Telegram Web Link
Today,s Best photo
የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ካቴድራል
በሩስያዋ መስኮቭ (ሞስኮ) ከተማ
በረከቱ ይደርባችሁ

@ortodoxtewahedo
Audio
ስመለስ እከፍልሃለሁ

Size:-28.2MB
Length:-1:21:02

    በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
Audio
በወርቅ መቅረዞች መሐል ያለው
ራእይ 1÷13
👉በአዲስ አበባ ደ/ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ ግንቦት 16/2013ዓ.ም የተሰጠ ትምህርት

Size:- 27.2MB
Length:-1:58:56

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
Audio
አትባክኑ|| ተነሡ ከዚህ እንሂድ

Size:-33MB
Length:-1:34:46

    በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
የድንግል ማርያም ዓበይት በዓላት የምንላቸው ወር በገባ 21 ሳይጨመር

🔘መስከረም 10
🔸ጸዴንያ ማርያም

🔘መስከረም 21
🔸ግሸን ማርያም

🔘ህዳር 6
🔸ቁስቋም ማርያም

🔘ህዳር 21
🔸ጽዮን ማርያም

🔘ታህሳስ 3
🔸በዓታ ለማርያም

🔘ታህሳስ 22
🔸ብስራተ ገብርኤል

🔘ታህሳስ 28/29
🔸ልደት

🔘ጥር 21
🔸የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት

🔘የካቲት 16
🔸ኪዳነምህረት ቃል ኪዳን የተቀበለችበት

🔘ግንቦት 1
🔸ልደታ ለማርያም

🔘ግንቦት 24
🔸ስደት የጀመረችበት

🔘ግንቦት 21-25
🔸ለአምስት ቀናት ደብረ ምጥማቅ የተገለጠችበት

🔘ሰኔ 8
🔸ስለ ኃዘኗ ጌታችን ከደረቀ ዓለት ላይ ውኃ ያፈለቀበት

🔘ሰኔ 20
🔸ሕንጸተ ቤተከርስቲያን

🔘ሐምሌ 26
🔸ዕረፍቱ ለዮሴፍ አረጋዊ

🔘ነሐሴ 7
🔸ጽንሰታ ለማርያም

🔘ነሐሴ 16
🔸ዕርገተ ለማርያም

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
#ደብረ ምጥማቅ
ጻድቃኔ ማርያም ገዳም

💠በሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ የሚገኘው የደብረ ምጥማቅ ማርያምና የጻድቃኔ ቅድስት ማርያም መካነ ቅዱሳን አንድነት ገዳም በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በንጉሥ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ አማካይነት እንደተመሠረተ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡

💠ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ቤተ ክርስቲያኑን ሊያሠሩ የቻሉበት ዋነኛ ምክንያትም፤ በግብፅ ሀገር ሃይማኖት፤ ዘር፤ ቀለም ሳትለይ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስትገለጽ የነበረችበት ቤተ ክርስቲያን እሰላሞች በማቃጠላቸው እጅግ አዝነው ስለነበር በኢትዮጵያ ውስጥ ሰሜን ሸዋ ላይ ቤተ ክርስቲያኑን እንዳሠሩ የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡

💠በኢትዮጲያ ከሚገኙ የተባህትዎ ቦታዎች አንዷ የሆነችው ይህች ጻድቃኔ ማርያም ገዳም ከጥንት ጀምሮ ነገሥታት፣ ካህናትና ምእመናን ደጅ የጠኑባት፤ ሥጋቸውን ለነብሳቸው ያስገዙባት፤ ቃለ እግዚአብሔርን የሚማሩባት ነበረች፤ ለ500 ዓመታት ያህል ገዳሟ መናንያን የማይኖሩባት በቅዱሳን የምትጠበቅ ሆና ኖራለች፡፡

💠ከ500 ዓመታት በኋላ ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር እንዲሉ በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻና በ21ኛው መቶ ክፈለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ገዳሟ ዳግም አንሰራራች፤ ገዳሟ ምእመናን ፈቃደ ሥጋቸውን ለፈቃደ ነፍሳቸው የሚያስገዙባት፤ ፈውስ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ የሚያገኙባት፤ ሱባኤ ይዘው ከእግዚአብሔር መልስ የሚያገኙባት፤ መናንያን እንደ መላእክት የሚኖሩባት፤ የጽድቅ ተግባራት የሚከናወንባት፤ የእግዚአብሔር ቸርነቱ የበዛባት፤ የእመቤታችን ፍቅሯና ምልጃዋ የነገሰባት ቦታ ናት፡፡

💠በንጉሥ ዘርዐ ያዕቀብ የተመሠረተው ይህ ገዳም አሁንም ባለንበት ዘመን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በሕልም፤ በራዕይና በተከስቶ እየተገለጸች ምእመናንን እየተራዳች፤ በስሟ ከፈለቀው ጸበል እየጠጡና እየተጠመቁ ከተለያዩ ደዌያት በመፈወስ ላይ ናቸው፡፡

💠አሁን ላይ የጻድቃኔ ማርያም ቤተ ክርስቲያን እሰከ 25 ሚሊዮን ብር በሚደርስ ወጪ የቤተ ክርስቲያኑን ሕንፃ እየተገነባ ነው፤  የጽድቅ በር፤ የደኀንነት መድን የሆነችውን ቦታ ጠብቆና አስጠብቆ ማቆየት ደግሞ የሁሉም ክርስቲያን ግዴታ ነው፡፡

💠ዛሬ ከምናየውና ከምንሰማው መልካም ጅምር ተነስተን ለወደፊቱም ታስቦበት ገዳሙ ሰፍቶ፤ ምእመናን ተጽናንተውና ተፈውሰው የሚመለሱባት ቦታ እንድትሆን ማድረግ ኃላፊነት ስላለብን የበኩላችንን አስተዋኦ ማበርከት ይኖርብናል፡፡

   ከእናታች ከንጽህት ድንግል ማሪያም ረድኤት በከረት ይክፈለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
          ይቆየን

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
🔔 ከመምህራን የማንን ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇

┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ምሕረተአብ አሰፋ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ዘበነ ለማ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ሄኖክ ኃይሌ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ዮርዳኖስ አበበ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 አባ ገብረ ኪዳን
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ያረጋል አበጋዝ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር እዮብ ይመኑ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መምህር ገብረ እግዚአብሔር
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መምህር አባ ገብረ ኪዳን
┗━━━━━━━━━━━━━━┛

🔗የሁሉንም መምህራን ትምህርት ለማግኘት🔔
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ/ም ባደረገው የጠዋቱ የግንቦት ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ሰባት አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በመወያያ አጀንዳ አርቃቂነት ሰየመ።
በዚሁም መሰረት በመወያያ አጀንዳ አርቃቂነት የተሰየሙት ሰባት አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሕገ ቤተ ክርስቲያን በሚያዘው መሰረት ከቋሚ ሲኖዶስ ለምልአተ ጉባኤ እንዲቀርቡ የተመሩ እና ተጨማሪ የሚባሉ አጀንዳዎችን በመቅረጽ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የማስጸደቅ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።
በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴነት የተመረጡት አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚከተሉት ናቸው።

1.ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ
2.ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ
3.ብፁዕ አቡነ ማርቆስ
4. ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ
5. ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል
6. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ
7. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል

ኢኦቴቤ ሕዝብ ግንኙነት

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
📍 Saint Petersburg, Russia 🇷🇺

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
2024/09/27 23:15:20
Back to Top
HTML Embed Code: