Telegram Web Link
‹‹የጥቁሩን አህያ ራስ ከነጩ የነጩን አህያ ራስ ከጥቁሩ››

አቡነ ቶማስ የመርዓስ ሀገር ኤጲስ ቆጶስ ሲሆኑ ታላቅ ሰማዕትነትን የተቀበሉ ሃይማኖት ምግባራቸው እጅግ የቀና ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስ በነገሠ ጊዜ ክርስቲያኖቹን ሲያሠቃዩ በነበረበት ወቅት ከንጉሡ መኳንንት አንዱ ወደ መርዓስ ሄዶ አቡነ ቶማስን በጭፍሮቹ አሲያዛቸው፡፡ አባታችንን እንደያዟቸው ደብድበው በምድር ላይ እየጎተቱዋቸው ደማቸው እየፈሰሰ ወሰዷቸው፡፡ መኰንኑ ‹‹ለአማልክት ስገድ›› አላቸው፡፡ አቡነ ቶማስም ‹‹ከእግዚአብሔር በቀር የሚሰግዱለት አምላክ የለም›› አሉት፡፡ መኰንኑም እጅግ የበዙ ጽኑ ሥቃዮችን አሠቃያቸው፡፡ የነዳጅ ድፍድፍ አፍልተው በሰውነታቸው ላይ እንዲሁም በአፍና በአፍንጫቸው ጨመሩባቸው፡፡ ቶሎ ብለው እንዲሞቱ ሳይሆን በሥቃይ ሆነው እንዲቆዩ በማድረግ ለ22 ዓመታት በጨለማ ውስጥ እያሰሩ አሠቃዩአቸው፡፡ ከሃዲያኑም በየዓመቱ ወደ እስር ቤቱ እየገቡ አንድ አካላቸውን ይቆርጣሉ፡፡ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በየተራ ቆራረጧቸው፡፡ አፍንጫቸውን፣ ከንፈሮቻቸውን፣ ጆሮዎቻቸውን ሁሉ በየተራ እየቆረጡ ለ22 ዓመትታት ጣዖታቸውን ሲያጥኑበት ኖረዋል፡፡
አንዲት ደግ ክርስቲያን ሴት ግን የተጣሉበትን ጉድጓድ አይታ ስለነበር በድብቅ ሌሊት እየሄደች ትመግባቸው ነበር፡፡ ደገኛውና ጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ በነገሠ ጊዜ ይህች ሴት ሄዳ ስለ አቡነ ቶማስ ነግረችውና አባታችንን ከተጣሉበት ጉድጉድ አወጣቸው፡፡ ቆስጠንጢኖስ የከበሩ 318 ኤጲስ ቆጶሳትን በኒቅያ አገር እንዲሰበሰቡ ሲያደርግ አንዱ አቡነ ቶማስ ነበሩ፡፡ ወደ ጉባዔውም ሲሄዱ ደቀ መዛሙርቶቻቸው በቅርጫት አድርገው በአህያ ጭነው ወደ ጉባኤ ኒቂያ ይዘዋቸው ሄደዋል፡፡ በመንገድም ሳሉ ዐላዊያኑ አግኝተዋቸው አህዮቻቸውን ሌሊት ራስ ራሳቸውን ቆርጠው ጣሉባቸው፡፡ አቡነ ቶማስም ራሳቸው የተቆረጡትን አህዮች አምጡልኝ ብለው የጥቁሩን አህያ ራስ ከነጩ፣ የነጩን አህያ ራስ ከጥቁሩ ገጥመው ቢባርኳቸው ሁሉም አህዮች ከሞት ተነሥተዋል፡፡
ከጉባዔውም ሲደርሱ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጽድቃቸውን ዐውቆ ‹‹አባቴ በረከትዎ ትድረሰኝ›› በማለት በዐላዊያኑ የተቆራረጠ አካላቸውን ዳሶ ተባርኳል፡፡ አቡነ ቶማስ ዘመርዓስም ከሌሎቹ ኤጲስ ቆጶሳት ጋር ሆነው አርዮስን መክረውና አስተምረው እምቢ ቢላቸው አውግዘውት ወደ ሀገራቸው እንደተመለሱ ነሐሴ 24 በሰላም ዐርፈዋል፡፡

የአቡነ ቶማስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን

✞ ✞ ✞

@ortodoxtewahedo
Audio
ከልማድ ኃጢአት እንዴት እንላቀቅ

Size 2.5MB
Length 11:02

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
#22🕯🕯

#ቅዱስ ኡራኤል ሆይ

"ተራዳኢነትህ ሀገርን ከጥፋት ሕዝብን ከስደት ያድናልና ፡ ዑራኤል ሆይ ከፈጣሪ ይቅርታን አስገኝተህ የኃጥአንን ነፍስ የምትጎበኝ ነህና በዚያች የቁርጥ ፍርድ ቀን የሲኦልን ደጃፍ እንዳናይ ስለእመቤታችን ድንግል ማርያምና ስለልጅዋ ስለመድኃኔዓለም በቃል ኪዳንህ እንማጸንሐለን ።

(መልከአ ዑራኤል ቁ.፲፩እና፲፱ )

@ortodoxtewahedo
ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ

እንኳን ለሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን !!!

" የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው።"
ምሳ. ፲፥፯ /10፥7/

✝️ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገና በለጋ ዕድሜው ዓለማዊውን መንግሥት ንቆ ሰማያዊውን መንግሥት በመሻት ለክርስቶስ ታመነ

✝️ በእምነቱም የተነሳ ከጣኦት አምላኪ ነገሥታትና ወታደሮች ብዙ ስቃይና መከራ ደረሰበት

✝️ ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን በፅኑ መከራና ስቃይ ሳይሸነፍ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ

✝️ በክርስትናው ፀንቶ ጣኦት አምላኪዎችን ስለ ክርስቶስ እየሰበከ ደጋግመውም እየገደሉት አምላኩም ከሞት እያስነሳው ብዙ ድንቆችን እያደረገ ኖረ

✝️ ለአምላኩ የታመነው ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጨረሻም በአምላኩ ፍቃድ ሰማያዊ አክሊልን ተቀናጅቶ በሰማዕትነት ዐረፈ

አምላካችን እግዚአብሔር ከቅዱስ ጊዮርጊስ በረከት ያሳትፈን፤ ከሥጋና ነፍስ መከራም ይጠብቀን። አሜን።

@ortodoxtewahedo
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! እንኳን አደረሰን አደረሳችኹ።

ዕረፍቱ ለአቡነ ተክለሃይማኖት /ከ 1215-1313/

ተክለሃይማኖት ማለት ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው። ብሔረ ሙዳቸው ጽላላልሽ/ዞረሬ/ ነው። አባታቸው ጸጋ ዘአብ እናታቸው እግዚእ ኃረያ ይባላሉ።

ከበዓታቸው ገብተው ወደፊት ወደ ኋላ ቁጭ ብድግ እንዳይሉ ከፊት ከኋላቸው ከግራ ከቀኛቸው ስምንት ጦር ተክለው ሱባዔ ያዙ። ከቁመት ብዛት ከገድል ጽናት የተነሣ አንድ እግራቸው ጥር 24 ቀን 1306 ዓ.ም ተቆርጦ ወድቋል። ከዚህም በኋላ በአንድ እግራቸው ቆመው 7 ዓመት ኑረዋል።

ጊዜ ዕረፍታቸው ሲደርስ ጌታ እመቤታችንን መላእክትን ነቢያትን ሐዋርያትን ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትሎ መጥቶ ኦ ፍቁርየ ተክለሃይማኖት ወዳጄ ተክለሃይማኖት ሆይ ሰማዕኩ ጸሎተከ ወስእለተከ ልመናህን ሰምቼ ወናሁ አአርፈከ እምብዙኅ ጻማ ከድካምህ ላሳርፍህ መጣሁ ኀበ ሀሎ ፍስሐ ህየ አነብረከ መንፈሳዊ ደስታ ካለበት አሳርፍሃለው እምዝ ዳግመ ኢይረክብከ ሞት እንግዲህም ኹለተኛ ሞት አያገኝህም በተስፋህ ያመነውን በቃልኪዳንህ የተማጸነውን ሥጋህን የቆረስክበትን ደምህን ያፈሰስክበትንም ቦታ እጅ የነሣውን ሁሉ ከሞተ ነፍስ ከርደተ ገሃነም አድንልሀለሁ በዚህችህም ቦታ በተስፋ ጸንተው በኪዳንህ ተማጽነው የሚኖሩ ልጆችህን እንደ ሰማይ ኮከብ እንደ ባሕር አሸዋ አበዛልሀለሁ ብሎ ተስፋቸውን ነግሯቸዋል። ከዚህ በኋላ ሕማመ ብድበድ ለሞታቸው ምክንያት ሁኗቸው በተወለዱ በ99 ዓመት ከ10 ወር ከ10 ቀናቸው በዚህ ዕለት ዐርፈዋል።

ዕረፍታ ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ

ሀገሯ ቡልጋ ቅዱስጌ ነው። አባቷ ደርባኒ እናቷ ዕሌኒ ይባላሉ። ከመከራዋ ብዛት ከገድሏ ጽናት ሰውነቷ ተበሳስቶ የዓሣ መመላለሻ እስኪሆን ድረስ ከባህሩ ገብታ ወደ ግራ ወደ ቀኝ ሳትል 12 ዓመት ኑራለች። ጌታ መጥቶ ምን እንዳደርግልሽ ትወጂያለሽ አላት። ከእንጨት የማይጤስ ከብረት የማይዝግ ከሰውም የማይበድል የማይበድል የለምና ውሉደ አዳም እንዳይስቱ ዲያቢሎስን ማርልኝ አለችው። ምሕረትን ቸርነትን አይሻም እንጂ ከሆነልሽስ ጠርተሽ አምጪው አላት። ቅዱስ ሚካኤል ወስዶ ጽንፈ ሲኦል አደረሳት። ጌታ ምሬሐለሁ ብሏልና ና ውጣ አለችው። በምድር ፈልጌ ባጣሽ ሳዝን እኖር ነበር አሁንማ ከቤቴ መጣሽልኝ ብሎ ጎትቶ አስገባት። ቅዱስ ሚካኤል ተከትሎ ገብቶ በክንፉ ነጥቆ አውጥቶታል። ስትወጣም ስለ መከራዋ ብዛት ስለ ገድሏ ጽናት 6 ክንፍ ተሰጥቷት ነበር። በዚያ ነፍሳትን ማርካ ወጥታለች።

ከዚህ በኋላ ዜና ገድሏ በየአህጉሩ ተሰምቶ ከ1279 ያላነሱ ደናግል ተሰብስበውላት ጽሙና ብሕትውና የምታስተምራቸው ሆናለች። በፍጻሜ ዘመኗ በቁመቷ ልክ በዓት ሠርታ ከግራ ከቀኝ ከፊት ከኋላ 12 ጦር ተክላ ወዲያ ወዲህ ሳትል ቆማ 12 ዓመት ኑራለች። ከዚያውም ዘንድ እሰግዳለሁ እያለች ጎንበስ ቀና ስትል ሥጋዋ በጦር ተወግቶ ተፈቅቶ አልቋል።

ጌታም ይህን ሁሉ መከራዋን እንደ መስዋዕት ቆጥሮላት አእላፍ መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ በተስፋዋ ያመነውን በቃልኪዳኗ የተማጸነውን እስከ 10 ትውልድ ድረስ እንዲምርላት ተስፋዋን ነግሯት ክብርት ነፍሷን ከሥጋዋ ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላእክት አሳርጓታል።

ዕረፍቱ ለቶማስ ዘመርዓስ

በመርዓስ ኤጲስ ቆጶስነት ተሹሟል። ይህም ሰማዕት አርዮስን አውግዞ ሃይማኖት መልሶ ወደ ሀገሩ ከተመለሰ በኋላ ብዙም አልቆየም በዚህ ዕለት ዐርፏል።

ምንጭ፦ መዝገበ ታሪክ ክፍል ፪

👉 @ortodoxtewahedo
Audio
ደመናው አይቀደድም

Size 139MB
Length 2:30:15

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
2024/09/28 19:35:45
Back to Top
HTML Embed Code: