Telegram Web Link
እመቤቴ ማርያም ሆይ! እንደ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እለምንሻለሁ።
የአባ ኪሮስና የአባ ኪሩኮስ የአባ በርሱማና የአባ ብሶይ፣ የአባ አሞኒም የአባ አሳይና የአባ አርሳኒ በረከት፣ የአባ ለትጹንና የአባ አቡናፍር፣የመከሲሞስና የደማቴዎስ በረከት፣ የእስክንድርያው መቃርስና የሶርያው መቃርስ በረከት እንዲያድርብኝ ለምኚልኝ።

@ortodoxtewahedoo
እንኳን አደረሳችሁ!
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል
*-*-*-*-*-*-*-*-*-*-*-*-*-*-*-*-*-*-*-*
ዑራኤል የሚለው ስም `ዑር' እና 'ኤል' ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። ዑራኤል ማለት ትርጉሙ “የብርሃን ጌታ”፣ ”የአምላክ ብርሃን" ማለት ነው። ቅዱስ ዑራኤል ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነዉ። በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ፣ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። መጽ/ሄኖክ 6÷2 ምሥጢረ ሰማይና እውቀትንም ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለት የፀሀይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል። መጽ/ሄኖክ 28÷13 ቅዱስ_ዑራኤል_(ሱርያል)/ዑርኤል/
በመላእክት_ከተማ_በራማ_ካሉት_ሦስት ነገዶች ውስጥ አንዱ ነገድ ሥልጣናት ይባላል በሥልጣናት ላይ ከተሾሙ ሊቀና መላእክት ውስጥ አንዱ ሊቅን መላእክት ቅዱስ ሱርያል ይባላል ሱርያል የሚለውን ስም በአንዳንድ ድርስናት ካልሆነ በስተቀር እምብዛም አይታውቅም ትርጉሙም ፦፦ዐለቴ እግዚአብሔር ነው ፦፦ማለት ነው ሱርያል የቅዱስ ዑራኤል ሌላ ስሙ ነው ዑራኤል ማለት እግዚአብሔር_ብርሃን ነው ማለት ነው በቤተ ክርስቲያን በስፍት የሚታውቅው ስም ዑራኤል የሚለው ስም ነው።/ድርሳን ዑራኤል 1991 ገጽ 14/
• ቅድስት ድንግል ማርያምን፣ ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብጽ ስትሰደድ መንገድ የመራ፤
• ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ በተሰቀለ ጊዜ፣ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ፣ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨ፤
•እውቀት ለተሰዎረባቸው ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ጥበብን ያጠጣ፤
• አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመልአኩ አማላጅነት ብዙ ድርሰት የደረሱት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ጽዋ ሕይወትን ስላጠጣቸው ነው፣
• በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የተመሰረቱ ገዳማት በቅዱስ ዑራኤል መሪነት ነው፤
የመልአኩ የቅዱስ ዑራኤል በዓላት በዓመት 3 ናቸው።
• ጥር 22 በዓለ ሲመቱ፣
• መጋቢት 27 የጌታ ደሙን ለዓለም የረጨበት፣
• ሐምሌ 21 እና 22 ቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበት።
በጸሎቱ ለተማጸነ ከአምላኩ በረከትን ምህረትን የሚያሰጥ አዛኝ እሩህሩህ መልአክ ነው።
የቅዱስ ዑራኤል አማላጂነት አይለየን፤ ሁላችንንም ይጠብቀን፡፡

@ortodoxtewahedoo
ፓሪስ በኦሎምፒክ መክፈቻ ላይ የ"ቅሠፈኝ" ጥሪ አቀረበች:: በእርግጥ ይህ የኦሎምፒክ መክፈቻ ትዕይንት ሳይሆን የLGBTQ ክብረ በዓል ሊባል የሚችል ምስቅልቅል ያለ ትዕይንት ነበር:: እንደ ጠላት ያዩትን ክርስትና ለማቃለል ከጸሎተ ሐሙስ እስከ ራእየ ዮሐንስ አምባላይ ፈረስ በአስጸያፊ መንገድና በሚያስጠላ የሜካፕ ዝብርቅርቅ የዚህ ትርዒት ማላገጫ ሆነው አምሽተዋል:: ብዙ የሥነ ጽሑፍ የኪነጥበብና የሥነጥበብ ሰዎች መፍለቂያነትዋ በሚነገርላት ፓሪስ የሚታይ ጥበብ ጠፍቶ ለዓይን የሚቀፍ ዝብርቅርቅ መታየቱ ብዙኃንን አሳዝኖአል:: "የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" ያሰኛል::

2016 ላይ የSwitzerland tunnel ምርቃት ላይ ተመሳሳይ ጸረ ክርስትና ትርዒት በማሳየት መከፈቱ ይታወሳል:: ይህ ድፍረትና ጥላቻ ክርስትና ላይ ብቻ መሆኑ "ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደጠላኝ እወቁ" የሚለውን የመድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ቃል ያስታውሰናል:: በአሜሪካ የሚገኙ የCoptic Church ሊቃነ ጳጳሳት ተቃውሞውን አስጀምረውታል:: ክርስቲያን ነኝ የሚል ሁሉ ስለዚህ ድፍረት በሚችለው ተቃውሞውን ማሰማት አለበት:: በዓለም አቀፍ ሕግ በየትኛውም እምነት ላይ ይህ ሊደረግ መብት የለም:: በዓለም አቀፍ መድረኮች ክርስትናችን ከፍ ብሎ ሲታይ ደስ የሚለንን ያህል በእንዲህ ያሉ ጸያፍ ድፍረቶችም እንደምንቆስል በይፋ መናገር ይገባናል::

"መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ" ኤፌ. 6:12

@ortodoxtewahedoo
#ሐምሌ 22 እረፍቱ ለ ጳጳስ ዘ ምስራቅ ኢትዮጵያ ሰማዕት ወፃድቅ አቡነ ጴጥሮስ

አባ አቡነ እባ መምርነ መምርነ አባ አቡነ ጴጥሮስ እም አዕላፋ ህሩይ ለቤ/ክ

‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዚህ ጠላት እንዳይገዛ አውግዣለሁ፤ የኢትዮጵያ መሬትም ጠላትን ብትቀበል የተረገመች ትሁን፡፡››

📖አቡነ ጴጥሮስ ጳጳስ ዘምሥራቅ ኢትዮጵያ

"ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት"

አዬ፣ ምነው እመ ብርሃን? ኢትዮጵያን ጨከንሽባት?
ምነው ቀኝሽን ረሳሻት?
እስከመቼ ድረስ እንዲህ፣ መቀነትሽን ታጠብቂባት?
ልቦናሽን ታዞሪባት?
ፈተናዋን፣ ሰቀቀኗን፣ ጣሯን ይበቃል ሳትያት?
አላንቺ እኮ ማንም የላት….
አውሮጳ እንዲሁ ትናጋዋን፣ በፋሽስታዊ ነቀርሳ
ታርሳ፣ ተምሳ፣ በስብሳ
ሂትለራዊ እባጭ ጫንቃዋን፣ እንደኮረብታ ተጭኗት
ቀና ብላ እውነት እንዳታይ፣ አንገቷን ቁልቁል ጠምዝዟት
ነፍሷን ድጦ ያስበረከካት
ሥልጡን፣ ብኩን፣ መፃጉዕ ናት፤ ….
እና ፈርቼ እንዳልባክን፣ ሲርቀኝ የኃይልሽ ውጋገን
አንቺ ካጠገቤ አትራቂ፣ በርታ በይኝ እመ ብርሃን
ቃል ኪዳኔን እንዳልረሳት፣ እንዳልዘነጋት ኢትዮጵያን፡፡
አዎን፣ ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
እምፀናበት ልብ አጣሁ
እማማ ኢትዮጵያን መንፈሴ፣ ተፈትቶ እንዳይከዳት ሠጋሁ …
አዋጅ፣ የምሥራች ብዬ፣ የትብት ምግቤን ገድፌ
ከእናቴ ማኅፀን አርፌ
ከአፈርዋ አጥንቴን ቀፍፌ
ደሜን ከደሟ አጠንፍፌ
ከወዟ ወዜን ቀፍፌ
በሕፃን እግሬ ድሄባት፣ በህልም አክናፌ ከንፌ
እረኝነቴን በሰብሏ፣ በምድሯ ላብ አሳልፌ
ከጫጩት እና ከጥጃ፣ ከግልገል ጋር ተቃቅፌ፤
በጋው የእረኛ አደባባይ፣ ክረምት እንደወንዙ ፍሳሽ
በገጠር የደመና ዳስ፣ በገደል ሸለቆ አዳራሽ
ከቆቅ እና ከሚዳቋ፣ ከዥግራ ጠረን ስተሻሽ
በወንዝ አፋፍ ሐረግ ዝላይ፣ መወርወር መንጠልጠል ጥሎሽ
ከፍልፈል ጋር ሩጫ ስገጥም፣ ከቀበሮ ድብብቆሽ
ከናዳ ጫፍ ሣር አጨዳ፣ ለግት ላሜ ትንሽ ግጦሽ
ለጥጃዬ የሌት ግርዶሽ
ለጥማድ በሬዎች ራት፣ ለማታቸው ትንሽ ድርቆሽ
ለግልገሌ ካውሬ ከለል
እማሳው ሥር ጎጆ መትከል
ለፀሐይ የሾላ ጠለል፣ ለዝናብ የገሳ ጠለል
ውሎ የንብ ቀፎ ማሰስ፣ ያበባ እምቡጥ ሲፈነዳ
የግጦሽ ሣር ሲለመልም፣ ሲሰማሩ ሰደድ ሜዳ
አዝመራው ጣል ከንበል ሲል፣ ከብቱ ለሆራ ሲነዳ
ፈረስ ግልቢያ ስሸመጥጥ፣ ከወፎች ዜማ ስቀዳ
ልቤ በንፋስ ተንሳፎ፣ በዋሽንት ዋይታ ሲከዳ …..
ያቺን ነው ኢትዮጵያ የምላት
እመ ብርሃን እረሳሻት?
ያቺን የልጅነት የምሥራች? የሕፃንነት ብሥራት
የሣቅ የፍንደቃ ዘመን፣ የምኞት የተስፋ ብፅአት
ያቺን የልጅነት እናት?
አዛኚቱ እንዴት ብለሽ፣ ጥርሶችሽን ትነክሺባት?
ሥሜን በሥምሽ ሰይሜ፣ ባገልግሎትሽ ስዋትት
ከዜማ ቤት እቅኔ ቤት፣ ከድጓ ቤት እመጻሕፍት
ካንቺ ተቆራኝታ ዕድሌ፣ ካንቺ ተቆራኝታ ነፍሴ
ከቀፈፋ ደጀሰላም፣ ከቤተልሔም ቅዳሴ
እኰ፣ ቀፎ ዳባ ለብሶ
ቅኔ ዘርፎ ግስ ገሦ
መቅደስ አጥኖ ማኅሌት ቆሞ
በልብስ ተክህኖ አጊጦ፣ በብር አክሊል ተሸልሞ
እመ ብርሃን ያንች ጽላት፣ ነፍስ ላይ በእሳት ታትሞ
የመናኒው ያባ ተድላ፣ ረድ ሆኜ፣ አብሮኝ ታድሞ
ሕይወቴ እምነትሽን ጸንሶ
ሥጋ ፈቃዴ ተድሶ
ለሕንፃሽ መዲና ቆሞ፣ ለክብርሽ ድባብ ምሰሶ
ሥሜን በሥምሽ ሰይሜ፣ ሆነሺኝ የእምነቴ ፋኖስ
ለዋዜማሽ ግሸን ማርያም፣ ለክብርሽ ደብረ ሊባኖስ
ስሮጥ፣ በወንበሩ አኖርሺኝ፣ በአንበሳው በቅዱስ ማርቆስ
ታዲያ ዛሬ ኢትዮጵያ ስትወድቅ፣ ከምትሰጪኝ የፍርሃት ጦስ
ምነው በረኝነት እድሜ፣ ዓይኔን በጓጎጣት የሎስ
የጋኔል ጥንብ አንሳ ከንፎ፣ ወርዶ በጨለማ በርኖስ
ባክሽ እመ ብርሃን ይብቃሽ፣ ባክሽ ምስለ ፍቁር ወልዳ
ጽናት ስጪኝ እንድካፈል፣ የእናቴን የኢትዮጵያን ፍዳ፣
ከነከሳት መርዝ እንድቀምስ፣

@ortodoxtewahedoo
ሥራህን ሥራ (በአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ)

ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ሰጥቶታል ያንን መስራት የእሱ ፈንታ ነዉ። ቢቻለዉ እሱን ማገድ የዲያብሎስ ሥራ ነዉ። በእርግጥ ሥራዉን እግዚአብሔር እንደሰጠህ ያህል ሰይጣን ሊያግድህ ይሞክራል። ሌላ ነገር በበለጠ ደስ የሚያሰኝ ሊያቀርብልህ ይጥራል። በዓለማዊ ተስፋዎች ያባብልሃል የሐሜት ጎርፍ ያስወርድብሃል። ደራሲያን እንዲጠይቁህ እጅግ ስመ ጥሩ ሰዎችም በክፋ እንዲናገሩብህ ይጠቀምባቸዋል። ጲላጦስ፥ ሄሮድስ፥ ሀናንያ፥ ቀያፋ ሁሉም በአንተ ላይ ያድማሉ . . . አንተ ግን በፀና ውሳኔ በማያወላውል ቅናት በመጨረሻ ላደርገው የሰጠኽኝን ስራ ፈፀምኩ ሃይማኖቴንም ጠበቅሁ ለማለት እስክትችል ድረስ የሕይወትህን ዓላማ እና የተፈጠርክበትንም ግብ ተከተል።

አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ

@ortodoxtewahedoo
"አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው፤ ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያውያን የሚገዳቸው ነገር የለም። እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ። ኃላፊነትም ያለብኝ የቤተ ክርስቲያን አባት ነኝ። ስለዚህ ስለ ሀገሬና ስለ ቤተ ክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ። ከዚህ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም። ለፈጣሪዬ ብቻ የምናገረውን እናገራለሁ። እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ አውቃለሁ። ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ። ግን ተከታዮቼን አትንኩ።"

(ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሊቀ ጳጳስ ሰማዕተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ)

@ortodoxtewahedoo
#23 💚💛❤️

ሰማዕተ ኢየሱስ የእውነት ምስክር
ህያው ነው በሰማይ ብፁዕ ነው በምድር ።

የኢትዮጵያ ገበዝ
የአራዳው ንጉስ
የልዳው ኮከብ
ሊቀ ሰማዕት
ፍጡነ ረድኤት
ፈረሰኛው ቅዱስ ጊዮርጊስ አባቶቻችንን የረዳ ዛሬም ከኛ ጋር ነው ።

@ortodoxtewahedoo
2024/09/29 21:36:11
Back to Top
HTML Embed Code: