገቡ:: አስፈላጊውን የምንኩስና ፈተና ካለፉ በኋላም ምንኩስናን ከእነዚህ አባቶች ተቀበሉ:: በዚያው በገዳመ አስቄጥስ በጽኑ ገድል ተጠምደው ለ15 ዓመታት አገለገሉ::

ጻድቁ ከእርሳቸው በፊት የነበሩ ቅዱሳንን ተጋድሎ ጠዋት ማታእያነበቡ መንፈሳዊ ቅናትን ይቀኑ ነበር:: በተለይ የታላቁን ስምዖን ዘዓምድን ገድል ሲያነቡ ሕሊናቸውን ደስ ይለው: ይህንኑ ገድል ይመኙ ነበር:: እድሜአቸው 50 ዓመት በሞላ ጊዜ በልቡናቸው እንደ አባ ስምዖን ዘዓምድ ለመጋደል ወሰኑ:: ይህን ለገዳሙ አባቶች ቢያማክሯቸው አበው:- "ይበል! ሸጋ ምክር ነው:: እግዚአብሔር ያስፈጽምህ!" ብለው መርቀው አሰናበቷቸው:: አባ አጋቶን የዳዊትን መዝሙር እየዘመሩ ከገዳሙ ወጡ:: በጣምም ወደ ዓለም ሳይገቡ: ከዓለም (ከከተማም) በጣም ሳይርቁ አንድ ረዥም ምሰሶ አገኙና ከላዩ ላይ ወጡ::

ከዚህች ዕለት ጀምረው ጻድቁ ለ50 ዓመታት ከዚያች ዓምድ (ምሰሶ) ወርደው: ለሥጋቸውም ዕረፍትን ሰጥተውት አያውቁም:: ማዕከለ ገዳም ወዓለም ናቸውና ለምዕመናንም ሆነ ለመነኮሳት አጽናኝ አባት ሆኑ:: ለአካባቢውም የብርሃን ምሰሶ ሆኑ:: የታመመ ቢኖር ይፈውሱታል:: የበደለውን በንስሃ ይመልሱታል:: ሰይጣን የቋጠረውን ይፈቱታል:: ለራሳቸው ግን ከጸሎት: ከጾምና ከትሕርምት በቀር ምንም አልነበራቸውም:: በተለይ እነዚህ ስራዎቻቸው ይዘከሩላቸዋል::
1.አጥማቂ ነን እያሉ ሕዝቡን ያስቱ የነበሩ ሰዎችን እየጠሩ እንዲህ የሚያስደርጋቸውን ጋኔን ከእነሱ አስወጥተዋል::
2.እርሳቸውን ያልሰሙት ግን መጨረሻቸው ጥፋት ሆኗል::
3.ፍጹም ወንጌልን በሕይወትና በአንደበት መስክረዋል::
4.ሕዝቡን በንስሃ አስጊጠዋል::
5.ተግሳጽ የሚገባውን ገስጸዋል::

ጻድቁ አባ አጋቶን ዘዓምድ ከእነዚህ የቅድስና ዘመናት በኋላበተወለዱ በ100 ዓመታቸው በዚህች ቀን ዐርፈው በክብርና በዝማሬ ተቀብረዋል::

††† አቡነ ያሳይ ዘመንዳባ †††

††† እኒህ ኢትዮዽያዊ ጻድቅ በ14ኛው መቶ ክ/ዘ በጣና ገዳማትውስጥ ያበሩ ኮከብ ናቸው:: ከ7ቱ ከዋክብት (አባ ዮሐንስ፣ አባ ታዴዎስ፣ አባ ያፍቅረነ እግዚእ፣ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አባ ሳሙኤል ዘቆየጻና አባ ሳሙኤል ዘጣሬጣ ) እርሳቸው አንዱ ናቸው:: እነዚህ አበው ከገዳማዊ ሕይወታቸው ባሻገር በምስጉን የወንጌል አገልግሎታቸው የሚታወቁ ናቸው::

ገድላቸው እንደሚለው አቡነ ያሳይ የዐፄ ዐምደ ጽዮን ቀዳማዊ ልጅ ሲሆኑ የተወለዱትም በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ሽዋ: ተጉለት ውስጥ ነው:: ገና በልጅነታቸው ወደ አባታቸው ቤተ መንግስት የሚመጡ መነኮሳትን እግር እያጠቡ ሥርዓተ ምንኩስናን በድብቅ ያጠኑ ነበር::

ብሉይ ከሐዲስ የጠነቀቁ ናቸውና የአባታቸውን ዙፋን (ልዑልነት) ስለ ፍቅረ ክርስቶስ ንቀውት እየዘመሩ ጠፍተው ወደ ትግራይ ተጓዙ:: በዚህም ምክንያት 'መናኔ መንግስት' ይባላሉ:: በዚያም ወደ ደብረ በንኮል ገዳም ውስጥ ገብተው የታላቁ አባት የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደቀ መዝሙር ሆኑ::

ቀደም ሲል የጠቀስናቸው 7ቱ አበው በዚያ ነበሩና 7ቱም በአንድ ቀን ሲመነኩሱ ገዳሙ የተቃጠለ እስኪመስል ድረስ ብርሃን ወርዶ ነበር:: አቡነ ያሳይ በረድእነት በቆዩበት ዘመን ዛፎችን መትከል ይወዱ ነበር:: ከትሩፋት መልስም በልብሳቸው ውሃ እየቀዱ ያጠጡ ነበር:: በተለይ "ምዕራገ ጸሎት" የሚባለው ተአምረኛ ዛፍ ዛሬ ድረስ አለ ይባላል::

አቡነ ያሳይ ጊዜው በደረሰ ሰዓት ከአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ተባርከው: ከ2ቱ ባልንጀሮቻቸው (አቡነ ሳሙኤል ዘዋሊና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ) ጋር ወደ ጣና ሐይቅ መጡ:: በዚያም አካባቢ ተአምራትን እየሠሩ ሕዝቡንም እያስተማሩ ከቆዩ በኋላ ጌታ ወደየፈቀደላቸው ቦታ ተለያዩ::

አቡነ ሳሙኤል ወደ ዋልድባ: አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ወደ ገሊላ: ከዚያ ወደ ጉጉቤ ሲሔዱ አቡነ ያሳይ መንዳባ ውስጥ ገቡ:: ጻድቁ ወደ አርባ ምንጭ ሒደው ታቦተ መድኃኔ ዓለምን ይዘው ሲመጡ ጣናን የሚሻገሩበት አጡ:: ጌታን ቢማጸኑት:- "ምነው እሷን ድንጋይ ባርከህ አትቀመጥባትም?" አላቸው:: እሳቸውም በእምነት: ድንጋይ ላይ ተቀምጠው ጣናን ተሻገሩት:: ይህንን ከርቀት ያዩ የዘመኑ ሰዎች "ብዙ ተአምር አይተናል: ነገር ግን ማን እንደ አባ! ጣናን በድንጋይ የተሻገረ" ሲሉ አድንቀዋቸዋል::

ጻድቁ ጣናን ተሻግረው: ገዳም መሥርተው: ብዙ አርድእትን አፍርተው: በተጋድሎ ሕይወታቸው ቀጥለዋል:: በተለይ ዛሬ ድረስ የሚተረከው የ'አትማረኝ' ታሪክም የሚገኘው እዚሁ ገዳም ውስጥ ነው:: ታሪኩም በየዋህነት "አትማረኝ" ብለው ጸልየው ጣናን ያለ ታንኳ በእግራቸው የረገጡ አባትን የሚመለከት ሲሆን ከአቡነ ያሳይ ጋርም ወዳጅ ነበሩ::

አባታችን አቡነ ያሳይ ለዘመናት በቅድስና ኑረው: ቅዱሳንንም ወልደው መስከረም 14 ቀን ታመሙ:: "ጌታ ሆይ!" ብለው ቢጠሩት መድኃኔ ዓለም መጣላቸው:: ጣና በብርሃን ተከበበች:: ጌታም "ወዳጄ! ስለ ድካምህ: ደጅህን የረገጠውን: መታሰቢያህን ያደረገውን: በስምህ የተማጸነውን ሁሉ ከነትውልዱ እምርልሃለሁ" ብሏቸው ነፍሳቸውን አሳረገ:: አበውም ሥጋቸውን ገንዘው እዚያው መንዳባ መድኃኔ ዓለም ውስጥ ቀበሩት:: ዐጽማቸው ዛሬም ድረስ ይገኛል::

††† አምላከ ጻድቃን በምልጃቸው የበዛች ኃጢአታችንን ይቅር ይበለን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::

††† መስከረም 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ አጋቶን ዘዓምድ
2.አቡነ ያሳይ ዘመንዳባ
3.አባ ጴጥሮስ መምሕረ ጻና (ጣና)
4.ቅዱስ ዴግና ቀሲስ

††† ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
2.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
3.ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው)
5.አባ ስምዖን ገዳማዊ
6.አባ ዮሐንስ ጻድቅ
7.እናታችን ቅድስት ነሣሒት

††† "ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል:: ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም::" †††
(ማቴ. ፲፥፵፩)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ መስከረም ፲፮ (16) ❖

✞✞✞ እንኩዋን ለቅድስት ሃገር #ኢየሩሳሌም: ለቅዱስ #ጦቢት እና ለአባ #አጋቶን_ባሕታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ #ሕንጸታ_ለኢየሩሳሌም +"+

=>ኢየሩሳሌም በብሉይም: በሐዲስም ቅድስት ሃገረ
እግዚአብሔር ናት:: '#ኢየሩ' ማለት 'ሃገር' ማለት ሲሆን
'#ሳሌም' ደግሞ 'ሰላም' ማለት ነው:: ስለዚህ በቁሙ
'ሃገረ ሰላም': '#ሃገረ_ክርስቶስ' ማለት ነው::

+ኢየሩሳሌም የሚለው ቃል በቁሙ ቅድስት ሃገርን
ሲመለከት በምሥጢሩ ግን የቤተ ክርስቲያን: የመንግስተ
ሰማያት እና የአማናዊት ሃገረ ሰላም #ድንግል_ማርያም
መጠሪያ ነው:: ኢየሩሳሌምን በከተማ ደረጃ የመሠረታት
ታላቁ ካህን #መልከ_ጼዴቅ ሲሆን 'ንጉሠ ሳሌም'
ተብሎም ኑሮባታል::

+ይህች ቅድስት ሃገር በብሉይ ዘመን እግዚአብሔር
በረድኤት ቢገለጥባት: ጻድቃነ ብሊት ቢኖሩባት
ተቀድሳለች:: በሐዲስ ኪዳን ግን አምላካችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ከሰማያት ወርዶ 33 ዓመት ከ3 ወር ያህል
የድኅነ ትሥራውን ቢፈጽምባት: ለድንግል ማርያምና
ለብዙ ቅዱሳን ቤት ብትሆን የበለጠ ተቀድሳለች::

+ዛሬም ድረስ ከተለያዩ ክፍላተ ዓለማት በብዙ ድካምና
ወጪ ሊያዩዎት ይጉዋዛሉ:: የቀደመው ዘመን
አባቶቻችንም ይህችን ቅድስት ከተማ ለመሳለም እስከ
ደም ጠብታ ከፍለዋል::

+ወደ ዋናው ጉዳያችን እንለፍና የኢየሩሳሌምን መታነጽ
እንይ:: ኢየሩሳሌም በአሕዛብ እጅ ብዙ ጊዜ ፈርሳ
ታንጻለች:: እኛ ግን ዛሬ የምናከብረው የከተማዋን
መታነጽ ሳይሆን በከተማዋ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ
መንገድ በአንድ ጊዜ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት
መታነጻቸውን ነው:: ይሕስ እንደምን ነው ቢሉ:-

+ከክርስቶስ ዕርገት 300 ዓመታት በሁዋላ ለቤተ
ክርስቲያን የተነሳችው #ቅድስት_ዕሌኒ በጐ ሃሳብ
በሕሊናዋ ተመላልሷልና ተነሳች::

#ጉባኤ_ኒቅያ ከተጠናቀቀ በሁዋላ ልጇ ቆስጠንጢኖስ
በነገሠ በ20 ዓመቱ በ227 ዓ/ም አካባቢ ቅዱስ ዕጸ
መስቀሉን ትፈልግ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ጉዞ አደረገች::

+መስቀሉን ፈልጋ ያገኘችበት ታሪክ ለነገ ይቆየንና
መስቀሉን ካገኘችው በሁዋላ በሙሉ ከተማዋ ላይ
አብያተ ክርስቲያናትን ለማነጽ ከልጇ ጋር ተስማማች::

+ለሕንጻው የሚሆን ብዙ ወርቅ: ብርና እንቁ ጭና
ማምጣቷን የተመለከቱት #አባ_መቃርስ (የኢየሩሳሌም
ሊቀ ዻዻስ ናቸው) "ልምከርሽ! ቤተ ክርስቲያኑን
በጠንካራ አለት ላይ ሥሪ:: ወርቅና ብሩን ግን ለነዳያን
በትኚ" ስላሏት በአካባቢው ላሉ ነዳያን ታላቅ ፌሽታ
ሆነ:: እጅግ ብዙ ሠራዊት: ብዙ ሺህ ሠራተኞች
ታጥቀው 80 አብያተ ክርስቲያናትን ያንጹ ጀመሩ::

+ሥራው ረቂቅና ብዙ ሥለ ነበረ እጅግ አድካሚ ነበር::
ቅድስት ዕሌኒ ሃገሪቷን በቤተ መቅደሶች መሸፈን ስለ
ፈለገች እንዲታነጽ ያዘዘችው የቤተ ክርስቲያን ቁጥር 80
ደረሰ:: እነዚህም ጌታ ከጽንሰቱ እስከ ዕርገቱ
የረገጣቸውና #እመ_ብርሃን የረገጠቻቸው ቦታዎች
ናቸው::

+#ቤተ_ልሔም: #ዮርዳኖስ: #ደብረ_ሊባኖስ:
#ደብረ_ታቦር: #ደብረ_ዘይት: #ጐልጐታ: #ጌቴ_ሴማኒ:
#ቤተ_ሳይዳ: #ጽርሃ_ጽዮን ደግሞ ዋና ዋናዎቹ ናቸው::
በአካባቢው ያሉ ነዳያን ሳይርባቸው: ሠራተኞችም ደሞዝ
ሳይቸግራቸው: 80ው አብያተ ክርስቲያናት በፈጣሪ
ረዳትነት: በ10 ዓመታት ታነጹ::

+ቀጥሎም ንጉሡ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ በዓለም ያሉ
ታላላቅ ቅዱሳን ሊቃነ ዻዻሳትን ጠርቶ: ሁሉም እስከ
መስከረም 15 ቀን ወደ ኢየሩሳሌም በተሰበሰቡበት
የሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ቅዳሴ ቤት በአንድ ላይ
ሲከበር ከዝማሬው ብዛት: ከአምላክ ጸጋ የተነሳ
በከተማዋ ታይቶ የማይታወቅ ሐሴት ተደረገ::

*ኢየሩሳሌም ፍጹም አጊጣ እስከ መከራ ቀን (አሕዛብ እስከ ተነሱበት) ቆይታለች::

+"+ #ቅዱስ_ጦቢት (ጻድቅ ነቢይ) "+

=>ከክርስቶስ ልደት በፊት እሥራኤላውያን ክፋትን
ሲያበዙ ጠላት መጥቶ ይማርካቸው: ንስሃ ሲገቡ ደግሞ
በድንቅ ተአምር ይወጡ ነበር:: ሕዝቡ ሲማረክ ነቢያት
እረኞች ናቸውና ያለ ጥፋታቸው አብረው ይማረኩ ነበር::
በዚያም ሕዝቡን ያስተምራሉ: ያጽናናሉ::

+በተመሳሳይ እሥራኤላውያን ተማርከው ወደ #ነነዌ
በወረዱበት ወራት ጦቢት የሚሉት ደግ ሰው
በመካከላቸው ነበር:: ይህ ደግ ሰው ከምርኮ በፊት
መልካም አምልኮት የነበረው: አሥራቱን በኩራቱን
የሚያወጣ: ለነዳያን የሚራራ ነበር::

+ከተማረኩ በሁዋላም ሕዝቡ ከአሕዛብ ጋራ ሲቀላቀሉ
እርሱ ንጽሕናውን ጠብቆ እግዚአብሔርን ያመልክ ነበር::
ቅዱስ ጦቢት በተለይ የሞተ ሰው ሲያገኝ ሳይቀብር
እህል አይቀምስም ነበር:: በዚህም ምክንያት የዘወትር
ጦመኛ ነበር::

+ይሕ ቅዱስ እድሜው 58 በሆነ ጊዜ ዓይኑ ጠፋ:: ብዙ
በመሰቃየቱም ሞቱን ለመነ:: በሌላ አቅጣጫ ደግሞ
#ሣራ 'አስማንድዮስ' የሚባል ጋኔን 7 ባሎቿን እየገደለ
አሳቅቁዋት ነበርና እርሷም ሞቷን ተመኘች::

+እግዚአብሔር ግን መልአኩን ልኮ: #ቅዱስ_ሩፋኤል
አዛርያን መስሎ የጦብያና የሣራን ጋብቻ ባርኩዋል::
ጋኔኑንም በጥልቁ አስጥሞታል:: በዓሣ ሐሞትም
የጦቢት ዓይኑ በርቶለት በእድሜው ላይ 100 ዓመታት
ተጨምረውለታል:: ቅዱስ ጦቢት ብዙ ሕብረ ትንቢቶችን
ተናግሮ በ158 ዓመቱ በዚህች ቀን ዐርፏል::

+"+ #አባ_አጋቶን_ባሕታዊ +"+

=>ይህንን ቅዱስ የማያውቅ የቤተ ክርስቲያን ሰው
ይኖራል ብየ አልገምትም:: እርሱ ታላቅ ጻድቅ: ገዳማዊና
የእግዚአብሔር ሰው ሲሆን አንደበቱን ከክፋት ይከለክል
ዘንድ ለ30 ዓመታት ድንጋይ ጐርሶ ኖሯል::

+ይህንን ቅዱስ #ሊቃውንት ሲገልጹት "ክምረ ክምር
ጽድቁ እስከ አስተርአየ" ይሉታል:: ትእግስቱ: ደግነቱ:
አርምሞው: ትሩፋቱ ከመነገር በላይ ነው:: በነበረበት
በ4ኛው መቶ ክ/ዘመንም እንደ ኮከብ ያበራ ታላቅ አባት
ነው::

=>አምላከ ቅዱሳን የኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያንን
ሰላምና ደስታ ያሳየን:: ከበዓላቱ ከሚገኘውም ጸጋ
በረከት አይለየን::

=>መስከረም 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት=
1.ሕንጸታ ለኢየሩሳሌም
2.ቅድስት እሌኒ ንግሥት
3.ቅዱስ ጦቢት ነቢይ
4.ቅዱሳን ጦብያና ሣራ
5.አባ አጋቶን ባሕታዊ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም)
2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት)
3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ (የቅ/
ላሊበላ ወንድም)
4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ
6.አባ ዳንኤል ጻድቅ
7.ቅዱስ አባ ዮሐንስ ጻድቅ (ወንጌሉ ዘወርቅ)

=>+"+ ወደ #እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ:: #ኢየሩሳሌም ሆይ እግሮቻችን በአደባባይሽ ቆሙ:: ኢየሩሳሌምስ እርስ በርሷ እንደ ተገለጠች ከተማ ተሠርታለች . . . ስለ ወንድሞቼ ስለ ባልንጀሮቼም በውስጥሽ ሰላም ይሁን አልሁ:: ስለ አምላካችን ስለ እግዚአብሔር ቤት ላንቺ መልካምነትሽን ፈለግሁ:: +"+ (መዝ. 121:1-9)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

ሰው ሁሉ ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን !
(ያዕቆብ 1፥19)

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን # ለብርሃነ_መስቀሉ እና # ለቅዱሳኑ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

✞✞✞ # ቅዱስ_ዕፀ_መስቀል ✞✞✞

=>ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ቸር አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማያዊ ክብሩ ወደ ምድር ወርዶ: በማሕጸነ # ማርያም_እግዝእት በኪነ ጥበቡ ተጸንሶ: በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: በፈቃዱ መከራ መስቀልን ተቀብሎ:
¤ከግራ ቁመት:
¤ከገሃነመ እሳት:
¤ከሰይጣን ባርነት:
¤ከኃጢአት ቁራኝነትም አድኖናል::

=>+"+ እምእቶነ እሳት ዘይነድድ አንገፈነ +"+ እንዳለ ሊቁ::
+ምንም መስቀል በብሉይ የወንጀለኞች መቅጫ ሆኖ ቢቆይም እግዚአብሔር ለዓለም መዳኛነት የመረጠው ነውና ሕብረ ትንቢቶች ሲነገሩለት: በብዙ ሕብረ አምሳልም ሲመሰል ኑሯል:: ከተፈጥሯችን ጀምሮ ዓለም ራሷ አርአያ # ትዕምርተ_መስቀል ናት::

+እግዚአብሔር ለቃየን እንዳይገድሉት ከሰጠው ምልክት (ዘፍ. 4:15) ጀምሮ
¤# ይስሐቅ ሊሰዋ የተሸከመው እንጨት (ዘፍ. 22:6):
¤# ቅዱስ_ያዕቆብ ያያት የወርቅ መሰላል (ዘፍ. 28:12):
¤ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች የባረከበት መንገድ (ዘፍ. 48:14):
¤ባሕረ ኤርትራን የከፈለችው # የሙሴ_በትር (ዘጸ. 14:15):
¤# የናሱ_ዕባብ የተሰቀለበት እንጨት (ዘኁ. 21:8) ጨምሮ በርካታ ምሳሌዎች ለቅዱስ መስቀሉ መኖራቸውን መተርጉማን ተናግረዋል::

+ # ቅዱስ_ዳዊትን የመሰሉ ነቢያት ደግሞ "ለሚፈሩሕ ከቀስት ያመልጡ ዘንድ ምልክትን ሰጠሃቸው" እያሉ መስቀሉን ከርቀት ተመልክተዋል:: (መዝ. 59:4)
+በሐዲስ ኪዳን ግን ምሳሌው ገሃድ ሆኖ: ጌታ በዕፀ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሥጋውን ቆረሰበት: ደሙን አፈሰሰበት: ዓለምንም አዳነበት:: ስለዚህም "

# መስቀል_ብርሃን_ለኩሉ_ዓለም :
# መሠረተ_ቤተ_ክርስቲያን " ተብሎ የሚመሰገን ሆኗል::
+ # ቅዱስ_ያሬድ ሊቁ አክሎ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር" ብሎ ጠላትን ማሳፈሪያ መሆኑን ይነግረናል::
# ብርሃነ_ዓለም # ቅዱስ_ዻውሎስም ስለ መስቀሉ አምልቶ አጉልቶ አስተምሯል:: መመኪያችን ነውና::
(1ቆሮ. 1:18, ገላ. 6:14)

+አንዳንዶቹ እኛን 'የተሰቀለውን ትታቹሃል' ይሉናል:: የተሰቀለውማ የጌቶች ጌታ: የነገሥታት ንጉሥ: የአማልክት አምላክ: ሁሉ በእጁ የተያዘ: # ኢየሱስ_ክርስቶስ ነውና ከኦርቶዶክስ በላይ የሚያመልክ በወዴት አለና::

+ነገር ግን መስቀሉን ንቆ የተሰቀለውን ማክበር አይቻልምና እኛ ለመስቀሉ የጸጋ ስግደትን እንሰግዳለን: እናመሰግነዋለን: እናከብረዋለን: ቤዛ: ጽንዕ: መድኃኒት: ኃይል እያልንም እንጠራዋለን:: አባቶቻችን በመስቀሉ ምርኩዝነት ማዕበለ ኃጢአትን: ባሕረ እሳትን ተሻግረዋል::

+በመስቀሉ ቢመኩ አጋንንትን ድል ነስተዋል:: ጠላትንም አሳፍረዋል:: እኛም በመስቀሉ አምነን ከብረን: ገነን እንኖራለን:: ተጠቅመንበታልና ከራሳችን ሕይወት በላይ ምስክርን አንፈልግም::

+"+ # በዓለ_መስቀል +"+
=> # መድኃኔ_ዓለም ክርስቶስ ካረገ ከዓመታት በሁዋላ አይሁድ በአንድ ነገር ተቸገሩ:: የክርስቶስን ሐዋርያት እያሳደዱ ቢገድሉም ከመስቀሉና ሥጋ ክርስቶስ አርፎበት ከነበረው ጐልጐታ ላይ የሚደረገውን ተአምር ግን መግታት አልተቻላቸውም::

+መቼም ለተንኮል አያርፉምና ቅዱስ መስቀሉን ሽፍቶቹ ከተሰቀሉባቸው ጋር ደርበው አርቀው ቀበሩት:: አካባቢው የጉድፍ መጣያ እንዲሆንም አዋጅ ነገሩ:: ለክፋት ሲሆን ተባባሪው ብዙ ነውና ለ270 ዓመታት ያህል ቆሻሻ ቢጥሉበት ተራራ ሆነ::

+ከዚህ ሁሉ ነገር በሁዋላ እናታችን ቅድስት # እሌኒ (ሔለና) በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት: በቅዱስ # ኪራኮስ መሪነት: በቅዱስ
# ሚካኤል ረዳትነት ደመራ አስደምራ: እጣን አጢሳ መካነ መስቀሉን አገኘች::

+መስከረም 17 ቀን የተጀመረው ቁፋሮ መጋቢት 10 ቀን ተጠናቆ: ንጹሕ መስቀሉ ወጥቶ ብርሃን በርቷል: ሙታን ተነስተዋል:: ከ10 ዓመት በሁዋላም የመስቀሉ ቤተ መቅደስ ታንጾ መስከረም 17 ቀን ተቀድሷል::

+ይህ ቅዱስ ዕፀ መስቀልም በደጉ # አፄ_ዳዊት ዘመን ወደ ሃገራችን መጥቶ: በጻድቁ #አፄ_ዘርዓ_ያዕቆብ አማካኝነት በደብረ ከርቤ ( #ግሸን_ማርያም ) ተለብጦ ተቀምጧል::

+ # ቅዱስ_አውዶኪስ_ቀሲስ +

=>ይህ ቅዱስ ሰው ለቅዱስ መስቀሉ ከነበረው ፍቅር የተነሳ በብዙ ድካም ወደ # ኢየሩሳሌም በእግሩ ተጉዞ ነበር:: ከብዙ መንገደኞች ጋር በጐዳና ላይ ሳሉ ታዲያ አንድ አይሁዳዊ (ሰማርያዊ) ተቀላቀላቸው:: በወሬ በወሬ የት እንደሚሔዱ ሲጠይቃቸው "መካነ መስቀሉን ለመሳለም ወደ # ጐልጐታ ነን" አሉት::

+እሱ ግን ከት ብሎ ስቆ "እንዴት እንጨት ትሳለማላችሁ" በሚል አፌዘባቸው:: የፀሐዩ ሐሩር እጅግ ጠንቶ ነበርና ቅዱስ አውዶኪስ ኃይለ መስቀሉን ሊያሳይ ወደደ:: በመንገድም መርዝነት ያለው ውሃ ነበርና ቅዱሱ ቀርቦ ጸልዮ በመስቀሉ ባረከውና ፈጥኖ ወደ ጣፋጭነት ተቀየረ::

+ምዕመናኑ ደስ ብሏቸው ሲጠጡ ያ አይሁዳዊ 'እጠጣለሁ' ብሎ ቢቀርብ ወደ ነበረው ተመለሰበት:: 'በኮዳ የያዝኩትን እማልጠጣ' ብሎ ቢከፍተው ደግሞ ተልቶ አገኘው:: እጅግ ደንግጦ አለቀሰ:: በጣም ጠማው: ግን ምኑን ይጠጣ!
+አማራጭ ሲያጣ ወደ ቅዱስ አውዶኪስ ሒዶ እግሩ ላይ ወድቆ አለቀሰ:: በመስቀሉ ቢማጸን መራራው ጣፈጠለት:: በዚህ ምክንያትም ወደ ክርስትና ተመልሷል:: ቅዱሱ በመልካም ሽምግልና ሲያርፍ ውሃው የተቀየረበት ቦታ ላይ ቤተ መቅደስ ታንጾ በዚህ ቀን ተቀድሷል::

+"+ # ቅድስት_ታኦግንስጣ +"+

=>በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረችው ሮማዊቷ እናት መንገድ ላይ ቁማ # ወንጌል ስታነብ በንጉሥ ወታደሮች ተማርካ ወደ
# ሕንድ ተወስዳለች:: በዚያም በመስቀል አማትባ ሙት በማስነሳቷ የሃገሩ ሰው ወደ ክርስትና ከነ ንጉሡ ተመልሰዋል:: እርሷም ገዳም አንጻ: ደናግሉን ሰብስባ በንጽሕና ኑራለች:: በዚህ ቀን ዐርፋ ሲቀብሯት የብርሃን መስቀል መቃብሯ ላይ ተተክሏል::

=>አምላከ ቅዱሳን በኃይለ መስቀሉ: በሞገሰ መስቀሉ ይጠብቀን:: ከበረከቱ አሳትፎ በዓሉን የሰላም ያድርግልን::

=>መስከረም 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=

1.ቅዱስ ዕፀ መስቀል
2.ቅድስት እሌኒ ንግስት
3.ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ
4.ቅዱስ መቃርስ ሊቀ ዻዻስ
5.ቅዱስ አውዶኪስ ቀሲስ
6.ብጽዕት ታኦግንስጣ ሮማዊት
7.ቅዱስ ዲዮናስዮስ ሊቀ ዻዻሳት

=>ወርኀዊ በዓላት

1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ)
3.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
4.አባ ገሪማ ዘመደራ
5.አባ ዸላሞን ፈላሢ
6.አባ ለትጹን የዋህ
7.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆዽሮስ)

+ የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና . . . መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ:: የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ:: እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን::

+ (1ቆሮ. 1:18-23

<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
በዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo.

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

#መልካም እለተ ይሁንልን

ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በመንገዳችን ላይ ውብ የጋሞ እናት እና ወጣቶች መስቀልን ለማክበር ጉዞ ወደ መስቀል አደባባይ።
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔

ኦ አባይ ሀገር በሀኪ ኢትዮጵያ
ሀገረ ነጎድጓድ ሀገረ እግዚአብሔር

ተንስኢ ወልበሲ ሀይለ እግዚአብሔር እስመ ተንስኡ ፀላእትኪ ወአብቀዋ ኦሙ ላይለ ህዝብኪ

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

#መልካም እለተ ይሁንልን

ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼.
#አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ 40 በላይ ድርሰቶቹ መካከል በአብዛኞቻችን ዘንድ የሚታወቁት 34ቶቹ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፤
1. ✼ ኆኀተ ብርሃን
2. ✼ መዝሙረ ኢየሱስ (ሰላመ ማርያም)
3. ✼ መዝሙረ ድንግል
4. ✼ የማርያም የምስጋና ሰላምታ
5. ✼ ውዳሴ መላእክት
6. ✼ ውዳሴ ነቢያት
7. ✼ ውዳሴ ሐዋርያት
8. ✼ ውዳሴ ሰማዕታት
9. ✼ ውዳሴ ጻድቃን
10. ✼ መጽሐፈ ብርሃን
11. ✼ መጽሐፈ ምሥጢር
12. ✼ መጽሐፈ ሰዐታት ዘመዓልት ወዘሌሊት
13. ✼ መጽሐፈ አርጋኖን
14. ✼ አርጋኖነ ውዳሴ
15. ✼ መሰንቆ መዝሙር
16. ✼ እንዚራ ስብሐት
17. ✼ ውዳሴ መስቀል
18. ✼ ፍካሬ ሃይማኖት
19. ✼ ፍካሬ ሐዋርያት
20. ✼ መጻሕፍተ ቅዳሴያት
21. ✼ ቅዳሴ እግዚእ ካልዕ
22. ✼ መዐዛ ቅዳሴ
23. ✼ ሕይወታ ለማርያም (ሕይወተ ማርያም)
24. ✼ ውዳሴ ስብሐት
25. ✼ ውዳሴ ማርያም ካልዕ
26. ✼ ውዳሴ ስብሐት ወሰላምታ
27. ✼ ማኅሌት ዘነቢያት ወዘሐዋርያት
28. ✼ የሰባቱ ጊዜያት ጸሎት (መልክአ ሕማማት)
29. ✼ ጸሎተ ፈትቶ (ጸሎተ ማዕድ)
30. ✼ ጸሎት ዘ(ቤት)ውስተ ቤት
31. ✼ መልክአ ቊርባን
32. ✼ ተአምኆ ቅዱሳን
33. ✼ ተአምኆታ ለእግዝእትነ ማርያም
34. ✼ ክብረ ቅዱሳን

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
2024/09/28 13:20:33
Back to Top
HTML Embed Code: