Telegram Web Link
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

📖 ሰላም ለልሳንከ በደብረ ታቦር ዘአልኆሰሰ ለብርሃን ዓቢይ እስከ ጽላሎቱ ተሐውሰ ነበልባለ እሳት ክርስቶስ ዘተዋሐድከ ጳጦሰ በዋዕየ ፍቅርከ ከመ ሥርወ አዕዋም የብሰ ውሳጤ ሕሊናየ ነደ ወልብየ ጤሰ


ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ በታቦር ተራራ ምሥጢር መለኮትህን ለመግለፅ ለተንቀሳቀሰው አንደበትህ ሰላምታ ይገባል ከድምፅህ ግርማ የተነሳ የታላቁ ብርሃን ዓምድ ተነዋውጿልና

ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ ያለማቃጠል የሲናን ዕፅ የተዋሐደው የእሳት ነበልባል አንተ ነህ የዛፎች ግንድ በእሳት እንደሚቃጠል ሁሉ በፍቅርህ ነበልባል ልቦናዬ ጤሰ ኅሊናዬም ነደደ

💠(መልክአ ኢየሱስ)💠


🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

እንኳን አደረሳችሁ መልካም በአል

💠እስቲ ቡሄ እንበል💠

ቡሄ በሉ......ሆ (2)
ሰዎች ሀሉ.....ሆ
የኛማ ጌታ......ሆ የአለም ፈጣሪ.....ሆ
የሰላም አምላክ.....ሆ ትሁት መሀሪ...ሆ
በደብረ ታቦር........ሆ የተገለጠው ...ሆ
ፊቱ እንደፀሀይ...ሆ በርቶ የታየው....ሆ
ልብሱ እንደብርሃን....ሆ ያንፀባረቀው...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛም በራልን(2)
........
ያዕቆብ ዩሀንስ...ሆ እንዲሁም ጴጥሮስ...ሆ አምላክን
አዩ....ሆ ሙሴ ኤልያስ...ሆ
አባቱም አለ ....ሆ ልጄን ስሙት....ሆ
ቃሌ ነውና .....ሆ የወለድኩት...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና (2)
የቡሄው ብርሃን ለኛም በራልን(2)
.......
ታቦር አርሞንኤም...ሆ ብርሃን ታየባቸው ........ሆ
ከቅዱስ ተራራ...ሆ እጅግ ደስ አላቸው....ሆ
ሰላም ሰለም.....ሆ የታቦር ተራራ....ሆ
ብርሃነ መለኮት......ሆ ባንቺ ላይ አበራ....ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛ በራልን(2)
.....
በአባቴም ቤት ....ሆ አለኝ ለከት.....ሆ
በእናቴም ቤት....ሆ አለኝ ለከት...ሆ
በአጎቴም ቤት ....ሆ አለኝ ለከት...ሆ
በአክስቴም ቤት....ሆ አለኝ ለከት...ሆ
ተከምሯል...ሆ እንደኩበት....ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2(
የቡሄው ብርሃን ለኛ በራልን (2)
.......
የአመት ልምዳችን...ሆ ከጥንት የመጣ...ሆ
ከተከመረው ....ሆ ከመሶቡ ይምጣ
በደብረ ታቦር ...ሆ ጌታ ስለመጣ...ሆ
የተጋገረው ....ሆሙልሙሉ ይምጣ...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛ በራልን(2)
.......
በተዋህዶ...ሆ ወልድ ያከበረው....ሆ
የእግዚአብሔር አብ ልጅ....ሆ ወልደ ማርያም ነው...ሆ
ቡሄ በሉ ...ሆ ቡሄ በሉ .....ሆ
የአዳም ልጆች...ሆ ብርሃንን ...ሆ ተቀበሉ...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛም በራልን(2)
........
ኢትዮጽያውያን....ሆ ታሪክ ያላችሁ...ሆ
ባህላችሁን....ሆ ያዙ አጥብቃችሁ...ሆ
ችቦውን አብሩ..ሆ እንደአባቶቻችሁ...ሆ
ሚስጥር ስላለው...ሆ ደስ ይበላችሁ...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛም በራልን(2)
......
ለድንግል ማርያም...ሆ አስራት የሆንሽ...ሆ
ቅዱሳን ፃድቃን ....ሆ የሞሉብሽ ...ሆ
በረከታቸው ያደረብሽ...ሆ ሁሌም እንግዶች ...ሆ
የሚያርፉብሽ....ሆ
ሀገረ እግዚአብሔር ....ሆ ኢትዪጵያ ነሽ...ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛምበራልን(2)
........
ለሀዋርያት ...ሆ የላከው መንፈስ ...ሆ
ዛሬም ለኢትዮጵያ ...ሆ ፀጋውን ያፍስስ ....ሆ
በበጎ ምግባር ...ሆ እንድንታደስ ...ሆ
በቅን ልቦና ...ሆ በጥሩ መንፈስ...ሆ
በረከተ ቡሄ...ሆ ለሁላችን ይድረስ....ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛም በራልን (2)
አመት አውደ አመት ድገምና አመት ድገምና...........
..............እንኳን አደረሳችሁ መልካም በአል
ይሁንላችሁ

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
(የማቴዎስ ወንጌል  17)
----------
1፤ ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው።

2፤ በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።

3፤ እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው።

4፤ ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን። ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ።

5፤ እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።

6፤ ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር።

7፤ ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና። ተነሡ አትፍሩም አላቸው።

8፤ ዓይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም።

----------
9፤ ከተራራውም በወረዱ ጊዜ ኢየሱስ። የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያያችሁትን ለማንም አትንገሩ ብሎ አዘዛቸው።

10፤ ደቀ መዛሙርቱም። እንግዲህ ጻፎች። ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ ይገባዋል ስለ ምን ይላሉ? ብለው ጠየቁት።

11፤ ኢየሱስም መልሶ። ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል፤

12፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ኤልያስ ከዚህ በፊት መጣ፤ የወደዱትንም ሁሉ አደረጉበት እንጂ አላወቁትም፤ እንዲሁም ደግሞ የሰው ልጅ ከእነርሱ መከራ ይቀበል ዘንድ አለው አላቸው።

13፤ በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለ መጥምቁ ስለ ዮሐንስ እንደ ነገራቸው አስተዋሉ።

14፤ ወደ ሕዝቡም ሲደርሱ አንድ ሰው ወደ እርሱ ቀረበና ተንበርክኮ። ጌታ ሆይ፥ ልጄን ማርልኝ፥ በጨረቃ እየተነሣበት ክፉኛ ይሣቀያልና፤

15፤ ብዙ ጊዜ በእሳት ብዙ ጊዜም በውኃ ይወድቃልና።
.
16፤ ወደ ደቀ መዛሙርትህም አመጣሁት ሊፈውሱትም አቃታቸው አለው።
----------
17፤ ኢየሱስም መልሶ። የማታምን ጠማማ ትውልድ ሆይ፥ እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደዚህ ወደ እኔ አምጡት አለ።

18፤ ኢየሱስም ገሠጸው ጋኔኑም ከእርሱ ወጣ፥ ብላቴናውም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ተፈወሰ።

19፤ ከዚህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ብቻቸውን ወደ ኢየሱስ ቀረቡና። እኛ ልናወጣው ያልቻልን ስለ ምን ነው? አሉት።

20፤ ኢየሱስም። ስለ እምነታችሁ ማነስ ነው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ። ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም።

21፤ ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም አላቸው።

📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

ሰው ሁሉ ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን !
(ያዕቆብ 1፥19)

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
(የማርቆስ ወንጌል  9)
----------
2፤ ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ልብሱም አንጸባረቀ፤

3፤ አጣቢም በምድር ላይ እንደዚያ ሊያነጣው እስከማይችል በጣም ነጭ ሆነ።

4፤ ኤልያስና ሙሴም ታዩአቸው፥ ከኢየሱስም ጋር ይነጋገሩ ነበር።

5፤ ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን። መምህር ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ አለው።

6፤ እጅግ ስለ ፈሩ የሚለውን አያውቅም ነበር።

7፤ ደመናም መጥቶ ጋረዳቸው፥ ከደመናውም። የምወደው ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።

8፤ ድንገትም ዞረው ሲመለከቱ ከእነርሱ ጋር ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም።

9፤ ከተራራውም ሲወርዱ የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያዩትን ለማንም እንዳይነግሩ አዘዛቸው።

10፤ ቃሉንም ይዘው። ከሙታን መነሣት ምንድር ነው? እያሉ እርስ በርሳቸው ተጠያየቁ።

11፤ እነርሱም። ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ እንዲገባው ጻፎች ስለ ምን ይላሉ? ብለው ጠየቁት።

12፤ እርሱም መልሶ። ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናናል፤ ስለ ሰው ልጅም እንዴት ተብሎ ተጽፎአል? ብዙ መከራ እንዲቀበል እንዲናቅም።

13፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ኤልያስ ደግሞ መጥቶአል፥ ስለ እርሱም እንደ ተጸፈ የወደዱትን ሁሉ አደረጉበት አላቸው።


📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

ሰው ሁሉ ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን !
(ያዕቆብ 1፥19)

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
(የሉቃስ ወንጌል  9:28:36)
----------
28፤ ከዚህም ቃል በኋላ ስምንት ቀን ያህል ቈይቶ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ያዕቆብንም ይዞ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ።

29፤ ሲጸልይም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም ተብለጭልጮ ነጭ ሆነ።

30፤ እነሆም፥ ሁለት ሰዎች እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤

31፤ በክብርም ታይተው በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ስለ መውጣቱ ይናገሩ ነበር።

32፤ ነገር ግን ጴጥሮስንና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንቅልፍ ከበደባቸው፤ ነቅተው ግን ክብሩንና ከእርሱ ጋር ቆመው የነበሩትን ሁለት ሰዎች አዩ።

33፤ ከእርሱም ሲለዩ ጴጥሮስ ኢየሱስን። አቤቱ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ አለው፤ የሚለውንም አያውቅም ነበር።

34፤ ይህንም ሲናገር ደመና መጣና ጋረዳቸው፤ ወደ ደመናውም ሲገቡ ሳሉ ፈሩ።

35፤ ከደመናውም። የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።

36፤ ድምፁም ከመጣ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ሆኖ ተገኘ። እነርሱም ዝም አሉ ካዩትም ነገር በዚያ ወራት ምንም ለማንም አላወሩም።


📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

ሰው ሁሉ ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን !
(ያዕቆብ 1፥19)

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
Audio
በእለተ እሁድ የሚነበብ የሚተረጎም የሚጸለይ የእመቤታችን ምስጋና ይህ ነው።

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
አሐደ ለከ
ዝማሬ ዳዊት
የደብረ ታቦር መዝሙር

#አሐደ_ለከ

አሐደ ለከ ወአሐደ ለሙሴ /2/
ወአሐደ ለኤልያስ ንግበር ማይደረ /4/

📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
ዜኖኩ ጽድቀከ
♡የመዝሙር ግጥሞች♡
ዜኖኩ ጽድቀከ ወነገርኩ አድኅኖተከ
ከሠትኩ ቃላቲከ ለሕዝብከ ኢትዮጵያ(፪)
በጸጋሁ ለመንፈስ ቅዱስ ወመሀርክዎሙ
አነ ይቤ ያሬድ ካህን(፪)

ጽድቅህን ነገርኩ አዳኝነትህን አስተማርኩ(፪)
ቃላትህን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ገለጥኩ
እኔም በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ አስተማርኩአቸው አለ ያሬድ ካህን(፪)

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
❍ አምላካችን ናና
❍ የቡሄ መዝሙር
#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

🔔 ነሐሴ 12 🔔

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

👉ዲያቆን
📖1ኛ ቆሮ 9÷17....
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ይሁዳ 1÷8-14
👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረ ሐዋርያያ 24÷1-22

👉ምስባክ
📖መዝ 71፥1-3

እግዚኦ ኩነኔከ ሀቦ ለንጉስ
ወጽድቀከኒ ለወልደ ንጉሥ
ከመ ይኮንኖሙ ለሕዝብከ በጽድቅ

👉ትርጉም
አቤቱ ፍርድህን ለንጉስ ስጥ
ጽድቅክንም ለንጉስ ልጅ
ሕዝብክን በጽድቅ ችግረኛዎችክንም
በፍርድ ይዳኝ ዘንድ

📖ወንጌል
ማቴ 22÷1-15

📣ቅዳሴ
ዘእግዝእትነ

🔰 @ortodoxtewahedo

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ
ወይሴብሑ ለስምከ መዝራዕትከ ምስለ ኀይል

መዝ 88፥12-14

ለመቀላቀል👉 @ortodoxtewahedo

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
Audio
ዋዜማ ዘደብረ ታቦር

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
ቡሄ በሉ 16k
ዝማሬ ዳዊት
#ቡሄ_በሉ

📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
"ከስድስት ቀንም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ጴጥሮስን ያዕቆብንና ወንድሙ ዮሐንስን ይዞ ለብቻቸው ወደ ረዥም ተራራ አወጣቸው ..... ከዚህም በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ እንደ ነገራቸው ዐወቁ"

ማቴዎስ 17፥1-14

ለመቀላቀል👉 @ortodoxtewahedo

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
#አማን በአማን
ተሰብሐ በደብረ ታቦር

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
#አማን በአማን
ተሰብሐ በደብረ ታቦር

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo.
#አማን በአማን
ተሰብሐ በደብረ ታቦር

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo.
🔔 ነሐሴ 13 🔔

👉ዘነግህ ምስባክ
📖መዝ 67፥15

ደብር ርጉዕ ወደብር ጥሉል
ለምንት ይትነሥኡ አድባር ርጉዓን
ደብር ዘሠምሮ እግዚአብሔር የኀድር ውስቴቱ

👉ትርጉም
የጸና ተራራና የለመለመ ተራራ ነው
የጸኑ ተራራዎች ለምን ይነሣሉ?
እግዚአብሔር ይህን ተራራ ያድርበት ዘንድ ወደደው

📖ወንጌል
ማቴዎስ 17፥1-14

"ከስድስት ቀንም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ጴጥሮስን ያዕቆብንና ወንድሙ ዮሐንስን ይዞ ለብቻቸው ወደ ረዥም ተራራ አወጣቸው.....ከዚህም በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ እንደ ነገራቸው ዐወቁ"

🔔 በዕለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ መልእክታት፣ ወንጌልና ምስባክ

👉ዲያቆን
📖ዕብ 11፥23-30

"ሙሴ በተወለደ ጊዜ በእምነት ሦስት ወር በአባቱ ቤት ሸሸጉት.......በደረቅ ምድር እንደ መሄድ የኤርትራን ባሕር በእምነት ተሻገሩአት የግብፅ ሰዎች ግን ሲሞክሩ ሰጠሙ"

👉ንፍቅ ዲያቆን
📖2ኛ ጴጥ 1፥15........

"ደግሞም ይህች ትእዛዝ ዘወትር በእናንተ ዘንድ እንድትኖር ከሞቴም በኋላ እንድታስቡአትና እንደ አዘዝኋችሁ እንድታደርጉ እተጋለሁ......ትንቢት ከቶ ከሰው ፈቃድ አልመጣምና ዳሩ ግን ቅዱሳን ሰዎች ከእግዚአብሔር ተልከው በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ተናገሩ"

👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረ ሐዋርያት 7፥44-51

"ሙሴን ተናግሮ እንደ አዘዘው በአሳየው ምሳሌ የሠራት የምስክር ድንኳን በአባቶቻችን ዘንድ በምድረ በዳ ነበረች.........ይህን ሁሉ እጆቼ የሠሩት አይደለምን"

👉ምስባክ
📖መዝ 88፥12-14

ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ
ወይሴብሑ ለስምከ
መዝራዕትከ ምስለ ኀይል

👉ትርጉም
ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል
ክንድህ ከኀይልህ ጋራ ነው

📖ወንጌል
ሉቃስ 9፥28-38

📣ቅዳሴ
ዘእግዝእትነ
📖📖📖📖📖📖📖📖📖

ለድንግል ማርያም አስራት የሆንሽ
ቅዱሳን ፃድቃን የሞሉብሽ
በረከታቸው ያደረብሽ ሁሌም እንግዶች የሚያርፉብሽ
ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዪጵያ ነሽ

📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
📖📖📖📖📖📖📖📖📖

ለድንግል ማርያም የሆንሽ
ቅዱሳን ፃድቃን የሞሉብሽ
በረከታቸው ያደረብሽ ሁሌም እንግዶች የሚያርፉብሽ
ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዪጵያ ነሽ

📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
2024/09/29 23:21:04
Back to Top
HTML Embed Code: