Telegram Web Link
#ሐምሌ 23

"ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ! አንተን በመታመን ለጠራህ ሁሉ ፈጥነህ ስትደርስለት ከዓውሎ ነፋስ ይልቅ በተፋጠነ ሩጫ ነው።
ጊዮርጊስ ሆይ! የዘወትር ጸሎቴንና የቃሌንም የልመና ጩኸት ትቀበል ዘንድ ለይቅርታና ለምሕረት ፈጥነህ ወደ እኔ ቅረብ።"

(መልክአ ጊዮርጊስ)

@ortodoxtewahedoo
​​👼 ቅዳሴ ማለት ምንም ማለት ነው?
🤔 በቅዳሴ ጊዜ 5ቱ ምሥዋዕቶች ምን ምን ናቸው?
🥰 14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት እነማን ይሆኑ?

😇 ካህናት በቅዳሴ ወቅት 2: 3: 4: 5: 7: 12: ወይም 24: ሆነው ከቀደሱ ምሳሌነቱ ምን ምን ይሆን?
🧎‍♂ እኛ ክርስቲያኖች ቅዳሴን ባስቀደስን ቁጥር 4 ነገሮች እናገኛለን ምን ይሆኑ?
👼 አምስቱ የስሜት ሕዋሳት በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ያስቀድሳሉ እንዴት?


            ይ🀄️🀄️ሉ ይማሩ
                  👇🏾👇🏾👇🏾

https://www.tg-me.com/addlist/AQPOMxHXz_42NDE0
(የማቴዎስ ወንጌል 7 : 1-29)
----------
1-2፤ እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፥ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል።

3፤ በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፥ በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም?

4፤ ወይም ወንድምህን። ከዓይንህ ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ እንዴትስ ትለዋለህ? እነሆም፥ በዓይንህ ምሰሶ አለ።

5፤ አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ፥ ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዓይን ጉድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ።

6፤ በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፥ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ።

7፤ ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።

8፤ የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።

9፤ ወይስ ከእናንተ፥ ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው?
----------
10፤ ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን?

11፤ እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው?

12፤ እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና።

13፤ በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤

14፤ ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።

15፤ የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።

16፤ ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን?

17፤ እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል።

18፤ መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም።
----------
19፤ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።

20፤ ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።

21፤ በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።

22፤ በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።

23፤ የዚያን ጊዜም። ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።

24፤ ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል።

25፤ ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ አልወደቀም።

26፤ ይህንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን ይመስላል።

27፤ ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት መታው፥ ወደቀም፥ አወዳደቁም ታላቅ ሆነ።
----------
28፤ ኢየሱስም ይህን ነገር በጨረሰ ጊዜ ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ፤ እንደ ጻፎቻቸው ሳይሆን

29፤ እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበርና።

#መልካም ቀን

@ortodoxtewahedoo
ሐምሌ 26 በዚህች ዕለት መልካም ሽምግልና የነበረው የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጠባቂዋ ድካሟን ለመሳተፍ ክብር ይግባውና ለጌታችንም አሳዳጊው ለመሆኑ የተገባው #ጻድቁ_ዮሴፍ አረፈ። በአረፈበትም ጊዜ ጌታችን ወደ እርሱ መጥቶ እጆቹን በላዩ ላይ ጫነ ለሥጋውም መፍረስና መበስበስ እንዳያገኘው ኃይልን ሰጠው በአባቱ በያዕቆብም መቃብር አኖሩት።
(መጽሐፈ ስንክሳር)
በረከቱ ይደርብን!

@ortodoxtewahedoo
Audio
እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር ይኑራችሁ
        
Size:-26.4MB
Length:-1:15:56

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedoo
Audio
"እመቤታችን ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር ነበር" ምን ማለት ነው??

መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን
መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ(ዶ.ር)
መጋቤ ብሉይ ዮሴፍ ደሳለኝ

@ortodoxtewahedoo
።።።።።።።።።። + ሐምሌ 26 + ።።።።።።።።።።
አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

ደብረ መድኃኒት አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን አንድነት ገዳም!
በዚኽች ዕለት ሐምሌ 26 ቀን በዓመታዊ የዕረፍት በዓላቸው ታስበው የሚውሉት ማር ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ያደረጉት ታላቅ ተአምር ይኽ ነው:-

‹‹ምንም ሳያስታጉል በየቀኑ ዕጣን የሚያሳርግ ወደ እግዚአብሔር መጸለይን የሚያበዛ ለአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ቤተ ክርስቲያን የሚላላክ አንድ መነኩሴ ነበር፡፡ ከዕለታትም በአንዲት ቀን እንቅልፍ መጥቶበት ተኝቶ ሳለ በዚያች ዕለት ሕልመ ሌሊት አገኘው፡፡ ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ሕልመ ሌሊት እንዳገኘው አይቶ ስለ አቡነ ሰላማ ቤ/ክ ማዕጠንት መታጎል ታላቅ ኀዘን አዘነ፡፡ ያንጊዜም ሰይጣን ከሰይጣን ጋራ ‹‹…ወዳጄ ይህን መነኩሴ ዛሬ ጣልኩት፣ ከአገልግሎቱም አስታጎልኩት አየህን!›› እያለ ሲናገር ሰማው፡፡ ሌላኛውም ሰይጣን መልሶ ‹‹…ወዳጄ መልካም አድርገሃል፣ መጥጠተህ አፌን ሳመኝ›› አለውና ሁለቱም እርስ በእርሳቸው አፍ ለአፍ ሲሳሳሙ ያ መነኩሴ ይህን አይቶና ሰምቶ በመናደድ ድጋሚም በዚህ እንዳይፈተን በማሰብ ስለት ባለው ምላጭ አባለ ዘሩን ቆርጦ ጣለውና የብልቱን ቁራጭ ወደታላቅ ገደል ወረወረውና ለሰይጣን ‹‹ይህን እንካ እንደውሻ ቆጥሬልሃለሁና›› አለው፡፡

ሰይጣኑም ወዲያው በዱር አሞራ ተመስሎ የብልቱን ቁራጭ ጠልፎ ወሰደ፡፡ ነገር ግን የእግዚብሔር ሰው ድንቅ ተአምራትንም የሚያደርግ አባታችን ማር ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ወዲያው ታላቅ የሆነ ነጭ ንስር መስሎ እየበረረ ሔዶ የመነኩሴውን የብልቱን ቁራጭ ከሰይጣን አፍ ቀምቶ ያንን ሰይጣን በሰይፍ ቆረጠውና ወደ አገልጋዩ መነኩሴ ቢሔድ ስለአገልግሎቱ መታጎል እያዘነ አገኘው፡፡ አባታችንም ‹‹…ወዳጄ አገልጋዬ ሆይ! እነሆ የሰውነትህን ብልት እንካ እንደቀድሞው ከሰውነትህ መልሼልሃሁ፤ እግዚአብሔር የፈጠረውን አካል ዳግመኛ አትቁረጥ፣ አስቀድሞም ከነበሩ በኋላም ከሚነሡ ይህንን ፈተና ታግሠው ካላላፉ ጽድቅ የለምና በቤተ ክርስቲያን ክህነትና ማዕረግ አይኖርህምና አካልህን አታጉድል፣ ሳትመረር ፈተናውን ታገሥ እንጂ፡፡ ያለመከራና ያለሥቃይ ጸጋ አትገኝምና…›› እያለ ከመከረው በኋላ ብፁዕና ቅዱስ ማር አቡነ ሰላማ ከመነኩሴው ተሰውሮ ዐረገ፡፡

ከዚህ በኋላ ያ መነኩሴ ፈጽሞ ፈጣሪውን አመሰገነ፡፡ እስካረፈበት ዕለት ድረስ ጸሎትን አበዛ፡፡ በሞት ባረፈም ጊዜ በአባታችን ጸሎት መንግሥተ ሰማያትን ወረሰ፡፡›› (ገድለ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ገጽ 81-82)

አባታችን ባረፈ ጊዜ በዚህ አስደናቂ ገዳም ላይ ራሱ ጌታችን በአካል ለአባታችን ተገልጦላቸዋል፡፡ አባታችን ማር ሰላማም ቡሩካን በሆኑ እጆቹ ምድሪቱን እንደመሶብ አንሥቶ በሥሉስ ቅዱስ መንበር ፊት አቅርቦ አስባርኳታል፡፡ የገዳሙ አቀማመጥ እጅግ አስገራሚ ነው-ልክ እንደ ግሸን መስቀለኛ ቅርጽ ያለው ሲሆን በአራቱም አቅጣጫ የተለያዩ ምሥጢራት አሉት፡፡ በገዳሙ ምዕራባዊ ክፍል አስደናቂው ፍልፍል ዋሻ ቤተ መቅደስ፣ በስተምሥራቅ የጻድቁ ቅዱስ መካነ መቃብር፣ በስተደቡብ መግቢያ በሩ፣ በስተሰሜን ጻድቁ ከዐለት ላይ ያፈለቋቸው ፈዋሽ ጠበሎች ይገኛሉ፡፡

ለማር አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ከሰማይ የወረደላቸው የእጅ መስቀላቸውና ቅዱስ መካነ መቃብራቸው በዚሁ ገዳም ይገኛሉ፡፡ ታላቅ ጻዲቅ፣ መናኝ፣ ሐዋርያ፣ ጳጳስ....የሆነው ማር ሰላማ ከሣቴ ብርሃን በድፍን ኢትዮጵያ በአራቱ አቅጣጫ እየዞረ በተአምራቱ ድውያንን እየፈወሰ፣ ሙታንን እያስነሣ፣ ወንጌልን እያስተማረ፣ እያጠመቀ፣ አብያተ ክርስቲያናትን እየሠራና አገልጋይ የሚሆኑ ቀሳውስትን እየሾመ በሀገራችን ላይ ብርሃንን የፈነጠቀ ለኢትዮጵያ መግለጽ ከሚቻለው በላይ ታላቅ ባለውለታዋ ነው፡፡ ከአቡነ ሰላማ በፊት እኛ ኢትዮጵያውያን ክርስቶስን ከማመን በቀር ጥምቀትና ሥጋ ወደሙ የመቀበል ልማድ አልነበረንም፡፡ በድንኳን ካለችው ታቦተ ጽዮን በቀርም ታቦታትና አብያተ ክርስቲያናትም ፈጽሞ አልነበሩንም፡፡ ይህን ሁሉ ያገኘነው በማር ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ነው፡፡ ይሄ ሁሉ ሲታሰብ ከአባ ሰላማ ውለታ አንጻርና እንደሠራላት እጅግ ታላቅ ሥራ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ጻድቁን እንደሚገባው መጠን አላከበረችውም ማለት ይቻላል፡፡ ጌታችንም በመጨረሻ ቃልኪዳን ሲሰጠው ‹‹ስለ ትምህርትህና ስለ ስብከትህ ኢትዮጵያን ከጨለማ አውጥተህ በሃይማኖት ስለ አበራሃት ከፍ ያሉ ክብራትንና ማዕረጋትን ፈጽሜ ሰጠሁህ›› ነው ያለው፡፡

የማር አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!

(ጽሑፍ ከ ገድላት አንደበት ገጽ የተወሰደ
ሥዕለ ቅዱስ በሠዓሊ ዘሪሁን ገ/ወልድ

@ortodoxtewahedoo
#መድኃኔዓለም

" ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው ፣
ይህን ያህል ትዕግስት እንደ ምን ያለ ትዕግስት ነው ፣
ይህን ያህል ዝምታ እንደ ምን ያለ ዝምታ ነው ፣
ይህን ያህል ቸርነት እንደ ምን ያለ ቸርነት ነው ፣
ይህን ያህል ሰውን ማፍቀር እንደ ምን ያለ ፍቅር ነው "

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በቅዳሴው ።

@ortodoxtewahedoo
Audio
ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው
        
Size:-13.8MB
Length:-39:45

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedoo
† "በጽዮን መለከትን ንፉ:: ጾምንም ቀድሱ:: ጉባዔውንም አውጁ:: ሕዝቡንም አከማቹ:: ማሕበሩንም ቀድሱ:: ሽማግሌዎችንም ሰብስቡ:: ሕጻናቱንና ጡት የሚጠቡትን አከማቹ:: ሙሽራው ከእልፍኙ: ሙሽራይቱም ከጫጉላዋ ይውጡ::"

†(ኢዩ. 2:15)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
#እንካን ለጾመ ፍልሰታ አደረሳቹ አደረሰን💠!

👉ጾም በሐዲስ ኪዳን፡- የሐዲስ ኪዳን ጾም ከብሉይ ኪዳን ጾም የተለየ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን የነበረው ጾም ሥጋዊ ችግርን የሚመለከት ሲኾን፤ በሐዲስ ኪዳን ግን የምንጾመው ለጽድቅ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የመጀመሪያ ሥራ ያደረገው ጾምን ነው፤ እንደዚሁም ያስተማራቸው ደቀ መዛሙርት ከሥራቸው በፊት ጾምን እንደ ጌታቸው አስቀደሙ፡፡ የሚከተሉት ጥቅሶች በሐዲስ ኪዳን ጾም እንደታዘዘ የሚያመለክቱ ናቸው፡፡
ማር.፱፣፳፱፣ ማር.፪፣፳፣ ማቴ.፮፣፮፣ ሉቃ.፮፣፳፩፣ የሐ.ሥራ.፲፫፣፫፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያናችን እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አብነት በማድረግ ጾምን በአዋጅ እንድንጾም በቀኖናዋ (በሥርዐቷ) ደንግጋለች፡፡
በቤተክርስቲያናችን የአዋጅ ጾም የሚባሉት ሰባት ናቸው፡፡ እነርሱም፡-

💠ዐቢይ ጾም (ጾመ ኩዳዴ)

💠ጾመ ነነዌ

💠 ጾመ ድኅነት (የረቡዕና ዐርብ)

💠ጾመ ጋድ

💠ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም)

💠 ጾመ ፍልሰታ

💠ጾመ ነቢያት (የገና ጾም)

💠ጾመ ፍልሰታ💠

ፍልሰታ የግእዝ ቃል ነው፤ ፈለሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ተለየ፣ ሄደ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መሄድን ያመለክታል፡፡ ጾመ ፍልሰታ ሐዋርያትን አብነት አድርገን፤ ሐዋርያት የተቀበሉትን በረከት ለማግኘት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የምንጾመው ታላቅ ጾም ነው።

እመቤታችን እንደ ሰው ልማድ ሞትን ትቀምስ ዘንድ ግድ ስለኾነ፤ ጻዕርና ሕማም በሌለበት አሟሟት፤ ዕዝራ በመሰንቆ፥ ዳዊት በበገና እያጫወቷት፤ በተወለደች በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን በ48 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ አርፋለች። ሐዋርያትም እንደምታርፍ በመንፈስ ቅዱስ ስለተገለጸላቸው ከያሉበት (ከየሀገረ ስብከታቸው) ወደ መኖሪያ ቤቷ (የሐዋርያው ቅድስ ዮሐንስ ቤት) ተሰባስበው ነበር።

ነፍሷ ከሥጋዋ እንደተለየች አስከሬኗን ገንዘውና ከፍነው ወስደው ለመቅበር ወደ ጌቴሴማኒ ሲሄዱ አይሁድ ሰምተው መጡና ሐዋርያትን ከበቧቸው። የአይሁድ ተንኮል አስከሬኗን ከሐዋርያት እጅ ቀምተው በእሳት ለማቃጠል ነበር፤ ይህንንም ማድረግ የፈለጉበት ምክንያት፤ የሐዋርያት ትምህርት (የጌታችን ከሞት መነሳትና ለፍርድ ተመልሶ መምጣት)ከአይሁድ አልፎ ዓለም ሁሉ እያመነበት ስለመጣ እመቤታችንም ተነሥታ ዐርጋለች እያሉ ሐዋርያት ያስተምራሉ በሚል ስጋት ነበር።

‹‹የፈሩት ይነግሣል፥ የጠሉት ይወርሳል›› እንዲሉ አበው፤ የእመቤታችን ትንሣኤም ሆነ ዕርገት አይቀሬ ሁኗል። አይሁድ የእመቤታችንን ሥጋ ለመንጠቅ በሞከሩበት ጊዜም ታውፋኒያ የተባለ ጎልማሳ ሰው በጉልበቱና በድፍረቱ በአይሁድ ዘንድ ተመርጦ የእመቤታችንን ሥጋዋ ያረፈበትን ቃሬዛ ከሐዋርያት ነጥቆ መሬት ላይ ለመጣል ሲሞክር፤ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ ሁሉቱንም እጆቹን ቀንጥሶ (ቆርጦ) ጥሏቸዋል። ነገር ግን ጥፋቱን አውቆ ወዲያው ስለተፀፀተና ይቅርታ ስለጠየቀ በአምላክ ፈቃድ በእመቤታችን አማላጅነት በቅዱስ ጴጥሮስ አማካኝነት እጆቹ እንደገና ተመልሰውለት የእመቤታችንን እመ አምላክነት (የአምላክ እናት መሆኗ)ና ክብርን ለመመስከር በቅቷል።

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ በመላእክት ተነጥቆ ከተወሰደ በኋላ በገነት ውስጥ በዕፀ ሕይወት ሥር መቀመጡ ከዮሐንስ በስተቀር ለሌሎች ሐዋርያት ለጊዜው ምሥጢር ሆኖባቸው ቆይቶ ነበር።

ቆየት ብሎ ግን ሐዋርያው ዮሐንስ ስለእመቤታችን ሥጋ ነገራቸው። ቅዱሳን ሐዋርያትም ለእመቤታችን ካላቸው ክብርና ፍቅር የተነሳ ለምን አልቀበርናትም? ለምንስ የሥጋዋ ምሥጢር ለዮሐንስ ተገልጾ ለኛ ይደበቅብናል? በማለት እያዘኑና እየለመኑ ከጥር 21 አንስተው ለስድስት ወራት ከዐሥር ቀናት ቆይተዋል። ከዚህም በኋላ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ይዘው ለ14 ቀናት እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት ጠየቁት። በመጨረሻም የነገሩትን የማይረሳ፥ የለመኑትን የማይነሳ ልጇ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነሐሴ 14 ቀን ሥጋዋን አምጥቶ ስለሰጣቸው፤ ሳይውሉ ሳያድሩ በዕለቱ በጌቴሴማኒ በታላቅ ክብርና ዝማሬ ቀበሯት። በተቀበረችም በ3ኛው ቀን በነሐሴ 16 ከተቀበረችበት መቃብር ተነሥታ ወዲያውኑ በታላቅ ክብር በመላእክት አጃቢነት ወደ ሰማይ ዐርጋለች።
ጥበበኛው ሰሎሞንም “ውዴ እንዲህ ይለኛል ሙሽራዬ ውዴ ሆይ! ተነሺ የእኔ ውብ ሆይ ነዪ አብረን እንሂድ” በማለት አመሣጥሮ የተናገረው በጥበበ እግዚአብሔር ተመርቶ እንደ ክርስቶስ ሆኖ ውዴ ያላት እመቤታችን መሆኗንና ልጇ ተነሥቶ እንደ ዐረገ እሷም መነሣቷንና ማረጓን እንረዳለን። /መሓ.፪፥፲/። እመቤታችን ባረገችበት ጊዜ ሐዋርያው ቶማስ በመንፈስ ቅዱስ ጥበብ በደመና ተጭኖ ከሀገረ ስብከቱ (ሕንድ) ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ እመቤታችን በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ ተገናኙ። በዚህ ጊዜ ቶማስ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ አሁንም ደግሞ እርሷን ሳልቀብራት ከትንሣኤዋም ሳልደርስ ቀረሁ ብሎ አዘነ ከደመናው ላይ ሊወድቅም ፈለገ፤ ሆኖም እመቤታችን ዕርገቷን ከእርሱ በቀር ሌሎች አለማየታቸውን ገልጻ አረጋጋችው፤ ዕርገቷንም ለሐዋርያት እንዲነግርና ምልክትና ማስረጃ እንዲሆነው ተገንዛበት የነበረውን ሰበኗን/የከፈን ጨርቅ/ ሰጥታ አሰናበተችው።

ቶማስም መሬት ለይ ወርዶ መቀበሯን፣ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያላወቀ መስሎ ሐዋርያትን ስለ እመቤታችን ሥጋ ጉዳይ ጠየቃቸው፤ እነርሱም ሱባዔ ገብተው እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቃቸውን፣ ከሱባዔያቸው በኋላ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ሥጋዋን መላእክት አምጥተው እንደሰጧቸውና እንደቀበሯት አስረዱት።

እርሱ ግን ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር›› እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲል ተከራከራቸው። ሐዋርያትም ቶማስን ለማሳመንና ለማሳየት ወደ መቃብሯ ወሰዱት፤ ሆኖም መቃብሯ ባዶ ሆኖ አገኙትና ተደናገጡ፤ በዚህ ጊዜ ቶማስ የሆነውን ሁሉ ገልጾ ለምልክትና ለማረጋገጫ የሰጠችውን ሰበኗን /ተገንዛበት የነበረውን ጨርቅ/ አሳያቸው፤ የራሱን ድርሻም አስቀርቶ አከፋፍሎ ሰጣቸው፤ ዛሬም ካህናት ከእጅ መስቀላቸው ጋር የሚይዙት እራፊ ጨርቅ የሚይዙበት ምክንያት ሐዋርያት የተከፋፈሉት የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ ነው።

ሐዋርያትም የዕርገቷን ምሥጢር ካመኑ በኋላ ዕርገቷን ለማየት በዓመቱ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደገና ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ለሁለተኛ ጊዜ ሁለት ሱባዔ ገቡ፣ እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ በነሐሴ ወር በ16ኛው ቀን ጌታችን ሐዋርያትን ወደ ሰማይ አውጥቷቸው እመቤታችንን አግኝተዋት ከሷ ተባርከው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረዘይት ተመልሰዋል።

በአጠቃላይ የእመቤታችን ለሐዋርያት በተለያዩ ጊዜያት መታየት፣ የሥጋዋና የነፍሷ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ፍልሰት ሲባል ከዚህ የተነሣ የነሐሴ ጾም በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዐት መሠረት ሐዋርያት ያገኙን በረከት ለማግኘት ጾመ ፍልሰታን እንጾማለን። ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤት በረከት ይክፈለን።

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
4_5902366013483123708.pdf
12.5 MB
#ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ

ሰው ሁሉ ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን !

(ያዕቆብ 1፥19)

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
2024/11/18 06:31:28
Back to Top
HTML Embed Code: